Get Mystery Box with random crypto!

ለማሸነፍ የተሽነፋ ሰዎች የህይወት አላማው መኖር ነው። life is meant for livin | 🇲 🇪ድያ Success



ለማሸነፍ የተሽነፋ ሰዎች

የህይወት አላማው መኖር ነው። life is meant for living ይላል ታዋቂው አቀንቃኝ ፍራንክ ሲናትራ። መኖር ዘመቻ ነው ፣ ጦርነቱ ከህይወት ጋር ነው። ጦርነቱን ለማሸነፍ ብቃትና ታክቲክ ከተለያዩ አንጋፋ ሰዎች በጥቅስም ፣ በተረት፣ በስነ ልቦና እና መነባንቦች አንግበን እንዘምታለን።

ለምሳሌ ሩድያርድ ኪፕሊን ''IF'' በምትባል ታዋቂ ግጥሙ ህይወትን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል በተዋቡ ቃላቶቹ ጠቅሶ ይነግረናል። ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በታሪክና ምሳሌ መጽሐፋቸው ይኼንኑ ግጥም "ሰው ለመሆን ብትፈልግ'' ብለው ተርጉመው ያቀርቡታል። ግጥሙ ላይ ያለውን የህይወት ፈተና እና ውጣ ውረድ ማሸነፍ ይከብዳል።

ያሽነፈው ደግሞ የሚሰጠው ማዕረግ ከባድ ነው። '' ሰው'' ተብሎ ይጠራል። '' ባልጠራ ይቅርብኝ'' የሚለው ፈሪ ወይንም ከጂ ተብሎ ሊሰየም ይችላል። እሱም ግን መኖሩን ይቀጥል፣ ወደ ኋላ እያፈገፈገም ቢሆን።

ሄሚንግዊይ የሚባል ስለ ሰው እና የህይወት ፈተና ቁልጭ አድርጎ በመግለጽ የሚታወቅ ከባድ ሚዛን ደራሲ...

ህይወት ሰውን ያጠፋው ይሆናል እንጂ አያሸንፈውም.. ይላል ( A man may be destroyed but not defeated) ::

በሰውና ህይወት መሀል በሚደረገው ፍልሚያ ሰው ያሸንፋል።

ቢሸነፍ እንኳን ግን እጅ ሰጥቶ አይደለም ይለናል። ይኸው ደራሲ ጭንቅላቱን በራሱ እጅ በጥሶ ጥሏል። እንግዲህ እዚህ ላይ ማን አሸናፊ ማን ተሸናፊ እንደሆነ ያጠያይቃል።

ህይወትን ለመግደል ብሎ ራሱን ጥሎ ይሆን? ህይወት ሲታጨድ ሞት በህይወት ምትክ ተዘርቶ መብቀል ይቀጥላል።

ከደራሲው የተሰወረበት እውነት ምናልባት ፤ ህይወት የሚኖረው ሰው ላይ መሆኑ ሊሆን ይችላል። ህይወትን ማሸነፍ ማለት ራስን ማሸነፍ ነው። ህይወትን ማዳን ራስን ማዳን፤ ህይወትን ማጥፋትም ራስን ማጥፋት መሆኑ ነው።

ነገር ግን ሄሚንግዌይን የመሰለ ለብዙ ተከታታይ ዘመናት የድርስት ከባድ ሚዛን ቀበቶ የወሰደ ደራሲ ይኼንን ያጣዋል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።

እንዲያውም ፤ በአንድ ታዋቂ አጭር ልብወለድ ድርሰቱ መግቢያ ላይ ይሄንኑ በሰው እና ህይወት መሀል የሚደረግ ፍለጋ እና አደን ላይ ተመርኩዞ በተለዋጭ ዘይቤ መልክ የሚለው ነገር አለ፦ ...

በበረዶ የተሸፈነው የኪሊማንጅሮ ተራራ የምዕራቡ ጫፍ የእግዜር ቤት ተብሎ ይጠራል።

እዛው ጫፍ አቅራቢያ በቅዝቃዜ የደረቀ የነብር ሬሳ ይገኛል። ነብሩ ምን ፈልጎ ወደ ቀዝቃዛ ተራራ ጫፍ እንደወጣ ማንም ማስረዳት አልቻለም.. ይለናል። ነብሩን ሰው አድርገን ብንወስደው አዳኝና ታዳኝ ህይወትን ተመስለው ይታዩናል። ነብሩ መሬት ላይ ያሉትን አራዊት አድኖ ወይንም አሸንፎ ከፍ ያለ ነገር ፍለጋ ተራራው ላይ ወጥቷል። ነብር አዋቂ፣ ጠንቃቃ እና ብቸኛ አዳኝ ነው። እንደሚያገኘው እርግጠኛ ያልሆነውን ጠረን ተከትሎ ያን ያህል ርቀት አይጓዝም። ምናልባት ድሮውኑ አሽትቶ ለማደን የተከተለው የራሱን ጠረን ይሆን እንዴ? የህይወት ትርጉም ራስን መፈለግ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው።


ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