Get Mystery Box with random crypto!

Muhammed Computer Technology (MCT)

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedcomputertechnology — Muhammed Computer Technology (MCT) M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedcomputertechnology — Muhammed Computer Technology (MCT)
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedcomputertechnology
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.76K
የሰርጥ መግለጫ

#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
አስተያየት ካላችሁ @ma1000me ልታገኙኝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-09 11:29:01 Plagiarism Checker X 8.0.3.0
ፕላጅያሪዝም ቸከር ምርጥ ነው ይጠቀሙበት!
#PlagiarismChecker


ለተመራቂ ተማሪዎች
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርባለሁ!
Automatic References
Automatic List of tables
Automatic List of figures
Citation እንዴት እንሰራለን?
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!





ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
Automatic Tables of Content.
Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ




~><~~~~
የYouTube ቻናሉን Subscribe በማድረግ ምርጥ ምርጥ ትምህርቶችን ይማሩ!
የ YouTube ቻናል ሊንክ

https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

Join on telegram
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
https://t.me/researchRC
3.6K viewsedited  08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 05:19:39 በኢትዮጵያውያን የተቋቋመው BExANet IT Solution PLC (ቤክሳኔት አይቲ ሶሊሽን) በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተቋቋመ ድርጅት ነው።
ይህ ድርጅት የሀገራችን የዲጅታል ቴክኖሎጂን ለማዘመንና ሀገራችንን ከውጩ አለም ጋር በዲጅታል ቴክኖሎጂ ማህበረሰባችን ስራውንና አሰራሩን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆንለት በማሰብ የተቋቋመ ድርጅት ነው።
ስለሆነም ቤክሳኔት አሁን ላይ በሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ የዲጅታል ቴክኖሎጂ ስራዎችን በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በትምህርት፣ በጤና፣ በገንዘብ፣ በሰው ሀብት ልማት፣ና በተለያዩ የሀገራችን መስሪያቤቶች ችግር የሆኑትን ኋላቀር አሰራሮችን በመንቀስና ለችግሮቹ መፍትሄ የሚሆኑትን ቀላልና ቀልጣፋ የዲጅታል ሲስተሞችን በመስራት ወደ ገበያ እያቀረበና የተጠቃሚዎችንም ቁጥር በማብዛት ስራዎቹን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ከቤክሳኔት ጋር በጋራ ለመስራት የምትፈልጉ እንዲሁም ከቤክሳኔት የተሰሩ የዲጅታል ቴክኖሎጂዎችን ለእናንተ ተቋም ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሲል በታላቅ ግብዣ ነው።
"Empowering Digital Excellence !"

የምሰጣቸው አገልግሎቶች!
Software Developement
SystenSystem
Web development
Customization
Integration
Data migration
API Developement
BackUp configuration
Vichel GPS Tracking

Network & infrastructure
Installing new network
Configuring core network
SetUp security Monitoring tool
Network scaleUp
Performance Troubleshooting
Network Design
Security Cammera

Training & Consultancy
ICT Training
Research & Proposal
Expertise Advisory
Risk Analysis

AI & Machine Learning
Expert System
Robotics
Data Science
Data Analysis
Data Insight & Analytics
Data Engineering

  BExANet (ቤክሳኔት) ከዚህ በተጨማሪም በብዙ ሴክተሮች ችግሮችን በመለየት በሀገራችን ያለውን አለም የደረሰበትን የዲጅታል ቴክኖሎጂን አጠቃቀም ሀገራችንና ማህበረሰባችን እንዲጠቀሙበት በማድረግ ስራን፣ አሰራርን ቀላል፣ ቀልጣፋና ምቹ እንዲሆን የማድረግን ስራ እየሰራን እንገኛለን።

  BExANet የሚያበለጽጋቸውን የዲጅታል ቴክኖሎጂዎን ሁሉም ተቋማት እንዲጠቀምባቸው ታላቅ ግብዣ እናቀርባለን።

ስለ  BExANet ትክክለኛ መረጃ ከፈለጋችሁ

አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0955220055
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/BExANetplc
በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/BExANet
email: bexanetplc@gmail.com
ዌብሳይት www.bexanet.com
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL

የቤክሳኔትን የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
Subscribe
https://youtube.com/@bexanetitsolutionplc
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
3.4K views02:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 21:12:03 ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች እንዴት ነው የሚገቡት?

