Get Mystery Box with random crypto!

Lighthouse Training & Consulting PLC

የቴሌግራም ቻናል አርማ lighthouselearningcenter — Lighthouse Training & Consulting PLC L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lighthouselearningcenter — Lighthouse Training & Consulting PLC
የሰርጥ አድራሻ: @lighthouselearningcenter
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.97K
የሰርጥ መግለጫ

በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግል እና ሙያዊ አቅምን የሚያጎለብቱ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን እንሰጣለን።
ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ!
አስተያየትዎን ለመስጠት:-https://t.me/addlist/bKMEnwP0DG83ZGM0

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 57

2022-07-16 17:11:24
ኪስህ ገንዘብ ሲኖር ገብተህ የምትመዘው
ከጎንህ ሰው አለ እንደልጅ ምታዘው።
ብዙ አፋሽ አጎንባሽ በዙሪያህ ታያለህ
ገና ሳታስነጥስ ይማርህ የሚልህ።
ጥላ ላይም ቁመህ ጥላ ሚዘረጋ
የቆለፍከውን በር ሩጦ የሚዘጋ፤
በአቧራ ስትሄድ ከፊት ሳር አንጣፊ
ኪስህ ገንዘብ ካለ ሞልተዋል አጣፊ።

አጣሁ ያልክ እለት ግን ኪስህ ሲሆን ባዶ
አንተ በዚህ ስትሄድ እነሱ በማዶ።
አይደለም እንቅፋት ስትውል ብታስነጥስ
ለሞት ብታጣጥር ሰው የለም የሚደርስ።
ነገ ለሚነጋ ዛሬ ቀን ቢጨልም
እንኳን ያበላኸው…..
እንኳን ያጠጣኸው….
የራስህ ጥላ እንኳን ካንተ ጋር አይደለም።

እናማ ወዳጄ ኪስህን ደባብሰው
አለሁ ባይህ ኪስህ....
የወደክ ለታ አለ "ሺህ ገንዘብህ
አደናቅፎህ ብትወድቅ ሟጭሮህ ብትደማ
በማንም አትዘን … ማንንም አትማ።
መንገድ ሁሉ እንቅፋት በሆነበት አለም
መነሳት ነው እንጅ መውደቅ ብርቅ አይደለም።
ሰው ብታጣ ዛሬ አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን ያስተምራል እድሜ።
ሲኖርህ የኖረህ ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ ከፊት ባታገኘው፤
የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።
መሙላት ቢቸግርህ ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ ቀና በል ቀን አለ።

(በአርቲስት ሜሮን ጌትነት)
3.0K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:11:57 የዛሬ ዓመት ግድም ካንሰር ተገኘብኝ፡፡ ጠዋት 1፡30 ላይ የተደረግኩት ስካን ጣፊያዬ ላይ ያለውን ዕብጠት (Tumor) ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ዶክተሮቹ በአብዛኛው ሊሆን የሚችለው ፈውስ የለሹ የካንሰር ዓይነት ስለሆነ፤ ከሦስት እስከ ስድስት ወር በላይ እንደማልኖር አረዱኝ፡፡ ዶክተሬ፤ ወደ ቤቴ ሄጄ ነገሮችን ሁሉ ቦታ ቦታ እንዳስይዝ መከረኝ። ይሄ እንግዲህ በዶክተሮች ቋንቋ ምን ማለት ነው፤ “ለመሞት ተዘጋጅ” ነው፡፡ ይሄ ማለት እንግዲህ፣ ለልጆችህ በቀጣይ አሥር ዓመታት እነግራቸዋለሁ ብለህ ያሰብከውን ሁሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ንገራቸው - ልትነግራቸው ሞክር ነው፡፡ ይህም ማለት ሁሉንም ነገር ውሉን አስይዘህ፣ ለቤተሰብህ በተቻለ መጠን መለየትህን አቅልልላቸው ነው፣ ተሰናበት ነው።

በዚሁ ስሜት ቀኑን አሳለፍኩ፡፡ የዛኑ ዕለት ምሽት ላይ ኢንዶስኮፕ የሚባል መሳሪያ በጉሮሮዬ ሰደው፣ በጨጓራዬ በኩል ወደ አንጀቴ ላኩና በመርፌ ከጣፊያዬ ዕብጠት (Tumor) የህዋስ ናሙና ወሰዱ፡፡ በማደንዘዣ ራሴን ስቻለሁ፡፡ ሚስቴ ስትነግረኝ ግን፣ ዶክተሮቹ ህዋሳቶቹን በማሮክሮስኮፕ ሲመለከቷቸው በእንባ ታጠቡ። የያዘኝ ለካ ከስንት አንዴ የሚያጋጥመውና በቀዶ ጥገና ሊፈወስ የሚችለው የጣፊያ ካንሰር ነውና፡፡ ቀዶ ጥገናው ተከናወነ እናም አሁን በደህና ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፡፡

