Get Mystery Box with random crypto!

የእግዚአብሔር ፀጋ- THE GRACE OF GOD👑

የቴሌግራም ቻናል አርማ one_way_he — የእግዚአብሔር ፀጋ- THE GRACE OF GOD👑
የቴሌግራም ቻናል አርማ one_way_he — የእግዚአብሔር ፀጋ- THE GRACE OF GOD👑
የሰርጥ አድራሻ: @one_way_he
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.63K
የሰርጥ መግለጫ

⏩የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
⏩ዝማሬዎች
⏩የተለየ ስነ ጹሑፍዎች ,ስብከቶች,ምስሎች
⏩እንዲሁም ሌሎች ብዙ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች አሉን
ወንጌልን በማህበራዊ ድህረገፅ ላይ እንስበክ።
https://www.instagram.com/invites/contact/?i=1sv9qzb281lw
Tiktok https://vm.tiktok.com/ZMeFsNuu6/
ለአስተያየት እንዲሁም መልዕክት ለማስተላለፍ 👉 @The_grace_bot 👈

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 08:43:13 መስታወት.....

ብዙዎቻችን መንፈሳዊ ዓለም የማይነካና የማይጨበጥ ይመስለናል ልንረዳ የሚገባው ነገር ግን መንፈሳዊው ዓለም ከስጋዊው ዓለም በላይ እውነተኛና የበለጠ ተጨባች መሆኑን ነው።

ንፋስ ስላላየነው የለም እንደማንለው ሁሉ መንፈሳዊውን ዓለም ስላላየነው የለም ማለት አንችልም ምክንያቱም ሳናየው ተፅዕኖውን ስለምናየው ነዉ።

እግዚአብሔር የሚነካ ነገር ሆኖ ከመንፈሳዊ ዓለም የሰጠን ትልቁ መሳሪያ መፅሐፍ ቅዱስ ነው።

“ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤”
— ያዕቆብ 1፥23

#ቃሉ_ለመንፈሳዊው_ዓለም_መስታወት_ነው_!

ብዙዎቻችን መንፈሳዊው ዓለም ምን እንደሆነ እንገምታለን እግዚአብሔር ግን እንዳንገምት በመጽሐፍ ጽፎ አስቀምጦልናል።

ስለዚህ ክርስቲያን በግዑዙ ዓለም የሚኖረው ሕይወት የሚወሰነው መንፈሳዊውን አለም ባወቀውና በተረዳው ልክ ነው።

ለዚህ ነው ክርስቲያን ለቃሉ ጊዜና ዋጋ ሊሰጥ የሚገባው ምክንያቱም ቃሉ ምርኮአችንን እና ርስታችንን ይሰጠናል።

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።”
— መዝሙር 119፥162

ብዙ ሰዎች ስኬት ከስራ ቦታ የሚጀምር ይመስላቸዋል ነገር ግን ስኬት የሚጀምረው ከስጋዊ ዓለም ሳይሆን ከመንፈሳዊው ዓለም ነው!

መልካም ቀን


https://t.me/One_way_He
18 views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:40:58 '' እግዚአብሔር ጨርሶ የሚጀምር
ጀምሮ የሚጨርስ ድንቅ አምላክ ነው!! ''




ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!

#ELDAAH-KNOWLEGE OF GOD


JOIN US


@ONE_WAY_HE
@ONE_WAY_HE
@ONE_WAY_HE
@ONE_WAY_HE

ይ ላ ሉ


https://t.me/One_way_He
116 views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:16:23

84 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:14:18
56 views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:56:22 ፀሎት አፅናፈ አለምን ከፈጠረና ከሚቆጣጠር፣ እንዲህ ታላቅ ሆኖ ሳለ ደግሞ ዝርዝርና ትናንሽ በሆኑ የሕይወታችን ክፍሎች ውስጥ ሳይቀር ድርሻ እንዲኖረው ከሚሻ የፍቅር አምላክ ጋር የምናደርገው ጥልቅ ውይይት ነው፡፡
እግዚአብሔርን መቅረብም ሆነ ማነጋገር የምንችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ በኩል ብቻ ነው። የትኛውም መልካም ስራችን ቅዱሱ እግዚአብሔር ፊት ሊያቀርበን እንደማይችል መረዳት ይኖርብናል፡፡ በፀሎት ወደዚህ ቅዱስ አምላክ  ፊት መቅረብን እንደ ታላቅ እድል መቁጠር ይኖርብናል፡፡





“ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ዝግጁ ሁን፤ በታላቅ ትዕግሥትና በማስተማር አቅና፤ ገሥጽ፤ አበረታታም።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2



ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!

