Get Mystery Box with random crypto!

አንድ አባት እና ሴት ልጁ በፓርክ ውስጥ እየተጫወቱ ነበር ፡፡ ትነሿ ልጁ አንድ የፖም (አፕል) ሻ | 🇲 🇪ድያ Success



አንድ አባት እና ሴት ልጁ በፓርክ ውስጥ እየተጫወቱ ነበር ፡፡ ትነሿ ልጁ አንድ የፖም (አፕል) ሻጭ አየች ፡፡ ወዲያም አባቷን ፖም እንዲገዛላት ጠየቀችው ፡፡ አባት ብዙ ገንዘብ አልያዘም ነበር ፣ ነገር ግን ሁለት ፖም ለመግዛት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ነበረው ፡፡ ስለዚህ ሁለት ፖም ገዝቶ ለልጁ ሰጣት ፡፡

ልጁም ሁለቱን ፖም በሁለት እጆቿ አንድ አንድ ያዘች ፡፡ አባትም አንድ ፖም ልታካፍለው ትችል እንደሆነ ጠየቃት ፡፡ ሴት ልጁ ይህን ስትሰማ በፍጥነት አንደኛውን ፖም በትንሹ ግምጥ አደረገቸው ፡፡ እናም አባቷ ተናግሮ ከመጨረሱ በፊት ከሁለተኛው ፖምም በትንሹ ግምጥ አደረገች ፡፡

አባት በሁኔታው ተገረመ እንዲሁም አዘነ ፡፡ ‘ምን ዓይነት ስግብግብ እና እራስ ወዳድ ልጅ ነው ያሳደኩት? እንደወላጅ የቱ ጋር ነው ያጠፋሁት እስዋን ሳሳድግ?’ እያለ ማሰብ ጀመረ ፡፡ አዕምሮው በብዙ በሀሳቦች ተወጥሮ ነበር ፡፡ እንዴት ብሎ ሴት ልጁን ስለ መጋራት እና ስለመስጠት ማስተማር እንዳለበት በማሰብ ፈገግታው ከፊቱ ላይ ጠፋ ፡፡

እናም በድንገት ሴት ልጁ በአንድ እጇ ላይ አንድ ፖም ይዛ “አባዬ ይህን ውሰድ ፣ ይህኛው በጣም ለስላሳና እና ጣፋጭ ነው” ብላ እጇን ዘረጋችለት ፡፡ አባቷም በሆነው ነገር ተገርሞ ቃላት ስላጣ ዝም አለ ፡፡ ስለ አንድ ትንሽ ልጁ በፍጥነት ወደ ድምዳሜ በማምራቱ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማው ፡፡ ልጁ በፍጥነት አፕሎቸን የገመጠችበት ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገባው ተደሰተም ተገረመም ፡፡ አሁን ፈገግታው ተመልሷል ፡፡


በፍጥነት ማንኛውንም ነገር አይፍረዱ ወይም መደምደሚያ ላይ አይደርሱ። ከመፍረድዎ በፊት ነገሮችን በተሻለ ለመረዳት ይሞክሩ ።


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─


Via ከ ስነ-ፅሁፍ አለም(Inspire Abyssinia )

ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot
#share
#ሚድያ_Success

Join @mediasuccess

ውብ አሁን ተመኘሁ