Get Mystery Box with random crypto!

➠#የሙመይዓዎች መስራች ዐሊየል ሐለቢ፣የሙመይዓዎችን ብልሹ የሆኑ ቃዒዳዎችን ከመፍብረኩ ( ከመመስረ | አቡ ሙስዐብ & ሙሀመድ ሰልማን

➠#ሙመይዓዎች መስራች ዐሊየል ሐለቢ፣የሙመይዓዎችን ብልሹ የሆኑ ቃዒዳዎችን ከመፍብረኩ ( ከመመስረቱ) በፊትና ከመሰረተ በኃላ።

#ከኢንግላንዳዊው ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ (ሀፊዘሁሏህ) ዌብሳይት የወሰድኩት ጽሁፍ።

ክፍል ⓵

ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ ❨ሀፊዘሁሏህ) በዚህ ጽሁፍ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል፦

እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀለቢን ያገኘሁት ከ24 አመታት በፊት August (በነሐሴ ) 1993 G.c በሌስተር ኮንፈረንስ እንግሊዝን ሲጎበኝ ነበር ያየሁት።

አሁንም በድጋሜ ለሁለተኛ ጊዜ August 1995 G.c ተመልሶ በበርሚንግሃም ያሉትን ሰለፊዎች ጎበኘ። የጎበኘውም ብቻውን እንበረም፣ አል-ሀለቢሳሊም አል-ሂላሊ እና ሙሐመድ ሙሳ ናስር ይገኙበታል።

በርሚንግሃም የሚገኙትን ሰለፊዮች ከጎበኙ በኃላ፤ የኔንም #ቤት ጎብኝተን ነበር። ስንቀጥል አቡ ሙንተሲር የተባለን ሰው ለመምከር ጉዞ አቀናን፣ምክንያቱም ገናና ከሆኑ ቁጥብዮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው እንደ ሰፈር አል-ሃዋሊ፣ ሰልማን አል-ዐውዳ ፣ዐሊ ተሚሚ...ካሉ የቁጥቢዮችን ርዕዮተ ዓለም አቀንቃኞቻቸው ጋር ስላለው ግንኙነት ለመምከር አብረን ወደ #ኢፕስዊች ተጓዝን።

እ.ኤ.አ በ1990ዎቹ ዐሊ ሐሰን አል-ሐለቢ ከሐዲስ እና የሱና ኢማም ፣ ሙጀዲድ ከሆኑት ከሸይኽ ሙሐመድ ናሲር አድ-ዲን አል አልባኒን (ረሒመሁላህ) ይቀርባቸው ነበር፣የሸይኽ አል አልባኒ ተጽእኖ አድሮበት ነበር። ለእርሳቸው (አልባኒን) የቀረበ ለሀዲስ፣ለሱና ያላቸው ፍቅር፣ ቢድዓን በመቃወም፣ በቁጥቢዮችና እና ከተክፊሪ አስተሳሰቦች ጋር የሚያደርጉት ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ መጣ። የሰለፊ ወጣቶችን እንደ አሊ ሀሰንን መሰል ሰዎች የሳባቸው ከአልበኒ (ረሒመሁላህ) የተማሩት የሰለፊ መንሃጅን አጥብቆ መያዝ ነበር። እንደ ሸይኽ ረቢዕ፣ ሸይኽ ሙቅቢል፣ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አል-ጃሚ፣ ሸይኽ አህመድ አን-ነጅሚ፣ ከመሳሰሉት ቀደም ቀደም አይልም ነበር እና ራሱንም እንደዛ አድርጎ አልቆጠረም። በዚያን ጊዜ ወጣት ነበር (ሐለቢ) የመዲናን ዑለማዎችንም ያከብራቸው ነበር፣ከነሱም መረጃን ይጠቀማል (ይጠቅሳል) ይዘይራቸውም ነበር። በተለይም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል-መድኸሊ (ሀፊዘሁሏህ) በተደጋጋሚ ይዘይራቸው ነበር።

እ.ኤ.አ ከ1994-96 ጀምሮ በበርሚንግሃም የሚገኘው የሰለፊ ማህበረሰብ ከሌሎች እንደ ዮርዳኖሶች ይልቅ ከመዲና ሸይኾች ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንደፈጠረ ያለ ጥርጥር መናገር ይቻላል። ይህ የሆነው በብዙ ምክንያቶች ነው። በወቅቱ አቡ ሃኪም በመዲና እየተማረ ነበር እና ከመዲና ዑለማዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት ነበረው።

አቡ ጦልሃ ዳውድ ቡርባንክ ከጥቂት አመታት በፊት ከመዲና ዩኒቨርሲቲ ተመልሶ ነበር፣ አማር በሺር ለመዲና ዑለማዎች ቅርብ ነበር። ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ እና ሸይኽ ዐብዱሰላም በርጂስ ከ1996 እስከ 2000 G.c ባሉት ጊዜያት ብዙ ጊዜ መከተባ አስ-ሰለፊያህ በበርሚንግሃም የሚገኘውንጎብኝተው ነበር የኩዌት ሸይኾችም ጎብኝተዋል።

በቀጣዮቹ አመታት #ሐለቢ በአል-መክታባህ አስ-ሰለፊያህ በርሚንግሃም የሚገኘውን የሰለፊ ህትመቶችን ማወደሱ የሚታወስ ነው።

ዐሊ አል-ሐለቢ ወደ መክተበቱ ሰለፊያህ የመጨረሻ ጉብኝት ያደረገው August 2000 G.c በበርሚንግሃም በሃምድ ሃውስ በኮንፈረንሳችን ላይ ተገኝቶ ነበር። ከዚያም በ2000 G.c ክረምት መገባደጃ ላይ አቡ ዒያድ፣ እኔ፣ሳሊም አል ሂላሊ እና ኡሳማህ አል ኩሲ ከእንግሊዝ ተነስተን #በዲትሮይት ዩኤስኤ ወደሚገኘው የ QSS ( Quran and sunnah society) [(የቁርዓን እና የሱና ማህበር)] ኮንፈረንስ አብረን ነበር ጉዞ ያደረግነው። እዚያም ኮርስ ሰጥተናል።

ከወንድማችን አቡ ኡወይስ ዐብዱላህ አህመድ ዐሊ (ረሂመሁላህ) እና ሌሎችም ጋር... በዚያ ኮንፈረንስ ላይ ዐሊ አል-ሀለቢ ተገኝቶ ብዙ ሰአታት ከሱ እና ከሌሎች ሸይኾች ጋር አሳልፈናል።

ትዝ ይለኛል ከሰጥናቸው ኮርሶች በአንዱ ላይ ኢኽዋን የሆነው ሙብተዲዕ #አድናን_አር ዑርን ተችተነው ነበር። አድናን አር-ዑር የሐለቢ የቅርብ ጓደኛው ነበር። አል-ሒላሊ እና ሌሎችም አድናን አር-ዑር ላይ በሰነዘርነው ትችት ቅር ተሰኙ።

ኢንሻ አላህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል...
➘➘
https://t.me/semirEnglish