Get Mystery Box with random crypto!

Lighthouse Training & Consulting PLC

የቴሌግራም ቻናል አርማ lighthouselearningcenter — Lighthouse Training & Consulting PLC L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lighthouselearningcenter — Lighthouse Training & Consulting PLC
የሰርጥ አድራሻ: @lighthouselearningcenter
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.97K
የሰርጥ መግለጫ

በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግል እና ሙያዊ አቅምን የሚያጎለብቱ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን እንሰጣለን።
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ!
አስተያየትዎን ለመስጠት:-https://t.me/addlist/bKMEnwP0DG83ZGM0

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-03 17:35:29
2.8K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 16:43:15
2.6K viewsLighthouse- Academy of Success, 13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 19:01:47
የKFC መስራች አይበገሬው አዛውንት ኮሎኔል ሳንደርስ:-

☞በ5 ዓመቱ አባቱ ሞተ
☞በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋረጠ
☞በ17 ዓመቱ 4 የተለያዩ ስራዎቹን አጥቶ ነበር
☞ከ18 እስከ 22 ዓመቱ የባቡር ትኬት ቆራጭ ሆኖ ሰራ ነገር ግን አልተሳካለትም
☞የሀገሩን መከላከያ ቢቀላቀልም ተባረረ
☞ህግ ለመማር አመለከተ አልተሣካለትም
☞ለአንድ ኢንሹራንስ ድርጂት ግብይት ሰራተኛ ሆነ..ይህም አልተሣካለትም፡፡
☞በ19 ዓመቱ ደግሞ ልጅ ወልዶ ነበር 2ዐ ዓመቱ ላይ ሚስቱ ልጃቸዉን ይዛ ጥላዉ ሄደች፡፡
☞በአንዲት ትንሽየ ካፌ ምግብ አብሳይና ሰሃን አጣቢነት መስራት ጀመረ
.
.
.
☞65 ዓመት ሲሞላዉ ጡረታ ወጣ
☞ጡረታ በወጣ በመጀመሪያዉ ቀን የ$105 ቼክ ከመንግስት ደረሠዉ..እሱ ግን የተረዳዉ መንግስት "ራስህን መመገብ አትችልም" እንዳለዉ ነበርና ከዚህ በኋላ መኖሩ ጥቅም እንደሌለዉ ራሱን አሣምኖ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አደረግ....ይህም ሳይሆን ቀረ፡፡
☞አንድ እለት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ምኞቶቹን ወረቀት ላይ ማስፈር ፈለገ የፃፈዉ ግን በህይወቱ ሊያደርጋቸዉ እየቻለ ሳያደርጋቸዉ ስለቀሩ ነገሮች ነበር...ከዝያም በእርግጠኝነት ማድረግ እንደሚችለዉ የሚያዉቀዉን አንድ ነገር አሰበ...ምግብ ማብሰል፡፡
☞ወዲያዉም የመንግስትን የዉለታ ቸክ መልሶ $87 ተበደረ፡፡
☞በዚያች ብድርም ቅመሞቹን ሸምቶ ፍራይድ ችክን አዘጋጀ...እናም በኬንታኬይ ለሚኖሩ ጎረቤቶቹ በራቸዉ ድረስ እየሄደ መሸጥ ጀመረ፡፡
☞ግን በ68 ዓመቱ የኬንታኬይ ፍራይድ ችክን KFC ኢምፓየር መስራች ቢሊየነር ሆነ!!!
3.7K viewsLighthouse- Academy of Success, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 18:57:26
ህጋዊ እውቅና እና ፍቃድ ያለው ድርጅታችን Lighthouse Training and Consulting PLC/ላይትሃውስ ስልጠና እና ማማከር ኃ.የተ.የግ. ማህበር/ ልጆችዎ ትልቅ ህልም ያላቸው፣ በትምህርታቸው ብሎም በሁለንተናዊ ህይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ የሚረዳ #ከ7ኛ እስከ #12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች

#ለ2 ወራት የሚቆይ፤ #የአስተሳሰብ #ለውጥ ላይ ያተኮረ ልዩ #የክረምት #የስብዕና #ማበልፀጊያ ስልጠና አዘጋጅቷል።

#ምዝገባ #ጀምረናል!

በሳምንት 3 ቀናት:-

ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብ
ወይም
ማክሰኞ፣ ሐሙስ፣ ቅዳሜ

#ሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ይጀምራል።

#ስልጠናው_የሚሰጥበት_ቦታ:-
አልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ 4 ኪሎ፤ ወ.ወ.ክ.ማ አጠገብ በሚገኘው ካምፓስ

#የቢሮ #አድራሻችን:-
አዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ወሰን ግሮሰሪ፣ የአብስራ ህንፃ፣ ቢሮ ቁጥር 05

ለበለጠ መረጃ:-
በ+251-911- 37-91-79
ወይም
+251-703-37-91-79 ይደውሉልን

ኢሜይል:-lighthouseacademyofsuccess@gmail.com
4.4K viewsLighthouse- Academy of Success, edited  15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 18:14:52
ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው
ከጎንህ ሰው አለ እንደልጅ ምታዘው።
ብዙ አፋሽ አጎንባሽ በዙሪያህ ታያለህ
ገና ሳታስነጥስ ይማርህ የሚልህ።
ጥላ ላይም ቁመህ ጥላ ሚዘረጋ
የቆለፍከውን በር ሩጦ የሚዘጋ፤
በአቧራ ስትሄድ ከፊት ሳር አንጣፊ
ኪስህ ገንዘብ ካለ ሞልተዋል አጣፊ።

