2022-07-13 17:39:20
በአዲስ አበባ ሰሞኑን የወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውደቅ ተደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 1 ቀን 2014 ያወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ውድቅ አደረገ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ባሳለፍነው ሐምሌ 1 ቀን 2014 የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውድቅ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ዕጣው የተሰረዘውም የከተማ አስተዳደሩ ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት መኖሩ በመረጋገጡ ነው ተብሏል፡፡
በእጣው የሚካተቱት 79 ሺህ ቆጣቢዎች መሆን ሲገባው ÷ ምርመራ ሲደረግ ግን በእጣው ውስጥ የተካተቱት ሰዎች ቁጥር 172 ሺህ መሆኑ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡
ይህ ማለትም 93 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በተጭበረበረ መንገድ ዕጣ በሚያወጣባት የቴክኖሎጂ ሲስተም ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር ድርጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
2.0K views14:39