Get Mystery Box with random crypto!

Muhammed Computer Technology (MCT)

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedcomputertechnology — Muhammed Computer Technology (MCT) M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedcomputertechnology — Muhammed Computer Technology (MCT)
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedcomputertechnology
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.73K
የሰርጥ መግለጫ

#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
አስተያየት ካላችሁ @ma1000me ልታገኙኝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-01 21:36:16 ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ ምንድን ነው?
*****************************
ባዮሜትሪክስ የሚለው ቃሉ ቀጥታ ከግሪክ የተወሰደ ሲሆን “ባዮ” ማለት ህይወት፣ “ሜትሪክስ” ደግሞ መለካት ወይም ልኬት ማለት ነው። ሁለቱ ቃላት በአንድነት ሲነበቡ ደግሞ የህይወት መለኪያ/ልኬት የሚለውን ትርጉም ይሰጣሉ። ባዮሜትሪክስ የአንድን ነገር ተፈጥሯዊ ባህሪ ማለትም የዲ ኤን ኤ አደራደር፣ የዓይን ቀለምና ምጣኔ፣ የእጅ አሻራ፣ የድምፅ ሞገድ፣ የልብና ነርቭ መንገድ እንቅስቃሴ የሚያጠና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። ወይም ደግሞ ባዮሜትሪክስ የአንድን ሰው ማንነት በግልጥ በሰውነት ገፅታው ወይም በውስጣዊ ሥነ ህይወታዊ ባህሪው መረጃ ላይ በመመስረት ስለ ሰውየው አጠቃላይ ሁኔታ ማውራት የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። እነዚህ ባህሪያት በቀላሉ የማይረሱ፤ የማይጋሩና የማይሰረቁ መሆናቸው ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ ነው፡፡
የባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ በጥንት ጊዜ ከክስቶስ ልደት በፊት ከ500BC ጀምሮ የባቢሎናውያን የንግድ ልውውጦች የጣት አሻራዎችን ሸክላ ላይ በማስቀመጥ ይጠቀሙ የነበረ ቢሆንም በትክክል በዘማናዊ ቴክኖሎጂ መልክ ይዞ ግን በስፋትና በረቀቀ መልኩ አገልግሎት መስጠት የተጀመረው እኤአ ከ1981 በኋላ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ በዚህም መሰረት ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ አሁን ካለንበት የቴክኖሎጂ ጣሪያ ላይ ደርሶ የረቀቁ ወንጀሎች ሲፈፀሙ የሰዎችን ማንነት ለማወቅ የሚጠቅም የአሻራ ቴክኖሎጂ በመሆን በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ባዮሜትሪክስ ትልቅ ፋይዳ ያለው የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፤ አስፈላጊነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የዓለም የደህንነት ጥያቄ በመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል። በተለይም በትምህርት ተቋማት፣ ህክምና ተቋማት፣ በታላላቅ ኢንዱስትሪዎች፣ መንግስታዊ በሆኑና ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በደህንነት ተቋማት እና በሌሎችም ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂዎች መገለጫዎች
* ዩኒቨርሳሊቲ፡ በአለም ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ ሊኖረው ይገባል
* ልዩነት፡ በአጠቃላይ ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት ባሕርይ የላቸውም ፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ የሆኑ መንትዮች ለመለየት ከባድ ናቸው ፡፡
* ዘላቂነት፡ የሰዎች የባዮሜትሪክስ ባህሪ ከጊዜ ጋር ልዩነት ሊኖራቸው አይገባም ለምሳሌ ፣ የአንድ ሰው ፊት ከእድሜ ጋር ሊለወጥ ቢችልም በቴክኖሎጂው የመለየት እድሉ ሰፊ ነው።
* ተቀባይነት፡ በሁሉም አለማት ላይ ተመሳሳይ መሆኑና ሁሉም የተቀበሉት መሆኑ
* አስቸጋሪነት፡ ይህም ማለት ሰዎች ለመሸወድ ወይም ለማጭበርብር የማይሞክሩት መሆኑ
ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል፡-
1. የጣት አሻራ ቴክኖሎጂ
2. የፊት ገፅታን የሚለይ ቴክኖሎጂ
3. የአይን እይታ ቴክኖሎጂ
4. የድምፅ ቴክኖሎጂ የሚሉት ከብዙዎች መካከል ጥቂቶች ናቸው፡፡
የባዮሜትሪክስ ጠቀሜታ
* የወንጀል ድርጊት ከመፈፀሙ በፊትና ከተፈፀመ በኋላ የሰዎችን ማንነት ለመለየት የሚያገለግል ቴክኖሎጂ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ሰው የተለያዩ አለማትን በሚዞርበት ወይም በሚጎበኝበት ወቅት በሚዳረስባቸው ቦታዎች በሚገኙ የኢሚግሬሽን ጣቢያዎች ላይ የጣት አሻራ እንዲሰጥ ይጠየቃል ይህም በሀገር እና ግለሰብ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ወይም የወንጀል ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡
* በበርካታ የመንግስትና የግል ድርጅቶች፣ ባንኮች እና የገንዘብ ተቋማት እንደ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይጠቅማል
* የባዮሜትሪክ ሥርዓቶች ሰዎችን በፍጥነት፣ በቋሚነት እና በአስተማማኝ ሁኔታ በመለየት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ
ምንጭ፡ biometricupdate.com እና Si Tech Bufe
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
9.4K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 17:26:34 በዋትሳፕ ይግቡ
https://chat.whatsapp.com/CYoBaQ9ixRVIXv08TkUNTV
8.9K viewsedited  14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 20:30:48 ሪሰርች Research የጥናትና ምርምር የመረጃ ምንጮች(Source of data) ናሙና አመራረጥ (Sampling) ምንድን ናቸው?
በምርጥ አቀራረብ ይመልከቱት








9.8K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 06:45:00 የጥናትና ምርምር (Research)  መሰረታዊ ዋና ዋና ክፍሎች  ምንድን ናቸው?

