Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሰው የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ (empathy) እንዳላዳበረ የሚያሳዩ ምልክቶች። ምን | 🇲 🇪ድያ Success



አንድ ሰው የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ (empathy) እንዳላዳበረ የሚያሳዩ ምልክቶች።

ምንም እንኳን የሰው ልጅ በተፈጥሮ ማኅበራዊ ፍጡር ቢሆንም፣ የሰዎችን ስሜት እንደራስ አድርጎ የመረዳት ችሎታ በተፈጥሮ ሙሉ በሙሉ እንደማይሰጠው የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ። አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች በበለጠ የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ አላቸው። በዚህም ችሎታቸው መሰረት ከሌሎች ጋር እጅግ ቅርብ የሆነ ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ።

አንዳንዶቹ ደግሞ ይህ ችሎታ በእጅጉ ይጎድላቸዋል፣ ችግሩም በሳይንሳዊው አጠራር Empathy Deficit Disorder (EDD) በመባል ይጠራል። አንድ ሰው በዚህ ችግር ሲያዝ እራሱ ከሚያስብበት እና ከሚኖርበት
ምህዋር ውጭ ወጥቶ ሌሎች የሚያስቡትን፣ የሚያምኑትን እና የሚሰማቸውን ስሜት ወደራሱ አምጥቶ ለመረዳት ይቸገራል። ይህም ችግር ከእራሱ ጋር እንዲጣላ፣ ሌሎችን እንዲጠላ እና እንዲያስወግድ ፣ ከሌሎች ጋር
እንዳይቀራረብ ያደርገዋል።

አንድ ሰው ይህ ችግር እንዳለበት ከሚጠቁሙ ምልክቶች ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋና እንደሆኑ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

➣ እራሱን በሌሎች ጫማ ውስጥ አስቀምጦ ነገሮችን ከማየት ይልቅ ሌሎች ሰዎችን ለመንቀፍ ይቸኩላል።

➣ ለታመሙ፣ ጥሩ ሁኔታ ላይ ላልሆኑ ወይም ላልታደሉ ሰዎች ሃዘኔታ የለውም።

➣ በራሱ ሃሳቦች ወይም እምነቶች ትክክለኛነት 100% ያምናል፣ እናም የሌሎችን እምነት እንደ ስህተት ሰዎችንም አላዋቂ አድርጎ ይቆጥራል።

➣ ስለ ሌሎች የመደሰት ችሎታ ወይም ዝንባሌ አይኖረውም።

➣ ጓደኞችን ማፍራት ወይም ዘላቂ ጉዋደኝነት መመስረት አይችልም።

➣ ከቤተሰብ አባላት ጋር ለመግባባት ይቸገራል።

➣ ሌሎች ለሱ ጥሩ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ያስባል። ከሌሎች እርዳታን ሲያገኝም ተገቢውን ምስጋና አያቀርብም። በአንፃሩ ሌሎች እርዳታቸውን ከከለከሉት እጅግ አድርጎ ይበሳጫል።

➣ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ ስለሌሎች ሳያስብ እና ሳይጨነቅ አራሱን ያስቀድማል።

➣ ጓደኛውን ወይም የሚወድደውን ሰው የሚጎዱ ነገሮች ካረገ በሁዋላ ጥፋቱን የነሱ እንደሆነ አድርጎ ይቆጥራል።

በህይወትዎ ዙሪያ እነዚህ ሰዎች ካሉ በእነሱ የተነሳ እለት ተእለት የሚገጥምዎን ችግር ለመቀነስ ይረዳ ዘንድ ባለሙያዎች የሚከተሉትን ምክሮች ይለግሳሉ

አብሮ ለመኖርም የሚረዱ ሙያዊ ምክሮች

1. በቁጣቸው እና በሚያሳዩዋችሁ መጥፎ አቀራረብ አትከፉ።

እነዚህ ሰዎች በጣም ጥልቅ በሆነ ደረጃ ከሌሎች ጋር በስሜት የመገናኘት ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለመሆናቸው እራስዎን ያስታውሱ። ይህንም በማድረግ ነገሩን ችላ ብሎ በማለፍ እራስዎን ከስሜታውዊነት ያወጣሉ።

2. ስሜታችሁን እንዲረዱላችሁ ለማድረግ አትጣሩ

እነዚህ ሰዎች ችግርዎትን እንዲረዱ መሞከር ጊዜዎን እና ጉልበትዎን ማባከን ነው። እነሱንም የባሰ ከማስቆጣት እና ስሜታዊ ከማደረግ ያለፈ ውጤት አያመጣም።

3. ከእነዚህ ሰዎች ጋር መነጋገር ሲኖርባችሁ በግል አስተያየት (opinion) ይልቅ በእውነታ (facts) ላይ ያተኮረ ንግግር አድርጉ።

ምን እንደሚሰማዎት ወይም እነሱ እንዴት እንዳደረጉ እንዲነግሯችሁ ከማድረግ ይልቅ ስለ ተጨባጭ ሁኔታዎች ይነጋገሩ።

4. ከነዚህ ሰዎች ጋር የማይኖሩ ከሆነ እራስዎን ከአካባቢያቸው ለማራቅ ይሞክሩ።

ጓደኝነታችሁን ማቋረጥ የለባችሁም ወይም የቤተሰባችሁን አባል ማግለል የለባችሁም። ነገር ግን የተወሰነ ገደቦችን ማዘጋጀት እና ከነሱ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ጥልቅ እንዳይሆን ማድረግ ከሚገጥማችሁ ጭቅጭቅ ለመዳን ይረዳቹሃል።


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