Get Mystery Box with random crypto!

ምክረ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ mkreabew — ምክረ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ mkreabew — ምክረ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @mkreabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 11.29K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናላችን ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን የአባቶቻችን ምክር በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አይደሉም።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2020-10-29 16:19:31 ከ1ሺ ሜምበር በላይ ቻናል ያላችሁ የተዋህዶ ልጆች #promotion መግባት ምትፈልጉ ቦታ ስላለ መመዝገብ ትችላላችሁ።

@Yaromare
@Yaromare
@Yaromare

ማናገር ትችላላችሁ
17.9K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-15 22:45:24 ምክረ አበው pinned «" ሌሎችን የመመልከት አሳብ እኔን የተሻለ ኣያደርገኝም። " ታላቁ ቅዱስ ካህኑ ኤስድሮስ(abba ISIDORE the priest ብዙ ሰው በሰዎች ሃጥያት ላይ መፍረድ ይቀለዋል። በ ታሪክ የሚያውቃቸው መልካም ነገር ያልሰሩ ሰዎች ስም እየጠራ ሲተች ይሰማል፤ ከዚህ አልፎ የ ገዛ ሃጥያቱ ከነዚያ ሰዎች ያነሰ እንደሆነ በማሰብ ስለ ፅድቁ ሲመፃደቅ ይታያል ።እውነት ነው እነዚያ ሰዎች ክፉ ነገር…»
19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-15 12:38:25 " ሌሎችን የመመልከት አሳብ እኔን የተሻለ ኣያደርገኝም። "
ታላቁ ቅዱስ ካህኑ ኤስድሮስ(abba ISIDORE the priest


ብዙ ሰው በሰዎች ሃጥያት ላይ መፍረድ ይቀለዋል። በ ታሪክ የሚያውቃቸው መልካም ነገር ያልሰሩ ሰዎች ስም እየጠራ ሲተች ይሰማል፤ ከዚህ አልፎ የ ገዛ ሃጥያቱ ከነዚያ ሰዎች ያነሰ እንደሆነ በማሰብ ስለ ፅድቁ ሲመፃደቅ ይታያል ።እውነት ነው እነዚያ ሰዎች ክፉ ነገር በመስራታቸው በ ቅድሱ መፅሓፍ ጭምር የ ክፋት ታሪካቸው ለ ትውልድ ትምህርት እንዲሆን ተፅፏል ። እኛ ግን ለ ስድብ ና ራሳችንን በማኩራራት ለማቅረብ ካልሆነ ትምህርት ወስደንባቸው ስንጠቅምባቸው አይታይም። ለምሳሌ አስቆረታዊው ይሁዳ እንይ ብዙ ጊዜ ለ ሁሉ ከሃዲ ሰው ይሁዳ ብለን እንሳደባለን ፤ጌታውን በ 30 ዲናር ከሸጠው ይሁዳ የተሻልን እንደሆንን እናስባላን።እውነታው ግን ሂወታችን ስንመለከተው ግን በ ይሁዳዊ ፍቅረ ንዋይ የታወረ ልብ፤ ይሁዳዊ የሆነ ክርስቶስን ና ክርስትናን ያልተረዳ አእምሮ ፤ ለ ክርስትና ሃይማኖት የተከፈለው የ ክርስትናችን ዋጋ እንኳን ስንት እንደሆነ በቅጥ ሳናዉቅ የ ውስጥ መቅደሳችን ለ አጋንንት ከፍተን በ ጥቂት ዲናር የምንሸጥ፤ ፀፀት እንጂ በ ንስሃ ያልተቃኘን ትዕቢተኛና ዕብሪተኛው ልባችን ስናየው "ይሁዳ =ምስጉን፣ታማኝ " የሚል ክቡር የስም ፍቺ ይዞ በ ክፋት "የ ሰላሜ ሰው"(መዝ 41:9) ብሎ የጠራውን ቸሩ መምህሩ ክርስቶስን የሸጠ ።፤ እኛም የወደደን ጌታ ፥ ባርያየ ሳትሆኑ "ልጆቼ "ናቹ ብሎ ለጠራለን ጌታ ትተን የዚህ ዓለም ባርያ ለመሆን ዳዴ የምንል ከንቱ መሆናችን ሳስብ በ ይሁዳ ታሪክ መመፃደቃችን ለምንድነው

ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱስ ካህኑ ኤስድሮስ እስክንድርያ ደርሶ ወደ ገዳም ሲመለስ በገዳሙ ያሉ መነኮሳት " በከተማ ውስጥ ምን እየተደረገ ነው?? በማለት ይጠይቁታል ።

እርሱም "ወንድሞቼ ከ ሊቀ ጳጳሱ ፊት በስተቀር የማንም ፊት አልተመለከትኩሁም "ብሎ ሲመልስላቸው በተናገረው ነገር በጣም ተጨንቀው "አባታችን እንደዚህ የሚሉን በዚያ ችግር ስለደረሰ ነው" ብለዉ መነኮሳቱ ሲያስቡ አባ ኤስድሮስ ኣይዋቸዉና ከዚያም ዐይኖቻቸው ጥፋትን ከ መመልከት ፤ አእምሯቸው ጥፋትና ጉድለት ላይ ከማተኮር እንዲከለከሉ እንዲህ በማለት አስተማርዋቸው "እናንተ እንዳሰባችሁት ያጋጠመን ነገር የለም። ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር " ሌሎችየመመልከት አሳብ ፤ የተሻለ ሰው ኣያደርግም።" ራስህን መመልከት ካለመቻል ነው የሌሎች ስህተት ላይ እንድናተኩር የሚያደርገን።

አንድ የ ቤተክርስትያን አገልጋይም ሂወቱን ሳያስተካክል እንዲሁ በዘልማድ ሰዎች ከስህተት ለማረም ፤ ከ ሃጥያት ለ መመለስ የሚጥር ከሆነ በ መርፌ ይመሰላል።መርፌ ብዙ ቀዳዳዎችን ይሰፋል፤ይሸፍናልም ። የራሱ ቀዳዳ ግን መሸፈን አይቻለውምና ።በ ቤተክርስትያን በ ተለያዩ የ አገልግሎት ክፍሎች ያሉ አገልጋዮች የ ዓለሙን ሃጠያት ተመልክተው እንዲያወግዙ፤ ሰውን ከ ሃጥያት እንደመጠበቃቸው ልክ ፤ የ ገዛ ሰውነታቸው ከ ሃጥያት መጠበቅ ይገባችዋል ይህ የሚሆነው ደግሞ ለራሳቸው ጊዜ ሰጥተው ውስጣቸውን የሚያደምጡበት ችሎታ ሲኖራቸው ነው።
"ሰው ዓለሙን ዅሉ አትርፎ ራሱን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል"ሉቃ 9፥25 ስለዚህ አገልጋዮች አስቀድመው ሂወታቸውን ማየት፤ የወደቁበትን ማሰብ ይገባችዋል።

@ ሄኖክ ታደሰ
31.3K viewsedited  09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-09 22:34:20 በ ብዙ የ በረሃ አባቶች ጭምር መንፈሳዊነቱና ከፍ ያለ እዉቀቱ የሚነገርለት ከ 360 ዓ.ም-449ዓ.ም የነበረዉ ቅዱስ አባ አርሳኔዎስ /abba arsenius/ አንድ ታሪክ ና ወርቃማ አባባል :

በ አንድ ዘመን አንዱ መነኩሴ ወደ አባ አርሳኔዎስ ዘንድ በመሄድ " ለምንድር ነው የምታገልለን" በማለት ጠየቀዉ ።

አባ አርሳኔዎስ ደግሞ እንዲህ አሉት "እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል። ይሁን እንጂ በ አንድ ጊዜ ከሰውና ከ እግዚአብሔር ጋር መኖር አልችልም። እልፍ አእላፋት የሆኑት መላእክት ያላቸው ፈቃድ አንድ ነው፤ የ ሰዎች ፈቃድ ደግሞ ብዙ ናቸው። ስለዚህ ከሰዎች ጋር ለመሆን ብዬ እግዚአብሔር አልተውም።"

" ከሰዎች ጋር ለመሆን ብዬ እግዚአብሔር አልተውም።"
23.7K viewsedited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-07 20:32:16
ፍቅረ ቢጽ ከ ፍቅረ እግዚአብሔር የሚያደርሰው ነው።(አረጋዊ መንፈሳዊ)


