Get Mystery Box with random crypto!

Lighthouse Training & Consulting PLC

የቴሌግራም ቻናል አርማ lighthouselearningcenter — Lighthouse Training & Consulting PLC L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lighthouselearningcenter — Lighthouse Training & Consulting PLC
የሰርጥ አድራሻ: @lighthouselearningcenter
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.97K
የሰርጥ መግለጫ

በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግል እና ሙያዊ አቅምን የሚያጎለብቱ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን እንሰጣለን።
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ!
አስተያየትዎን ለመስጠት:-https://t.me/addlist/bKMEnwP0DG83ZGM0

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-29 17:51:32 ቀናነት ቀና ያለ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ ቅንነት በተንኮል ያልታጠፈ፣ በምቀኝነት ያልተቆለመመ፣ በራስወዳድነት ያልተንጋደደ ሃሳብና ምግባር ነው፡፡ የተንጋደደ ማንነት ቀጥ ያለ ሰውነትን አያስገኝም፡፡ ገዳዳ አስተሳሰብ ሕይወትን ያንጋድዳል፡፡ አንዴ ከአስተሳሰብህ ከተጣመምክ በስራህ መቼም ቢሆን ቀጥም ቀናም አትልም፡፡ የጎበጠ ማንነት፣ አንገት የደፋ ሕሊና ቀጥ ብሎ መቆም አይችልም፡፡ በሌሎች የሚዘወር ጭንቅላት የራሱ መሪ የለውም፡፡ በትንሹ ተፈትኖ የወደቅ በትልቁ ሊታመን አይችልም፡፡ ሲያስብ የተሳሳተ ምግባሩም ሆነ ተግባሩ የተሳሳተ ነው የሚሆነው፡፡ ሰው የዘራውን ያንኑ ነውና የሚያጭደው!

ታላቁ የጥበብ ሰው ሩሚ፡-

‹‹የመበላሸትን ወይም የመበከልን ተፈጥሮ ተረዳ፡፡ አንዴ ቁልፍህ ከተጣመመ ወይም ከታጠፈ መቼም ቢሆን ቁልፍህ አይከፍትም፡፡›› ይላል፡፡

እውነት ነው! ራስህን መረዳት ስትጀምር አካሄድህን ታጤናለህ፣ አስተሳሰብህን ትገመግማለህ፣ የምትከተለውን ትመረምራለህ፤ ከፊትህ ያለውን በደንብ ማየት ትጀምራለህ፡፡ መሪህን ትመነጥራለህ፣ ዓላማህን ቀስ ብለህ ትሾፈዋለህ፤ ግብህን ታልማለህ፡፡ መድረሻህን ገና መንገድ ሳትጀምር ወጪና ኪሳራውን ቀድመህ ታሰላዋለህ፡፡፡፡ እየተራመድክበት ያለው “የሕይወት መንገድ አዳላጭ ነው፤ ወይስ ወስዶ ወስዶ ከገደል አፋፍ የሚያደርስ ነው” የሚለውን ለማወቅ አንተነትህን፣ መንገድህንና ዓላማህን መረዳት ይጠበቅብሃል፡፡

የመንገድህን መበላሸት፣ የዓየርህን መበከል፣ የአካሄድህ ግራገብነትን የምትረዳው ራስህንና ዓለሙን ስትረዳ ነው፡፡ የመበላሸት ተፈጥሮን ማወቅ ራስን ከብልሽት ማዳን ነው፡፡ የመኪና መነፋነፍ የብልሽት ምልክት ነው፡፡ የአስተሳሰብ መዛነፍም ውድቀትን ጠቋሚ ነው፡፡ ከብልሽቱ ዓለም ለመውጣት አስተሳሰብን መጠገን ግድ ይላል፡፡ ሊሰምጥ ጫፍ የደረሰ ሰውነትን መታደግ ከምንም በላይ አኩሪና አርኪ ነው፡፡ በሃሳብ ባህር ቀዝፎ፤ በህይወት ውቅያኖስ ተንሳፎ፣ በቀና አስተሳሰቡ ታንኳ የሕይወት ወጀቡንና የኑሮ ሞገዱን የሚያልፍ እሱ በአስተሳሰቡ የጠነከረ፤ ከኑሮው ልምድ የቀሰመ ነው፡፡

