Get Mystery Box with random crypto!

አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

የቴሌግራም ቻናል አርማ jebrilsultan — አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን
የቴሌግራም ቻናል አርማ jebrilsultan — አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን
የሰርጥ አድራሻ: @jebrilsultan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.01K
የሰርጥ መግለጫ

✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 12:08:39 السلام عليكم ورحمةالله وبركاته

አስደሳች ዜና ለአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ለሉ ወንድም እና እህቶች በሙሉ


አዲስ ተከታታይ ሙሓደራ እና ኮርስ ለክርምት ተማሪሆች እና ለሌሎችም የተዘገጀ ፕሮግራም በተለያዩ ኡስታዞች

የሙሓደራው ቦታ እና ቀን

አዲስ አበባ ካራቆሬ ውሃ ልማት ብላል ኢብኑ ረባህ መድረሳ

እነሆ እሁድ በቀን 17/112014 ነው።

https://t.me/AbraribnAwal
448 views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 08:39:37 ሳትወድ ወላጆች የዳሯት ከሆነ…

የፈትዋ ቁጥር


መልስ
በሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ


በዚህ የፈታዋ ብቻ ቻናል
https://t.me/FATTAWAS


የፈትዋ ጥያቄ ለመጠየቅ
https://forms.gle/1iDs6V7JPMHREx4GA
931 views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 18:08:41 ➠#የሙመይዓዎች መስራች ዐሊየል ሐለቢ፣የሙመይዓዎችን ብልሹ የሆኑ ቃዒዳዎችን ከመፍብረኩ ( ከመመስረቱ) በፊትና ከመሰረተ በኃላ። #ከኢንግላንዳዊው ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ (ሀፊዘሁሏህ) ዌብሳይት የወሰድኩት ጽሁፍ። ክፍል ⓵ ➘ ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ ❨ሀፊዘሁሏህ) በዚህ ጽሁፍ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል፦ እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀለቢን ያገኘሁት ከ24 አመታት በፊት August (በነሐሴ ) 1993 G.c በሌስተር…
1.1K views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 18:07:19 ➠#ሙመይዓዎች መስራች ዐሊየል ሐለቢ፣የሙመይዓዎችን ብልሹ የሆኑ ቃዒዳዎችን ከመፍብረኩ ( ከመመስረቱ) በፊትና ከመሰረተ በኃላ።

#ከኢንግላንዳዊው ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ (ሀፊዘሁሏህ) ዌብሳይት የወሰድኩት ጽሁፍ።

ክፍል ⓵

ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ ❨ሀፊዘሁሏህ) በዚህ ጽሁፍ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል፦

እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀለቢን ያገኘሁት ከ24 አመታት በፊት August (በነሐሴ ) 1993 G.c በሌስተር ኮንፈረንስ እንግሊዝን ሲጎበኝ ነበር ያየሁት።

አሁንም በድጋሜ ለሁለተኛ ጊዜ August 1995 G.c ተመልሶ በበርሚንግሃም ያሉትን ሰለፊዎች ጎበኘ። የጎበኘውም ብቻውን እንበረም፣ አል-ሀለቢሳሊም አል-ሂላሊ እና ሙሐመድ ሙሳ ናስር ይገኙበታል።

በርሚንግሃም የሚገኙትን ሰለፊዮች ከጎበኙ በኃላ፤ የኔንም #ቤት ጎብኝተን ነበር። ስንቀጥል አቡ ሙንተሲር የተባለን ሰው ለመምከር ጉዞ አቀናን፣ምክንያቱም ገናና ከሆኑ ቁጥብዮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው እንደ ሰፈር አል-ሃዋሊ፣ ሰልማን አል-ዐውዳ ፣ዐሊ ተሚሚ...ካሉ የቁጥቢዮችን ርዕዮተ ዓለም አቀንቃኞቻቸው ጋር ስላለው ግንኙነት ለመምከር አብረን ወደ #ኢፕስዊች ተጓዝን።

እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ ዐሊ ሐሰን አል-ሐለቢ ከሐዲስ እና የሱና ኢማም ፣ ሙጀዲድ ከሆኑት ከሸይኽ ሙሐመድ ናሲር አድ-ዲን አል አልባኒን (ረሒመሁላህ) ይቀርባቸው ነበር፣የሸይኽ አል አልባኒ ተጽእኖ አድሮበት ነበር። ለእርሳቸው (አልባኒን) የቀረበ ለሀዲስ፣ለሱና ያላቸው ፍቅር፣ ቢድዓን በመቃወም፣ በቁጥቢዮችና እና ከተክፊሪ አስተሳሰቦች ጋር የሚያደርጉት ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጣ። የሰለፊ ወጣቶችን እንደ አሊ ሀሰንን መሰል ሰዎች የሳባቸው ከአልበኒ (ረሒመሁላህ) የተማሩት የሰለፊ መንሃጅን አጥብቆ መያዝ ነበር። እንደ ሸይኽ ረቢዕ፣ ሸይኽ ሙቅቢል፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አል-ጃሚ፣ ሸይኽ አህመድ አን-ነጅሚ፣ ከመሳሰሉት ቀደም ቀደም አይልም ነበር እና ራሱንም እንደዛ አድርጎ አልቆጠረም። በዚያን ጊዜ ወጣት ነበር (ሐለቢ) የመዲናን ዑለማዎችንም ያከብራቸው ነበር፣ከነሱም መረጃን ይጠቀማል (ይጠቅሳል) ይዘይራቸውም ነበር። በተለይም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል-መድኸሊ (ሀፊዘሁሏህ) በተደጋጋሚ ይዘይራቸው ነበር።

እ.ኤ.አ ከ1994-96 ጀምሮ በበርሚንግሃም የሚገኘው የሰለፊ ማህበረሰብ ከሌሎች እንደ ዮርዳኖሶች ይልቅ ከመዲና ሸይኾች ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንደፈጠረ ያለ ጥርጥር መናገር ይቻላል። ይህ የሆነው በብዙ ምክንያቶች ነው። በወቅቱ አቡ ሃኪም በመዲና እየተማረ ነበር እና ከመዲና ዑለማዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ነበረው።

አቡ ጦልሃ ዳውድ ቡርባንክ ከጥቂት አመታት በፊት ከመዲና ዩኒቨርሲቲ ተመልሶ ነበር፣ አማር በሺር ለመዲና ዑለማዎች ቅርብ ነበር። ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ እና ሸይኽ ዐብዱሰላም በርጂስ ከ1996 እስከ 2000 G.c ባሉት ጊዜያት ብዙ ጊዜ መከተባ አስ-ሰለፊያህ በበርሚንግሃም የሚገኘውንጎብኝተው ነበር የኩዌት ሸይኾችም ጎብኝተዋል።

በቀጣዮቹ አመታት #ሐለቢ በአል-መክታባህ አስ-ሰለፊያህ በርሚንግሃም የሚገኘውን የሰለፊ ህትመቶችን ማወደሱ የሚታወስ ነው።

ዐሊ አል-ሐለቢ ወደ መክተበቱ ሰለፊያህ የመጨረሻ ጉብኝት ያደረገው August 2000 G.c በበርሚንግሃም በሃምድ ሃውስ በኮንፈረንሳችን ላይ ተገኝቶ ነበር። ከዚያም በ2000 G.c ክረምት መገባደጃ ላይ አቡ ዒያድ፣ እኔ፣ሳሊም አል ሂላሊ እና ኡሳማህ አል ኩሲ ከእንግሊዝ ተነስተን #በዲትሮይት ዩኤስኤ ወደሚገኘው የ QSS ( Quran and sunnah society) [(የቁርዓን እና የሱና ማህበር)] ኮንፈረንስ አብረን ነበር ጉዞ ያደረግነው። እዚያም ኮርስ ሰጥተናል።

ከወንድማችን አቡ ኡወይስ ዐብዱላህ አህመድ ዐሊ (ረሂመሁላህ) እና ሌሎችም ጋር... በዚያ ኮንፈረንስ ላይ ዐሊ አል-ሀለቢ ተገኝቶ ብዙ ሰአታት ከሱ እና ከሌሎች ሸይኾች ጋር አሳልፈናል።

