Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.00K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2022-08-27 21:19:53 የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

  "ከአቡበክር በስተቀር ማንኛውንም ሰው ወደ እስልምና ስጋብዘው ያላመነታና ያላንገራገረ የለም።..." ረሱል ﷺ
   
                    ክፍል አምስት

   አቡበክርም (ረ.ዐ) “እሺ ስንት ልክፈልህና ነፃ ትለቀዋለህ?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ “በሰባት ወቄት ወርቅ እሸጥልሃለሁ” ይላል። አቡበክርም (ረ.ዐ) “እሺ እከፍላለሁ” በማለት ይስማማሉ።
ከዚህም ኡመያ ሳቅ ይልና እንዲህ ይላቸዋል፡፡ “ታውቃለህ አቡበክር
ስአራት ወቄት ካልሆነ አልወስድም ብትለኝ ኖሮ እንኳ እሽጥለህ ነበር።” አቡበክርም (ረ.ዐ) መልሰው “ወላሂ መቶ ወቄት ብትጠይቀኝ እንኳ ከፍዬህ እወስደው ነበር፡፡” ይላሉ፡፡ ከዚያ ክፍያውን ፈጸሙና ቢላልን በነፃ ለቀቁት። ከቢላል በኋላም ሕፃናትንና ሴቶችን በገንዘባቸው ነፃ አውጥተዋል።

      አባታቸው ከደካማዎች ይልቅ ይመሰገኑ ዘንድ ጠንከር ያሉትን
ነፃ ቢያስወጡት እንደሚሻል ደጋግመው ቢነግሯቸውም አቡበክር (ረ.ዐ) ግን "ይህን የማደርገው የአላህን (ሱ.ወ) ውዴታ ለማግኘት እንጂ ለሌላ ለምንም አይደለም፡፡” ብለው ይመልሱላቸው ነበር፡፡

   መልካም ድርጊታቸውን ጭቃ ሊቀቡ የተነሱ የመካ ሙሽሪኮች
የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎችን በአቡበክር (ረ.ዐ) ላይ ይነዙ ጀመር፡፡ “ቢላልን ነፃ እንዲወጣ ያደረገው እርሱ እንደሚለው የአላህን ውዴታ ለማግኘት ሳይሆን ከዚህ በፊት ቢላል የዋለለትን ዉለታ ለመመለስ ብሎ ነዉ።" እያሉ ሥራቸውን በማንኳሰስ አንጓጠጡ፡፡ በዚህ ጊዜ አላህ (ሱ.ወ) የሚከተለውን የቁርኣን አናቅጽ አወረደ

{ وَمَا لِأَحَدٍ عِندَهُۥ مِن نِّعۡمَةࣲ تُجۡزَىٰۤ (19) إِلَّا ٱبۡتِغَاۤءَ وَجۡهِ رَبِّهِ ٱلۡأَعۡلَىٰ (20) وَلَسَوۡفَ یَرۡضَىٰ (21) }

“ለአንድ ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡ ግን የታላቅ
ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህን ሠራ)፡፡ ወደፊትም በእርግጥ
ይደሰታል፡፡” (አል-ለይል፡ 19-21)

    ሱረቱል ለይል በውስጧ ያካተተችው መልእክት በአቡበክር (ረ.ዐ) ላይ የተነዛው ሀሰት መሆኑን መግለጫ ነው፡፡ ሃያ አንድ አናቅፅን አካታለች፡፡

              ከሶሐቦች ሁሉ ጀግና
    አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ምንም እንኳ ጉልበታቸው ደካማና
ሰውነታቸው ለስለስ ያለ ቢሆንም በሐቅ ጉዳይ ግን መንፈሳቸው ጠንካራ ነበር። በአላህ(ሱ.ወ) ጉዳይ ማንንም አይፈሩም፡፡

