Get Mystery Box with random crypto!

'ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል' - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሕወሐት | Prosperity Party A.A ብልፅግና

"ሕወሐት ወረራውን እያስፋፋ መጮኹን ቀጥሎበታል"
- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በየአቅጣጫው በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋ ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፣ ሕዝብ እየተፈናቀለ፣ ንብረትም እየወደመ ነው።

አሁን እንደሚታየው አሸባሪውን ሕወሐት ከሀገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል። ምክንያቱም ፦

1. የሽብር ቡድኑ ሰላማችንን እንዳያደፈርስና ሀገራችንን እንዳያፈርስ መከላከል ስለሚገባ፤

2. ሕወሐት ወደ ትግራይ የሚላከውን ርዳታ ለተቸገረው ሕዝብ እንዳይደርስ፣ በተቃራኒው ርዳታው ለጦርነት እንዲውል እያደረገ በመሆኑ መንግሥት ርዳታው ለተረጂው ሕዝብ
እንዲደርስና ትግራይ ውስጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሕዝቡን ከችግር የመከላከል ግዴታ ስላለበት፤

3. ሕወሐት በእኩይ ተግባሩ ሕዝብን በረሃብ ለመቅጣት ዐቅዶ ተደጋጋሚ ጦርነት የሚከፍተው በክረምት የግብርና ወቅት በመሆኑ መንግሥት ወረራውን እየተከላከለ ያለው
ሕዝብን ከረሃብ የማዳን ግዴታ ስላለበት ጭምር ነው።
ይሁንና በሕወሐት የሽብር ቡድን እየደረሰሱ የሚገኙ ጥፋቶችን ለማስቆም መንግሥት ለሰላማዊ አማራጭ ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ፣ አሸባሪውን ሕወሐት መጫን ሲገባቸው "ሁለቱም ወገኖች" በሚል የሚወጡ መግለጫዎች ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው ተቀባይነት የላቸውም።

በመሆኑም ሕወሐት ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በመግፋት የከፈተው ጥቃት ሃገራችንን እንዳይበትን፣ የመከላከያ ኃይላችን በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተበትን ወረራ ከሰላም ወዳዱ ደጀን ሕዝብ ጋር በመሆን በጽኑ ጀግንነት በመከላከል ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት