Get Mystery Box with random crypto!

🇲 🇪ድያ Success

የቴሌግራም ቻናል አርማ mediasuccess — 🇲 🇪ድያ Success  
የቴሌግራም ቻናል አርማ mediasuccess — 🇲 🇪ድያ Success
የሰርጥ አድራሻ: @mediasuccess
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.36K
የሰርጥ መግለጫ

#Motto
በልሕቀት እያደግን እናሳድጋለን

⭐️ስብእናችንን እንገንባ🇪🇹
⭐️አስተሳሰባችንን እንቀይር🇪🇹
ማንኛውንም አይነት ሀሳብ ለመስጠት
በ @ZHibretbot ወይም
@Zhibret24💟 ይጠቀሙ።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-30 19:08:29

አንዳንድ ሰዎች አለመቻልና መተው ይደበላለቅባቸዋል መተው አለመቻል አይደለም ሰው የቻለውን ሁሉ አያደርግም

...ማድረግ ያለበትን ብቻ ነው ማድረግ ያለበት የሚችለው ነገር ቢሆን እንኳን ማድረግ ከሌለበት ይተወዋል ያቅተዋል ሳይሆን ይተወዋል

..ሰው መጮህ ስለቻለ ዝም ብሎ አይጮህም ....

..መሳቅ ስለቻለ ያለምክንያት አይስቅም

..መልበስ ስለቻለ ያገኘውን አይለብስም

... ለራሱ በተረዳውና ባመነበት መንገድ መስመር ያበጃል.....ካሰመረው መስመር ላለማለፍ የሚችለውንም ይተወዋል

ማድረግ ስላልቻለ አይደለም መስመር ማለፍ ስላልፈለገ ነው እንጂ


─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia

@media_success
@media_success
1.5K viewsየሆነ ሰው, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-25 00:02:16

በቀን 20 የመጽሐፍ ገጾችን ብናነብ፤ በዓመት 30 መጽሐፍትን አንብበን እንጨርሳለን።

በቀን ከገቢያችንም፣ ከወጪያችንም ቀናንሰን 30 ብር ብናስቀምጥ፤ በዓመት 10,800 ብር ይኖረናል። በዚህም በየዓመቱ አዲስ አክስዮን መግዛት እንችላለን ወይም ያለንን አክስዮን በ10ሺ ብር ማሳደግ እንችላለን ማለት ነው።

በቀን 20 ፑሽ-አፕ ብንሰራ በዓመት 7,200 ፑሽ-አፕ ይሆናል። ይህም ጤናማ ሰውነት እና ቅርጽ እንዲኖረን ያስችለናል!

በቀን 1 አዲስ የቢዝነስ ቃል ወይም አዋጅ ብናውቅ በዓመት 365 አዲስ የቢዝነስ ህጎችን እናውቃለን።

ሁሉም ነገር የሚጀመረው ከትንሹ ነው።

ብዙ ጊዜ ሰዎች ዕቅዳቸውን እና ሕልማቸውን ለመጀመር የሚቸገሩት፤ በትልቁ መጀመርን ስለሚያስቡ ነው። ነገር ግን በጥቂቱ በመጀመር፤ የጀመሩትን ስራ ልምድ ማድረግ ይችላሉ። ( Making Those Tasks a Habit )

ትንንሽ ነገሮች ሲጠራቀሙ ነው ትልቅ የሚሆኑት። "ገንዘብ እና ኃጥያት ተጠራቃሚ ነው! " ይላሉ አባቶች።

ትንንሽ ነገሮችን አትናቋቸው፤ በትንሹ ስንታመን ነው በትልቁ የምንሾመው።

ከትንሽ ስንነሳ ነው የትልቅነትን መንገድ የምናገኘው ወይም የምንረዳው።

ለዚህም ራሳችንን ታማኝ በማድረግ መጀምር ያለብን!