በቀጣይ ጥቂት አስርት ዓመታት ውስጥ ከዚህ የበለጠ እንደማይቀርበኝ ተስፋ እያደረግኩ፤ ይህ ወደ ሞት በጣሙን የተጠጋሁበት አንዱ አጋጣሚ ነው፡፡ በውስጡ ስላለፍኩበትም ሞትን እንደ ጥሩ አነቃቂ ምሁራዊ እሳቤ ከመገንዘብ በጠለቀ አንዳች የእርግጠኝነት ስሜት ይህንን ልላችሁ እችላለሁ፤ ማንም ቢሆን መሞት አይፈልግም ! መንግስተ ሰማያት መግባት የሚሹ ሰዎች እንኳ በዚህ መልክ እንዲሆን አይፈልጉም፡፡ ቢሆንም ግን ሞት የሁላችንም የጋራ መዳረሻችን ነው። ማንም ሊያመልጠው የቻለ የለም፡፡ መሆንም ያለበት ነው ደግሞ። ምክንያቱም፣ ሞት ምናልባትም ብቸኛው የህይወት ምርጡ ፈጠራ ነው፤ አሮጌውን አፅድቶ ለአዲሱ ጎዳና ቀያሽ፡፡ የህይወት የለውጥ ወኪሏ!

አሁን አዲሱ እናንተ ናችሁ፡፡ አንድ ቀን ግን፤ ከዛሬ ብዙም ባልራቀ ጊዜ፤ ቀስ በቀስ እያረጃችሁ መወገዳችሁ አይቀርም፡፡ ይህን በማለቴ አዝናለሁ፣ ግን እውነት ነዋ! ጊዜያችሁ ውስን ነው። በመሆኑም የሌላን ሰው ህይወት በመኖር አታባክኑት፡፡ ተራ ቀኖና አይሸብባችሁ። ማለትም፣ በሌሎች ሰዎች አስተሳሰብ አትመሩ፡፡ የሌሎች ሰዎች ዕሳቤ የውስጣችሁን ረቂቅ ድምፅ፣ ልባችሁ የሚነግራችሁን፣ እንዳያውክ ተጠንቀቁ፡፡ ውስጣዊው ድምፅ፣ ቀድሞውኑ ነገር፣ የምር መሆን የምትፈልጉትን ይነግራችኋል። ሌላ ማንኛውም ነገር ከዚህ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡

ወጣት ሳለሁ The whole Earth Catalogue (የመላው ዓለም ማውጫ) የሚሰኝ፣ ከእኔ ትውልድ ቅዱስ መፅሐፍት እንደ አንዱ የሆነ፣ ድንቅ ህትመት ነበረ፡፡ የህትመቱ ፈጣሪ ስትዋርት ብራንድ ይባላል። ቅኔያዊ ለዛ አፍስሶበት ህይወት ዘርቶበታል፡፡ ጊዜው 1960ዎቹ ማለቂያ ግድም ሲሆን፤ ኮምፒዩተሮችም ሆነ የሕትመት ሶፍትዌር የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህ በታይፕራይተር፣ በመቀስና በፖላሮይድ ካሜራ ነው የተዘጋጀው፡፡ ጉግል በመፅሐፍ መልክ፤ ጉግል ከመምጣቱ ከ35 ዓመታት በፊት በሉት፡፡ ፍፁም የፀዳ፣ ምናባዊና ማለቂያ የለሽ በሆኑ ምርጥ ስልቶች የታጀበ ነበር፡፡ ስቱዋርት እና ቡድኑ የመላው ዓለም ማውጫን ተከታታይ ህትመት ካሳተሙ በኋላ፣ በስተመጨረሻ፣ የማጠቃለያው ዕትም ወጣ፡፡ ወቅቱ በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ ነበር - እኔም ልክ በእናንተ ዕድሜ ላይ ነበርኩ፡፡

