2023-04-04 17:03:25
1. ተስፋ አድራጊ መሆን ረጅም ርቀት ይዞህ ይሄዳል፡፡
በጣም አስከፊ በሆኑ ጊዜያት እንኳ ተስፋ ባለመቁረጥ ችግሮችን መጋፈጥና ለመቀየር መቁረጥ የመፍትሄ መላ እንዲመጣልን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጨለምተኛ አትሁን፡፡
2. መርህ፣ አቋም፣ ያመንክበት ጉዳይ ይኑርህ ነገር ግን ለመስተካከል ቦታ ይኑርህ፡፡
በደረስክበት እውቀት መሰረት በነገሮች ላይ አቋም ሊኖርህ ይገባል፡፡ ነገር ግን የህይወት ዘመን ሁሉ ተማሪ ከሆንክ በአንድ ወቅት የያዝከው አቋም ትክክል እንዳልሆነ ስትረዳ ያመንክበትን ጉዳይ ማስተካከል ይኖርብሃል፡፡
3. አዋዋልህን እና ጓደኞችህን ምረጥ፡፡
አስተሳሰብህን እና ድርጊትህን በገንቢ ጎን ከሚተቹና ከሚገነቡ ሰዎች ጋር የምታደርግ ከሆነ በየጊዜው እየተሻሻልክ የምትሄድ ሰው ትሆናለህ፡፡ ባህሪህ እና ህይወትህ እያደር የሚመስለው የጓደኞችህን ነው፡፡
4. መሆን የምትፈልገውንና መስራት የምትፈልገውን በጊዜ አውቀህ ጀምር፡፡
በወጣትነት ጀምረህ መርጠህ የምትሄበት መንገድ እያደር አንተንም እየቀረፀህ ስለሚሄድ በዛው የመቀጠል እድል ይጨምርልሃል፣ አይቻልም ለሚሉህ በቀላሉ ላትሸነፍ ትችላለህ፣ በእድሜህ ብዙ ሳትገፋ ስኬታማ እና ብዙ ተፅእኖ አምጪ ትሆናለህ፡፡ የራስህን ራእይ የማትገነባ ከሆነ ሌሎች ቀጥረውህ ራእያቸውን እንድትገነባላቸው ያደርጉሃል፡፡
5. ከሌሎች ጎበዞች ጋር በጥምረት ስራ፡፡
ከጎበዞች ጋር በጥምረት ስትሰራ አንተ የማታውቃቸውን ነገሮች ያሳውቁሃል፣ አንተ ልታገኛቸው የማትችላቸውን ሰዎች እንድታገኝ እድል ይከፍቱልሃል፣ ይበልጥ ወደፊት ያራምዱሃል፡፡
6. በቅፅበት ከፍተኛ ደረጃ እደርሳለሁ አትበል፡፡
ከትምህርት ቤት አንደወጣህ ወዲያው ሃብታም፣ ባለስልጣን፣ ወይም ስኬታማ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ቢኖርህ እንኳ ስኬታማ ለመሆን ብዙ ልምድ ያስፈልግሃል፡፡
7. ስለ ስህተቶችህ ሌሎችን ሳይሆን ራስህን ውቀስ ተማርባቸው፡፡
ስህተቶች እንድንቆጭባቸው ሳይሆን እንድንማርባቸው ካደረግን ደግመን አንሰራቸውም፡፡
8. በተቀጣጠለ መንፈስና መሰጠት ስራ፡፡
መርጠህ ወይም ፈልገህ የምትሰራውን ስራ በከፍተኛ ትጋት፣ መሰጠት፣ መቀጣጠል የምታደርግ ከሆነ ስራ አስደሳችና ቀላል ይሆንልሃል፡፡ የምትሰራው ስራ ውስጥ እነዚህ ነገሮች ከጠፉ ወይም የምትሰራው የሚሰለችህ ከሆነ የምትሰራው ነገር የውስጥ ፍላጎትህን ማንፀባረቁ አጠራጣሪ ነው፡፡
9. ምርጡ ትምህርት ቤት ኮሌጅ ሳይሆን ህይወት ነው፡፡
ምንም ያህል መፅሀፎች ብታነብ፣ ፈተናዎችን ብትወስድና ብታልፍ፣ በህይወት ሂደት የምትማረውን ያህል ብቁ አያደርጉህም፡፡ ስራዎች እና የስራ ሃላፊዎች ያስተምሩሃል፣ ያበቁሃል፡፡
10. እውነተኛ ኑሮና ህይወት በቴሌቪዥን እንደምታየው አይደለም፡፡
