" ስህተት መስራት ሰዋዊ ነው ፤ በስህተት መጽናት ግን ድድብና ነው ። " የሰው ልጅ አካባቢውን ይመስላል የሚባለው ስህተት ነው ። አካባቢው ነው የሰውን ልጅ የሚመስለው ። የቆሸሸ አስተሳሰብ ከሌላችሁ ዙርያችሁ ሊቆሽሽ አይችልም ። የተሳሳተ ግንዛቤ ከሌላችሁ ሰው መሳሳቱን እያወቃችሁ ዝም ለማለት አትደፍሩም ። ስህተት መስራታችሁን ተረድታችሁ ስህተታችሁን ለማረም ካልሞከራችሁ ወይም ስህተት መሆኑን አላመናችሁም ወይም በስህተታችሁ ለመቆየት ፈልጋቹሃል ያ ደግሞ አለማሰብ ሳይሆን ድድብና ይባላል ። ብዙ ሰዎችን በሕይወታችን አስተውለን ከሆነ ስህተታቸውን ከማመን እና ከማረም ይልቅ...እገሌም እኮ እንዲህ አርጓል እያሉ የነሱን ድክመት ከሌላ ሰው ጋር በማናፃፀር ጥፋታቸውን ለመሸፈን ሲማስኑ ይውላሉ ። የተሸፈነ ጥፋት ማለት ግን አንድ ቀን አይኑን አፍጦ የሚወጣ እንጂ...የቀረ ወይም የታረመ ስህተት ማለት አይደለም ። በአስተሳሰብ ሆነ በምግባር በኩል ያሉብንን ክፍተቶችና ስህተቶች እናርማቸው እንጂ አንደብቃቸው ። ለሀሳብዎ➝ @ZHibretbot #share #ሚድያ_Success Join @mediasuccess ውብ አሁን ተመኘሁ 1.8K viewsየሆነ ቦታ የሚኖር የሆነ ሰው, 06:17