   በአንድ ወቅት ስይድ ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ "ከሰዎች ሁሉ ጀግና
ማንነው? እርሶ ነዎት አሚረል ሙእሚኒን?” ተብለው ሲጠይቁ
የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ" የለም! ከሰው ሁሉ ጀግናው አቡበክር አስ-ሲዲቅ ናቸው። በአንድ ወቅት የቁረይሽ ከሃዲዎች ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ከበው ሲያንገላቷቸው ተመለከትኩ፡፡ እኛ ራቅ ብለን ሁኔታውን እንመለከት ነበር፡፡ ለብቻቸው ሆነው ከሃዲዎቹን ገፈታተሯቸው፡፡ ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ዙሪያ ገለል አደረጉዋቸው፡፡ “አላህ ጌታዬ ነው የሚልን ሰው ልትገድሉ ነው እንዴ?” በማለት ተናገሯቸው፡፡ ከሐዲዎቹም ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ተወት አደረጉና አቡበክርን ያዟቸው፡፡ ዑቅበት ቢን አቢ ሙዐጥ የሚባል ከሐዲ መጣና የአቡበክርን (ረ.ዐ) ፊት ይመታ ጀመር፡፡ ፊታቸው እስኪያባብጥ ድረስ በጫማው ደበደባቸው፡፡ አፍንጫቸው
እስኪቀላ ድረስ ፊታቸው አበጠ፡፡ ከፊታቸው ላይም ደም ይፈስ ጀመር፡፡ አቡበክር ሲዲቅ ራሳቸውን ሳቱ፡፡

     ትንሽ ቆይቶም የአቡበክር (ረ.ዐ) ጎሳዎች የሆኑ በኒ ተሚሞች
መጡና ወደ ቤታቸው ይዘዋቸው ሄዱ፡፡ ከመጎዳታቸው ብዛት ከሞት እንደማይተርፉ እርግጠኛ ነበሩ፡፡ ለእናታቸውም 'በሕይወት ከቆየ መግቢው፣ አጠጭውም' ብለዋቸው ሄዱ፡፡ ከዚያም ወደ ዑቅበት ተመልሰው ሄዱና አቡበክር (ረ.ዐ) ከሞት ሊበቀሉት እንደሚችሉ ዝተው ተመለሱ፡፡

    አቡበክር (ረ.ዐ) ከጉዳታቸው ትንሽ መለስ በማለት ዓይናቸውን
እንደከፈቱ ወዲያው የጠየቁት ጥያቄ «ረሱል እንዴት ናቸው?” የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ያልሰለመችው እናታቸው አጠገባቸው ነበረችና አሁንም ታስታውሰዋለህ እንዴ! አለቻቸው... እርሳቸውም "ወላሂ ያሉበትን ሁኔታ አውቄ ነፍሴ እስክትረጋጋ ድረስ እህልም ሆነ ውሃ አልቀምስም” ይላሉ፡፡

    በመቀጠልም "ወደ ኡሙ ጀሚል ፋጢማ ቢንት አል-ኸጣብ
(የሰይድ ዑመር እህት) ዘንድ ሂጅና ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ያሉበትን ሁኔታ
ጠይቂያት፡፡” አሏቸው፡፡ የአቡበክር (ረ.ዐ) እናት ወደ ተባሉበት ቦታ
ይሄዳሉ፡፡ ያኔ ቢንት አል-ኸጣብ መስለሟን ደብቃ ትኖር ነበር፡፡
የአቡበክር (ረ.ዐ) እናት ስለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሁኔታ ይጠይቋታል።
እርሷም እንዲህ ትላለች "ወላሂ! ልጅሽንም ሆነ መሐመድን አላውቅም፡፡ ነገር ግን ደስ ካለሽ ልጅሽን ለመጠየቅ አብሬሽ ልመጣ እችላለሁ፡፡”

     ከዚያም ተከታትለው ወደ አቡበክር (ረ.ዐ) ዘንድ ይሄዳሉ፡፡
አቡበክርም "ፋጢማ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዴት ናቸው?” ሲሉ
ይጠይቋታል፡፡ እርሷም "እኔ ሙሐመድ ማን እንደሆነ አላውቅም፡፡”
ስትል ትመልሳለች፡፡ አቡበክርም ነገሩ ገብቷቸው "አትፍሪ እርሷ እናቴ ነች።” ይሏታል፡፡ ከዚያም “ደህና ናቸው ምንም አልሆኑ፡፡” ትላለች አቡበክርም "ወላሂ! በዓይኔ እስካላየኋቸው ድረስ እህልም ሆነ ውሃ አልቀምስም” ይላሉ፡፡ እናትየውም "እግርህ እስኪሻልህ ድረስ ትንሽ ጠብቅ” ይሏቸዋል፡፡