#ELDAAH-KNOWLEGE OF GOD


JOIN US


@ONE_WAY_HE
@ONE_WAY_HE
@ONE_WAY_HE
@ONE_WAY_HE

ይ ላ ሉ

ለአስተያያት ሆነ ለጥያቄ
https://t.me/Neri_God
103 views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:37:36
134 views04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:35:11 "እግዚአብሄር ይቅርታ አድራጊ ነው" መዝ 103፥6

የእውነት እግዚአብሄር ይቅርታ አድራጊ ነው። ይቅርታም ሲያደርግ አመንትቶ አይደለም ከባህሪው ነው። ሰው ይቅርታ የሚለው በደልን ደብቆ ይዞ ነው፤ ደግመን ስንቀያየም ከዚህ በፊትም እንዲህ አርገኸኝ ነበር ይላል እግዚአብሄር ግን ደግመን እንደምንበድለው እንደምናስቀይመው እያወቀ ይቅር ይለናል።እርሱ ብዙ እድል ይሰጠናል ሰው ግን የመጨረሻ እድል ይሰጠናል ከዚህ በኃላ ይህ የመጨረሻ እድልህ ነው ይላል እግዚአብሄር ግን ብዙ እድል ይሰጠናል። የመጨረሻ እድል የማይሰጥ ሁሌም የይቅርታ ልብ ያለው አባት ስሙ ይባረክ። ጴጥሮስን አስቡት ሽምጥጥ አርጎ እየካደ ይቅርታን ያገኘ ዳግመኛ እድልን ያገኘ ሰው ነው። ብዙ መገለጥና መገልበጥ በህይወቱ ያየው ጴጥሮስ አንተ ከሀዲ ነህ ሳይለው ግልገል ጠቦት ለማሰማራትም እረኛ አደረገው። በትላንት ስህተታችን ሳይሆን ነገን አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ጉዞን የሚያስጀምር ጌታ ነው።ይቅርታ የሚጠይቀው ሰው የበደለው ብቻ አይደለም።በአለም ስርዓት በዳይ ይቅርታ ይጠይቅ ይሆናል በክርስትና ግን ተበድሎም ይቅርታ ይላል።ትክክል
ብትሆንም ይቅርታ መጠየቅ ወሳኝ ነገር ነው።ይቅርታ መጠየቅ ያለብህ የተሳሳተ ነገር በማድረግህ ሳይሆን የተሳሳተ ስሜት በመፍጠርህ ነው እርሱም ቅሬታ ነው።ትክክል ሆነህ የተሳሳተ ስሜት ከፈጠርክ የሚስተካከለው በይቅርታ ሀይል ነው።ትክክል ብትሆንም ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ ያለብህ ክርስቲያን ስለሆንክ ነው ሲቀጥልም ቅሬታው አንተ የፈጠርከው የተሳሳተ ስሜት በመሆኑ ነው።ስለዚህ ይቅርታ የምትጠይቀው ስለተሳሳትክ ሳይሆን ትክክል ብትሆንም ለቅሬታው መፈጠር የአንተ አስተዋፅኦ የመኖሩን ያህል ቅሬታውን ለማጥፋትም የአንተ አስተዋፅኦ መኖር ስላለበት ነው። "በምድር ላይ መድሀኒት የታጣላቸው በሽታዎች የሚፈወሱት በይቅርታ ነው"።
እስቲ ሁለት በጣም የሚዋደዱ ፍቅረኛሞችን አስቡ እነዚህ ሁለት ፍቅረኛሞች የሚዋደዱት መሀላቸው ግጭት ስለማይፈጠር ወይም ስለማይጣሉ አይደለም ይቅርታ ስለሚባባሉ ነው።የተጎዳው ፍቅር የሚስተካከለው በይቅርታ ሀይል ስሜት ሲጠገን ነው።የጉዋደኛ ልብ የስሜት ሸራ ነው።ስትፈልግ ፍቅርን ሳትፈልግ ጥላቻን ትስልበታለህ።ጥላቻ ስእል ሳይሆን የልብ መጎዳት ነው።ፍቅር ግን ልብን የሚያሳምር ያማረ ስዕል ነው።ስዕሉ የሚደበዝዘው በቆሸሸ ብሩሽ ተነካክቶ በቅሬታ ስሜት ፍቅር ሲደበዝዝ ነው።ቅሬታ ማለት ፍቅር ተበላሽቶ የሚፈጠር የተሳሳተ ስሜት ነው።ቅሬታውን ወደ ፍቅር ለመመለስ የሚቻለው በይቅርታ ላጲስ የተሳሳተውን ስሜት ማጥፋት ሲቻል ነው።ቅሬታ ልብ ላይ ለመቆየት የራሱ አቅም የለውም።ቅሬታ የተሳሳተ ስሜት ሆኖ ልብ ላይ የሚቆየው በይቅርታ ላጲስ ጠፍቶ በፍቅር እስኪተካ እንዲሁም ልብ በጥላቻ ተጎድቶ ቅሬታን መሸከም የማይችልበት ደረጃ እስኪደርስ ነው። ይቅርታ የአራት ፊደሎች ጉዳይ ብቻ አይደለም። ያቆሰልነውን ልብ የምናክምበት ለቁስሉ የፈውስ ዘይት የሚሆን አካል ያለው ቃል ነው።እስቲ ልባችሁ ይቅርታ ያላደረገላቸውን ውስጣችሁ የሚርመሰመሱትን ሰዎች አስቡ ለነዚህ ሰዎች ዛሬ የይቅርታ መድረክ ዘርጉላቸው ይቅርታ አድርጉላቸው በእውነት ትታደሳላችሁ ውስጣችሁ ያርፋል ሰላም ያገኛል።መፅሀፍ በ 1ኛ ቆሮ 2፥16 ላይ "እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን" ይላል ታዲያ የክርስቶስ ልብ ምን አይነት ነው ይቅርታ አድራጊ ነው ያውም እየሞተ ይቅርታ የሚለምን ነው። ይቅርታ ማድረግ እስካልቻልን ድረስ የክርስቶስ ልብ የለንም ምክንያቱም የክርስቶስ ልብ ከፊል ደመናማ አይደለም ምሉዕ ብርሀን እንጂ።
የይቅርታ ቀን ይሁንልን