ከራሱ ጋር የመነጋገር ልምድን ያዳበረ ጠማማ አስተሳሰቡን ተረድቶ ወደቀናው አስተሳሰብ ይሸጋገራል፡፡ ከራስህ ጋር ለመወቃቀስ ከራስህ ጋር መግባባት ይኖርብሃል፡፡ ወቀሳን የሚቀበል ጭንቅላት ካልፈጠርክ የራስህ ከሳሽ ራስህ ትሆናል፡፡ ከወቀሳ ይልቅ ክስ ውጤቱ ጥሩ አይደለም፡፡ ክስ በመጨረሻ ፍርድ አለው፡፡ ወቀሳ ግን ለራስህ ይቅርታ እንድታደርግለት ነጭ ነጩን ነግሮ ምክር ይለግስሃል፡፡ ወቃሹም ተወቃሹም ራስ ለራስ ነው፡፡

የሚዛናዊነት፣ የአስተዋይነትና የብልህነት ቁልፍ ከታጠፈ ደግ ነገር ሁሉ ላይከፈት ተቆልፎ ይኖራል፡፡ ልብ ከተከረቸመ ቀናነትም ይጠረቀምበታል፡፡ አዕምሮ ከተዘጋ መልካም አስተሳሰብም የተዘጋ ይሆናል፡፡ ሕሊና በምክንያት መውደድና መጥላት ካልቻለ እንደጋሪ ፈረስ በማንም ደመነፍስ ይሾፈራል፡፡ ቁልፍ የሌለው ቤት ለሌባ እንደሚመች ሁሉ ቁልፍ አስተሳሰብ የጎደለውም የማንም ግብስብስ ሃሳብ መጫወጫ ይሆናል፡፡

የሕይወት ጋኑን የሚከፍት ቁልፍ ቅን አስተሳሰብና ምክንያታዊነት ብቻ ነው፡፡ ጋኑ አዕምሮ ነው፤ ቁልፉም አስተሳሰብን ይወክላል፡፡ ብዙ ተመሳስለው የሚሠሩ ቁልፎች ወይም ሃሳቦች አሉ፡፡ የቁልፉን ጋን የሚከፍተው ግን አንዱ ቁልፍ ብቻ ነው፡፡ ያ ቁልፍ የሕይወትህን መስመር፣ የአንተነትህን ጎዳና በርግዶ የሚከፍት ነው፡፡ አዎ ቁልፉ ስሪቱ ከአመለካከትህ ነው፡፡ ጥሬ ዕቃው የበሰለ ሃሳብህ ነው፡፡ በቀላሉ በማንም የማይከፈት ቁልፍ ለማድረግ ግን ማስተር ቁልፍ ያስፈልግሃል፡፡ ስትፈልግ የምትከረችመው፤ ሲያሻህ የምትበረግደው፡፡ የአዕምሮህን ቁልፍ በቀላል ሃሳብ ካዋቀርከው የማንም ተመሳሳይ የሃሳብ ቁልፍ ይከፋፍትብሃል፡፡ አንተ የእኔ የምትለው ሃሳብ ስለሌለህ የሌሎች ሃሳብ መኖሪያና መፈንጫ ትሆናለህ፡፡ በራስህ ሃሳብ እንዳትራመድ አንቆ ይይዝሃል፡፡