ክርስቲያን ወንድምህን በፍቅር ባየሀው ጊዜ እግዚአብሔር ማየትህ ነው።(ቀሌሜንጦስ)


ባልንጀሮችህ አንድ ሺ ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ያንተን ምሥጢር ደብቆ የሚይዘው ግን አንድ ነው።(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )


ከላይህ ያለ ሰው አስተማሪ የሚሆነው በ እውቀቱ ከሆነ ሊቅ ልትሆን ትችላለህ በ ህይወቱ ከሆነ ግን ክርስትያን ትሆናለህ።(አቡነ ሺኖዳ)


የትህትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው። የመጀመርያውን እንድትከተል ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክራለሁ።(አባ ኤስድሮስ)


በሌሎች ላይ መፍረድ የ አንድ ሰው የ ትዕቢት ውጤት ነው፤ ትሑት ሰው ግን ሁሉ ሰው ያከብራል፤ከ እርሱ የተሻሉ እንደሆኑ ያስባል።(ቅዱስ ዕንባቆም)


ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን በወዳጅህ አትክፋ።(ቅዱስ ፖሊካርፐስ)


የ እውቀት ደግነቱ ከሁሉ ጋር መስማማትና መግባባት ነው፤የማይቻለውን እሸከማለሁ የሚል ሰው ለመሸከም የሚችለውን ያጣል።(አንጋረ ፍላስፋ)
24.9K viewsedited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-29 20:43:12 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በምስጋና መጠለፍ ና ከንቱ ውዳሴ

ምስጋና የ ባህርይ ገንዘቡ የሆነዉ ለ እግዚአብሔር ነው ።1ኛ ዜና 16፥25, መዝ 18፥3 መዝ 96፥4 ,2ኛ ሳሙ 22፥4 እኛ ሰዎች ደሞ ከ አፈር የተበጀን ፈጣሪ የሰራን ፍጥረቱ ነን በ እኛ ዘንድ የ ፈጣሪ ክብር እንዲገለጥ ይገባል። ለ ፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብም አንደበት ተሰርቶልናል። መዝ 34፥1 "ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው።" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ።

ሆኖም ግን ለ ፈጣሪ የሚገባውን ምስጋና ለ ራስ ማድረግ መጣጣር በዘመናችን አገልጋዮች በስፋት ይታያል። በዘመናችን በብዙ አገልግሎቶች ስብከቱ፣ ዝማሬው ፣ ክህነቱ የራሳቸው እስከሚመስል አገልጋዮች ሲመፃደቁበት ማየት የተለመደ እየሆነ መጥትዋል ። በዚህ የተነሳ ለ ቤተክርስትያን እኛ እናውቅልሻለን የሚል አካል እየበዛ ፤ አገልጋዮች ከሚሰበከው ወንጌል በላይ ስለ ድምፅ ጥራት ና ስለ መድረክ አያያዝ ጉዳይ ሲጨነቁ ማየትም የተለመደ ነው።



አንድ መርከብ በ ውሃ የተሞላ ውቅያኖስ ላይ ሳይሰጥም መከሄድ ይችላል። መርከቡ መስመጥ የምትጀምረው በ ራስዋ ቀዳዳ ተከስቶ፤ በ ውሃ ከተሞላ ውቅያኖስ ውሃው ሰርስሮ የገባ ጊዜ ነው። አንድ አገልጋይም በሚያገልግልበት ጊዚያት የ ምስጋና ብዛት የ መቆለጳጰስ ጥግ ስለተነገረው ሳይሆን ፤ በ ልቡ ለ ምስጋናዎቹ ና አድናቆቶች ቦታ መስጠት ሲጀምር ነው በ ከንቱ ውዳሴ ተጠልፎ የሚወድቀው።

በርግጥ ምእመናን ናቸው አገልጋዮች በ ከንቱ ዉዳሴ እንዲወድቁ ፆር እየሆኑ ያሉት ። ታቦት ያላቸው ብዙ መካናት ትቶ አገልጋዮች ተከትሎ ሚዋትት ፤ እግዚአብሔር ሳይሆን አገልጋዮች የሚያመልክ ስለ ክርስቶስ ከመስበክ ይልቅ ላንቃዉ እስኪያመው ስለ መምህር እገሌ ዘማሪት እገሊት ሲኸራከር የሚውል ምእመን እንደ ፈሪሳውያኑ በ ነቀፋ የተሞላ ክርስትና የሚኖር ከሆነ ቆይትዋል። ምእመናን ለ እናታችን ሄዋን እንዳሳታት ዲያብሎስ ያለ የ ሽንገላ ቃላትም ለ አገልጋዮች ከ መናገር መከልከል ይገባናል።