በመጨረሻው ዕትም የጀርባ ሽፋን ላይ አንድ ፎቶግራፍ ነበረ። ማለዳ ላይ የተነሳ የገጠር መንገድ ምስል። በጀብደኝነት በእግራችሁ ስትጓዙ የሚያጋጥማችሁ አይነት የማለዳ የገጠር መንገድ ምስል፡፡ ከስሩ እንዲህ የሚሉ ቃላት ሰፍረዋል፡፡

Stay Hungry, Stay Foolish
(ይራባችሁ ፣ ሞኝ ምሰሉ)

አጠቃላዩን ህትመታቸውን ሲያጠናቅቁ የተጠቀሙበት የስንብት መልዕክት ነበር፡፡

Stay Hungry, Stay Foolish
(ይራባችሁ ፣ ሞኝ ምሰሉ)

እናም…እኔም…ለራሴ ሁሌም እመኘው የነበረው ይህንኑ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ፣ እናንተም ተመርቃችሁ ህይወትን እንደ አዲስ ስትጀምሩ፣ የምመኝላችሁ ይህንኑ ነው።

Stay Hungry, Stay Foolish
(ይራባችሁ ፣ ሞኝ ምሰሉ)

ሁላችሁንም በጣም አመሰግናለሁ፡፡
------///-----
(ይህን ጽሁፍ ያገኘነው በግሩም ተበጀ ከተዘጋጀው ' ግሩም የዓለማችን ምርጥ ታሪኮች' መጽሃፍ ነው።)
2.5K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:11:56 የስቲቭ ጆብስ የስራ፣ የፈጠራና የህይወት ታሪክ በብዙዎች ዘንድ እጅግ መሳጭና መንፈስ አነቃቂ ታሪክ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ፣ በ2005፣ በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ በዓል ላይ ተገኝቶ ያቀረበው ድንቅ የምረቃ በዓል ንግግሩ (Commencement Address) የበርካቶችን ልብ የነካ ነበር፡፡ ይህ የሚሊዮኖችን ልብ ያነቃቃውን የክፍለ ዘመናችን ድንቅ ንግግር አሁንም ድረስ ሚሊዮኖች እየተቀባበሉ የሚደመሙበት ነው።
ሙሉ ንግግሩ እንደሚከተለው ቀርቧል።


<<አንዳንዴ ህይወት አናታችሁን ትቀውራችኋለች፡፡ እምነት ግን አትጡ!>>

የመጀመሪያው ታሪኬ ስለማፍቀርና ማጣት ነው፡፡ ዕድለኛ ነኝ፡፡ ማድረግ የምፈልገውን ያገኘሁት ገና በለጋ ዕድሜዬ ነበር፡፡ ጓደኛዬ ዎዝ እና እኔ አፕልን በቤተሰቦቼ ጋራዥ ውስጥ ስንጀምር ገና የ20 ዓመት ወጣት ነበርኩ፡፡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል ፈግተን፣ በ10 ዓመት ውስጥ፣ አፕል በሁለታችን ጋራዥ ውስጥ ከተቋቋመ ኩባንያነት ተነስቶ 4,000 ተቀጣሪዎች ወዳሉት የባለ 2 ቢሊዮን ዶላር ግዙፍ ኩባንያነት ተመነደገ፡፡ የመጨረሻው ድንቁ ፈጠራችንን፣ ማኪንቶሽ (ኮምፒዩተር)ን ከአንድ ዓመት በፊት ለዓለም አበርክተናል። እናም እኔ 30ኛ ዓመቴን እንደያዝኩ ተባረርኩ! ...እንዴት ነው ራሳችሁ ካቋቋማችሁት ኩባንያ የምትባረሩት?

ነገሩ እንዲህ ነው። አፕል እያደገ ሲመጣ በጣም ክህሎት አለው ብዬ ያመንኩበት ሰው አብሮኝ ኩባንያውን እንዲመራ ቀጠርነው፡፡ በመጀመሪያ ዓመት አካባቢ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበሩ። ቀስ በቀስ ግን የድርጅቱን መፃኢ ዕድል በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ራዕያችን እየተራራቀ መጣና በስተመጨረሻ ጭርሱኑ ተለያየን፡፡ ስንለያይ፣ የዳይሬክተሮቹ ቦርድም ለእሱ ወገኑና፣ በ30 ዓመቴ ተባረርኩ። ሀገር ባወቀው አሳፋሪ ሽንፈት፤ ተባረርኩ! ህይወቴን የሰጠሁለት ነገር በአንዴ ከእጄ በንኖ ጠፋ፡፡ ይጎዳል፤ ተጎዳሁ፡፡ ለጥቂት ወራት ያህል ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን አላወቅኩም ነበር፡፡