ብዙዎቻችን የተቸገርንበት ጉዳይ ይሄ ይመስለኛል፡፡ የአዕምሯችንን ቁልፍ ለምናደንቃቸው፣ ለምንወዳቸው፣ ከአኛ በላይ ያውቃሉ ለምንላቸውና በግል ለምናከብራቸው ሰዎች ስላስረከብን እነሱ ሲወድቁ እኛም እንወድቃለን፣ በአመለካከታቸው ሲፍገመገሙ እኛም እንፍገመገማለን፡፡ በክፉ ሃሳባቸው ምክንያት የሃሳብ ጢሻ፣ የሃጢዓት ገደል ውስጥ ሲገቡ እኛም ገደል እንገባለን፡፡ ሲፎክሩ እንፎክራለን፣ ጃስ ሲሉን እንናከሳለን፤ ያዘው ሲሉን እናሯሩጣለን፤ በለው - ቁረጠው ሲሉን እጃችን ለመሰብሰብና አንድ ጊዜ እንኳን ለማሰብ ጊዜ የለንም፡፡ አድርጉ የተባለውን ነገር ለማድረግ አናቅማማም፡፡ ከአመክንዮ ጋር ተጋጭተን ስለምንኖር ለምን እንዴት ብለን አንጠይቅም፡፡ ለራሳችን ሃሳብ ፍሬን አላዘጋጀንለትም፡፡ ለአስተሳሰባችን ቁልፍ የለንም፡፡ ሕይወታችን የሚሽከረከረው በሌላ ነው፡፡ ፍሬኑ እንደተበጠሰ መኪና ወደፊት መብረር እንጂ የዓለምን አራቱንም አቅጣጫ አይተንና አስበን አንሄድም፤ተረጋግተን የሕይወትን መንታ መንገድና መሰናክል አንሻገርም፡፡

ወዳጄ ሆይ… የአንተነትህ ምስል የአስተሳሰብህ ስዕል ነው፡፡ እይታህ የሚወለደው ከአመለካከትህ ነው፡፡ ምግባርህና ማንነትህ የሚታወቀው በስራህ ነው፡፡ ስራህ ደግሞ ተምጦ የሚወለደው ከሃሳብህ ነው፡፡ ሃሳብህ ከተበላሸ፣ የዘራኸው ከመከነ ፍሬህ አይጎመራም፡፡

አዎ! የትዕግስትህ ቁልፍ የደስታህን በር ይከፍታል፡፡ የታጠፈ ወይም የተጣመመ የአስተሳሰብ ቁልፍህ ግን የሕይወት ጋንህን፣ የአዕምሮህን ካዝና መክፈት አይችልም፡፡ የሕይወት ቁልፍህን ቀጥ አድርገህ ትሰራ ዘንድ አስተሳሰብህን አቅና፡፡ የቀና አስተሳሰብ የአዕምሮውን በር ወለል አድርጎ ይከፍታልና፡፡

ቅንነት ለሁሉ የተከፈተ ማንነት ነው፡፡ የደግነት የትየለሌ ትርፉ ደግ ከዋልንለት የበለጠ ለራስ ነው፡፡

ቸር ቅንነት! ቸር መጣመም የሌለበት ማንነት!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
2.9K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 17:51:27
2.3K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 15:28:20
በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ መሪዎች ሊማሩበት የሚገባ ሃላፊነትን የመውሰድ courage!

ጀግናዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአትሌቲክስ ቡድናችን አባላት ወደ ዛምቢያ ለውድድር ባቀኑበት ወቅት የደረሰባቸውን እንግልት በሚመለከት ያስተላለፈችው መልእክት

"እኔ በግሌ ይቅርታ እጠይቃለሁ ።
አሳዛኝ ክስተት ነው። በዛምቢያ አትሌትቲክስ ቡድናችን ላይ ለደረሰው እንግልት ኃላፊነት እወስዳለሁ። ከብዙ ጥረት በኋላ አትሌቶቻችን ማረፊያ ሆቴል እንዲያገኙ እንዲረጋጉ አድርገናል። በመሪዎች ችግር በሃገሬ የማየው ምስቅልቅል እኔ በምመራው ተቋም ውስጥ ልጆቼ(አትሌቶች) እንዲህ በብርድ በየመንገዱ ኩርምት ብለው ሲዋረዱ በፍፁም ማየት አልሻም። ጉድለቱ ከኔ ከመሪዋ ደራርቱ ነው አርማለሁ። ይቅርታም እጠይቃለሁ። "
2.6K viewsLighthouse- Academy of Success, edited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 16:33:02
ጓደኝነትህን ከፍ ያለ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር አድርግ፡፡ ካንተ የተሻሉ ሰዎችጋ የምትውል ከሆነ እንደ እነሱ መሆን ትጀምራለህ፡፡ ተራ የሆነ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር ስትሆን ተቃራኒውን ትሆናለህ፡፡

