Get Mystery Box with random crypto!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hu_main_campus_gibi_gubae — ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hu_main_campus_gibi_gubae — ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ
የሰርጥ አድራሻ: @hu_main_campus_gibi_gubae
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.35K
የሰርጥ መግለጫ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን ሀዋሳ ማዕከል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ መደበኛ ቻናል
በዚህ ቻናል
👉 ትምህርታዊ ጽሑፎች
👉 የግቢ ጉባኤ መልዕክት
👉 የክፍላት ማስታወቂያ ይተላለፍበታል።
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ከታች ባለው አድራሻ ይላኩልን
👇👇👇
@ZHawassa_GGbot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-20 06:03:15 ዲ/ን ዘአማኑኤል ገዛሀኝ

ሁለቱ ጸሐፍያን በደብረ ታቦር

እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ሦስቱ ወንጌላውያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን ምስጢር አዘል ታሪክ በተመሳሳይ ሁኔታ መዝግበዋል ። ምንም እንኳን ሶስቱ ወንጌላውያን በደብረ ታቦር ተራራ የተከናወነውን ድንቅ ክስተት ቢመዘግቡም የተለያየ የታሪክ አጻጻፍ ተክትለዋል ። አንዱ ያጎደለውን አንዱ አንዱ እየጨመረ ፣ አንዱ የረሳውን አንዱ እያስታወሰ ጽፈዋል ። ማቴ 17 ፥ 1-9 ፣ ማር 9 ፥ 2 - 10 ፣ ሉቃ 9 ፥ 28 -36

ይህን የደብረ ታቦር ታሪክ በተመለከተ የሶርያውያን ፀሐይ ፣ የኤዴሳው ዲያቆን ቅዱስ ኤፍሬም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮት የተገለጠበት ተራራ ላይ የተፈጸመውን <> << የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ ፤ ቅዱሱ ሙሴ ቅዱስ ጴጥሮስን አየው የአብ እንደራሴ የወልድን አገልጋይ ተመለከተው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ድንግል ኤልያስ የሐዲስ ኪዳኑን ድንግል ዮሐንስን አየው፡፡ በእሳት ሰረገላ ላይ የተሳፈረው ኤልያስ ወደ እሳታዊው ክርስቶስ ደረት የተጠጋውን ዮሐንስን አየው፡፡ የታቦር ተራራ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ሆነ ፤ ክርስቶስም ሁለቱን ኪዳናት አዋሐዳቸው!’ >> በማለት በንጽጽር ድንቅ ምስጢር ይነግረናል ።
​​
ቅዱስ ኤፍሬም<< የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የሐዲስ ኪዳን ጸሐፊዎችን አዩ>> በማለት የሙሴንና የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስን ነገር አነሳ ። ለምን? ብለን መጻሕፍትን ስንመረምር <<ዓለሙም በእርሱ ሆነ >> ብሎ የተናገረው የሐዲስ ኪዳኑ ዘፍጥረት(የዮሐንስ ወንጌል) ጸሐፊ ከብሉይ ኪዳኑ የኦሪቱ ዘፍጥረት ጸሐፊ ጋር ተገናኝቷልና ። << በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ > ብሎ የሥነ ፍጥረትን መነሻ የጻፈው ቅዱስ ሙሴ << በመጀመርያ ቃል ነበር ብሎ >> ብሎ ፍጥረት የተፈጠረበት የቃልን ነገር ከተናገረው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ተገናኝቷልና ። ስለ መላእክት መፈጠር ያልተናገረው ሙሴ << ሁሉ በእርሱ ሆነ >> ብሎ ነገረ ፍጥረትን ጠቅልሎ ከጻፈው ዮሐንስ ጋር ተገናኝቷልና ። << ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር። እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ ( Darkness, Light, and Life)>> ብሎ የጻፈው ሙሴ << በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።(Life, Light, and Darkness)>> ብሎ ከጻፈው ወንጌላዊው ጋር ተገናኝቷልና ።

<< ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት በበደል መሥዋዕት በግ ያስተሰርይለታል የሠራውም ኃጢአት ይቀርለታል።>> ብሎ የእስራኤል ዘሥጋን ኃጢአት ስለሚያስተሰርየው በግ የጻፈው ሙሴ << እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።>>ብሎ የእስራኤል ዘነፍስን ኃጢአት ስለሚያስተሰርየው የእግዚአብሔር በግ ከጻፈው ወንጌላዊ ጋር ተገናኝቷልና ። << ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።>> ተብሎ ምስጢር የተሰወረው ሙሴ <<ኢየሱስም ይወደው የነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ደረት ላይ ተጠጋ፤>>ተብሎ ምስጢር ከተገለጠለት ዮሐንስ ተገናኝቷልና ። የኤደን ገነቱ የሰርግ ታሪክ ጸሐፊ ከቃናው የሰርግ ታሪክ ጸሐፊ ተገናኝቷልና ። የብሉይ ኪዳኑ ወንጌል(ዘፍጥረት ) ጸሐፊ ሙሴ <<አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ >> አየም ደስም አለው።>>ብሎ ኦሪት ሳትሰራ ወንጌል እንደነበረች ከመሰከረለት ወንጌላዊ ዮሐንስ ጋር ተገናኝቷልና ። ስለዚህም በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ጸሐፊ የሐዲስ ኪዳኑን ጸሐፊ አየ ።

እግዚአብሔር አምላክ ልቡናችንን የታቦር ተራራ አድርጎ በመለኮታዊ ብርሃኑ እንደ ሊቀ ነቢያት ሙሴ አእምሮአችንንና ማደሪያ ቤተመቅደሱ የሆነውን ሰውነታችንን ያብራ፡፡ መለኮታዊው ብርሃኑም ለአእምሮአችን ማስተዋልን በመጨመር በጽድቅ እንድንመላለስ ያብቃን ለዘለዓለሙ አሜን!!!
426 views03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 11:08:26
362 views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 21:47:28 ተወዳጆች ሆይ በዚህ የፆም ወቅት ጉልበታቸውንና መልካቸውን ያረገፉልንን ወላጆቻችንን በብርቱ እንታዘዝ ዘንድ ይገባናል። በፊታችን ያለች በምጥ የወለደችን እናታችንን ሳንታዘዝ በመስቀል መከራ ለወለደን ክርስቶስ የታዘዝን ከመሰለን ከሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን። ለወላጆቻችን በመታዘዝ ብድራታቸውን በመክፈል ልጆቻቸው እግዚአብሔርን መምሰላችንን ልናሳያቸው ይገባናል። [ጢሞ 5:4] ይህ 'የሚገባም ጌታን ደስ የሚያሰኝም' ነውና። [ኤፌ 6:1,ቆላ 3:20]

ልንወደድ የማይገባን ስንሆን ሊጠሉን እስከማይቻላቸው ድረስ የወደዱንን ወላጆቻችንን በመታዘዝ እና መሻታቸውን በመፈፀም ልጅነታችንን እናሳያቸው ዘንድ ይገባናል። አዲስ ፍቅር ፍለጋ የምንባክነው እስከመቼ ነው? ለጠሉን ሰዎች ከሚወዱን ወላጆቻችን በላይ ዋጋ የምንሰጠው አስከመቼ ነው? ትላንት የተዋወቅነውን ሰው ለማስደሰት ደስታቸውን ያጡልንን ወላጆች የምንዘነጋቸው እስከመቼ ነው? በሰው ፊት ይህንን የምናደረገው ለራሳችን ፍቅር ስለሌለን ይሆን?