የቀድሞውን ትውልድ ስራ ፈጣሪዎች ራዕይ ያበላሸሁ፤ ለእኔ የተላለፈልኝን ሰንደቅ እንደጣልኩ ተሰማኝ፡፡ ዴቪድ ፓካርድና ቦብ ኖይስን አግኝቼ ለከፋው ሽንፈቴ ይቅርታ ልጠይቅ ተፍጨረጨርኩ፡፡ በህዝብ ፊት ነበራ የተዋረድኩት። ከኮምፒዩተር ዓለሙ ማማ፤ ከሲልከን ቫሊውም ሹልክ ብዬ ልጠፋ አሰብኩ፡፡ ግና…ቀስ በቀስ አንዳች እውነት ይገለፅልኝ ጀመር፡፡ ምንም ይሁን ምን፤ እስከዛሬ የሰራሁትን እወደዋለሁ፡፡ አፕል ውስጥ ከተከሰቱት ሁነቶች አንዳችም የተለወጠ ነገር የለም፤ አሁንም እንደተባረርኩ ነው፡፡ ቢሆንም ግን፣ አሁንም ድረስ፣ የምሰራውን እወደዋለሁ። እናም፣ እንደገና፣ እንደ አዲስ ለመጀመር ወሰንኩ፡፡

ያኔ ባይታየኝም ከአፕል መባረሬ ለእኔ በህይወቴ ሊያጋጥሙኝ ከሚችሉት ታላላቅ ክስተቶች አንዱ ሆነ፡፡ የስኬታማነት ሸክም በውድቀት ሳቢያ በሚከሰት የእንደገና ጀማሪነት ቅለት ተተካ፤ ስለ ሁሉም ነገር ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ የማይኮንበት ጅማሮ፡፡ የህይወቴ እጅጉን በፈጠራ የተንበሸበሸው ወቅት ይፈነጥቅ ዘንድ መንፈሴ ነፃ ወጣች፡፡

በቀጣይ አምስት ዓመታት ኔክስት እና ፒክሳር የተሰኙ ኩባንያዎችን አቋቋምኩ፡፡ አሁን ላይ ሚስቴ ከሆነችው አስደናቂ ሴት ጋር በፍቅር ወደቅኩ፡፡ ፒክሳር የዓለማችን የመጀመሪያው የሆነውን የኮምፒዩተር አኒሜሽን ፊቸር ፊልም፣ ቶይ ስቶሪን፣ ለመስራት በቃ። እናም የዓለማችን እጅጉን ስኬታማው የአኒሜሽን ሲቱዲዮ ለመሆን ቻለ፡፡

አስደናቂ በሆነ የክስተቶች መገጣጠም ሳቢያ፣ አፕል ኔክስትን ሲገዛ ደግሞ፣ እኔም በዛው አፕልን ዳግም ተቀላቀልኩ፡፡ ኔክስት ውስጥ ያጎለበትናቸው ፈጣራዎችም የአፕል የወቅቱ ህዳሴ ስረ መሰረት ሆኑ፡፡ ሎረን እና እኔ አሁን ላይ አስደሳች ቤተሰብ መስርተናል፡፡

ከአፕል ባልባረር ኖሮ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ላገኝ እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በዕርግጥ በጣም መራር መድኃኒት ነበር። ግን እንደምገምተው ለበሽተኛው የግድ አስፈላጊ ነበረ፡፡ አንዳንዴ ህይወት አናታችሁን ትቀውራችኋለች፡፡ እምነት ግን አትጡ፡፡ በሽንፈቴ ውስጥ ሁሉ እንዳላቆም ፣ እንድቀጥል የረዳኝ የምሰራውን መውደዴ ለመሆኑ ጨርሶ ጥርጥር የለኝም፡፡ የምታፈቅሩትን ልታገኙ ይገባል፤ ይህ ደግሞ ለስራችሁም ሆነ ለፍቅራችሁ ወሳኝ ነው፡፡

ስራችሁ የህይወታችሁን ትልቁን ክፍል የሚይዝ ነው። እናም በስራችሁ ልትረኩ ዘንድ የምትሰሩት ነገር ታላቅ መሆኑን ልታምኑበት ይገባል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የምትወዱትን ስትሰሩ ነው! የምትወዱትን ሥራ እስካሁን ካላገኛችሁት ለመፈለግ አትቦዝኑ። ፈልጉ፤ አትርጉ፡፡ እናም፣ እንደሁሉም ከልብ የሆነ ነገር ሁሉ፣ ሰታገኙት ታውቁታላችሁ። እንደሁሉም ታላላቅ ግንኙነቶች ሁሉ፣ ዓመታት በነጎዱ ቁጥር፣ ይበልጡን እያማረና እየሰመረ ሂያጅ ነው፡፡


“…እያንዳንዱን ቀን ልክ የህይወትህ የመጨረሻው ቀን እንደሆነ እያሰብክ ከኖርክ፤ በዕርግጥም አንድ የሆነ ቀን ትክክል ትሆናለህ!”

