Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ሶቅራጥስን የስኬት ምስጢር ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል። ሶቅራጥስ ከወጣቱ | Lighthouse Training & Consulting PLC

በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ሶቅራጥስን የስኬት ምስጢር ምን እንደሆነ ይጠይቀዋል። ሶቅራጥስ ከወጣቱ ጋር በነጋታው ጠዋት ከወንዝ ዳርቻ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዘ።

በነጋታው ሁለቱም እየተራመዱ ወደ ወንዙ ገቡ። ውሀው አንገታቸው ላይ ሲደርስ በድንገት ሶቅራጠስ ልጁን ጎትቶ ውሀው ውስጥ ደፈቀው። ልጁ ለመውጣት ቢታገልም ጉልበቱ ከሶቅራጥስ ጋር ሊመጣጠን ስላልቻለ ጥረቱ አልተሳካለትም።

በመጨረሻ ወጣቱ ፊቱ ወደ ሰማያዊነት መቀየር ሲጀምር ለቀቀው። ልጁ አየር ስቦ ከተረጋጋ በኋላ ሶቅራጥስ ጥያቄውን አቀረበለት "ለመሆኑ ውሀ ውስጥ እያለህ ከምንም ነገር በላይ አስፈልጎህ የነበረው ነገር ምንድነው?" ልጁ ምንም ሳያመነታ "አየር" ብሎ መለሰ።

"የስኬትም ሚስጢር ይሄ ነው፤ ልክ አየር የፈለከውን ያህል ስኬትንም ፈልገውና ታገኘዋለህ፤ ሌላ ሚስጥር የለውም" ብሎ መለሰለት።

"ያለህበት አለም የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን የሌሎችን የስኬት ጉዞ ካነበብክ ለስኬት የሚያበቃህን እምነት መፍጠር ትችላለህ!"

--- አንቶኒ ሮቢንስ