እነዚህ 16 ነጥቦች ልብ ይበሉ!

የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡
ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡
በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡
ይመልከቱት በምርጥ አቀራረብ የተዘጋጀ!











9.9K views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 18:02:10 ጠቃሚ ዌብሳይቶች!
Some websites where you can get almost any book for free (May be some paid)

1. libgen.io
2. Pdfdrive.net
3. Allitebooks.com
4. Bookrix.com
5. Gutenberg.org
6. Freebooks.com
7. b-ok.org

#Anyone Need Research paper or Books

1) http://gen.lib.rus.ec
2) http://sci-hub.org
3) http://sci-hub.cc
4) http://sci-hub.bz or .tw
4) http://search.crossref.org
5) http://booksc.org/
6) http://libgen.io/
7) http://gen.lib.rus.ec/scimag/
8) http://airccj.org/csecfp/library/index.php

#For Text Books these are Some More Links

1) http://libgen.org/
2)http://gen.lib.rus.ec/
3) http://en.bookfi.org/
4) http://lib.freescienceengineering.org/
5) http://bookza.org/
6) http://bookzz.org/


ለ ጓደኞቻችሁ ሼር አርጉላቸው

Join and share


✦Join➬ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
✦Join➬ https://t.me/MuhammedComputerTechnology
9.7K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 13:15:32 #ፍላሽ_ዲስክ_እንዴት_በፓስዎርድ_ማሰር_ይቻላል?
በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለን! ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው የምትፈልጉት ዳታ(ፋይል፣ቪድዮ፣ፎቶዎች ወዘተ) በፍላሽ ዲስክ ትይዛላችሁ።
ስለዚህ ሚስጥራዊ ዳታችሁን ከናንተ ውጪ ማንም ሰው እንዳያየው ወይም እንዳይጠቀምበት የግድ ፍላሽ ዲስኩን በፓስወርድ መቆለፍ ይኖርባችኋል።
እሺ windows 10 የምትጠቀሙ ሰዎች ፍላሽ ዲስካችሁን በፖስወርድ ለመቆለፍ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል መቆለፍ ትችላላችሁ።
1-ፍላሽ ዲስኩን ኮምፒውተራችሁ ላይ ሰኩት እና"This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ አድርጉት
2- "This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ ስታደርጉት የሚመጣው ቦክስ ውስጥ ፍላሽ ዲስካችሁ ይመጣል
3- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አድርጉ
4- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አ.ስታደርጉ "Turn BitLocker on" የሚለውን ሴሌክት ማድረግ
5- ከዚያ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል፣ የማትረሱት ፓስወርድ አስገቡና "next" በሉት
6- ከዚያ "Encrypt entire drive" የሚለውን ሴሌክት በማድረግ "next" ማለት። በቃ አለቀ።ፍላሽ ዲስኩ በፓስውርድ ተቆለፈ።
ከዚህ በኋላ ያለ እናንት ሌላ ማንም ሰው ፍላሹን መጠቀም አይችልም።
ፍላሽ ዲስኩን መጠቀም ስትፈልጉ ኮምፒውተራችሁ ላይ ፍላሹን ደብል ክሊክ ስታደርጉ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል።ፓስወርድ በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ
3.4K viewsedited  10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 07:55:17 ምርጥ የC++ ቪዲዮ ይከታተሉ አሁን ክፍል አራት ደርሰናል።
ቻናሉን በብስክራይብ እንድታደርጉ እየጋበዝኩ።
በእያንዳንዱ ቪዲዮ ምርጥ ምሳሌዎችን እየሰራን ነው። ስለሆነም ለጀማሪ ተማሪዎች ምራጥ ትምህርት ነው።

ሁሉንም ክፍሎች እንደሚከተለው አስቀምጬላችኋለሁ!

ፕሮግራሚንግ ክፍል አራት 4
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይማሩ



C++ Programming part 3 የC++ ፕሮግራሚንግ ክፍል ሶስት 3
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይማሩ



C++ Programming part 2 የC++ ፕሮግራሚንግ ክፍል ሁለት
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይማሩ



C++ Programming part 1 የC++ ፕሮግራሚንግ ክፍል አንድ
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይማሩ




የ YouTube ቻናል ሊንክ
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
7.7K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:28:14 ኢድ ሙባረክ!
ተቀበላለሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አዕማል
2.2K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 22:34:55 C++ Programming ፕሮግራሚንግ እየተመቻችሁ ነው?
ኮሜንት አድርጉልኝ

https://t.me/meme_comp_tech
4.5K viewsedited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 22:28:37 ፕሮግራሚንግ ክፍል አራት 4
ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይማሩ


4.5K views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