የ17 ዓመት ልጅ ሳለሁ፣ እንዲህ የሚል ጥቅስ አንድ ቦታ አነበብኩ፤ “…እያንዳንዱን ቀን ልክ የህይወትህ የመጨረሻው ቀን እንደሆነ እያሰብክ ከኖርክ፤ በዕርግጥም አንድ የሆነ ቀን ትክክል ትሆናለህ!” ጥቅሷ በጣሙን ስለመሰጠችኝ ላለፉት 33 ዓመታት ሁሌ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ፤ መስታወት ፊት እቆምና ራሴን እንዲህ ስል እጠይቃለሁ፤ “…ዛሬ…የህይወቴ የመጨረሻዋ ቀን ብትሆን በዛሬዋ ዕለት የምሰራውን ስራ እሰራ ነበርን?” ለተከታታይ ቀናት መልሴ “አይ…” ከሆነ አንድ የሆነ ነገር መለወጥ እንዳለብኝ ይገባኛል፡፡ በቅርቡ እንደምሞት ማስታወስ በህይወቴ ካጋጠሙኝ፤ በህይወቴ ውስጥ ታላላቅ ውሳኔዎችን እንድወስን ከረዱኝ ነገሮች ውስጥ ዋንኛው ነው፡፡ ምክንያቱም፣ ሁሉም ነገር ማለት ይቻላል፣ መላው ከውጭ የምንጠብቃቸው ነገሮች፣ ክብሬ የምንለው፣ እወድቅ ይሆን፣ ብዋረድስ የሚሉት ፍራቻዎቻችን ሁሉ፣ እኒህ ሁሉ ነገሮች ሞት ፊት ሲቀርቡ በንነው ይጠፉና በቦታው እውነተኛዎቹ አስፈላጊ ነገሮች ብቻ ይቀራሉ፡፡ እኔ እንደማውቀው፣ እንደምትሞት ማስታወስ ማለት፣ አንዳች ነገር አጣ ይሆን ከሚል አሳሪ አስተሳሰብ የሚገላግልህ ምርጡ ስልት ነው፡፡ በመጀመሪያውኑም እኮ ምንም የለህም፤ እርቃንህንኮ’ ነህ ! የልብህን መንገድ የማትከተልበት ምንም አይነት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡
2.2K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:10:04
2.0K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 14:36:15
2.5K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:46:47
2.7K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 18:20:26
2.9K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:31:19
በህይወታችን የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት ጥረት ስናደርግ ተማሪ ቢኒያም የገጠመውን አይነት ፈተና ብዙዎቻችን ሊገጥመን ይችላል።

ሆኖም ፈተናዎችን መጥላት ሳይሆን ፊት ለፊት መጋፈጥ ጀግንነት ነው።

ፈተናዎች ተመጣጣኝ የሆኑ ብሎም የተሻሉ መልካም እድሎችን ይዘው እንደሚመጡ ስናምን ተስፋ መቁረጥ የሚባል ነገር ድራሹ ይጠፋል።

ተማሪ ቢኒያም ለዚህ ምሳሌ የሚሆን ጀግና ልጅ ነው።

ትምህርትህን በስኬት አጠናቀህ ለሌሎች የምትተርፍ ድንቅ የህክምና ባለሙያ እንደምትሆን እምነታችን ነው።

መልካሙን ሁሉ ተመኘን!
3.1K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:30:04 በሥነ-ልቦናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በሥራ አካባቢ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለውን ግኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ኢየን መክሪ እና ኤድሪየን ፈርሃም በተሰማሩበት ሙያ ስኬታማ የሚያደርጉ ስድስት የስብዕና መገለጫዎችን አስቀምጠዋል።

መክሪ እንደሚለው እያንዳንዱ መገለጫዎች የራሳቸው የሆነ ውስንነት እና ጠንካራ ጎን አላቸው። ስለዚህ የእያንዳንዱ መገለጫ ጥቅም የሚወሰነው ግለሰቦች በሚሰሩት ሥራ ላይ ስለሆነ መለኪያው ከእያንዳንዱ ሁኔታ ጋር ይቀያየራል።

