Get Mystery Box with random crypto!

የለቅሶ ቤት ድግስ በሸሪአችን የተደነገገውና ሱናው ለሟች ቤተሰቦች ምግብ ሰርቶ ማ | አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

የለቅሶ ቤት ድግስ


በሸሪአችን የተደነገገውና ሱናው ለሟች ቤተሰቦች ምግብ ሰርቶ ማቅረብና ማፅናናት እንጂ እነሱ ደግሰው ማብላትን አይደለም። ምክንያቱም የሟች ቤተሰቦች ምግብ ሰርተው እንዳይበሉ የሚያደርግ ሀዘን ስላጋጠማቸው ነው።

ለሀዘን ተብሎ የሟች ቤተሰቦች ማረድና መደገስ ይህ በሸሪአችን የተወገዘ ተግባር ነው። አዲስ መጤ ቢድአም ጭምር ነው። ይህንን ከሚደግፋ መካከል ከቀደምቶች ሀነፍያዎችና ሻፍእያዎች ከዘመናችን ኡለማዎች ደግሞ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ኡሰይሚንና ሸህ አልባንይ ተጠቃሽ ናቸው።

ነገር ግን ጎረቤት ለሟች ቤተሰቦች ሰርተው ባመጡት ምግብ ላይ ደርሰው አብረው ቢመገቡ ችግር የለውም።

የሟች ቤተሰቦች ለሀዘኑ ብለው ሳይሆን ለእንግድነት በተለምዶ ሌላ ጊዜ የሚሰሩትን ምግብ ሰርተው በዛ ላይ ከሩቅ የመጣ እንግዳቸውን ቢቀበሉ ችግር የለውም።

الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله


https://t.me/AbraribnAwal
https://t.me/AbraribnAwal
https://t.me/AbraribnAwal