Get Mystery Box with random crypto!

ምክረ አበው

የቴሌግራም ቻናል አርማ mkreabew — ምክረ አበው
የቴሌግራም ቻናል አርማ mkreabew — ምክረ አበው
የሰርጥ አድራሻ: @mkreabew
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 11.29K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናላችን ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን የአባቶቻችን ምክር በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አይደሉም።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2020-09-25 08:39:00 † ኦርቶዶክሳዊ ሰርግ - ፲ †

እየተነጋገርን ያለነው ወደ ድኅነት ስለሚያደርስ ጋብቻ ነው፡፡ አምላክ መጀመሪያውኑም ጋብቻን የሰጠው፣ ያገቡም ያላገቡም ቅዱሳን ስለ ጋብቻ አብዝተው ያስተማሩት ጥንቱንም እንደ ተሰጠበት ዓላማ የሰው ልጆች ይድኑበት ዘንድ ነው፡፡ እኛም አስቀድመን ስለ ጋብቻ ጥንተ መጥነትና እድገት ያለውን ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርት የተመለከትነው፥ እንዲሁ ዕውቀትን ብቻ እንድንጨምር ሳይኾን ጋብቻችን ወደ ድኅነት የሚያደርሰን ጋብቻ እንዲኾን በማሰብ ነው፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ስለ ኦርቶዶክሳዊ ሰርግ እንነጋገራለን፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ሰርግ ማለት ትንሽዋ ቤተ ክርስቲያን የምትመሠረትበት፣ የባልና የሚስት አንድነት በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ የሚጸናበት፣ ባለትዳሮች በአንድነት ድኅነታቸውን ለመፈጸም ሰማያዊ ጉዞአቸውን በይፋ የሚጀምሩበት መንፈሳዊ ሥርዓት ማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከግራኝ አሕመድ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መጋባት የተለመደ አልነበረም፡፡ በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ባሕላዊ የሰርግ ሥርዓቱ ስለ ነበረ፥ ብዙውን ጊዜ በሥርዓተ ተክሊል ይጋቡ የነበሩት ካህናት ናቸው፡፡ ጥቂቶች ደግሞ በባሕላዊ ሥርዓት ተጋብተው ከቆዩ በኋላ በአንድነት ይቈርባሉ፡፡ ይህ ኋለኛው ብዙውን ጊዜ በዕድሜ በገፉ ባልና ሚስት ይከናወን የነበረና አሁንም የሚከናወን ሥርዓት ነው፡፡ ይህ የሚኾንበት ምክንያትም ግራኝ አሕመድ በምእመናን ሕይወት ላይ ካመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ በተጨማሪ እንዳይፋቱ ወይም ድጋሚ እንዳያገቡ በመፍራት ነው፡፡

ይህም ብቻ ሳይኾን ያለ ካህን ፈቃድ ማግባት (ዕቁባት ማስቀመጥ)፣ በኾነ ባልኾነው ሚስት ከባሏ፥ ባል ከሚስቱ መፋታት፣ ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጅ መውለድ፣ በአጠቃላይ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸመውን ምሥጢራዊ ተሳትፎ ማለት ንስሓንና ቁርባንን ተክሊልን እየረሱት መኼዳቸው ግራኝ አሕመድ ጥሎት የኼደው እስላማዊ ልማድ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ከላይ እንደ ተጠቀሰው እስላማዊ ልማድ መኾኑን ተገንዝበን ልናስተካክለው የሚገባን ሥርዓት ነው፡፡

ጋብቻችንን እውነተኛና የክርስቲያን ጋብቻ የሚያደርገው ቅዱስ ቊርባን ነው፡፡ “አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ኹለት አይደሉም” እንደ ተባለ ባልና ሚስት፥ ከኹለት አካል አንድ አካል የምንኾነው በቅዱስ ቊርባን ነው (ማቴ.19፡6)፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋእለ ስብከቱ፥ በአንድ መልኩ መንግሥተ ሰማያት “ለልጁ የሰርግ ድግስ ያደረገ ንጉሥን” እንደምትመስል የተናገረው (ማቴ.22፡1)፥ በሌላ መልኩ ደግሞ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ ለሙሽሮችና ለሰርገኞች መስጠቱ እውነተኛ ጋብቻና ቅዱስ ቊርባን የማይለያዩ መኾናቸውን በግልፅ የሚያስረዳን ነው (ዮሐ.2፡1-11)፡፡

ቅዱስ ቊርባን በራሱ ሰርግ ነው፤ ሥጋችን ሥጋው አጥንታችን አጥንቱ የሚኾንበት ምሥጢር ነው፡፡ ሰርግም እንደዚሁ በሥጋ ወደሙ፡- “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ሥጋዬ ናት” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር እውን የሚኾንበት (ዘፍ.2፡23)፣ ከሥጋዊ አንድነት በላይ የመንፈስን አንድነትና ፍቅርን ገንዘብ የምናደርግበት ነው፡፡ በጋብቻችን ካህናት ከሌሉና ኹለታችን አንድ የምንኾንበትን ሥጋ ወደሙ ካልተቀበልን ይህ ምሥጢር አይፈጸምልንም፡፡

ምሥጢረ ጥምቀት አንድን ሰው ከፍጥረታዊ ሰው ወደ መንፈሳዊ ወይም ወደ ቤተ ክርስቲያናዊ ሰው እንደሚያሳድገው፥ ቅዱስ ቊርባንም ለጋብቻ አዲስ ትርጕም እንዲኖረው ያደርገዋል (1ኛ ቆሮ.2፡14-15)፡፡

ዛሬ ይህ በኹለት መንገድ የሚፈጸም ሲኾን፥ የመጀመሪያው ሥርዓተ ተክሊል ነው፤ ኹለተኛው ደግሞ ሥርዓተ መዓስባን ነው፡፡ ስለዚህ እንደየአለንበት ደረጃ፥ በዚህ መንገድ ትንሽዋን ቤተ ክርስቲያን መመሥረት ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ በፊት ያለዚህ ምሥጢር የተጋባን ከኾንን ደግሞ ዛሬ ይህን ካወቅንበት ጊዜ አንሥቶ፣ ንስሓ ገብቶ አብሮ በመቊረብ ይህን ሕይወት መጀመር እንችላለን፡፡ ዋናው ቁም ነገር ከዚህ በኋላ እንደ ፈቃዱ ለመጓዝ መወሰናችን ነውና፡፡ ስለዚህ አስቀድመን አበ ነፍስ እንያዝ፤ አባታችን በሚነግሩን መሠረትም ቀኖናችንን ጨርሰንና ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን ወደዚህ አሁን ወደምንናገርለት ሕይወት መግባት እንችላለን፡፡
14.1K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