በዚህ የቴክኖሎጅ ዘመን ኮምፒውተራችን አልያም ስማርት ስልኮቻችን ሁነኛ የመረጃ ማግኛ እና መዝናኛ ከሆኑ ሰነባብተዋል።

ይሁን እንጂ የሰዎችን መረጃ አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ለመጠቀም ብሎም መረጃ እና ንብረትን ወደ ግል ለማዞር የሚሞክሩ ሰዎች ስጋት ከሆኑም ቆይተዋል።

ቫይረሶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ ኮምፒውተራችን ሲገቡ ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ከጥቅም ውጭ ሊያደርገው ይችላል፤
የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎቻችንም ለሌሎች አሳልፈው የመስጠት እድልም አላቸው።

እናም በተቻለ መጠን ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተራችን ገብተው ጉዳት እንዳያደርሱብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦችም የኮምፒውተር ቫይረሶች ወደ ኮምፒውተሮች የሚገቡበትን መንገድ ያስገነዝባሉ።

የማንቂያ መልዕክቶችን (ኖቲፊኬሽን) ሳናነብ መቀበል
ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን ከሚገባባቸው መንገዶች ዋነኛው የማንቂያ መልዕክቶችን ሳንረዳ መክፈት ነው።
ለምሳሌ፦
1. በኢንተርኔት መረጃዎችን ስናፈላልግ a unique plugin is necessary is required የሚል ማስታወቂያ ሲመጣ ምንም አይነት የደህንነት ስጋት ይኑረው አይኑረው ሳናውቅ እንዲከፍትልት የሚያዘንን ቅደም ተከተል መከተል፤

2. በነፃ የሚለቀቁ ፕሮግራሞችን ከጫንን በኋላ በተደጋጋሚ እንድንጭናቸው የምንጠየቀውንና እያንዳንዱን የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ለመረጃ በርባሪዎች አሳልፈው የሚሰጡ ፕሮግራሞችን ማውረድ
የተበከለ ሶፍትዌር መጫን
ከኢንተርኔት
የምናወርዳቸው ነገሮች ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ካወረድን በኋላ ወደ ኮምፒውተራቸን ስንጭን (install ስናደርግም አንቲቫይረስ ሶስትዌር ሊኖረን ይገባል።

ላኪያቸው የማይታወቁ የኢሜል መልዕክቶችን መክፈት
ማንኛውንም ላኪያቸውን የማናውቃቸውን የኢሜል መልዕክቶች ከመክፈታችን በፊት በኦንላይን አንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች ስካን ማድረግ ይኖርብናል።

በኢሜል መልዕክቶች አማካኝነት የተለያዩ ቫይረሶች ስለሚላኩ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

የተበከሉ ውጫዊ ስቶሬጅ መሳሪያዎች (ሚሞሪ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሀርድ ዲስክ ወዘተ ኮምፒውተራችን ላይ መሰካትም ሌላኛው ቫይረስ ወደ ኮምፒውተራችን የሚገባበት መንገድ ነው።

የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን በየጊዜው አለማሳደግ አፕዴት አለማድረግ ችግር ላይ እንደሚጥል ይታመናል።
911 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 20:04:16 የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡
1.8K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 19:36:41 በኢንተርኔት አጭበርባሪዎች እንዳትታለሉ!
መፍትሄዎቹን ልብ ይበሉ!

በሰለጠነው ዓለም በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈጸም ማታለል የተለመደ ነው፡፡ ይሁንእንጂ ይህ ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እየተስፋፋ መጥቷል። በኢንተርኔት የሚፈጸም ማጭበርበር  በሸማቾች ላይ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። 

ከዚሁ ጎንለጎን በኮምፒውተር ቫይረስ አማካኝነት የሚሰነዘረው ጥቃትም በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መካከል ጉዳት ማድረሱን የተለያዩ ምንጮች በቅርብ ጊዜ ገልጸው ነበር፡፡

ለማንኛውም ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁንም ይሁን ወደፊት የዚህ ችግር ተጠቂ መሆኗ አይቀርምና እንዲህ ካለው አደጋ እያንዳንዱ ዜጋ ራሱን መጠበቅ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ማሳወቅ ተገቢ ነው፡፡

በመጀመሪያ ግን የኢንተርኔት ላይ አታላዮች ከሚጠቀሙባቸው በርካታ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን እንመልከት።

የማታለያ ዘዴዎቻቸው ምንድናቸው?