እድገትህ ያለው ከፊትህ እንጂ ከኋላህ (ካለፈው) አይደለም፣ የፊትህ ላይ አተኩር፡፡

ከምንም በላይ ራስህን አሳድግ፡፡ በፅሁፍም ሆነ በንግግር ሃሳብህን በሚገባ ለመግለፅ ተማር፣ ስልጠና ውሰድ፡፡ ይሄ ብቻ ተፈላጊነትህን በ50% ይጨምራል፡፡

በተቻለ መጠን ውስጥህ መሆን የሚፈልገውን ሁን፤ የሚያስደስትህን ስራ፡፡
ትሁት ሁን፡፡ ትሁት ሰው እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ አይልም፡፡ ከሌሎች ይማራል፤ ያለማቀረጥ ያነባል፣ ሎሎችን ይሰማል፣ ይማራል፡፡

አካልህን እና አእምሮህን በሚገባ ተንከባከብ፡፡ በምድር ላይ ስትኖር የሚኖርህ አንድ አካል እና አንድ አእምሮ ስለሆነ በትጋት ጠብቀው ተንከባከበው፡፡
1.9K viewsLighthouse- Academy of Success, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 18:02:53
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።

በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።

አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።

በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።

በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል። ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።

በኖረበት ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።

አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።

#ከዚህ ታሪክ የምንማረው:-
የተሰጠን ዛሬ እንደሆነ አውቀን የተዳፈነውን ችሎታችንን አውጥተን ለሌሎች የብርሃን ችቦን እንለኩስ።
3.8K viewsLighthouse- Academy of Success, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 16:56:30
በህይወት ውስጥ ገንዘብ የማይገዛው በዋጋ ሊተመን የማይችል ነገር ምንድን ነው?
2.7K viewsLighthouse- Academy of Success, 13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:44:18 “አንድ ባህል ወደ ቀጣይ ትውልድ እንዳይተላለፍ
ከተፈለገ መፀሀፎችን ማቃጠል አያስፈልግም። ይልቅ ሠዎቹ መፀሀፍ ማንበብን እንዲያቆሙ ማድረግ በቂ ነው።”
(ራይ ብራድበሪ)

“የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአካላችን የሚጠቅመውን ያህል ንባብም ለአእምሯችን ይጠቅማል።”
(ሪቻርድ ስቲላ)

“ሸረሪቶች እንደተወለዱ በተፈጥሮ ድርን የመስራት ክህሎትን እንደሚያገኙ ሁሉ ህፃናትም ሲወለዱ የመናገር ጥበብና ችሎታ አብሯቸው ይወለዳል። ግና ማንበብ መቻልን እኛ ነን ልናለማምዳቸውና ልናስተምራቸው የሚገባን።”
(ስቴቨን ፒንከር)

“መርከበኞች በአንጸባራቂ ደሴት ላይ ከሚያገኙት
ሀብት በላይ ብዙ ሀብት የሚገኘው መፅሀፍቶች ውስጥ ነው።”
(ዋልት ዲስኒ)

“አንተ ጋር ሲመጡ መፀሀፍ በእጃቸው ያልያዙ ሠዎችን በፍፁም አትመን።”
(ሊሞኒ ስኒኬት)

“ለማንበብ ግዜ የለኝም ካልን ለማውራትና ለመፃፍ
እንዴት ግዜ እናገኛለን?”
(ስቴቨን ኪንግ)

“ህፃናት እንደሚያደርጉት ለመገረም ብለው መፀሀፍን አያንብቡ። ለመማርም ሆነ ህልመኛ ለመሆንም ፈልገው አያንብቡ። ይልቅ አዎ! ለመኖር ሲሉ ነው ማንበብ ያለብዎት።”
(ጉስታቮ ፍላውበርት)

“እኔና ጥቂት ሰዎች ስለራሳችን መልካም ነገር
የምናስበውና ጥሩ ስሜት የሚሠማን መፀሀፍ ስናነብ ነው።”
(ጄን ስሜይሊ)