ትዝ ይለኛል ከሰጥናቸው ኮርሶች በአንዱ ላይ ኢኽዋን የሆነው ሙብተዲዕ #አድናን_አር ዑርን ተችተነው ነበር። አድናን አር-ዑር የሐለቢ የቅርብ ጓደኛው ነበር። አል-ሒላሊ እና ሌሎችም አድናን አር-ዑር ላይ በሰነዘርነው ትችት ቅር ተሰኙ።

ኢንሻ አላህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል...
➘➘
https://t.me/semirEnglish
1.3K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 16:11:16
1.2K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 23:11:50 በጣም ከገረሙኝና ከደነቁኝ ተፍሲሮች

=========================

አላህ በሱረቱል አንዓም አንቀፅ 112 እንዲህ ይላል:-
{ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِنِّ يُوحِي بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ زُخْرُفَ الْقَوْلِ غُرُورًا ۚ وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ مَا فَعَلُوهُ ۖ فَذَرْهُمْ وَمَا يَفْتَرُونَ }

እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል ልብስብስን ቃል ይጥላሉ፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው፡፡

ቀታዳ ሙጃሂድ እና ሃሰን ይህን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ :- " ልክ የጂን ሰይጣን እንዳለ ሁሉ የሰውም ሰይጣን አለ ። "

ማሊክ ቢን ዲናር ደሞ እንዲህ ይላሉ :-
ከጂኑ ሸይጣን ይልቅ የሰዉ ሸይጣን የከፋ ነው ይህም የሆነበት ምክንያት እኔ ከጂኑ ሸይጣን በአላህ ሲጠበቅ ( _አዑዙቢላሂ ሚን አሽ_ሸይጣን _አር_ረጂም ሲል _ ) ከኔ ይሄዳል ይሸሻል የሰዉ ሸይጣን ግን እንደዛ ቢልም ተከትሎኝ ይመጣል በግልፅም ወደ ወንጀል ይጎትተኛል ።
[البغوي: ٢/٥٦]

ዱዓ ተደርገህ ያ አላህ ከእሱ ጋር አገናኘኝ ተብሎ ዱዓ ተደርጎብህ የምትገኝ እንጂ አዑዙቢላሂ ስትባል የማትሸሽ የሰው ሸይጣን አትሁን !!

ጅብሪል ሱልጣን
ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan
1.2K views20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 20:25:24 መቼም አይረሳኝም !!
=========================

እንናታችን አዒሸት ረዲዓላሁ አንሃ የቅጥፈቱ ወሬ የተወራባት ግዜ ሁሉም ሰዎች ራቋት አዒሸት በጣም ክፍት ብሏት ነበር በዚህ ግዜ አንድ ከአንሳር የሆነች ሴት አዒሻ ጋር ገባችና አንድም ቃል ሳትተነፍስ ከአዒሸት ጋር ስቅስቅ ... ብላ አለቀሰች ቆይታም ወጣች ለአዒሻ በጭንቋ ሰዓት ከጎኗ ሆነችላት አዒሻ ስለዚህች ሴት ስታወራ :-

" መቼም አልረሳትም !! " ትላለች

ከዕብ ቢን ማሊክን አላህ ተውበቱን የተቀበለው ሰዓት በደስታ እየሮጠ ወደ መስጂድ ገባ የዚህኔ ሁሉም ከዕብን አንዱ በደስታ አንዱ በፈገግታ ቁጭ ብሎ ስያየው አንድ ጠለሃ የሚባል ሰው ብቻ ደስታው አላስችል ብሎት በደስታ እየፈነጠዘ እየሮጠ ሄዶ በደስታ ከዕብን እቅፍ አድርጎ አቀፈው ... ከዕብ ስለዚህ ሰው ስያወራ :-
" ይህቺን የጠለሃን ውለታ መቼም አልረሳትም " ይላል

ብዙ ሰዎች ጓደኛህ ባገኘ ግዜ ይቀርቡታል ባጣ ግዜ ደሞ ይርቁታል አንተ ባገኘም ግዜ ባጣም ግዜ ፣ በደስታም ግዜ በሃዘንም ግዜ ሳትሰላች ቅረበው ውደደው እቅፍህ ውስጥ አስገባው ከምትበላት ግማሿን አጉርሰው አለመጥገብ የገደለው ሰው በታሪክ ዬለም ተሰምቶም አይታወቅም አይኖርምም ስለዚህ ካልጠገብኩ አትበል ግማሿን ለራስህ ጎርሰህ ግማሿን ለሌላ ለተራበ አጉርስ የዛኔ አንተ ጀግና ነህ ። ይህን የሚያደርጉልን ሰዎች ከቶ መች ከአዕምሯችን ይጠፉና ??

