Get Mystery Box with random crypto!

በጣም ከገረሙኝና ከደነቁኝ ተፍሲሮች ========================= አላህ በሱረ | አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

በጣም ከገረሙኝና ከደነቁኝ ተፍሲሮች

=========================

አላህ በሱረቱል አንዓም አንቀፅ 112 እንዲህ ይላል:-
{ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِنِّ يُوحِي بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ زُخْرُفَ الْقَوْلِ غُرُورًا ۚ وَلَوْ شَاءَ رَبُّكَ مَا فَعَلُوهُ ۖ فَذَرْهُمْ وَمَا يَفْتَرُونَ }

እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል ልብስብስን ቃል ይጥላሉ፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው፡፡

ቀታዳ ሙጃሂድ እና ሃሰን ይህን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ :- " ልክ የጂን ሰይጣን እንዳለ ሁሉ የሰውም ሰይጣን አለ ። "

ማሊክ ቢን ዲናር ደሞ እንዲህ ይላሉ :-
ከጂኑ ሸይጣን ይልቅ የሰዉ ሸይጣን የከፋ ነው ይህም የሆነበት ምክንያት እኔ ከጂኑ ሸይጣን በአላህ ሲጠበቅ ( _አዑዙቢላሂ ሚን አሽ_ሸይጣን _አር_ረጂም ሲል _ ) ከኔ ይሄዳል ይሸሻል የሰዉ ሸይጣን ግን እንደዛ ቢልም ተከትሎኝ ይመጣል በግልፅም ወደ ወንጀል ይጎትተኛል ።
[البغوي: ٢/٥٦]

ዱዓ ተደርገህ ያ አላህ ከእሱ ጋር አገናኘኝ ተብሎ ዱዓ ተደርጎብህ የምትገኝ እንጂ አዑዙቢላሂ ስትባል የማትሸሽ የሰው ሸይጣን አትሁን !!

ጅብሪል ሱልጣን
ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
https://t.me/Jebrilsultan