Get Mystery Box with random crypto!

Prosperity Party A.A ብልፅግና

የቴሌግራም ቻናል አርማ prosperityaddis — Prosperity Party A.A ብልፅግና P
የቴሌግራም ቻናል አርማ prosperityaddis — Prosperity Party A.A ብልፅግና
የሰርጥ አድራሻ: @prosperityaddis
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.52K
የሰርጥ መግለጫ

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:14:10
ሰራዊታችንን እንደግፋለን፤
ኢትዮጵያን እንጠብቃለን!!
592 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 16:04:40
ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን መቆም ክብርም ኩራትም ጭምር ነው!!
1.1K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:48:44
"ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል"
- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሐት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም ፦

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው ርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት ርዳታው ለተረጂው ሕዝብ
እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት ዐቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው
ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።
ይሁንና በሕወሐት የሽብር ቡድን እየደረሰሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሐት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

በመሆኑም ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
1.3K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:16:31
"አካባቢያችንን የምናለማ፣ ሰላማችንን የምናረጋግጥ፣ ብልፅግናችንን የምናመጣ፣ እርስ በእርስ የምንዋደድ፣ ለጥፋት ይቅር የምንባባል ከሆነ የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ ይቻላል።"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
1.2K viewsedited  07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:32:23

1.2K views05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:08:36
"የሕወሓት ዕብሪት ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንዲታጠፉ እያስገደደ ነው!" - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

መንግሥት ለሰላም አማራጭ ዕድል ለመስጠት ሲል የሕዝብ ማዕበል አስነሥቶ ሕጻናትን፣ ወጣቶችንና አረጋውያንን ለመማገድ የመጣውን የሕወሐት ታጣቂ፣ በምሥራቅ አማራ በኩል በጀግንነት ሲከላከል ቆይቷል።

ሕወሐት በምሥራቅ አማራ በኩል በቆቦና አካባቢው የከፈተው ወረራ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በደጀኑ ሕዝብ ጠንካራ የመከላከል ብቃት የተነሣ ባሰበው ልክ አልሄደለትም።

በዚህም ምክንያት ለሰላም የተሰጠውን ሁለንተናዊ አማራጭ አሽቀንጥሮ ጥሎ ወረራውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እያስፋፋ ይገኛል።

ያለ ጦርነት መኖር የማይችለው ሕወሐት በዋግ፣ በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር አካባቢ ወረራ ከፍቷል። ይሄንን የሕወሐት ወረራ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት በተሟላ ዝግጅትና በጽኑ ቁመና እየተከላከለ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈቱበትን ጥቃቶች በጽናት እየተከላከለ፣አሁንም ለሰላም አማራጮች የዘረጋቸውን እጆች ዛሬም ድረስ አላጠፈም።

ለሰላም የተዘረጋው እጅ በሕወሐት ዕብሪታዊ ወረራ ምክንያት እንዳይታጠፍ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚቻለውን እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁንም ያሳስባል። ወገናችን የሆነው የትግራይ ሕዝብም ይሄንን የዕብሪት ወረራ በማውገዝ ሕወሐት ከሚያስከትልበት መከራ ራሱን ነጻ እንዲያወጣ ጥሪ እናቀርባለን።
1.2K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:07:09

1.0K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:53:10 ጳጉሜን በመደመር!!

ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ ቀን!!

- የተመረጠበት ምክንያት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ባህል እየሆነ የመጣዉንና ከፍተኛ ዉጤት የተገኘበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እሴትን ይበልጥ ለማጠናከር ነዉ፡፡
• እለቱ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት እንዲሳካ ያደረገ፣ በዙ አቅመ ደካሞችን የቤት ባለቤት ያደረገ፣ በደም ዕጦት ሲያልፍ የነበረዉን ህይወት ለመታደግ ያስቻለ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራን ይበልጥ ባህል በሚያደርጉ ተግባራት ይከበራል፡፡
• እለቱ ት/ቤቶችንና መኖሪያ አካባቢዎችን በማፅዳት፣ ደም በመለገስ፣ አቅመ ደካሞችን በማጋዝና በመሳሰሉት ተግባት ይከበራል፡፡

ጳጉሜ 2 የአምራችነት ቀን!!