ጅብሪል ሱልጣን
ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan
1.2K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:39:36 ➛አንድ ሰው በተላኩበት እስካላመነ እና በነቢይነታቸው እስካልመሠከረ ድረስ እምነቱ ትክክለኛ አይሆንም።
መልዕክተኛውን የታዘዘ ጀነት ገባ፤ ትዕዛዛቸውን የነቀፈ ደግሞ እሳት ገባ።
አሏህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦

فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡ (አን-ኒሳዕ:65)

➩ነቢዮች ሁሉ የተላኩት ለራሳቸው ህዝቦች በተለየ ሲሆን፣ ሙሐመድ ﷺ ግን በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ተልከዋል። ይህን አስመልክቶ አሏሁ ﷻ እንዲህ ይላል፦
وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا كَافَّةً لِّلنَّاسِ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
➩አህሉስ-ሱንና ወልጀማዐህ፦ የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ አሏህ ﷻ ግልፅ እና አስደናቂ በሆኑ የተለያዩ ተአምራቶች አግዟቸዋል ብለው ያምናሉ።

◉ከነዚህ ተአምራቶች መካከል ትልቁ አሏህ ﷻ በንግግር ችሎታ እና ጥበብ ታዋቂ የሆኑ ምሁራንን ያሸነፈበት ቁርአን ነው።
◉ከቁርአን በመቀጠል ታላቁ ነቢዩ ﷺ ተአምር የኢስራዕ ለሊት ያደረጉት ጉዞ በአካላቸው መሆኑን እንዲሁም ወደ ሰማይ የወጡት በዚሁ መልክ በውናቸው እንደሆነ በእርግጠኝነት ያምናሉ።ጉዟቸው በለሊት የተከናወነ ሲሆን ከመስጅደል ሐራም ተነስተው መስጅደል አቅሷ ደርሰዋል። አሏህ ﷻ እንዲህ ይላል፦

سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

"ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡" (አል-ኢስራዕ፡1)

➛ከዚያም የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ አሏህ ከሻው ሰባተኛው ሰማይ ላይ ጀነት አቅራቢያ "ሲድረቱል ሙንተሃ" በሚባል ቦታ ደርሷዋ።
አሏህ ﷻ ነቢዩን ﷺ በሚፈልገው ነገር በመናገር አስከበራቸው አላቃቸው። በለሊት እና በቀን የሚሰገዱ አምስት ወቅት ሶላቶችን ሰጣቸው። የጀነት እና የእሳት አገሮችን እንዲጎበኙ ጅብሪል የሚባለውን መላኢካ በተፈጥሮ ቅርፁ እንዲመለከቱ ተደረገ። ነቢዩ ﷺ በአይን ብሌናቸው የተመለከቱትን ሁሉ ልባቸው አልዋሸችም።ከሌሎች ነቢያቶች እና መልእክተኞች በደረጃ የሚበልጡ መሆናቸውን ለማሳወቅ ነው። ከዚያም በይተል መቅዲስ ወረዱ ነቢያቶችን ኢማም ሆነው አሰገዱ። ከዚያም ወደ መካ ከፈጅር በፊት በመመለስ (አስደናቂውን ጉዞ) አጠናቀቁ። አሏህ ﷻ እንዲህ ይላል፦

◉ وَلَقَدْ رَآَهُ نَزْلَةً أُخْرَى عِنْدَ سِدْرَةِ الْمُنْتَهَى عِنْدَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَى إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَى مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَى لَقَدْ رَأَى مِنْ آَيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَى أَفَرَأَيْتُمُ اللَّاتَ وَالْعُزَّى

ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?
በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡
በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤
እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡
ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡
ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡
ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡(አን-ነጅም ፡12-18)

#ይ_ቀ_ጥ_ላ_ል.....