ከመነኮሳት ታሪክ አንድ ታሪክ ለማስታወስ ያክል።

ከዘመናት በ አንዱ አንዲ ወጣኒ መነኩሴ በ መንፈሳዊ አገልግሎቱ የተነሳ በብዙ ምእመናን ዘንድ አድናቆትመንፈሳዊ ና ዉዳሴ ማግኘት ጀመረ በዚህም የተነሳ ደስ ብሎት ወደ አበመኔቱ ሄደና ስለ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በብዙ ምእመናን መወደዱን አድናቆት ና ዉዳሴ ማግኘቱን ነገራቸው።
አበመኔቱ እንዲህ ብለው ምክር ሰጡት "ልጄ ሂድና ሙታንን ተሳደብ አሉት እንዳሉትም ወደ መቃብር ስፍራ ሄዶ ሙታንን ተሳደበ ። በ ሁለተኛው ም ቀን ሂደህ ሙታንን አመስግናቸው አሉት ፤እንዳሉትም ወደ መቃብር ስፍራ ሄዶ ሙታንን አመስግኖ ወደ አበመኔቱ ተመለሰ።አበመኔቱም ሙታን ስትሰድባቸው ሆነ ስታመሰግናቸው ምን አሉህ አሉት ። ወጣኒ መነኩሴዉም ምንም መልስ አልሰጡኝም አላቸው።አበመኔቱም ለ መነኩሴዉም ልጄ አንተም ልብህ ለ ሰዎች ምስጋና ና ለ ሰዎች ስድብ ክፍት አድርገህ ኑር አሉት።"ስለዚህ ኣእምሮህን ገዝተህ ምስጋና ለ መቀበል እንደምንደረደረው ሁሉ ስድብ የ መቀበልን ፀጋ ቢኖረን ከ ከንቱ ውዳሴ መራቅ እንችላለን። መፅሓፍ ቅዱስም እንዲህ ይለናል "ሰዎች ስለሰው ልጅ ሲጠሏችኹ ሲለይዋችኹም ሲነቅፏችኹም ስማችኹንም እንደ ክፉ
ሲያወጡ ብፁዓን ናችኹ እንሆ ሰርቶም በ ሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችኹ ዝለሉም አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።" ሉቃ 6፥ 22 -23 ስለዚህ ክርስትያን ቅን ሰርቶም ለሚመጣበት ዘለፋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል።ከንቱ ዉዳሴ የተሞላን ከሆንን ግን እሄ ማድረግ ይከብደናል።

ለ አንድ ነገር በ ሃላፊነት ስሜት ኣድርጌዋለው ብሎ መናገር ከንቱ ውዳሴ መፈለግ አይደለም። ይልቁ ግን ስለ ችሎታህ ና ስለ ዓቅምህ ከሌሎች የ ምስጋና ችሮታ መጠበቅ ከንቱ ውዳሴ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ በ ቂሳርያ መንፈስቅዱስ የገለጠለትን የ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ሲመሰክር በ ጌታ ዘንድ ሞጎስ አግኝትዋል ። በራሱ ፍቃድ ሲደገፍ የ ወንድሞቹ የ እነ ዮሃንስ ትጋት ግምት ውስጥ ሳያስገባ "ሁሉ ቢተዉህ እኔ እስከ መጨረሻ እከተልሃለው " የሚል ከንቱ ዉዳሴ ፈልጎ የተናገረዉ ንግግር ግን ያመጣው ውጤት መልካም አልነበረም። እኛም ስናገለግል ጌታ በ እኛ እንዲናገር ፈቅደን የ ወንድማችንን አገልግሎት አክብረን ሊሆን ይገባል። ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላቹ ወዮላችሁ"ሉቃ 6፥26 ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን በ ከንቱ ዉዳሴ ተጠልፈክ የሚደረግ እዩኝ እዩኝ ማለት የሚሰጠን በረከት ፤ የሚጨምርልን ፀጋ የለም።ስለዚህ ከ ውዳሴ ከንቱ የ ራቀ ቅን አገልግሎት እንድናገለግል ይገባል።