ተወዳጆች ሆይ በዚህ የፆም ወቅት የቀረበልንን ማዕድ ከመመገባችን አስቀድመን ማንም ምንም የእናታችንን መዳፍ የአባታችንን ጉልበት በመሳም እንደምንወዳቸው እና ውለታቸውን እንዳልረሳን እንደማንረሳ እናሳያቸው።

ይህንን የምላችሁ ስለነፍሳችሁ ድህነትም እንጂ በመካከላችን እንዲህ ማድረግ መልካም ስለሆነ እና ለወላጆቻችን በመታዘዝ እድሜያችን ይረዝም ዘንድ ስላለን አይደለም። ስለዚህም ተወዳጆች ሆይ ለወላጆቻችሁ የምታደርጉትን ሁሉ ለእግዚአብሔር እንደሚያደርግ ሁሉን በትጋት አድርጉ።

ለወላጆቻችን በመታዘዝ ደስ እናሰኘው ዘንድ የወደደ እግዚአብሔር ይመስገን! [ቆላ 3:20]


የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ
ሐምሌ 24-2014 ዓ.ም
መልካም ጾም(በዓል)
806 views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 08:09:12 ​​#ቅዱስ_ገብርኤል

እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡

ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡

መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡

መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡

በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡

እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡

ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡

አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡

​​ የቀጠለ

እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡

ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡

ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡

አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል።
1.2K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:41:13 የንስሐ መንገዶች
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

አምስት የንስሃ መንገዶች አሉ ። የተለያዩ ቢሆኑም ቅሉ ሁሉም የሚያደርሱት ግን ርስት መንግስተ ሰማያት ነው ። እነርሱስ ምን ምን ናቸው ? ያልከኝ እንደሆነ እንድህ ብየ እመልስልሃለሁ፦

፩ኛ • የመጀመሪያው መንገድ "የራስን ኃጢአት ማመን፣ መጥላትና ማውገዝ ነው።

ይኽውም ልዑል ቃል ኢሳይያስ "እንድትጸድቅ መጀመሪያ ኃጢአትህን ተናገር እንዳለው" (ኢሳ 43 ፥26 )፤ ክቡር ዳዊትም "በደሌን አልሸፈንኩም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እንግራለሁ አልሁ ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውኽልኝ" ብሎ እንደተናገረ መዝ 31፥5 ስለዚህ አንተም ስለ ሰራኽው ኃጢአት እራስህን ውቀሰው። በዚህ እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ታደርገዋለህና። ይህ ብቻ ሳይሆን ስለ ኃጢአቱ እራሱን የሚወቅስና ኃጢአቱን የሚኮንን ሰው በተመሳሳይ ኃጢአት በቀላሉ አይወድቅምና። ስለዚህ በጌታ የፍርድ ዙፋን የሚወቅስህ እንዳይኖር ዛሬ እውነተኛ ወቃሽ በኾነው ሕሊናህን አንቅተህ በራስህ ላይ ወቃሽና ከሳሽ አድርገህ ሹመው። ይህ አንዱና ደገኛው መንገድ ነው ።

፪• ሁለተኛው የንስሐ መንገድ ደግሞ
የወገኖቻችንን በደል ይቅር ማለትና በበደሉህ ላይ ቅሬታና ቂም አለመያዝ ነው።

እንዲህ ስናደርግ "ለሰወች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ አባታችሁ እናንተንም ደግሞ ይቅር ይላችኋል" እንዲል እኛ በጌታችን ላይ ያደረግነውን በደል ይቅር እንባላለንና። ማቴ 6 ፡14

፫• ሦስተኛውን የንስሃ መንገድ መንበረ ጸባዖት የደርስ በትጋትና በጥልቅ ስሜት የሚደረግ "ከልብ የመነጨ ጸሎት ነው"

ጨካኙ ዳኛ እንዲርፈድላት ያደረገችው ያች መበለት እንዴት እንዲፈርድላት እንዳደረችገው አታያትም? ( ሉቃ 18፥3) አንተ ግን ሩኅሩኅና መሐሪ የኾነ ጌታ ነው ያለህ። እርሷ በጠላቶቿ ላይ እንዲፈርድላት ነው የጠየቀችው፤ አንተ ግን እምትጠይቀው ስለራስህ ድኅነት ነው።