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.4K viewsCEO MediaSuccess, 21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-14 17:16:22 #Digital_megazine
#Inspire_Abyssinia



─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share

@abyssinia_inspire
@abyssinia_inspire
1.4K viewsሽማግሌው የአሮጊቷ ምርኮኛ ነኝ, 14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-07 16:24:52 #Digital_megazine
#Inspire_Abyssinia


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share

─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share

@abyssinia_inspire
@abyssinia_inspire
1.6K viewsሽማግሌው የአሮጊቷ ምርኮኛ ነኝ, 13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-01 11:04:15

ለማሸነፍ የተሽነፋ ሰዎች

የህይወት አላማው መኖር ነው። life is meant for living ይላል ታዋቂው አቀንቃኝ ፍራንክ ሲናትራ። መኖር ዘመቻ ነው ፣ ጦርነቱ ከህይወት ጋር ነው። ጦርነቱን ለማሸነፍ ብቃትና ታክቲክ ከተለያዩ አንጋፋ ሰዎች በጥቅስም ፣ በተረት፣ በስነ ልቦና እና መነባንቦች አንግበን እንዘምታለን።

ለምሳሌ ሩድያርድ ኪፕሊን ''IF'' በምትባል ታዋቂ ግጥሙ ህይወትን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል በተዋቡ ቃላቶቹ ጠቅሶ ይነግረናል። ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በታሪክና ምሳሌ መጽሐፋቸው ይኼንኑ ግጥም "ሰው ለመሆን ብትፈልግ'' ብለው ተርጉመው ያቀርቡታል። ግጥሙ ላይ ያለውን የህይወት ፈተና እና ውጣ ውረድ ማሸነፍ ይከብዳል።

ያሽነፈው ደግሞ የሚሰጠው ማዕረግ ከባድ ነው። '' ሰው'' ተብሎ ይጠራል። '' ባልጠራ ይቅርብኝ'' የሚለው ፈሪ ወይንም ከጂ ተብሎ ሊሰየም ይችላል። እሱም ግን መኖሩን ይቀጥል፣ ወደ ኋላ እያፈገፈገም ቢሆን።

ሄሚንግዊይ የሚባል ስለ ሰው እና የህይወት ፈተና ቁልጭ አድርጎ በመግለጽ የሚታወቅ ከባድ ሚዛን ደራሲ...

ህይወት ሰውን ያጠፋው ይሆናል እንጂ አያሸንፈውም.. ይላል ( A man may be destroyed but not defeated) ::

በሰውና ህይወት መሀል በሚደረገው ፍልሚያ ሰው ያሸንፋል።

ቢሸነፍ እንኳን ግን እጅ ሰጥቶ አይደለም ይለናል። ይኸው ደራሲ ጭንቅላቱን በራሱ እጅ በጥሶ ጥሏል። እንግዲህ እዚህ ላይ ማን አሸናፊ ማን ተሸናፊ እንደሆነ ያጠያይቃል።

ህይወትን ለመግደል ብሎ ራሱን ጥሎ ይሆን? ህይወት ሲታጨድ ሞት በህይወት ምትክ ተዘርቶ መብቀል ይቀጥላል።

ከደራሲው የተሰወረበት እውነት ምናልባት ፤ ህይወት የሚኖረው ሰው ላይ መሆኑ ሊሆን ይችላል። ህይወትን ማሸነፍ ማለት ራስን ማሸነፍ ነው። ህይወትን ማዳን ራስን ማዳን፤ ህይወትን ማጥፋትም ራስን ማጥፋት መሆኑ ነው።

ነገር ግን ሄሚንግዌይን የመሰለ ለብዙ ተከታታይ ዘመናት የድርስት ከባድ ሚዛን ቀበቶ የወሰደ ደራሲ ይኼንን ያጣዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።

እንዲያውም ፤ በአንድ ታዋቂ አጭር ልብወለድ ድርሰቱ መግቢያ ላይ ይሄንኑ በሰው እና ህይወት መሀል የሚደረግ ፍለጋ እና አደን ላይ ተመርኩዞ በተለዋጭ ዘይቤ መልክ የሚለው ነገር አለ፦ ...

