Get Mystery Box with random crypto!

➛አንድ ሰው በተላኩበት እስካላመነ እና በነቢይነታቸው እስካልመሠከረ ድረስ እምነቱ ትክክለኛ አይሆን | አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

➛አንድ ሰው በተላኩበት እስካላመነ እና በነቢይነታቸው እስካልመሠከረ ድረስ እምነቱ ትክክለኛ አይሆንም።
መልዕክተኛውን የታዘዘ ጀነት ገባ፤ ትዕዛዛቸውን የነቀፈ ደግሞ እሳት ገባ።
አሏህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል፦

فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡ (አን-ኒሳዕ:65)

➩ነቢዮች ሁሉ የተላኩት ለራሳቸው ህዝቦች በተለየ ሲሆን፣ ሙሐመድ ﷺ ግን በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ተልከዋል። ይህን አስመልክቶ አሏሁ ﷻ እንዲህ ይላል፦
وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا كَافَّةً لِّلنَّاسِ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
➩አህሉስ-ሱንና ወልጀማዐህ፦ የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ አሏህ ﷻ ግልፅ እና አስደናቂ በሆኑ የተለያዩ ተአምራቶች አግዟቸዋል ብለው ያምናሉ።

◉ከነዚህ ተአምራቶች መካከል ትልቁ አሏህ ﷻ በንግግር ችሎታ እና ጥበብ ታዋቂ የሆኑ ምሁራንን ያሸነፈበት ቁርአን ነው።
◉ከቁርአን በመቀጠል ታላቁ ነቢዩ ﷺ ተአምር የኢስራዕ ለሊት ያደረጉት ጉዞ በአካላቸው መሆኑን እንዲሁም ወደ ሰማይ የወጡት በዚሁ መልክ በውናቸው እንደሆነ በእርግጠኝነት ያምናሉ።ጉዟቸው በለሊት የተከናወነ ሲሆን ከመስጅደል ሐራም ተነስተው መስጅደል አቅሷ ደርሰዋል። አሏህ ﷻ እንዲህ ይላል፦

سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

"ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡" (አል-ኢስራዕ፡1)

➛ከዚያም የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ አሏህ ከሻው ሰባተኛው ሰማይ ላይ ጀነት አቅራቢያ "ሲድረቱል ሙንተሃ" በሚባል ቦታ ደርሷዋ።
አሏህ ﷻ ነቢዩን ﷺ በሚፈልገው ነገር በመናገር አስከበራቸው አላቃቸው። በለሊት እና በቀን የሚሰገዱ አምስት ወቅት ሶላቶችን ሰጣቸው። የጀነት እና የእሳት አገሮችን እንዲጎበኙ ጅብሪል የሚባለውን መላኢካ በተፈጥሮ ቅርፁ እንዲመለከቱ ተደረገ። ነቢዩ ﷺ በአይን ብሌናቸው የተመለከቱትን ሁሉ ልባቸው አልዋሸችም።ከሌሎች ነቢያቶች እና መልእክተኞች በደረጃ የሚበልጡ መሆናቸውን ለማሳወቅ ነው። ከዚያም በይተል መቅዲስ ወረዱ ነቢያቶችን ኢማም ሆነው አሰገዱ። ከዚያም ወደ መካ ከፈጅር በፊት በመመለስ (አስደናቂውን ጉዞ) አጠናቀቁ። አሏህ ﷻ እንዲህ ይላል፦

◉ وَلَقَدْ رَآَهُ نَزْلَةً أُخْرَى عِنْدَ سِدْرَةِ الْمُنْتَهَى عِنْدَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَى إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَى مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَى لَقَدْ رَأَى مِنْ آَيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَى أَفَرَأَيْتُمُ اللَّاتَ وَالْعُزَّى

ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?
በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡
በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤
እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡
ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡
ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡
ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡(አን-ነጅም ፡12-18)

#ይ_ቀ_ጥ_ላ_ል.....

إِنْ شَاءَ ٱللّٰه

أم عبدالله السلفية

https://t.me/MenhajuAlAnbiya
https://t.me/MenhajuAlAnbiya