    እርሳቸውም እግራቸው መራመድ እያቃተውም ቢሆን ብድግ
ብለው በመነሳት ሁለቱም ሴቶች ደግፈዋቸው የአል-አርቀም ቢን አቢ አል-አርቀም ቤት ይደርሳሉ፡፡ በር ሲያንኳኩ ይከፍትላቸዋል፡፡ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) አቡበክርን ሲያዩዋቸው በጣም ያዝኑላችዋል። እቅፍ ያደርጓቸዋል፡፡ አቡበክር የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ማዘን ሲመለከቱ «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ወላሂ ከፊቴ በስተቀር ደህና ነኝ ምንም አልሆንኩም» ይላሉ። ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) በጣም አዝነው ዱዓ ያደርጉላቸዋል፡፡

    አቡበክርም እንዲህ ይሏቸዋል፡፡ "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ!
እናቴን አላህ ሙስሊም እንዲያደርጋት ዱዓ አድርጉላት፡፡” ነብዩም
(ሰ.ዐ.ወ) "አላህ ሆይ! የአቡበክርን እናት ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ምራት” ብለው ዱዓ ያደረጋሉ። የአቡበክር እናትም እዚያው እንደቆሙ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ናቸው፡፡” በማለት የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ፡፡

       አስ-ሲዲቅ ስለ እስልምና የነበራቸው ድንቅ አቋሞች

   ሰይድ አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) በእስልምና ዙሪያ የነበራቸውን
አቋሞች ስናይ ለዲን የነበራቸውን ፍቅር ከፍተኛነት መረዳት እንችላለን፡፡ አስ-ሲዲቅ ሁሉ ነገራቸውን ለዲን የበላይነት ሲሉ
ገብረዋል። ነፍሳቸውን፣ ገንዘባቸውን፣ ቤተሰባቸውን ደማቸውን ይህን ሃይማኖት ለማገልገል ሲሉ ሰጥተዋል፡፡ ለእስልምና የበላይነት ሲሉ ሁለመናቸውን ከፍለዋል፡፡

   ስለ አስ-ሲዲቅ አቋሞች ስንነጋገር ዋነኛው ዓላማችን ሁሉም
ሙእሚን በዓርአያነት እንዲከተላቸው ነው፡፡ አቡበክርን (ረ.ዐ) ተምሳሌት አድርገን ከእስልምና ረገድ ያለብንን ኃላፊነቶች ሁሉ በአግባቡ እንድንወጣ ያግዘናል።

            ዕለተ-አል ኢስራእ ወል ሚዕራጅ

   ምንም ዓይነት ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎት ባልነበረበትና
በማይታወቅበት ዘመን አንድ ሰው አንድ ሙሉ ሌሊት ባልሞላ ጊዜ
ዉስጥ ከመካ ተነስቶ ቁድስ ደርሶ ተመለሰ ተብሎ ቢነገር የሚታመን ነገር አልነበረም ::
1.8K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:42:37 ጥፋት ያለፈ ነገር ነዉ ሀላፊነት ደግሞ በተገኘዉ አጋጣሚ ነዉ ...ጥፋት የሚመጣዉ አስቀድመን
ባደረግናቸዉ ምርጫዎች ነዉ...ሀላፊነት የሚመጣዉ ደግሞ አሁን በየቀኑ በየሰከንዱ ከምናደርጋቸዉ ምርጫዎች ነዉ፡፡ አሁን እኔም የአባቴና የልጆቹ ሀላፊነት ተጋርጦብኛል
ስራዉን ሲያስብ ይቅርታ የማይደረግለት ስህተት ነዉና አዉፍ በማለቴ ተገረመ

እኔ አባቢን አዉፍ በማለቴ ረፍት ሲሰማኝ አባቢ ግን በሀዘን፤በቁጭት፤በፀፀት...እኔ ማን ነኝ ጨካኝ ፤አረመኔ አባት ወይስ.... "እያለ ማልቀስ ጀመረ ከልቡ ተፀፀተ ለካ ሰዉን በቀላሉ መበቀል ይቻላል የኔ ይቅርታ ማድረግ ለአባቢ ረፍት ነሳዉ ስራዉን ሲያስበዉ መረረዉ ህሊናዉ ወቀሰዉ...