ዓላማዉም በግብርና፣ በኢንደስትሪ፣ በትራንስፖርና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችና ተግዳሮቶችን በመለየት ለቀጣይ ዓመት በቂ ዝግጅት ለማድረግ ነዉ፡፡

ጳጉሜ 3 የሠላም ቀን!!

"ሠላም ለኢትዮጵያ"በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

• ዓላማዉም ለሰዉ ልጅም ሆነ ለአገራችን ሠላም እጅግ አስፈላጊ ሆነ ጉዳይ መሆኑን ለማስገንዘብና የሠላም እሴት ለማድረግ ነዉ፡፡
• እለቱ በማህበረሰብ ደረጃ እርቅ በማዉረድ፣ የሠላም እሴቶችን በማስተዋወቅና በመሰል መርሃ-ግብሮች ይከበራል፡፡

ጳጉሜ 4 የአገልጋይነት ቀን!!

"አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል" በሚል መሪ ቃል የሚከበር ይሆናል፡፡

• የአገልጋይነት ቀን መከበር ዓላማዉ በሁሉም የግልና የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተገልጋይ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲያገኝና ሁሉም ሠራተኛና አመራር የማገልገል ቃልክዳኑን የሚያድስበትና በአዲሱ ዓመት ሁሉም አካላት ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘጋጅ፣ ለበለጠ አገልግሎት ቃል የሚገቡበት ዕለት እንዲሆን ነዉ፡፡
• ዕለቱ ሁሉም ሠራተኛና አመራር ከደረጃዉ ዝቅ ብሎ አገልግሎት በመስጠት፣ የፅዳት ሥራን በማከናወን፣ ነፃ አገልግሎት በመስጠትና በተያያዝ ተግባራት ይከበራል፡፡

ጳጉሜ 5 የአንድነት ቀን!!

• የአንድነት ቀን መከበር ዓላማዉ ለዘመናት የቆየዉ የኢትዮጵያ እንድነትና ሉዓላዊነትን ለማስከበር የተከፈለዉን መስዋዕትነት በመዘከር ፤ አሁንም አገራችን ፈተናዎችን እየተሻገረች አንድነቷን ጠብቃ እየተጓዘች እንዳለች እና ቀጣይም በልጇቿ መስዋዕትነትና ጥረት አንድ ሁና እንደምትቀጥል ለማሳየት ነዉ፡፡
• የአንድነት ቀን መከበር አስፈላጊነቱ እንደ ሕዝብና አገር ህልዉናችን የሚረጋገጠዉ፣ ክብራችንና ነጻነታችን ዘላቂ የሚሆነዉ አንድ ሆነን ስንቆም ብቻ መሆኑን ለማስገንዘብና የአንድነታችን እሴቶችን ለማጎልበት ነዉ፡፡
• የጥንካሬያችን ምንጭ አንድነታችን መሆኑን፣ ጠላቶቻችንን ከጥንት እስከ ዛሬ እያሸነፍን የመጣነዉ አንድ ሆነን በመቆማችን እንደ ሆነ ለማስገንዘብ ጭምር ነዉ፡፡
• ዛሬም በብዙ ፈተናዎች ዉስጥ እንገኛለን፣ ለታሪካዊ ጠላቶቻችን የሚላላኩ በአሸባሪዉ ወያኔ ለ3ኛ ጊዜ የተወረርነበት ጊዜ ዉስጥ እንገኛለን፡፡
• ይህንን ወረራ በድል የሚኛጠናቅቀዉና ዘላቂ ሠላማችንን የምናረጋግጠዉ አንድ ስንሆን ብቻ ነዉ፡፡
• ጠላቶቻችን በብሔር፣ በኃይማኖትና በሰፈር ከፋፍሎን ሊያንበረክኩን ብዙ ለፍቷል፣
• የዉጭ ጠላቶችና የዉስጥ ባንዳዎች ግንባር ፈጥሮ ዘምቶብናል፣ ዘመቻዎቻቸዉን በድል የምንወጣዉ አንደነታችንን በማጠናከርና በአንድነታችን የተጎናፀፍናቸዉን ድል ለመዘከር ዕለቱ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
1.4K views05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:53:08
1.0K viewsedited  05:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:38:22
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንኳን ዛሬ ትናንትም አልተሸነፈም!!!
1.4K views18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