መልካም ቀን!!




ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!



https://t.me/One_way_He
123 views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 05:56:53 የማጉረምረም ውጤት...

ማጉረምረም ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ለፈለስን ለእኛ ፈጽሞ የማይገባ እና ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው።
ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር:

“እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ለራሱ የለያችሁ ሕዝብ ናችሁ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9 (አዲሱ መ.ት) ይላል

#የተጠራነው_ለማመስገን_እንጂ_ለማጉረምረም_አይደለም!

ሁል ጊዜ የሚያጉረመርም ሰው ለመልካም ነገሮች አይኑ የታወረና በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚያይ ሰው ነው።
የሚያጉረመርሙ ሰዎች የሚፈልጉት ነገር አጠገባቸው(ውስጣቸው) እያለ ያን ፍለጋ አገር ያስሳሉ። ጆሮአቸው ላይ እርሳስ አስቀምጠው እርሳሱን ኪሳቸው ውስጥ ይፈልጋሉ። አጉረምራሚዎች በእጃቸው የያዙትን ነገር በመፈለግ ብዙ ጊዜ ይባክናሉ። በዙሪያቸው መልካም ነገር ሲመጣ አነርሱ እያጉረመረሙ አልፏቸው ይሄዳል።

“በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤”
— ፊልጵስዩስ 2፥14-15

ማጉረምረም በሕይወታችሁ ላይ ብዙ ነገሮችን አንድታጡ ያደርጋችኋል። ከዛም በተጨማሪ የእግዚአብሔርን ሕልውና ሳይሆን የአጋንንትን ሕልውና በሕይወታችሁ እንዲመጣ ያደርገዋል።

“ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።”
— መዝሙር 50፥23

ስለዚህ በማጉረምረም የጎደለውን ሕይወታችን በምስጋና እንሙላው!