        ኋለኞች ፊት ፊተኞች ኋላ
        መሆን አይቀርም የኋላ የኋላ
        በሰፈርከው ቁና ትሰፈርበታለህ
        በመተርከው ሜትር ትመተርበታለህ
        ባስለቀሰው ስራህ ታለቅስበታለህ
         ባነሳሀው ዱላ ትመታበታለህ
         በወንጀልህ ልክ ትቀጣበታለህ
         ያጠፈሀው ጥፍት ትጠፋበታለህ
         ከፊት የነበርከው ከሆላ ትሆናለህ
        ከክብርህ ማማ ላይ ዝቅ ትላለህ
        ለምን ካለክኝማ ዱንያ ነዉ ልበልህ
        ከአንድ አላህ በቀር ነገን መች ታቀዋለህ?
        ነቅተህ መጠበቅ ነዉ ለሞት ተዘጋጅተህ
        ጭማሪ ደቂቃ የለም በሂወትህ!!!!



....ቤታችን አብሮኝ እንዲሄድ ብዙ ለመንኩት አሻፈረኝ አለ እሺ ልጆቹን ይዘህ ወዴት ነዉ የምትሄድ?? ስለዉ
....አባቢም እንዲህ አለኝ.....

ክፍል ➊➐

ይቀጥላል.......


Join
https://t.me/Islam_and_Science
1.9K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:42:20 #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊➏
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ




ወደ ውጭ ወጥቼ ወደ ምድር አንገቴን አስግጌ ልጁን ተመለከትኩት ከፊት ለፊቱ ወዳየው ሰው ሩጫ ቀጠለ ሩጫውን ተከትየ ሰመለከት አይኔን ማመን አቃተኝ .....

ከነመፈጠራችን የረሳንን አባቢን አየሁት ልጁን አቅፎ ሲሰመው ጉሮሮየን ሳግ አፈነው ቃል ማውጣት አልቻልኩም እንባ ከአይኔ ከመፍሰስ ውጭ መናገር አቃተኝ፡፡ ስጠላውና ስኮንነው የኖርኩት አባቴ ዛሬ በሀዘን ተንሰቅስቄ እንዳለቅሰ አረገኝ

ያ የሚያምረው ግርማ ሞገሱ ድምጥማጡ ጠፍቷል፡፡ስጋው አልቆ አጥንቱ ቀርቷል ሁለት ትላልቅ ጅማቶች ግንባሩ ላይ በትልቁ ተጋድመው ከሩቅ ያስታውቃል ጥርሱ አርንጓዴ አይሉት ቢጫ የነጭነቱ መልክ ጠፍቶ ወደ ጥቁነት ተቃርቧል ግንባሩ ላይ ያሉ ጅማቶች እጆቹንም ወረውታል ...ያረጀ ጫማ ኮሌታው
...ግንባሩ ላይ ያሉ ጁማቶች እጆቹንም ወረዉታል ያረጀ ጫማ ፤ኮሌታዉ የተቀደደ ሸሚዝ፤ የተቀደደ ሱሪ ...ለብሷል ደነገጥኩ ያ! ባለግርማ ሞገሱ አባቴ አልመስለኝ አለኝ በጣም አፈጠጥኩበት ከሚስቱ ጋር ከፍ ባለ ድምፅ እየጮሁ ይጨቃጨቃሉ ፡፡ ትንሽ ራቅ ስላልኩ በምን ተጣልተዉ እንደሚያጨቃጭቃቸዉ ማወቅ አልቻልኩም ብቻ ለደቂቃዎች አይኔ ከነሱ አልተነቀለም ጭቅጭቃቸዉ የሚያልቅ አይደለም

እኔም መጨረሻቸዉን ለማየት ጓጉቼ ቁሜ ቀረሁ ከመሀል ልጃቸዉ ፈይሰል ከሩቅ ሲያየኝ እየሮጠ መጣና በሀዘን አይኖቹ እያየኝ ልብሴን እየጎተተ በትናንሽ ጣቶቹ ወደእናትና አባቱ እያመለከተ እባክሽ ገላግያቸዉ የሚል ይመስላል