በበረዶ የተሸፈነው የኪሊማንጅሮ ተራራ የምዕራቡ ጫፍ የእግዜር ቤት ተብሎ ይጠራል።

እዛው ጫፍ አቅራቢያ በቅዝቃዜ የደረቀ የነብር ሬሳ ይገኛል። ነብሩ ምን ፈልጎ ወደ ቀዝቃዛ ተራራ ጫፍ እንደወጣ ማንም ማስረዳት አልቻለም.. ይለናል። ነብሩን ሰው አድርገን ብንወስደው አዳኝና ታዳኝ ህይወትን ተመስለው ይታዩናል። ነብሩ መሬት ላይ ያሉትን አራዊት አድኖ ወይንም አሸንፎ ከፍ ያለ ነገር ፍለጋ ተራራው ላይ ወጥቷል። ነብር አዋቂ፣ ጠንቃቃ እና ብቸኛ አዳኝ ነው። እንደሚያገኘው እርግጠኛ ያልሆነውን ጠረን ተከትሎ ያን ያህል ርቀት አይጓዝም። ምናልባት ድሮውኑ አሽትቶ ለማደን የተከተለው የራሱን ጠረን ይሆን እንዴ? የህይወት ትርጉም ራስን መፈለግ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው።


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.6K viewsCEO MediaSuccess, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-28 12:33:15

አንድ ሰው የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ (empathy) እንዳላዳበረ የሚያሳዩ ምልክቶች።

ምንም እንኳን የሰው ልጅ በተፈጥሮ ማኅበራዊ ፍጡር ቢሆንም፣ የሰዎችን ስሜት እንደራስ አድርጎ የመረዳት ችሎታ በተፈጥሮ ሙሉ በሙሉ እንደማይሰጠው የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በበለጠ የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ አላቸው። በዚህም ችሎታቸው መሰረት ከሌሎች ጋር እጅግ ቅርብ የሆነ ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ።

አንዳንዶቹ ደግሞ ይህ ችሎታ በእጅጉ ይጎድላቸዋል፣ ችግሩም በሳይንሳዊው አጠራር Empathy Deficit Disorder (EDD) በመባል ይጠራል። አንድ ሰው በዚህ ችግር ሲያዝ እራሱ ከሚያስብበት እና ከሚኖርበት
ምህዋር ውጭ ወጥቶ ሌሎች የሚያስቡትን፣ የሚያምኑትን እና የሚሰማቸውን ስሜት ወደራሱ አምጥቶ ለመረዳት ይቸገራል። ይህም ችግር ከእራሱ ጋር እንዲጣላ፣ ሌሎችን እንዲጠላ እና እንዲያስወግድ ፣ ከሌሎች ጋር
እንዳይቀራረብ ያደርገዋል።

አንድ ሰው ይህ ችግር እንዳለበት ከሚጠቁሙ ምልክቶች ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋና እንደሆኑ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

➣ እራሱን በሌሎች ጫማ ውስጥ አስቀምጦ ነገሮችን ከማየት ይልቅ ሌሎች ሰዎችን ለመንቀፍ ይቸኩላል።

➣ ለታመሙ፣ ጥሩ ሁኔታ ላይ ላልሆኑ ወይም ላልታደሉ ሰዎች ሃዘኔታ የለውም።

➣ በራሱ ሃሳቦች ወይም እምነቶች ትክክለኛነት 100% ያምናል፣ እናም የሌሎችን እምነት እንደ ስህተት ሰዎችንም አላዋቂ አድርጎ ይቆጥራል።

➣ ስለ ሌሎች የመደሰት ችሎታ ወይም ዝንባሌ አይኖረውም።

➣ ጓደኞችን ማፍራት ወይም ዘላቂ ጉዋደኝነት መመስረት አይችልም።

➣ ከቤተሰብ አባላት ጋር ለመግባባት ይቸገራል።

➣ ሌሎች ለሱ ጥሩ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ያስባል። ከሌሎች እርዳታን ሲያገኝም ተገቢውን ምስጋና አያቀርብም። በአንፃሩ ሌሎች እርዳታቸውን ከከለከሉት እጅግ አድርጎ ይበሳጫል።