፬• አራተኛ መንገድ አለ እርሱም "ምጽትዋ ነው " ይህም እጅግ በጣም ታላቅ የኾነ ኃጢአትን የሚስተርይ ኃይል አለውና።

ናቡከደነጾር ኃጢትን ንቅስ ጥቅስ አርድጎ ወደ ክኅደት ሁሉ በገባ ጊዜ እንድህ ብሎታልና፦ "ንጉስ ሆይ ! ምክሬ ደስ ያሰኝህ ኃጢአትህም ለጽድቅ በደልህን ለድኾች በመመጽወት አስቀር" (ዳ.ን 3፥27 ) ይህ ቸርነትና ሰውን መውደድስ ምንስ ይስተካከለዋል? እንዴት ያልከኝ እንደሆነ ስፍር ቁጥር የሌለውን ኃጢአት ከሰራ በኋላ ከዚያ ኹሉ በደል በኋላ እንደርሱ ለሆኑ ሰወች ርኅራኄን ቢያደርግ ከተገዳደረውና ከተጣላው አምላክ ጋር መታረቅ እንደሚችል ቃል ተገብቶለታልና ።

፭• አምስተኛው መንገድ "እንዲሁም ትሕትናና እራስን ማዋረድ ኃጢአትን ያደክማል"

ይህንንም ቀራጩ ያረጋግጥልናል አይኖቹን ወደ ሰማይ ለማንሳት እንኳንስ እስኪፈራ ድረስ በታላቅ ትሕትና ራሱን ባዶ ባደረገ ጊዜ "ጻድቅ ሆኖ ሄደ ተብሏልና ።(ሉቃ 18፥13) ስለዚህም ምንም ምግባር ቢኖርህም እንኳን በደልህን ከመናር በቀር በጎ ምግባርህን አታስበው። ያን ጊዜ እግዚአብሔር የበደል ሸምክህን ያራግፍልሃል።

ስለዚህ እነዚህን መንገደኞች ተመላለስባቸው እንጅ ሰነፍ አትኹን ።

("አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ" መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የቀረበ)
779 views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 13:00:40
909 views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:30:48 ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገባ' ካህን ብትመለከት፥ [በደፈናው] ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ ስለ ኾነ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡
ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ...

ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡

መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ችግር ነው እንጂ፡፡
ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ትንቢተ ኢሳይያስን በተረጎመበት ፬ኛ ድርሳን ላይ ከተናገረው የተወሰደ
1.2K views04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:34:31 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን .
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ማኅበር ቅዱሳን ሐዋሳ ማዕከል በግቢ ጉባኤያት መንፈሳዊ ትምህርት ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪወችን በአባቶች ቡራኬ ያስመርቃል።እናም ውድ የገቢ ጉባኤ ልጆች ተቀሳቅሰን የመርሃ ግብር ተሳ ተሳታፊ እንድንሆን
ማሳሰቢያ
ቀን እሑድ 26/10/2014
ቦታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
ሰዓት ከቅዳሴ በኋላ ማለትም 2፡00ጀምሮ
406 viewsedited  04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 08:53:09
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን .
ውድ ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ማኅበር ቅዱሳን ሐዋሳ ማዕከል በግቢ ጉባኤያት መንፈሳዊ ትምህርት ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪወችን በአባቶች ቡራኬ ያስመርቃል።እናም ውድ የገቢ ጉባኤ ልጆች ተቀሳቅሰን የመርሃ ግብር ተሳ ተሳታፊ እንድንሆን
ማሳሰቢያ
ቀን እሑድ 26/10/2014
ቦታ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
ሰዓት ከቅዳሴ በኋላ ማለትም 2፡30ጀምሮ
571 views05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