Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅረ ቢጽ ከ ፍቅረ እግዚአብሔር የሚያደርሰው ነው።(አረጋዊ መንፈሳዊ) ክርስቲያን ወንድምህን | ምክረ አበው

ፍቅረ ቢጽ ከ ፍቅረ እግዚአብሔር የሚያደርሰው ነው።(አረጋዊ መንፈሳዊ)


ክርስቲያን ወንድምህን በፍቅር ባየሀው ጊዜ እግዚአብሔር ማየትህ ነው።(ቀሌሜንጦስ)


ባልንጀሮችህ አንድ ሺ ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ያንተን ምሥጢር ደብቆ የሚይዘው ግን አንድ ነው።(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )


ከላይህ ያለ ሰው አስተማሪ የሚሆነው በ እውቀቱ ከሆነ ሊቅ ልትሆን ትችላለህ በ ህይወቱ ከሆነ ግን ክርስትያን ትሆናለህ።(አቡነ ሺኖዳ)


የትህትና ከፍታ እጅግ ታላቅ ነው፤የመታበይ ጥልቀት ደግሞ እጅግ ጥልቅ ነው። የመጀመርያውን እንድትከተል ወደዚህኛው ደግሞ እንዳትወድቅ እመክራለሁ።(አባ ኤስድሮስ)


በሌሎች ላይ መፍረድ የ አንድ ሰው የ ትዕቢት ውጤት ነው፤ ትሑት ሰው ግን ሁሉ ሰው ያከብራል፤ከ እርሱ የተሻሉ እንደሆኑ ያስባል።(ቅዱስ ዕንባቆም)


ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን በወዳጅህ አትክፋ።(ቅዱስ ፖሊካርፐስ)


የ እውቀት ደግነቱ ከሁሉ ጋር መስማማትና መግባባት ነው፤የማይቻለውን እሸከማለሁ የሚል ሰው ለመሸከም የሚችለውን ያጣል።(አንጋረ ፍላስፋ)