መልካም ቀን!!




ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!



https://t.me/One_way_He
103 views02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 05:51:13 ''ችግር ውስጥ ካላችሁ ፤ በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ጩሁ!!''




መልካም ቀን!!




ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!



https://t.me/One_way_He
105 views02:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:08:23 ልጅነት

ልጅነት የህብረት ውጤት ነው። ወንድና ሴት ህብረት ሲያደርጉ ልጅ ይወለዳል። የቃሉ ዘርና መንፈሱ ሲገናኙ መንፈሳዊ ልጆች ይገኛሉ። ከእግዚአብሄር ለመወለድ ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት ያስፈልጋል።
ልጅነት ጥልቅ የሆነ ማሰሪያ ነው። የልጅነትን ማሰሪያ በፍቃድ መቁረጥ አይቻልም። መሰረቱ ተፈጥሮ እንጂ ፍላጎት አይደለም። አባት የቀየረ ሰው አለ? እርግጠኛ ነኝ ማንም የለም። እኛም እግዚአብሄር በቃኝ ማለት አንችልም።
ልጅነት ጥልቅ ፍቅር ነው። የልጅነትን ፍቅር መሰረቱን ማግኘት አይቻልም ጥልቅ ነው። ልጆች አድካሚ ናቸው አይደል? የወለዳችሁ ወላጆች ታውቁታላችሁ ግን ፍቅር ድካሙን እንኳ እንዳትቆጥሩት አድርጓችኃል።
ልጅነት በነፃ መወደድ ነው። እግዚአብሄር በነፃ ሲወደን ልጆቹ አደረገን። ልጅነት የቤተሰብና የአለም አባል የምንሆንበት ነው። አንድ ልጅ በተወለደ ቅፅበት ለቤተሰቡ አባል ለአለም ደግሞ ዜጋ ይሆናል። ከእግዚአብሄር ስንወለድ በአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባል በአለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን ደግሞ ዜጋ እንሆናለን።
ልጅነት የእምነት ኑሮ ነው
ልጆች ከቤተሰብ ጋር የሚኖሩት በእምነት ነው ቤተሰቦቻችን ቢያጡ፣ ቢነጡ ፣ ቢቸገሩ ብለው አይሉም ።
በባዶ ካዝና ብዙ ነገር ያዛሉ። የነርሱ ቤተሰብ በአለም ላይ ካሉ ቤተሰብ ባለፀጋ ሁሉን ማድረግ የሚችሉ የመጀመሪያ አድርገው ነው የሚያስቡት። አባታቸውን አውሮፕላን ግዛልኝ የሚሉ ልጆች አሉ አባትዬው ትንሽዬ ነገር የመግዛት አቅም አይኖረው ይሆናል እኮ ልጆቹ ግን የኔ አባት የሚነሳው የለም ብለው ያስባሉ። እግዚአብሄርም እንደ ልጆች ካልሆናችሁ የሚለው ይሄንን ነው የኔ አባት እግዚአብሄር ምንም አይሳነውም እንዲህ ብለን እንድናምን እግዚአብሄር ይፈልጋል።
የማንታመነውን እኛን ልጆቻችን ይሄን ያህል ካመኑን እኛስ እግዚአብሄርን ይሄን ያህል እናምነው ይሆን።

ብዙ ጊዜ የተለያዩ ዜናዎችን ስትሰሙ ከመርከብ ከአውሮፕላን አደጋ የሚተርፉት ብዙ ጊዜ ህፃናት ናቸው። በዛ አደጋ ወቅት ራሳቸውን ለማዳን የሚያደርጉት ሁኔታ የለም ጥረት በማያድንበት ሁኔታ ትልልቁ ሰው ጥረት ሲያደርግ መስኮት ከፍቶ በር ከፍቶ ራሱን ይጥላል ህፃናት ግን በአደጋ ውስጥ እንኳ በእምነት በሰላም ነው ያሉት በአደጋ ውስጥ በእናት እቅፍ ውስጥ እንደተኛ ህፃን በብዙ አደጋም መከራ ውስጥ በእግዚአብሄር እቅፍ መሆን ያስፈልጋል።




መልካም ቀን!!




ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!



https://t.me/One_way_He
172 views10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