2022-06-24 21:00:43
ከF1 እስከ F12 ያሉ # የዊንዶውስ
ቁልፎች አገልግሎት
በኮምፒውተራችን ኪይቦርድ ከላይ ተደርድረው
የምናገኛቸው ከF1 – F12 ያሉ ቁልፎችን Function
Key እንላቸዋለን፡፡
በዋናነትም ከሌሎች # ቁልፎች ጋር
በማጣመር እንደ አቋራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ እንኘህ
ቁልፎች እንደ ምንጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና
ሶፍትዌሮች አገልግሎታቸው ይለያያል፡፡: በዛሬው
ቱቶሪያላችንም የተወሰኑትን እናያለን፡፡
F1
ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው እርዳታ ስንሻ ነው፡፡ በአብዛኛው
ሶፍትዌሮች F1 ስንጫን # የ Help መስኮትን ይከፍቱልናል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Start እና F1 መጫን የ
Microsoft Online Help ይከፍታል፡፡
F2
# የተመረጠን አይከን፤ፋይል ወይንም አቃፊ ስም ለመቀየር
F2 መጫን ይቻላል፡፡ ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን Alt
+ Ctrl + F2 መጫን #የ Open መስኮትን ይከፍታል፡፡፡
F3
ዴስክቶፕ ላይ ካን ስንጫን የፍላገ መስኮት ይከፈታል፡፡
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን ቃልን መርጠን Shift +
F3 መጫን # የተመረጠው ቃል ውስት የሚገኙ ፊደላትን
አንድላይ ካፒታል ወይን ስሞል ወይንም የመጀመሪያውን
ፊደል ካፒታል ያደርግልናል፡፡
F4
አሁንም ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ ካለን F4 # መጫን
ለመጨረሻ ጊዜ የተገበርነውን ይደግምልናን፡፡ ለምሳሌ
አበበ ብለን ብንጽፍ እና F4 ብናጫን በ የምትባለውን
ፊደለ በድጋሚ ይጽፍልናል፡፡ Alt + F4 መጫን አክቲቭ
#የሆነውን መስኮት ይዘጋልናል፡፡ Ctrl + F4 ስንጫን
ደግሞ አክቲቭ ከሆነው መሰኮት ውስጥ አክቲቭ የሆነውን
ታብ ይዘጋልናል፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው በ
ብራውሰራችን ከአንደ በላይ ታብ ከከፈትን Ctrl + F4
ስንጫን ያለንበትን ታብ ብቻ ይዘጋልናለን ነገር ግን Alt +
F4 ብንጫን ሙሉ በሙሉ ብራውሰሩን ይዘጋብና ማት
ነው፡፡
F5
አሁን ገበያ ላይ ባሉት አብዛኛዎ ብራውሰሮች ላይ F5
መጫን # Refresh ያደርገልና፡፡ ማይክሮሶፈት ወርድ ላይ የ
Find መስኮትን ይከፍትልናል፡፡ ማክሮሶፍት ፓወር ፖይንት
ላይ ደግሞ Slideshow ያስጀምርልና፡፡
F6
በአብዛኛው ብራውሰሮች ላይ F6 ስንጫን የማውሳችን
አቅጣጫ መጠቆሚያ #(cursor) ወደ አድራሻ መጻፊያው
ይወስድልና፡፡ ከአንድ በላይ የማይከሮሶፍት ወርድ
ከከፈትን Ctrl + Shift + F6 መጫን # ወደቀጣዩ
የማይክሮሶፍት መስኮትያሸጋግረናል፡፡
F7
ማይክሮሶፍት ወረድ ላይ Shift + F7 መጫን የ
#Thesaurus መስኮትን ይከፍትልናል የሚያገለግለውም
ሰፔሊንግ፤ ፍቺ እና ሰዋሰው ለማስተካከል ነው፡፡
F8
ኮምፒውተራችን ሲነሳ የ Windows፤ # Startup menu
ለመግባት የጠቅማል፡፡
F9
በዊንዶውስ ላይ ጥቅም የለውም ነገር ግን
በማይክሮሶፍት ኦፍስ እንጠቀምበታለን
#Ctrl + F9= እንዲህ አይነት ባዶ ቦታ ለማስገባት { }
ወይም የመረጥነው ቃል በዚህ ዉስጥ { } ለማስገባት
CTRL + SHIFT + F9 ሊንክ የነበረውን ሊንኩ
ለማጥፋት
F10
አክቲቭ የሆነውን ዊንዶው ሜኑ ባርን አክቲቭ ለማድረግ
ያስችላል፡፡ Shift + F10 መጨን # ራይት ክሊክ
እንደማድረግ ይቆጠራል፡፡
F11
በአብዛኛዎ ብርውሰሮች ላይ F10 ስንጫን
የምንመለከተው መስኮት ሙሉ በሙሉ የኮምውተራችንን
ስክሪን ይሞላዋል # (Fullscreen) ፡፡
F12
ማይክሮሶፍት ወርድ ላይ # የ Save as ማስኮትን
ይከፍትልናል፡፡ Ctrl + Shift + F12 ፐሪንት ያዛል፡፡
14.2K views18:00