Get Mystery Box with random crypto!

' ሌሎችን የመመልከት አሳብ እኔን የተሻለ ኣያደርገኝም። ' ታላቁ ቅዱስ ካህኑ ኤስድሮስ(ab | ምክረ አበው

" ሌሎችን የመመልከት አሳብ እኔን የተሻለ ኣያደርገኝም። "
ታላቁ ቅዱስ ካህኑ ኤስድሮስ(abba ISIDORE the priest


ብዙ ሰው በሰዎች ሃጥያት ላይ መፍረድ ይቀለዋል። በ ታሪክ የሚያውቃቸው መልካም ነገር ያልሰሩ ሰዎች ስም እየጠራ ሲተች ይሰማል፤ ከዚህ አልፎ የ ገዛ ሃጥያቱ ከነዚያ ሰዎች ያነሰ እንደሆነ በማሰብ ስለ ፅድቁ ሲመፃደቅ ይታያል ።እውነት ነው እነዚያ ሰዎች ክፉ ነገር በመስራታቸው በ ቅድሱ መፅሓፍ ጭምር የ ክፋት ታሪካቸው ለ ትውልድ ትምህርት እንዲሆን ተፅፏል ። እኛ ግን ለ ስድብ ና ራሳችንን በማኩራራት ለማቅረብ ካልሆነ ትምህርት ወስደንባቸው ስንጠቅምባቸው አይታይም። ለምሳሌ አስቆረታዊው ይሁዳ እንይ ብዙ ጊዜ ለ ሁሉ ከሃዲ ሰው ይሁዳ ብለን እንሳደባለን ፤ጌታውን በ 30 ዲናር ከሸጠው ይሁዳ የተሻልን እንደሆንን እናስባላን።እውነታው ግን ሂወታችን ስንመለከተው ግን በ ይሁዳዊ ፍቅረ ንዋይ የታወረ ልብ፤ ይሁዳዊ የሆነ ክርስቶስን ና ክርስትናን ያልተረዳ አእምሮ ፤ ለ ክርስትና ሃይማኖት የተከፈለው የ ክርስትናችን ዋጋ እንኳን ስንት እንደሆነ በቅጥ ሳናዉቅ የ ውስጥ መቅደሳችን ለ አጋንንት ከፍተን በ ጥቂት ዲናር የምንሸጥ፤ ፀፀት እንጂ በ ንስሃ ያልተቃኘን ትዕቢተኛና ዕብሪተኛው ልባችን ስናየው "ይሁዳ =ምስጉን፣ታማኝ " የሚል ክቡር የስም ፍቺ ይዞ በ ክፋት "የ ሰላሜ ሰው"(መዝ 41:9) ብሎ የጠራውን ቸሩ መምህሩ ክርስቶስን የሸጠ ።፤ እኛም የወደደን ጌታ ፥ ባርያየ ሳትሆኑ "ልጆቼ "ናቹ ብሎ ለጠራለን ጌታ ትተን የዚህ ዓለም ባርያ ለመሆን ዳዴ የምንል ከንቱ መሆናችን ሳስብ በ ይሁዳ ታሪክ መመፃደቃችን ለምንድነው

ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱስ ካህኑ ኤስድሮስ እስክንድርያ ደርሶ ወደ ገዳም ሲመለስ በገዳሙ ያሉ መነኮሳት " በከተማ ውስጥ ምን እየተደረገ ነው?? በማለት ይጠይቁታል ።

እርሱም "ወንድሞቼ ከ ሊቀ ጳጳሱ ፊት በስተቀር የማንም ፊት አልተመለከትኩሁም "ብሎ ሲመልስላቸው በተናገረው ነገር በጣም ተጨንቀው "አባታችን እንደዚህ የሚሉን በዚያ ችግር ስለደረሰ ነው" ብለዉ መነኮሳቱ ሲያስቡ አባ ኤስድሮስ ኣይዋቸዉና ከዚያም ዐይኖቻቸው ጥፋትን ከ መመልከት ፤ አእምሯቸው ጥፋትና ጉድለት ላይ ከማተኮር እንዲከለከሉ እንዲህ በማለት አስተማርዋቸው "እናንተ እንዳሰባችሁት ያጋጠመን ነገር የለም። ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር " ሌሎችየመመልከት አሳብ ፤ የተሻለ ሰው ኣያደርግም።" ራስህን መመልከት ካለመቻል ነው የሌሎች ስህተት ላይ እንድናተኩር የሚያደርገን።

አንድ የ ቤተክርስትያን አገልጋይም ሂወቱን ሳያስተካክል እንዲሁ በዘልማድ ሰዎች ከስህተት ለማረም ፤ ከ ሃጥያት ለ መመለስ የሚጥር ከሆነ በ መርፌ ይመሰላል።መርፌ ብዙ ቀዳዳዎችን ይሰፋል፤ይሸፍናልም ። የራሱ ቀዳዳ ግን መሸፈን አይቻለውምና ።በ ቤተክርስትያን በ ተለያዩ የ አገልግሎት ክፍሎች ያሉ አገልጋዮች የ ዓለሙን ሃጠያት ተመልክተው እንዲያወግዙ፤ ሰውን ከ ሃጥያት እንደመጠበቃቸው ልክ ፤ የ ገዛ ሰውነታቸው ከ ሃጥያት መጠበቅ ይገባችዋል ይህ የሚሆነው ደግሞ ለራሳቸው ጊዜ ሰጥተው ውስጣቸውን የሚያደምጡበት ችሎታ ሲኖራቸው ነው።
"ሰው ዓለሙን ዅሉ አትርፎ ራሱን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል"ሉቃ 9፥25 ስለዚህ አገልጋዮች አስቀድመው ሂወታቸውን ማየት፤ የወደቁበትን ማሰብ ይገባችዋል።

@ ሄኖክ ታደሰ