➣ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ ስለሌሎች ሳያስብ እና ሳይጨነቅ አራሱን ያስቀድማል።

➣ ጓደኛውን ወይም የሚወድደውን ሰው የሚጎዱ ነገሮች ካረገ በሁዋላ ጥፋቱን የነሱ እንደሆነ አድርጎ ይቆጥራል።

በህይወትዎ ዙሪያ እነዚህ ሰዎች ካሉ በእነሱ የተነሳ እለት ተእለት የሚገጥምዎን ችግር ለመቀነስ ይረዳ ዘንድ ባለሙያዎች የሚከተሉትን ምክሮች ይለግሳሉ

አብሮ ለመኖርም የሚረዱ ሙያዊ ምክሮች

1. በቁጣቸው እና በሚያሳዩዋችሁ መጥፎ አቀራረብ አትከፉ።

እነዚህ ሰዎች በጣም ጥልቅ በሆነ ደረጃ ከሌሎች ጋር በስሜት የመገናኘት ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለመሆናቸው እራስዎን ያስታውሱ። ይህንም በማድረግ ነገሩን ችላ ብሎ በማለፍ እራስዎን ከስሜታውዊነት ያወጣሉ።

2. ስሜታችሁን እንዲረዱላችሁ ለማድረግ አትጣሩ

እነዚህ ሰዎች ችግርዎትን እንዲረዱ መሞከር ጊዜዎን እና ጉልበትዎን ማባከን ነው። እነሱንም የባሰ ከማስቆጣት እና ስሜታዊ ከማደረግ ያለፈ ውጤት አያመጣም።

3. ከእነዚህ ሰዎች ጋር መነጋገር ሲኖርባችሁ በግል አስተያየት (opinion) ይልቅ በእውነታ (facts) ላይ ያተኮረ ንግግር አድርጉ።

ምን እንደሚሰማዎት ወይም እነሱ እንዴት እንዳደረጉ እንዲነግሯችሁ ከማድረግ ይልቅ ስለ ተጨባጭ ሁኔታዎች ይነጋገሩ።

4. ከነዚህ ሰዎች ጋር የማይኖሩ ከሆነ እራስዎን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይሞክሩ።

ጓደኝነታችሁን ማቋረጥ የለባችሁም ወይም የቤተሰባችሁን አባል ማግለል የለባችሁም። ነገር ግን የተወሰነ ገደቦችን ማዘጋጀት እና ከነሱ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ጥልቅ እንዳይሆን ማድረግ ከሚገጥማችሁ ጭቅጭቅ ለመዳን ይረዳቹሃል።


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.5K viewsCEO MediaSuccess, 09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-20 18:18:57

አንዳንዴ ህይወት ሚዛን ስታ
ላንዱ ቀጥ እያለች ለሌላው ተኝታ
መራመድ ማለፍ ቢያቅተን
ስጋት ቢያንዣብብ ፅልመቱ ቢከበን
ለሁሉም ጊዜያለው የዛሬው ጨለማ
ምንም ቢያይልም ምንም ቢበረታ
ለነገ ብሩህ ቀን ልባቹን አበርቱ
:
ብቻ እንዳትቆሙ መራመድ ቀጥሉ
ቀናትን ቅዘፉ ዘመን ተሻገሩ
:
አታልፉትም ለሚል አልፋቹ አሳዩ
አታቁም አትችሉም ብሎ ለሚናገር
:
ሙያ በልብ ነውና ነገሩ
ሰርቶ ማሳየትን ለሰው አስተምሩ
:
አታለፉም ላልዋቹ ወድያ ማዶ ቆመው
አትዘልቁም ላልዋቹ ቁልቁል ተመልክተው
:
በዚህ ግጥም ቅኔ መልክቴን እንካቹ

