Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት። ሰዓቱ ለእሱ ተራ አልነበረ | 🇲 🇪ድያ Success



አንድ ገበሬ፣ በረት ውስጥ ባለ የሳር ክምር ውስጥ የእጅ ሰዓቱ ጠፋበት። ሰዓቱ ለእሱ ተራ አልነበረም፤ ከሚወደው አያቱ የተሰጠው ማስታወሻው ነበር።

ክምሩ ውስጥም ላይ ታች ፈለገ፤ በኋላም ተስፋ ቆረጠ፡፡ ውጪ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህጻናትን እንዲረዱት ጠራቸው። ከእነሱም መሃል ሰዓቱን ላገኘ ሽልማት እንደሚሰጥ ቃል ገባ።

ልጆቹም ይህንን ሲሰሙ እየተሯሯጡ ወደ በረቱ ውስጥ ገቡ። ክምሩንም እየበታተኑ ፈለጉ። ሆኖም ሰዓቱን ሊያገኙት አልቻሉም። ገበሬው ተስፋ ቆርጦ ልጆቹን ይዟቸው ወደ ውጪ ወጣ፤ ከልጆቹ መሃል ያለ አንድ ብላቴና ሌላ እድል እንዲሰጠው ጠየቀ።

ገበሬውም ብላቴናውን ወደታች እየተመለከተው፤ በቅሬታ ፈገግታ “አይ ምን ጥቅም አለው ብለህ ነው፤ የሚገኝ አይመስለኝም” አለና ጉንጩን ቆንጠጥ አድርጎ የእጅ ሰዓቱን እንዲፈልግ ፈቀደለት።

ብላቴናው ወደ በረቱ ገባ፤ ከበረቱ ተመልሶ ሲወጣም በእጁ ሰዓት ይዞ ነበር!

ገበሬው ተደሰተም ተገረመም። ብላቴናውንም፤ “እኛ ፈልገን ያጣነውን አንተ ብቻህን እንዴት አገኘኸው?” ብሎ ጠየቀው።

ህፃኑም መለሰ፣

“ምንም አላደረኩም፤ በጸጥታ መሬት ላይ ተቀምጬ መስማት ጀመርኩኝ። ሰዓቱም ቲክ ቲክ… ሲል ሰማሁት። በድምጹም ተመርቼ አገኘሁት”

እናንተ እና እኔ ስንሯሯጥ እንውላለን፤ በጸጥታ እና በስክነት ውስጥ ከማሰብም ይልቅ፤ ምስቅልቅል ያለ እና ማሰርያ አልባ ቀንን እናሳልፋለን።

በጩኸት እና በግርግር ውስጥስ ማን ራሱን ያዳምጣል?

ሰላም ያለው፣ ጸጥ ያለ እና የተረጋጋ አእምሮ፤ ምስቅልቅል ውስጥ ከገባ እና ጥድፊያ ውስጥ ካለ አእምሮ በተሻለ ያስባል።

ለደቂቃዎች አእምሮኣችሁን ፀጥ አሰኙት፤ የልባቹንም ድምጽ … አድምጡ… ድው ድው ..ልባችሁ ውስጥ ምን አለ? ልባችሁ ምን ይፈልጋል?


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share


─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )
#Share

@abyssinia_inspire
@abyssinia_inspire