ኑሮ ቲቪ ላይ ስታይ እንዳለው ካፌዎች ሄዶ ዘና ማለት ከመሰለህ ተሳስተሃል፡፡ ስራ ሰርተህ ኑሮህን ህይወትህን ለመለወጥ ተንቀሳቀስ፡፡
11. ህይወት ሁሌም የቀና አይደለም፡፡
በህይወት ጉዞህ ትገጫለህ ትወድቃለህ፡፡ ኑሮ ፈተና ነው፣ ጌም መሳይ ነው፣ ተነስተህ እስኪሳካልህ ጉዞህን ቀጥል፡፡
12. የራስ ስራ መስራት ድፍረትና ብከስርም እሰራለሁ ማለትን ይጠይቃል፡፡
ቢዝነስ በአንድ ጎኑ አንደ ቁማር ነው፡፡ 100% ማሸነፍ መቻልህን ቀድመህ እርግጠኛ መሆን አትችልም፡፡ ከቁማር የሚለየው ግን ማጥናት፣ ማቀድና፣ ሁኔታዎችን እያየህና እየቀያያርክ በጥንቃቄ መተግበር መቻልህ ነው፡፡
13. ለስኬታማነት ትእግስት እና ጠንክሮ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ዘላቂ ስኬት የለም፡፡
14. ለራስህ ክብር ይኑርህ፣ በማንነትህ ኩራ፡፡
እያንዳንዳችን የተለያየን ስለሆንን ራስህን ከሌላው ጋር እያወዳደርክ ዝቅተኝነት አይሰማህ፡፡ በሌላው ውስጥ የሌለ አንተ ውስጥ ያለ ችሎታ ስላለ ፈልገህ አግኘው፣ ተቀበለው፣ እዛ ላይ አተኩር፣ አዳብረው፣ በራስህ ተማመን፡፡ ስኬታማ የምትሆነው በዚህ መንገድ ነው፡፡
15. ራስህን አታሳብጥ፡፡
ስኬታማና ታላቅ የመሆን ራእይ መሰነቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ ብትወጣ ነገ ደግሞ ታች መውረድ ሊገጥምህ ይችላል፡፡ ላይ መውጣትህ የብዙ ነገሮች ጥምር ውጤት ስለሆነ ራስህን አይነኬና ልዩ ፍጡር አድርገህ አታስብ፡፡
16. ነገሮችን በቀና በመውሰድ ተማር፡፡
በስራህ ያልተደሰቱብህ ደንበኞችና ትችቶቻቸው፣ ስህተቶችህ፣ ውድቀቶችህ ታላቅ የመማሪያ መሳሪዎች ናቸው፡፡ ከነዚህ የሚመጣውን አስተያየትና ትችት አጣመህ አትመልከት፣ ተማርባቸው፣ ራስህን ለውጥባቸው፡፡
17. በአለም ስላለው ከፍተኛ ድህነት፣ የሃብት ልዩነት፣ ችግር አስብ፡፡
ቴክኖሎጂና ሃብት እየተስፋፋ በሄደ መጠን አለም ከቀድሞ ይልቅ የተሻለች ቦታ እየሆነች ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎች የሚኖሩት አስከፊ ድህነት፣ በሽታ፣ ወዘተ ደግሞ ሊቀየር የሚገባው እና የሚችል መሆኑን አስብበት፡፡
18. ስኬትህን አካፍል፡፡
አንተ ከፊትህ ከነበሩት ስኬታማ ሰዎች ታሪክና ፍሬአቸው እንደ ተነቃቃህ፣ እንደተማርክ እና እንደተጠቀምክ ሁሉ አንተም የስኬትህን ምክንያቶች እና ውጤቶች ለሌሎች አካፍል፡፡ መሪነት ሌሎችን ለስኬት ማብቃት ነው፡፡
19. አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤነርጂ፣ እና ባዮ ሳይንስ ጥሩ የትምህርት ዘርፎች ስለሆኑ እነዚህን ተማሩ፡፡
እነዚህ የትምህርት ዘርፎች ወደፊት ከፍተኛ ተፅእኖ የሚፈጠርባቸው ናቸው፡፡
20. ደሃ ሆነህ ተወልደህ ከሆነ ጥፋቱ የአንተ አይደለም፤ ደሃ ሆነህ ልትሞት ከሆነ ግን ጥፋቱ የአንተ ነው፡፡
1.1K viewsLighthouse- Academy of Success, 14:03