“የልጆቻችንን ቀጣይ ህይወት ብሩህ ልናደርግላቸው የምንችልባቸው ጥቂት መንገዶች አሉ። ከነዚህ መንገዶች መሃል ሠፊውና አስተማማኙ በውስጣቸው የንባብ ፍቅርን መዝራት
ነው።”
(ማያ አንጄሎ)

“መፀሀፍ ማንበብ ነገሮችን እንድንረዳ ብቻ ሳይሆን ሌሎች እኛን በቀላሉ እንዲረዱን ይጠቅመናል።”
(ጆን ግሬን)

“አንተ ያላነበብከውን መፀሀፍ አንብብ ብለህ ለልጅህ አትስጠው።”
(ጆርጅ በርናንድ ሾው)

“አንተ ወይም እኛ የማናውቃቸው ነገሮች በሙሉ መፀሀፍት ውስጥ እንዳሉ እናውቃለን?”
(ሲድኒ ስሚዝ)

“እኔ አንብቤ ባስቀመጥኳቸውና በማነባቸው
መፀሀፎች ካልተከበብኩ እንቅልፍ በፍፁም አይወስደኝም።”
(ጆርጅ ሉዊሥ በርጌሥ)
1.1K viewsLighthouse- Academy of Success, edited  16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:44:11
1.1K viewsLighthouse- Academy of Success, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 18:50:42
እናንብብ!
ውድ ቤተሰቦቻችን:- ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ/link በመጫን ማንበብ የምትፈልጉትን መጽሐፍ ጠይቁን። እናጋራችኋለን
https://t.me/lighthouse4booksharing
1.1K viewsLighthouse- Academy of Success, edited  15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 17:06:05
መጻሕፍት ጠቃሚ የእውቀት ምንጭ ሲሆኑ ንባብ ደግሞ በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ላሉ ሰዎች የሚያስፈልግ መሠረታዊ ችሎታ ነው።

የአለም መጽሐፍ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ የንባብ ፍቅርን፣ የመጻፍ፣ የማተም እና የቅጂ መብትን ለማስተዋወቅ በየአመቱ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 23 ይከበራል። የዚህ ቀን መከበር ጠቀሜታ የማንበብና መጻፍ እንዲሁም የትምህርትን ግንዛቤ ለማሳደግ እና ንባብን ለማበረታታት ነው።

በዚህ ቀን የመጽሃፍ እና የንባብ ፍቅርን ለማስተዋወቅ በአለም ዙሪያ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ይዘጋጃሉ።

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ሚያዝያ 23 ቀን 1995 የመጀመሪያውን የዓለም መጽሐፍ ቀን አዘጋጅቷል።

የ2023 የዓለም መጽሐፍ ቀን ጭብጥ 'የአገር በቀል ቋንቋዎች' ሲሆን በአንድ ሀገር የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች ውስጥ ያለውን ልዩነት በማስተዋወቅ ላይ ያተኩራል። በኛ አገር ቀኑ በዚህ መልኩ መከበሩን በሚመለከት እስካሁን ያገኘነው መረጃ የለም።

የ2023 የዓለም መጽሐፍ ቀን አነቃቂ ጥቅሶች

"አለመቻቻል እና አለማወቅን ለመከላከል በጣም ውጤታማው መሣሪያ መጽሐፍ ነው"
- ሊንደን ቢ. ጆንሰን

"መጻሕፍት ጸጥ ያሉ እና ቋሚ ጓደኞች፣ በጣም ተደራሽ የሆኑ ከአማካሪዎች ሁሉ ጥበበኛ እና ከአስተማሪዎች በጣም ትዕግስተኛ ናቸው።"
- ቻርለስ ዊልያም ኤሊዮት

"የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።"
- ሃርፐር ሊ

"ዓለም ሥነ ምግባር የጎደላቸው ናቸው ብሎ የሚጠራቸው መጻሕፍት የዓለምን የራሷን ነውር የሚያሳዩ መጻሕፍት ናቸው።"
- ኦስካር ዋይልዴ

"መጽሐፍ በእጅህ የምትይዘው ሕልም ነው። " - ኒል ጋይማን

ምንጭ:- The Times of India
1.4K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