Get Mystery Box with random crypto!

መቼም አይረሳኝም !! ========================= እንናታችን አዒሸት ረዲዓላሁ | አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

መቼም አይረሳኝም !!
=========================

እንናታችን አዒሸት ረዲዓላሁ አንሃ የቅጥፈቱ ወሬ የተወራባት ግዜ ሁሉም ሰዎች ራቋት አዒሸት በጣም ክፍት ብሏት ነበር በዚህ ግዜ አንድ ከአንሳር የሆነች ሴት አዒሻ ጋር ገባችና አንድም ቃል ሳትተነፍስ ከአዒሸት ጋር ስቅስቅ ... ብላ አለቀሰች ቆይታም ወጣች ለአዒሻ በጭንቋ ሰዓት ከጎኗ ሆነችላት አዒሻ ስለዚህች ሴት ስታወራ :-

" መቼም አልረሳትም !! " ትላለች

ከዕብ ቢን ማሊክን አላህ ተውበቱን የተቀበለው ሰዓት በደስታ እየሮጠ ወደ መስጂድ ገባ የዚህኔ ሁሉም ከዕብን አንዱ በደስታ አንዱ በፈገግታ ቁጭ ብሎ ስያየው አንድ ጠለሃ የሚባል ሰው ብቻ ደስታው አላስችል ብሎት በደስታ እየፈነጠዘ እየሮጠ ሄዶ በደስታ ከዕብን እቅፍ አድርጎ አቀፈው ... ከዕብ ስለዚህ ሰው ስያወራ :-
" ይህቺን የጠለሃን ውለታ መቼም አልረሳትም " ይላል

ብዙ ሰዎች ጓደኛህ ባገኘ ግዜ ይቀርቡታል ባጣ ግዜ ደሞ ይርቁታል አንተ ባገኘም ግዜ ባጣም ግዜ ፣ በደስታም ግዜ በሃዘንም ግዜ ሳትሰላች ቅረበው ውደደው እቅፍህ ውስጥ አስገባው ከምትበላት ግማሿን አጉርሰው አለመጥገብ የገደለው ሰው በታሪክ ዬለም ተሰምቶም አይታወቅም አይኖርምም ስለዚህ ካልጠገብኩ አትበል ግማሿን ለራስህ ጎርሰህ ግማሿን ለሌላ ለተራበ አጉርስ የዛኔ አንተ ጀግና ነህ ። ይህን የሚያደርጉልን ሰዎች ከቶ መች ከአዕምሯችን ይጠፉና ??

ጅብሪል ሱልጣን
ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan