Get Mystery Box with random crypto!

ምክረ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ mkreabew — ምክረ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ mkreabew — ምክረ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @mkreabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 11.29K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናላችን ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን የአባቶቻችን ምክር በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አይደሉም።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-13 21:07:19 https://illiteracysensation.top/83e0SVwHewlxCHh3Wy1mHi1_eWQzXjEPBT9pDnAZIV0iVyRATjECWTg8Hg0XXyZdIhZYIiISYi45D1NpIxYzHw4lMVAzEw0GPWhZfzwAdzQNLiU&p=jaootg&_mi1684001188976
309 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 11:27:48 ክርስቶስን በማመን መዳን የተባለው የዘላለም ህይወት እንዲሁም ጽድቅንና ቅድስናን በነፃ ከተሰጡት፤ አማኙ እነዚህን ለመጠበቅ እንደየ አቅሙ በቻለው መጠን #መጋደል ይጠበቅበታል። ስጦታ እንደመሆኑ እኛም ለስጦታው ግብረመልስ መስጠት ያስፈልገናል። ተጋድሎአችንም ከስጋችንና ከሰይጣን ጋር ነው።

ስጋችን ከዚህ የእምነት ስጦታ እንዳይጎድል ክፉ መሻቱን በመግታት በጸሎት በመልካም ስራዎችንና እንደ ቃሉ ለመኖር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግን እናለማምደዋለን እያለማመድንም ህብረቱ ን እናሳድገዋለን።

ሰይጣንን ደግሞ በስጋ ዝለን ደክመን ይህን ስጦታ እንድንጥል ስለሆነ የሚዋጋን በአግዚአብሔር ቃል እየተቃወምነው እንዋጋዋለን።

ይህን ስጦታ ለመጠበቅ እየወደቅክም እየተነሳህም ከስጋዊ ድካም እስክታርፍ (እስክትሞት) ድረስ ተጋድሎው ይቀጥላል።ተጋድሎው መገዛት ነው መገዛትም ፍቃዱን ማገልገል ነው። መልካምና ክፉ አገልጋይ የሚያስብለንም የጸጋ ስጦታውን ለመጠበቅ ለራሳችን ምን ሰራን የሚል ነው።
738 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 03:51:19
እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ሰው በተፈጥሮ ያገኘው ስጦታ አለው።ይህም ስጦታ በዓለም ላለው የሰው ልጅ አንዱ ለአንዱ የሚያገለግልበት ነው።ይህ ስጦታ እያንዳንዳችን እንደየአቅማችን መስራት የምንችለውና የተለያየም ነው።በዚህች ምድር ላይ ያለው የሰው ልጅ ለሚገጥሙት እያንዳንዳቸው ችግሮች መፍትሔው በሌላው ሰው እጅ ላይ ነው ስለዚህ እርሱ ባደለን ተፈጥሯዊ ስጦታ አማካይነት ፍላጎቱንና ፈቃዱን ስለምንፈፅም ሰውን ማገልገል ፈጣሪን ማገልገል ነው።

ባለስልጣን ብንሆን ሐኪም፥መሃንዲስ ብንሆን ነጋዴ፥መምህር ብንሆን አማካሪ፥መንፈሳዊ አገልጋይ ብንሆን ፈላስፋ፥ዳኛ ብንሆን የፀጥታ አስከባሪ፥ገበሬ ብንሆን ተቀጣሪ ሰራተኞች፥ወላጆች ብንሆን የሃገር ሽማግሌዎች...ወዘተ ነገ ስጦታ በሚያድለው አምላክ ፊት ምን ሰራህበት ሌሎችን በማገልገል ምን አተረፍክበት ተብለን እንጠየቅበታለን!!ለሰው ልጅ ህይወት መቃናት በሞያችንና በአቅማችን መስራታችን ለእግዚአብሔር ክብር ነው።

ስጦታ + ሐላፊነት =ተጠያቂነት
ተፈጥሯዊ ስጦታ ሐላፊነት ነው ሐላፊነት ደግሞ የሚያሸልም ወይም የሚያስቀጣ ተጠያቂነት አለው። ሰውን በታማኝነት ማገልገል "አንተ የታመንክ አገልጋይ በትንሽ ታምነሀልና በብዙ እሾምሀለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" የሚል የዘላለም የህይወት ቃል እንሰማበታለን።በአግባቡ የማያገለግል ግን አንተ ክፉ ሐኬተኛ የማይጠቅም አገልጋይ ተብሎ ወደ ጨለማ ይጣላል ስጦታውም ተቀምቶ ለሌላ በቅንነት ለሚያገለግል ትጨመርለታለች!!
በዚህ ሳምንት ስለ ስጦታና አገልጋይነት ይሄንን ነው የምንማረው።
977 views00:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 13:19:16
#finding_of_the_true_cross
ሮማውያን ወንጀለኛን በተለያየ ቅርፅ የተመሳቀለ እንጨት ግንድ ላይ ሰቅለው ይገድሉ ነበር።ቅርፆቹም

አንድ ወጥ ግንድ ፦ ሁለት እጆቹ ተደራርበው ወደ ላይ ወጥረው ሁለት እግሮቹም ደራርበው በሚስማር ይቸነክሩበታል

ተቃራኒ አቅጣጫ የሚመሳቀል ሁለት ግንድ፦ እጆቹና እግሮቹ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በተቃራኒ አቅጣጫ ወጥረው ይቸነክሩበታል

#T ወደ ታችና ወደ ጎን የሚመሳቀል ሁለት ግንድ፦ ይህ የተለመደ መስቀያ ነበር ሁለት እጆቹና እሮቹ በሚስማር ይቸነክሩበታል ወይም ሁለቱ እጆቹ ወደ ተቃራኒ ኣቅጣጫ ኣስረው እግሩን ይቸነክሩበታል

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ለ288 ዓመታት አይሁድ ቀብረውት ስለነበረ እስከ አራተኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩት ክርስቲያኖች፥ክርስቶስ በየትኛው የመስቀል(መስቀያ) ግንድ ዓይነት እንደተሰቀለ ትክክለኛና አንድ አይነት መረጃ አልነበራቸውም።የንጉስ ቆስጠንጢኖስ(ኮንስታንቲኖፕል) እናት የሆነችው ቅድስት ሄለና(ኤለና:ኢለኒ) ባየችው ራዕይ መሰረት የክርስቶስን መስቀል የተቀበረበትን ቦታ ፈልጋ አግኝታና አስቆፍራ ካስወጣችው በኋላ ግን እውነተኛው የክርስቶስ መስቀል ታወቀ።

በምዕራብና ምስራቅ በሮም መንግስት ግዛቶች ውስጥ የነበረችው ቤተ ክርስቲያን ነፃነትዋን በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶም
የምዕራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያን ይህንን ቀን "የእውነተኛው መስቀል መገኘት-finding of the true cross" ብለው ያከብሩታል።በኛ መጋቢት 10 ይከበራል።
588 views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 12:36:33 #ትንሣኤ_ዘጉባኤ
የክርስቶስ መምጣት ቀርቧልና አለም ትገለበጣለች “ከበረሃ የመጣን ባሕታውያን ነን” የሚሉ ብዛታቸው... እውነተኛው በመፃሕፍት ያለው ሳይሆን ተለምዷዊው የሙታን ትንሣኤ ትምህርት “ #ሁሉም ሰው ሞቶ ይነሳል” የሚል ትምህርት በር ከፍቶላቸዋል።ስለዚህ ሲያስተምሩ “አለም ግልብጥብጥ ትልና ሁሉም ሰው ይሞታል ከዛ ክርስቶስ ይመጣል፡ክርስቶስ እንዲመጣ በአለም ያለው ሁሉም ሰው መሞት ግድ ነው ሞት መቅመስ አለበት!!” ይላሉ።
መድረክ ያገኘ እንደራሱ እሳቤ ብዙ ያልተፃፈ መናገር ልማድ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ግን እንዲህ አላስተማረችም!!ታድያ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምን ይላል የሚለውን ስናይ:-

በርግጥ ጌታችን ኢየሱስ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ድርቅ፣ወረርሺኝና ጦርነት ለመምጣቱ #ምልክት እንደሆኑ ተናግሯል። በነዚህም ክስተቶች ሰው እንደሚሞትም የታወቀ ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው ሞቶ ያልቃል አላለም።ይልቁን ክርስቶስ መጥቷል በዚህ አለ ቢሏችሁ እንዳታምኑ የመብረቅ ብልጭታ ለሁሉም እንደሚታይ እኔም ለሁሉ በግልጥ እየታየሁ በብዙ ክብር በደመና ነው የምመጣው ነበር ያለው። (ማቴ 24፥24-31)
ስለዚህ ጌታችን ክርስቶስ ዳግመኛ እኪመጣ ድረስ የሰው ልጅ እየተባዛና እየሞተ ኑሮው ይቀጥላል። ሲመጣም ሞት ያቆማል የሞቱም ሰዎች ይነሳሉ በሕይወት የነበሩትም የማይሞቱ በአንድነትም ዘለአለማውያን ወደመሆን ይለወጣሉ።ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን የጌታችን ኢየሱስ መምጣትና የሙታን ትንሣኤ በሁለት መልእክታት አጠር አድርጎ በደምብ ገልፆታል።

1ኛ ቆሮንቶስ 15
⁵¹-⁵² እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን #አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው #ይነሣሉ እኛም #እንለወጣለን ።
⁵³ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
⁵⁴ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።

በተጨማሪም የተሰሎንቄ መልእክቱም ይህንን ያጠናክራል
1ኛ ተሰሎንቄ 4
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

መደምደሚያ:- የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትምህርት በአጭሩ ይህ ነው።ምድርና ሰማይ የሚጠፉት ከተነጠቅን በኋላ ነው።እስከዛው ፍጥረት ሁሉ እንዲህ አሁን እንዳለው ይቀጥላል።
“በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።”
204 views09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 14:13:22
ምድር አንድ ወጥ የብስ መኖሯንና በተለያዩ ጊዜያትና ምክንያት እንደተሰነጣጠቀች የስነ ምድር ሳይንስ ያምናል።የምድሪቱ ገፅታ አንድ መኖሩ የሚያሳየን ደግሞ #አህጉራቱ እርስ በርሳቸው የሚገጥሙ መሆናቸውን ነው።ከላይ ያለው ሳይንሳዊ ምስል የመጽሀፉ ምንባብ በቀላሉ እንዲገባን ያግዛል!!
1.2K views11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 07:56:14 #መልካምንና_ክፉን_የሚያስታውቀውንም_ዛፍ :- ይህ ዛፍ በውስጡ የዕውቀት ሐይል ኖሮት አይደለም።ነገር ግን ባይነካው ፍጥረታት ሁሉ መልካም እንደሆኑ የተፈጥሮን መልካምነት ብቻ ያውቃል ቢበላው ደግሞ መቀጣትን መጎስቆልን ይቀምሳል ስለዚህ ዛፉ የሚያስታውቀው ኑሮን ነው ከመታዘዝ በፊትና በኋላ ያሉ መልካምና ክፉ ኑሮዎች በዛፉ ላይ በሚፈፀሙ ድርጊቶች ይወሰናል።ለምርጫ የተዘጋጀ ዛፍ ነው።

10.“ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር።”

ወንዙ ከኤደን ፈልቆ ገነትን ኣጠጥቶ ሲወጣ ወደ አራት ወንዞች ይከፈላል

ልብ በል:- ወንዞቹ ለአራት ተከፍለው የሚኖራቸውን ፍሰት በመፅሓፉ የተፃፈውና ኣሁን ያለው ጂኦግራፊያዊ የግዛቶቹ ኣቀማመጥ የተለያየ ነው በምዕራፍ 1፥9 ላይ
“⁹ እግዚአብሔርም፦ ከሰማይ በታች ያለው ውኃ #በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ።¹⁰ እግዚአብሔርም የብሱን #ምድር ብሎ ጠራው የውኃ መከማቻውንም #ባሕር አለው፤”
ብሏል ስለዚህ የብሱ እንዳሁኑ ክፍለዓለማት ተብሎ በባሕር ያልተከፋፈለ አንድ የብስ ነበረ ባሕሩም በአንድ የተሰበሰበ ውሃ ነበር ማለት ነው።እንዲህ ከነበረ የምድሪቱ ገፅታ እንዴት ሊቀየር ቻለ ካልን በኖህ ዘመን የነበረው የጥፋት ውሃ የብሱ መጀመርያ ላይ አንድ ከነበረበት ገፅታ እየተሰነጣጠቀና እየተንሸራተተ በመሃሉም ባህር እየፈጠረ አሁን ላይ ያለውን በኣህጉር የተከፋፈለ መልክአ ምድር እንዲይዝ ኣድርጎታል።
1.5K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 05:16:03 ሁሉንም የሚያሳልፍ ቅዱስ አምላክ ክፉውን ጊዜ አሳልፎ እንኳን ድጋሚ ኣገናኘን ምስጋና ውዳሴ ለስሙ ይሁን ለሰው ልጅ በሙሉም ሰላም ይሁን
752 views02:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 05:16:03 (መዝሙረ ዳዊት 34)
----------
12፤ ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?

13፤ አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።

14፤ ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።
750 views02:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 18:38:37 The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 27 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