አጣሁ ያልክ እለት ግን ኪስህ ሲሆን ባዶ
አንተ በዚህ ስትሄድ እነሱ በማዶ።
አይደለም እንቅፋት ስትውል ብታስነጥስ
ለሞት ብታጣጥር ሰው የለም የሚደርስ።
ነገ ለሚነጋ ዛሬ ቀን ቢጨልም
እንኳን ያበላኸው…..
እንኳን ያጠጣኸው….
የራስህ ጥላ እንኳን ካንተ ጋር አይደለም።

እናማ ወዳጄ ኪስህን ደባብሰው
አለሁ ባይህ ኪስህ....
የወደክ ለታ አለ "ሺህ ገንዘብህ
አደናቅፎህ ብትወድቅ ሟጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን … ማንንም አትማ።
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጅ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ።
ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው፤
የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።
መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ።
3.9K viewsLighthouse- Academy of Success, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 14:00:25
የክቡር ዶ/ር ሻለቃ አትሌት ኃይለገብረስላሴ ምክሮች ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን በአማራጭ የቴሌግራም ቻናላችን ገብታችሁ ታነቧቸው ዘንድ ጋብዘናል
@anki_books_review
3.9K viewsLighthouse- Academy of Success, 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 17:57:34 አንድ ፈረሰኛ ወደ አንድ ከፍተኛ ተራራ ይጓዝ ነበር፡፡ ወደ ተራራው ወገብ ላይ ሲደርስ አንድ ምስኪንና አንድ እግሩ ሽባ የሆነ ሰው እንዳቅሙ ቋጥኙን እየቧጠጠ ለመውጣት ሲፍጨረጨር ያገኛል፡፡

ፈረሰኛው፤
"ወዳጄ፤ ይህን የሚያህል ተራራ እንዲህ ተንፏቀህ የሚገፋ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንደምንም ፈረሴ ላይ ላውጣህና አፈናጥጬ ዳገቱ ጫፍ ላይ ላድርስህ?"

ሰውዬው፤
"እግዚአብሔር የባረከህ ሰው ነህ! ግን ሥጋቴ እንዳላጣብብህ ነው፡፡ ለማፈናጠጥ ይበቃል ብለህ ነውን?"

ፈረሰኛው፤
"እንደምንም ተጣበን እንወጣዋለን እንጂ በዚህ ሁኔታ በፍፁም ጥዬህ ብሄድ ግፍ ይሆንብኛል፡፡ ሰው እንኳ ባይኖር ተራራውም ይታዘበኛል፡፡ ስለዚህ ና ውጣ ግዴለህም፡፡"

ሰውዬው፤
"ፈጣሪ ምስክሬ ነው፤ ለእኔ የተላክ ውድ አዳኝ መልዐክ ነህ፡፡ አምላክ ውለታህን ይክፈልህ!"

ፈረሰኛው ተሸክሞ ፈረሱ ላይ አስቀመጠውና ተራራውን ተያያዙት፡፡ ጥቂት እንደሄዱ ግን፤

ሰውዬው
"ወዳጄ፤ ቅድም እንደፈራሁት በጣም ተጣበናል፡፡ ብወርድልህ ይሻላል፡፡"

ፈረሰኛው፤
"እንደሱማ አይሆንም፡፡ ባይሆን የተወሰነውን ዳገት እኔ በእግሬ ልሞክረው፤ አንተ ፈረሱን ያዝ" አለውና ፈረሱን ሰጥቶት ወረደ፡፡ ሰውየው እየጋለበ ዳገቱን እየወጣ እየራቀ ሄደ፡፡

ፈረሰኛው በእግሩ ዳገቱን ተያያዘው፡፡ ሆኖም ባለፈረሱ እየራቀ ሄደ፡፡ ፈረሰኛው ሥጋት እየገባው በተቻለው ፍጥነት ሊከተለውና ሊጠጋው ቢሞክርም ሰውዬው ፈረሱን ይብስ አፈጠነው፡፡

ፈረሰኛው መጣራት ጀመረ፡፡ ወይ የሚለው ግን አጣ፡፡ ሰውዬው ፈረሱን ይዞ ሊጠፋ መሆኑ ለፈረሰኛው ገባው፡፡

“አንተ ሰው፤ ግዴለም ፈረሱን ይዘኸው ትሄዳለህ፡፡ ግን አንድ ነገር ቆም ብለህ ስማኝ እባክህ፡፡ እንደማልደርስብህ ታውቃለህ፡፡ ጆሮህን ብቻ አውሰኝ?” ሲል ለመነው፡፡

ሰውዬው ርቀቱን በደንብ ካረጋገጠ በኋላ፤
“እሺ ምንድነው ልትነግረኝ የፈለከው?”

ፈረሰኛውም፤
“ወዳጄ፤ መቼም አንድ ቦታ ወርደህ ከሰው መቀላቀልህ አይቀርም፡፡ አደራህን ይሄን አሁን እኔን የሰራኸኝን ነገር ለማንም ሰው እንዳትነግር፡፡ አለበለዚያ ደግ የሚሰራ ሰው ይጠፋል!”

#ምንጭ:- "ታሪክና ምሳሌ" ከክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
4.0K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 17:57:30
3.3K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 14:55:13
እነዚህን 7 ልማዶች ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን በአማራጭ የቴሌግራም ቻናላችን ገብታችሁ ታነቧቸው ዘንድ ጋብዘናል
@anki_books_review
3.7K viewsLighthouse- Academy of Success, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 19:56:00
3.6K viewsLighthouse- Academy of Success, 16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