ጨለማን ቀዝፋቹ
ስጋትን ከድናቹ
ፅልመትን ገፍታቹ
ወደ ነገ ብርሀን ትሻገራላቹ
ላይኳን ነክታችሁ


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.4K viewsሽማግሌው የአሮጊቷ ምርኮኛ ነኝ, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-01 09:17:00

" ስህተት መስራት ሰዋዊ ነው ፤ በስህተት መጽናት ግን ድድብና ነው ። "


የሰው ልጅ አካባቢውን ይመስላል የሚባለው ስህተት ነው ። አካባቢው ነው የሰውን ልጅ የሚመስለው ። የቆሸሸ አስተሳሰብ ከሌላችሁ ዙርያችሁ ሊቆሽሽ አይችልም ። የተሳሳተ ግንዛቤ ከሌላችሁ ሰው መሳሳቱን እያወቃችሁ ዝም ለማለት አትደፍሩም ። ስህተት መስራታችሁን ተረድታችሁ ስህተታችሁን ለማረም ካልሞከራችሁ ወይም ስህተት መሆኑን አላመናችሁም ወይም በስህተታችሁ ለመቆየት ፈልጋቹሃል ያ ደግሞ አለማሰብ ሳይሆን ድድብና ይባላል ።

ብዙ ሰዎችን በሕይወታችን አስተውለን ከሆነ ስህተታቸውን ከማመን እና ከማረም ይልቅ...እገሌም እኮ እንዲህ አርጓል እያሉ የነሱን ድክመት ከሌላ ሰው ጋር በማናፃፀር ጥፋታቸውን ለመሸፈን ሲማስኑ ይውላሉ ። የተሸፈነ ጥፋት ማለት ግን አንድ ቀን አይኑን አፍጦ የሚወጣ እንጂ...የቀረ ወይም የታረመ ስህተት ማለት አይደለም ።

በአስተሳሰብ ሆነ በምግባር በኩል ያሉብንን ክፍተቶችና ስህተቶች እናርማቸው እንጂ አንደብቃቸው ።


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.8K viewsየሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-28 17:19:34

አንድ አባት እና ሴት ልጁ በፓርክ ውስጥ እየተጫወቱ ነበር ፡፡ ትነሿ ልጁ አንድ የፖም (አፕል) ሻጭ አየች ፡፡ ወዲያም አባቷን ፖም እንዲገዛላት ጠየቀችው ፡፡ አባት ብዙ ገንዘብ አልያዘም ነበር ፣ ነገር ግን ሁለት ፖም ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ነበረው ፡፡ ስለዚህ ሁለት ፖም ገዝቶ ለልጁ ሰጣት ፡፡

ልጁም ሁለቱን ፖም በሁለት እጆቿ አንድ አንድ ያዘች ፡፡ አባትም አንድ ፖም ልታካፍለው ትችል እንደሆነ ጠየቃት ፡፡ ሴት ልጁ ይህን ስትሰማ በፍጥነት አንደኛውን ፖም በትንሹ ግምጥ አደረገቸው ፡፡ እናም አባቷ ተናግሮ ከመጨረሱ በፊት ከሁለተኛው ፖምም በትንሹ ግምጥ አደረገች ፡፡

አባት በሁኔታው ተገረመ እንዲሁም አዘነ ፡፡ ‘ምን ዓይነት ስግብግብ እና እራስ ወዳድ ልጅ ነው ያሳደኩት? እንደወላጅ የቱ ጋር ነው ያጠፋሁት እስዋን ሳሳድግ?’ እያለ ማሰብ ጀመረ ፡፡ አዕምሮው በብዙ በሀሳቦች ተወጥሮ ነበር ፡፡ እንዴት ብሎ ሴት ልጁን ስለ መጋራት እና ስለመስጠት ማስተማር እንዳለበት በማሰብ ፈገግታው ከፊቱ ላይ ጠፋ ፡፡

እናም በድንገት ሴት ልጁ በአንድ እጇ ላይ አንድ ፖም ይዛ “አባዬ ይህን ውሰድ ፣ ይህኛው በጣም ለስላሳና እና ጣፋጭ ነው” ብላ እጇን ዘረጋችለት ፡፡ አባቷም በሆነው ነገር ተገርሞ ቃላት ስላጣ ዝም አለ ፡፡ ስለ አንድ ትንሽ ልጁ በፍጥነት ወደ ድምዳሜ በማምራቱ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው ፡፡ ልጁ በፍጥነት አፕሎቸን የገመጠችበት ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገባው ተደሰተም ተገረመም ፡፡ አሁን ፈገግታው ተመልሷል ፡፡


በፍጥነት ማንኛውንም ነገር አይፍረዱ ወይም መደምደሚያ ላይ አይደርሱ። ከመፍረድዎ በፊት ነገሮችን በተሻለ ለመረዳት ይሞክሩ ።


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ
1.6K viewsỮΜ🇿 , 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-08 19:02:15

አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት። ሰዓቱ ለእሱ ተራ አልነበረም፤ ከሚወደው አያቱ የተሰጠው ማስታወሻው ነበር።

ክምሩ ውስጥም ላይ ታች ፈለገ፤ በኋላም ተስፋ ቆረጠ፡፡ ውጪ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህጻናትን እንዲረዱት ጠራቸው። ከእነሱም መሃል ሰዓቱን ላገኘ ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገባ።

ልጆቹም ይህንን ሲሰሙ እየተሯሯጡ ወደ በረቱ ውስጥ ገቡ። ክምሩንም እየበታተኑ ፈለጉ። ሆኖም ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም። ገበሬው ተስፋ ቆርጦ ልጆቹን ይዟቸው ወደ ውጪ ወጣ፤ ከልጆቹ መሃል ያለ አንድ ብላቴና ሌላ እድል እንዲሰጠው ጠየቀ።

ገበሬውም ብላቴናውን ወደታች እየተመለከተው፤ በቅሬታ ፈገግታ “አይ ምን ጥቅም አለው ብለህ ነው፤ የሚገኝ አይመስለኝም” አለና ጉንጩን ቆንጠጥ አድርጎ የእጅ ሰዓቱን እንዲፈልግ ፈቀደለት።

ብላቴናው ወደ በረቱ ገባ፤ ከበረቱ ተመልሶ ሲወጣም በእጁ ሰዓት ይዞ ነበር!

ገበሬው ተደሰተም ተገረመም። ብላቴናውንም፤ “እኛ ፈልገን ያጣነውን አንተ ብቻህን እንዴት አገኘኸው?” ብሎ ጠየቀው።

ህፃኑም መለሰ፣

“ምንም አላደረኩም፤ በጸጥታ መሬት ላይ ተቀምጬ መስማት ጀመርኩኝ። ሰዓቱም ቲክ ቲክ… ሲል ሰማሁት። በድምጹም ተመርቼ አገኘሁት”

እናንተ እና እኔ ስንሯሯጥ እንውላለን፤ በጸጥታ እና በስክነት ውስጥ ከማሰብም ይልቅ፤ ምስቅልቅል ያለ እና ማሰርያ አልባ ቀንን እናሳልፋለን።

በጩኸት እና በግርግር ውስጥስ ማን ራሱን ያዳምጣል?

ሰላም ያለው፣ ጸጥ ያለ እና የተረጋጋ አእምሮ፤ ምስቅልቅል ውስጥ ከገባ እና ጥድፊያ ውስጥ ካለ አእምሮ በተሻለ ያስባል።

ለደቂቃዎች አእምሮኣችሁን ፀጥ አሰኙት፤ የልባቹንም ድምጽ … አድምጡ… ድው ድው ..ልባችሁ ውስጥ ምን አለ? ልባችሁ ምን ይፈልጋል?


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share


─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share

@abyssinia_inspire
@abyssinia_inspire
2.0K viewsỮΜ🇿 , 16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