የኢንተርኔት አጭበርባሪዎች ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚገናኙት በኢሜይል አማካኝነት ነው። ከገንዘብ ጉዳይ ጋር የተያያዙ የግል መረጃዎችን የሚጠይቅ የማታለያ መልእክት ፊሺንግ ኢሜይል ይባላል። ታዲያ በዚህ ዓይነቱ ኢሜይል የሚጠቀሙ አጭበርባሪዎችም ሕጋዊ የሚመስል ድረ ገጽ ተጠቅመው ሰዎችን በማታለል ፓስወርድ፣ የክሬዲት ካርድ ቁጥራቸውን ወይም የባንክ ሒሳብ መረጃቸውን እንዲሰጧቸው ያደርጋሉ።

እንደነዚህ ካሉት ፊሺንግ ኢሜይሎች መካከል አንዳንዶቹ ምንም ዓይነት መረጃ ባትሰጥ እንኳ አጭበርባሪዎች የፈለጉትን ነገር እንዲያገኙ ይረዷቸዋል። ምክንያቱም አንድን ኢሜይል መክፈትህ ብቻ ስፓይ ሶፍትዌር የሚባል ፕሮግራም ወደ ኮምፒውተርህ እንዲገባ ሊያደርግና በኮምፒውተርህ የምታከናውናቸውን ነገሮች ሊመዘግቡ ይችላሉ። አንዳንዶቹ የምትጫናቸውን የኮምፒውተር ቁልፎች የሚመዘግቡ ሲሆን አጭበርባሪዎቹ በዚህ ተጠቅመው የይለፍ ቃልህን እና የግል መረጃዎችህን መስረቅ ይችላሉ። ሌሎች ፕሮግራሞች ደግሞ አጭበርባሪ ወደሆኑ ድረ ገጾች የሚመሩህ ሊሆኑ ይችላሉ። 

ታዲያ ከእነዚህ አታላዮች እንዴት መጠንቀቅ ይቻላል
መፍትሄዎቹ አጭርና ግልጽ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ አጠራጣሪ ወደሆኑ ድረ ገጾች የሚመሩ ኢሜይሎች ሲደርሱህ ጥንቃቄ አድርግ። እንዲህ ያሉ ኢሜይሎችን ስትከፍት አጭበርባሪዎች ትሮጃን ሆርስ ወይም ትሮጃን በሚባለው ፕሮግራም አማካኝነት አንተ ሳታውቅ ኮምፒውተርህ ውስጥ ያሉ የግል መረጃዎችህን ሊያገኙ ይችላሉ። 

አጭበርባሪዎች ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘትና መረጃዎችን ለመስረቅ የሚያግዟቸውን ስፓይ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተርህ ላይ ለመጫን ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች መካከል የብልግና ምስሎችና ጽሑፎች የሚገኙባቸው ድረ ገጾች፣ ምንጫቸው የማይታወቅ ሶፍትዌሮችን የሚያቀርቡ ድረ ገጾች እና አንዳንድ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ይገኛሉ። አንዳንዴ ደግሞ የማይታመን ትርፍ ወይንም ገንዘብ እንደሚያስገኙ ለሚገልጹ የኢሜይሎች መልእክቶች መልስ መስጠት አያስፈልግም።

ምናልባት በኢንተርኔት አማካኝነት ሥራ የምትፈልግ ከሆነም አጭበርባሪዎች፣ የማታለያ ድረ ገጾችን በመጠቀም “የመመዝገቢያ ክፍያ” እና ሌላው ቀርቶ ከገንዘብ ጋር የተያያዙ የግል መረጃዎችን ሊሰበሰቡ ይችላሉ።

እነዚህ አጭበርባሪዎች ወደ ትላልቅ ኩባንያዎች ወይም ገንዘብ ነክ ተቋማት ሳይሄዱ ባሉበት ሆነው የድርጅቶቹን የመረጃ ማዕከል ጥሰው በመግባት መረጃዎችን መስረቅ እየቻሉ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜ አጭበርባሪ ሠራተኞችና የኮምፒውተር መረጃ ጠላፊዎች የሰረቋቸውን የክሬዲት ካርድ መረጃዎችንና የግለሰቦችን ሙሉ መረጃዎች በኢንተርኔት ላይ የሚሸጡበት የደራ ገበያ እንዳለ አንዳንድ ምንጮች ይገልጻሉ።

ስለዚህ አንተም ከላይ ከተጠቀሱ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ በኢንተርኔት እንዳትጭበረበር የኮምፒውተርህ መከላከያ (ፋየርዎል) ሁልጊዜ የሚሠራ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲሁም የቫይረስ መከላከያ ፕሮግራሞች ወይንም አንቲቫይረስ መጫን እና ሌሎች ፕሮግራሞች ጊዜ ያለፈባቸው አለመሆናቸውን ዘወትር ማረጋገጥ ብልህነት ነው፡፡ 