@ ሄኖክ ታደሰ ,መስከረም 19,2013 ዓ/ም ተፃፈ።
21.3K viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-29 20:18:01 ተወዳጆች ሆይ እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ (፳፻፲፫ ዓም)በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ

የተወደዳችሁ የ"የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ" ቻናል ቤተሰብና ተከታታዮች አገልግሎታችን ይበልጥ ለማስፋት ይቻል ዘንድ ይህን (@popeshenoudaa) ለሌሎች እህቶችና ወንድሞች ወዳጅ ጓደኞቻችን እንዲሁም ግሩፖችና ቻናሎች ሼር እናድርግ

@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa

ይህ ቻናል የአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ትምህርቶች እና አበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታልና ቤተሰቦቻችን በማብዛት አገልግሎቱን እናስፋ። forward እያደረግን ሼር እናድርግ።

@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa

ከእኛ ጋር°°° °°°ይቀላቀሉ
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa
@popeshenoudaa️


አስተያየት ወይንም ጥያቄ ካለዎት ይህንን ይጠቀሙ፦
➙@RomareBot
15.0K views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-29 12:16:50 Channel ከ #1k member በላይ #promotion መግባት ምትፈልጉ ቦታ ስላለ መመዝገብ ትችላላችሁ። @Yaromare
@Yaromare
@Yaromare

ማናገር ትችላላችሁ
12.9K viewsedited  09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-27 07:14:00 "ሀለዉ እለ ይቤሉ ለዕጽኑ ታመልኩ፣ወለዕጽኑ ትገብሩ በዓለ፣ኢቀደሶኑ በደሙ ክቡር ለዕጸ መስቀሉ ወበእንተዝ ናመልኮ /የምታመልኩት ዕጽን (የምትገዙለት ለዕጽ) ነውን? በዓልስ የምታደርጉት ለዕንጨት ነውን? የሚሉ አሉ ።በክቡር ደሙ መስቀሉን ቀድሶት የለምን? ስለዚህ እኛ እንሰግድለታለን ፣እንገዛለታለን"


(መጽሐፈ ድጓ ዘመስቀል)

እንቋዕ አብጸሐነ



13.8K views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-09-26 09:26:50 ​#ንግስት_እሌኒን_እናወድሳት_ዘንድ_ይገባል፡፡ ክብር የሚገባውን የአምላካችንን የጌታችንን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኝ እንደሆነ ብላ በእምነት ለመፈለግ ተግታለችና፡፡

የጌታችን መስቀል ቅዱስ ስጋው የተቆረሰበት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት ከሁሉ የተለየ ከሁሉ የተቀደሰ ሁሉንም የሚቀድስ እንደሆነ አስቀድማ ተገንዝባለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡

ንግስትነቷን በአለማዊ ቅምጥልናና ምቾት ታሳልፈው ዘንድ አልወደደችም ይልቁንስ የተወደደውን መስቀል ትፈልግ ዘንድ በመንፈስ ብርቱ ሆና በስጋ ደከማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

እጅግ የከበረውን መቅደስ ትፈልግ ዘንድ ስትጀምር በራሷ መታመን አልታበየችም ይልቁንስ ሁሉን ስለክርስቶስ ትቶ የወጣ ባህታዊ ኪራኮስን ታማክር ዘንድ ወዳለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

በተዋህዶ የከበረ የአብ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ይዞ እንዳላስቀረው ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳ ሁሉ ክቡር መስቀሉም ተቀብሮ ለዘላለም እንደማይኖርና ከተቀበረበትም እንደሚወጣ አምናለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል።

ከጌታችን መስቀል ጋር የተቀበሩት መስቀሎች ብዙ ናቸው የጌታየን እንዴት እለየዋለሁ? ብላ ሳትጨነቅ የክርስቶስ መስቀል ክብሩን ራሱ እንደሚገልፅ በልቧ ተማምና እስክታገኝው ደክማለችና በእውነት ምስጋና ይገባታል፡፡
14.4K views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