Get Mystery Box with random crypto!

የስልኮቻችንን ባትሪ ዕድሜ ለማራዘም እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ፍጆታን ለመቀነስ የሚረዱ ጠቃሚ ምክ | Muhammed Computer Technology (MCT)

የስልኮቻችንን ባትሪ ዕድሜ ለማራዘም እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ፍጆታን ለመቀነስ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ባለሙያዎች አስቀምጠዋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትን ተግባራት ቢያከናውኑ የስክዎን ባትር እድሜ ያራዝማሉ፤ የኢንተርኔት አጠቃቀም ወጪን ይቀንሳሉ።
1. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ባክግራውንድ(ዳታ) እንዳይሰሩ ማድረግ
2. ሞባይል ስልክዎን ቻርጅ ላይ ሰክተው አለመጠቀም
3. የማይጠቀሙባቸውን መተግበሪያዎች ወደ ስልክዎ ማሳወቂያ እንዳይልኩ ማድረግ
4. አቅጣጫ መፈለጊያ፣ ብሉቱዝ፣ 3ጂ/4ጂ እንዲሁም ዋይፋይ በማንጠቀምበት ጊዜ ማጥፋት
5. ትላልቅ ፋይሎችን ለማውረድ ገመድ አልባ ኢንተርኔት(ዋይፋይ) ብቻ መጠቀም
6. የሞባይል መተግበሪያዎችን ለማሻሻል ዋይ ፋይን ይጠቀሙ
7. ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ የሞባይልዎን ኢንተርኔት(ዳታ) ይዝጉ
8. አገልግሎት የማይሰጡ ወይም ጊዜ ያለፈባቸውን መተግበሪያዎችን ከስልክዎ ያስወግዱ
9. ሁልጊዜ የስልክዎ ስክሪን የሚጠፋበትን ደቂቃ ያሳጥሩ፤ ከተቻለም ወደ ሰኮንዶች ይቀንሱ
10. ለስልኩ የተሻለ ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌር ይጫኑለት።