እናንተስ ምን ትላላችሁ! በኢንተርኔት ላይ ላለመታለል ምን አይነት ጥንቃቄዎች ሊወስዱ ይገባል!
2.1K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 22:51:09 BExANet ቤክሳኔት
https://t.me/BExANet
https://t.me/BExANet
https://t.me/BExANet
በመረጡት ሶሻል ሚዲያ ገፆቻችንን ይጎብኙ፤ ይከተሉን!
1.3K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 19:55:02 ላፕቶፕ ሲገዙ ማገናዘብ ያለብዎ አስፈላጊ ነገሮች
1. ምን ሊሰሩበት አስበዋል?
ብዙ ሚፅፉ ከሆነ ኪቦርዱን ማየት ይገባል
ጌም ሚያበዙ ከሆነ ግራፊክስ ካርዱንና ስፒከሩን
ይመልከቱ
ለቪዲዮ ቅንብር (editing or software Engineering) ከሆነ ከፍተኛ የፕሮሰሰር አቅም ፣ ትልቅ ሳይዝ ራም high definition (HD) ስክሪን
መኖሩን ያረጋግጡ
2 አዲስ ከካምፓኒው እንደመጣ ( brand new ) ነው
ወይም በብልሽት ምክንያት ተመልሶ ካምፓኒው
ገብቶ የተሰራ (Refurbished ) መሆኑን ያረጋግጡ
3. የስክሪን ወይም የዲስፕለይ መጠን: ለርሶ ትክክለኛዉን የስክሪን መጠን ይምረጡ
(13.3” ,15.6”,17.3”)
4. የላፕቶፑን ስፔሲፊኬሽን በጥልቀት ይመርምሩ
ፕሮሰሰር (intel core 2 dou, core i3, core i5,
core i7 or AMD and others)
ራም (ስንት እንደሆነ 1GB,2GB,3GB,4GB , 8G and above)
ሀርድ ዲስክ (160 GB, 250GB, 320GB,500GB, 750GB and above)
ዲቪዲ ወይም ብሉሬይ ድራይቭ ( re-writable )
5. ባትሪ ይህ በጣም ወሳኝ ነው ። ሊደራደሩበት
አይገባም! ቢያንስ 3 ሰአት እና ከዛ በላይ ቢሆን አሪፍ ነው
6. የሚፈልጉት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይምረጡ:
ማክሮሶት ዊንዶውስ (windows 7, windows
8,windows10, windows11) , mac, Ubuntu,Linux ወዘተ
ዊንዶውስ 10 ወይም windows 11 ቢመርጡ ይመከራል!
ወደ ቴሌግራም ቻናሌ ይግቡ!

https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
2.7K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 19:46:38 ኮምፒውተር ላይ ማንኛውንም ፍላሽና ኤክስተርናል ሀርድ ዲስክ ሲሰካ እንዳይሰራ ማድረግ እንዴት እንችላለን በቪዲዮ ይመልከቱ



1. የኛን መረጃ ሌላ ሰው ያለእኛ ፈቃድ እንዳይወስድብን ለመዝጋትና
2ኛ. ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።
ቪዲዮውን ይመልከቱ

















2.8K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 17:30:23 BExANet ቤክሳኔት
https://t.me/BExANet
https://t.me/BExANet
https://t.me/BExANet
በመረጡት ሶሻል ሚዲያ ገፆቻችንን ይጎብኙ፤ ይከተሉን!

አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0955220055
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/BExANetplc
በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/BExANet
email: bexanetplc@gmail.com
ዌብሳይት www.bexanet.com
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100090537960178&mibextid=ZbWKwL

የቤክሳኔትን የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
Subscribe
https://youtube.com/@bexanetitsolutionplc
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!
2.8K viewsedited  14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 21:51:08 Telegra ካርድ እየበላ አስቸግሮታል?
ካርድ የሚጨርስበት ምክኒያት የተላኩልን message በራሱ ግዜ dawnload ስለሚያደርግባችሁ ስለሆነ የሚከተለውን ይሞክሩት

ቴግራማችሁ ላይ ትገቡና በግራ በኩል ከላይ ሶስት መስመሩን ትጫኑና settings የሚለውን ትፈልጉና ትጫናላችህ ከዛ ብዙ አማራጭ ያመጣ ከሱ ዉስጥ data and storage የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ዉስጥ authomatic media dawnload የሚል አለ ቀጥሎ ከሱ ታች when using mobile data የሚለውን ትጫናላችሁ እዛ ውስጥ
photos
voice message
videos
file
music
Gif
የሚሉትን ሁሉንም የራይት ምልክት(checkbox) ያለበትን ታጠፋላችሁ
ከዛ በኋለ በራሱ ግዜ ፎቶም ይሁን ሌሎችንም ዳውንሎድ አያደርግም
እንደተመቻችሁ ተስፋ አደርጋለሁ ይህን ማረጃ ለሌሎችም እንዲደርስ #Share አድርጉላቸው
@MuhammedComputerTechnology
@MuhammedComputerTechnology
3.5K viewsedited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