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ስድስት የስብዕና መገለጫዎች እንዴት ወደ ስኬት እንደሚወስዱ አመላእተዋል።

1. ጠንቃቃነት

ጠንቃቃ ሰዎች ሁሌም እቅዳቸውን በትክክል ይተገብራሉ።
የእያንዳንዱ ውሳኔያቸው የወደፊት ውጤት ተጽዕኖን ያውቃሉ። ስሜታቸውንም መቆጣጠር ይችላሉ። ይህ የጠንቃቃነት ባህሪ በህይወትዎ ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ነው።

በሥራ አካባቢ ለትንሽ ነገሮች ትኩረት መስጠት ስልታዊ በሆነ መልኩ እያንዳንዱን ሥራ ለማቀድ ይጠቅማል።

2. ከነገሮች ቶሎ መላመድ

ሁሉም ሰው የሚያስጨንቀው ነገር ያጋጥመዋል፤ ዋናው ጥያቄ ግን እንዴት ያልፈዋል የሚለው ነው። ይህ ማለት ሥራዎት እና ሌላ ህይወትዎ ላይ ጫና እንዳሳያሳድር ለመላመድ መሞከር ማለት ነው።

ይህ ባህሪ የሌላቸው ሰዎች የሥራ አካባቢ አፈጻጸማቸው ደካማ ነው። ነገር ግን ተገቢውን የሥነ-ልቦና እርምጃ ከወሰዱ ውጤታማ መሆን ችላሉ።

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውጤታማ ለመሆን ሲባል አስጨናቂ ጉዳዮች ላይ በደንብ ትኩረትን መስጠት ከተቻለ፤ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ያሰበውን ነገር ማሳካት ይችላል።

3. ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል

የማያውቁትን ነገር የማይፈሩ እና ግራ መጋባትን አምነው የሚቀበሉ ሰዎች የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን ይችላሉ። ብዙ ነገሮችንም ከግምት ውስጥ ያስገባሉ።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ትንሽ የምትባለው ነገር ትርጉም እስከምትሰጣቸው ድረስ ስለሚጨነቁ የራሳቸውን ውሳኔ የመጨረሻ አድርገው ሊወስዱ ይችላሉ።
ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል የሚችል ሰው ለማንኛውም አይነት ለውጥ ሁሌም ዝግጁ ነው።

4. ጉጉ መሆን

ጥናቶች እንደሚያሳዩት የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ያለን ጉጉት ሁሌም አዲስ ነገር ለመፍጠር ይረዳናል። ይህ ማለት ለአዳዲስ ነገሮች ክፍት የሆነ ጭንቅላት አለን ማለት ሲሆን፤ በምንሰራው ሥራ ደስተኞች እንድንሆን ይረዳናል።

5. አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም

ደስ የማይል ነገር ሲያጋጥምዎት ለጊዜው ስለቀለልዎት ብቻ ዝም ብለው ያልፋሉ ወይስ ምቾት ባይሰጦትም ጉዳዩን ተጋፍጠው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይሞክራሉ?
ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር እራስን ማላመድ መቻል ወደፊት ወደ አመራር ቦታ እንድንመጣ እና ለብዙ ነገሮች ውሳኔ መስጠት እንድንችል ይረዳናል።

6. ተፎካካሪ መሆን

ለስኬት ሲባል የሚደረግ ትንቅንቅ እና ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ወይም ቅናት ትልቅ ልዩነት አላቸው።
ፉክክር ሁሌም ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥረት እንድናሳይና እቅዳችንን እንድናሳካ ሊረዳን ይችላል። ሲበዛ ግን የቡድን ሥራዎችን ያስተጓጉላል።

እነዚህ ስድስቱ ባህሪያት በአንድነት በሥራ ገበታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። በተለይ ደግሞ ወደ አመራር ቦታ መምጣት ለሚፈልጉ ሰዎች።

ከላይ የተዘረዘሩት የሰዎች ባህሪያት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሥራችንን ፍሬ እና ውጤታማነታችንን ለመለካት ይረዱናል።
በመጨረሻም ተፎካካሪነት እና ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል ከሁሉም በተሻለ ተቀባይነትን ያገኙ ሲሆን፤ የተሻለ ገቢ እንደሚያስገኙም ተጠቁሟል።
3.1K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 15:29:59
2.7K viewsLighthouse-Success Coaching Center, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