إِنْ شَاءَ ٱللّٰه

أم عبدالله السلفية

https://t.me/MenhajuAlAnbiya
https://t.me/MenhajuAlAnbiya
1.1K views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:56:44 የለቅሶ ቤት ድግስ


በሸሪአችን የተደነገገውና ሱናው ለሟች ቤተሰቦች ምግብ ሰርቶ ማቅረብና ማፅናናት እንጂ እነሱ ደግሰው ማብላትን አይደለም። ምክንያቱም የሟች ቤተሰቦች ምግብ ሰርተው እንዳይበሉ የሚያደርግ ሀዘን ስላጋጠማቸው ነው።

ለሀዘን ተብሎ የሟች ቤተሰቦች ማረድና መደገስ ይህ በሸሪአችን የተወገዘ ተግባር ነው። አዲስ መጤ ቢድአም ጭምር ነው። ይህንን ከሚደግፋ መካከል ከቀደምቶች ሀነፍያዎችና ሻፍእያዎች ከዘመናችን ኡለማዎች ደግሞ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ኡሰይሚንና ሸህ አልባንይ ተጠቃሽ ናቸው።

ነገር ግን ጎረቤት ለሟች ቤተሰቦች ሰርተው ባመጡት ምግብ ላይ ደርሰው አብረው ቢመገቡ ችግር የለውም።

የሟች ቤተሰቦች ለሀዘኑ ብለው ሳይሆን ለእንግድነት በተለምዶ ሌላ ጊዜ የሚሰሩትን ምግብ ሰርተው በዛ ላይ ከሩቅ የመጣ እንግዳቸውን ቢቀበሉ ችግር የለውም።

الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله


https://t.me/AbraribnAwal
https://t.me/AbraribnAwal
https://t.me/AbraribnAwal
959 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 14:04:54
አሰላሙ ዓለይኩም ወሯህመቱሏሁ ወበረካትሁ

ይድረስ
ለቻናልና ግሩፕ ባለቤቶች
ለሱና እህት ወንድሞቻችን



እንደምታውቁት የሸዋሮቢት ሰለፍዮች በ4 ሚሊየን ሸዋሮቢት መሀል ከተማ ላይ የመስጅድ ቦታ መግዛታቸውን ተከትሎ ይህንኑ ብር ለማሟላት በተደረገው ጥረት 650,000 ተበድረን የመስጅዱን ክፍያ ማጠናቀቅ ችለናል።


ይሁን እንጂ በብድር ያመጣነው ብር 650,000(ስድስት መቶ ሀምሳ ሺ) ላበደሩን ጀግኖቻችን በሰአቱ መመለስ ስላለብን የተለያዩ የንያ ፕሮግራሞችን በማድረግ ወደ 450,000 ለማስነየት ተችሏል

አልሀምዱሊላህ

ስለሆነም አሁን የቀረችን 200,000(ሁለት መቶ ሺ) ስትሆን ይህንኑ የገንዘብ መጠን በዛሬው እለት ከምሽቱ 3፡00 በቴሌግራምና ዋትስአፕ በሚደረገው የንያ ፕሮግራማችን ላይ ማጠናቀቅ እንዲቻል ከታች ባሉት ሊንኮች በመቀላቀል የምትችሉትን ያክል አሻራችሁን በማኖር የዛሬው ፕሮግራማችን የመጨረሻ እንዲሆንልን እንድታግዙን እንጠይቃለን።


ሼር በማድረግ አድ በማድረግና በማነሳሳት ከእዳ ነፃ የሆነችን መስጅድ ለሸዋሮቢት ሰለፍዮች እናስረክባቸው።


የንያ ሊንኮቻችን

ዋትስ አፕ ግሩፓችን

https://chat.whatsapp.com/DEImR2g64OT2yBTQNtUsFy

ቴሌግራም ግሩፓችን

https://t.me/Yeshewarobitselefiyochgroup

የንያ ቦታችን በውስጥ ለመነየት

@Abusarrah65bot


ዛሬ ምሽት 3:00 እንገናኝ



ሼርርርርርር
1.0K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