እኔም በጉልበቶቼ በርከክ ብየ የፈይሰልን ፀጉር እያሻሸሁ ፈይሰል ምን ሁነህ ነዉ እየሮጥክ የመጣሀዉ?? ብየ ጠየቁት የፈይሰል መልስ እንዳሰብኩት ነበር
....."እማየና አባየ ተጣሉ" አለኝ
ከነሱ መጣላት የልጁ አንገት መድፋት ሳይ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም አለቀስኩ በእዝነት አይኔ እያየሁ ጥያቄየን ቀጠልኩ
.....ፈይሰል ሁሌም ነዉ ወይስ ዛሬ ብቻ ነዉ እናትና አባትህ የሚጣሉት ??? ብየ ጠየኩት
.....ፈይሰልም " ጥዋትም ማታም ሁሌም እንደሚጨቃጨቁ ሲጨቃጨቁ ጃሮዉን በእጆቹ ይዞ ተዉ ተዉ....እያለ ከቤት እንደሚወጣ ባስ ሲልም እርስ በርስ እንደሚመታቱና በተደጋጋሚ ጎረቢቶች እንደሚገላግሏቸዉ ነገረኝ ፡፡ አዘንኩ ወደ ኋላ በሀሳብ ተጓዝኩ እማየ ትዝ አለችኝ በርግጥም በዱንያም ሆነ በአኼራ ሰዉ የዘራዉን ያጭዳል አባቢ እማየን እንዳስለቀሳት አሁን ሚስቱ ታስለቅሰዋለች!!!

...."ፈይሰል የት ሂደህ ነዉ? ለምን እዚህ መጣህ?"የአባቢ ንግግር ነበር ከገባሁበት የሀሳብ ማእበል ያነቃኝ ደነገጥኩ ቀና ብየ ለማየትም ቀፈፈኝ እባቢ አይኑን ወደ መሬት ወርዉሮ የኔ ልጂ አመሰግናለሁ ና ፈይሰል" አለና ልጁን ይዛ ለመሄድ ሲቻኳል ፊቴን ወደመሬት ስላደረኩ አላየኝም ወይም ከነመፈጠሬ ረስቶኝ ይሆናል ብየ ሳስብ ፈይሰል"አልሄድም ከአንተ ጋር አልሄድም ብሎ ተጠመጠመብኝ
..... አባቢም ና ፈይሰል እኔ እቸኩላለሁ አለና ጎንበስ ሲል አይን ላይን ተገጣጠምን

ከፊቱ ያየሁትን የመደንገጥ፤የፀፀት፤ የደስታ፤የሀዘን...ድብልቅልቅ ያለ ስሜት መቸም አረሳዉም "መመመመመ...."እንዴት ችሎ ስሜን ይጥራዉ?? አልቻለም ደጋግሞ ሞከረ መመመመ"ከሚባሉ ፈደላት ዉጭ ሙሉ ስሜት ከአፉ ማዉጣት አቃተዉ እንባዉ ጉንጫቹን አልፎ በአንገቱ እየወረደ የለበሰዉን ሸሚዝ አራሰዉ እኔም ቁሜ ማልቀስ ጀመርኩ እንዴት ችየ አባቴ ልበለዉ?? አልቻልኩም የእማየ የስቃይ ሞት፤የኔ ሂወት፤ የእህቴና የወንድሜ በድህነት ማደግ የሁላችን ተጠያቂ እሱ እንጂ ማን ነዉ? እና እንዴት ችየ አባቴ ልበለዉ?! እንዴት? ከበደኝ!!!

... መጥቶ በሁለት እጁ እያለቀሰ በናፈቀ ስሜት አቀፈኝ ሩጨ የምሄድበት መሰለዉ አካሌን ከፀጉሬ ጀምሮ ዳበሰዉ አላምን አለ ......በደስታ አንዴ ይስቃል አንዴ ያለቅሳል በዚህ ስሜት እያለ ሚስት ተብየዋ መጥታ "አንተ ሰዉየ ጭራሽ እኔን ትተህ ቆንጆ መዳበስ ጀመርክ?? ይሄ ነበር የቀረህ!!!! እንዲህ ነችና በል እስከዛሬም ታግሸሀለሁ አሁን ትግስቴ አልቋል ልጂህን ተረከብ እና የምትዳብሳት ሴት ጋር መኖር ትችላለህ " ብላ ልጇቹን ሰጥታዉ ሲጋራዋን እያቦለለች አባቴን ገለማምጣዉ ጥላዉ ሄደች
...አባቢ ዝም ብሎ እኔን ከማየት ከመዳበስ ዉጭ እሷን ለማየትም ለመስማትም ጊዜ አልነበረዉም ጥለዉ ስትሄድ ምንም ቃላት ሳያወጣ ዝም አለ።

ከደቂቃዎች ቡኋላ ነበር ልጆቹን እናታቹህ የት ሄደች ??? ብሎ የጠየቃቸዉ ልጆቹም ጥላቸዉ እንደሄደች ነገሩት ...እናቲቱ በሰራችዉ ስራ በጣም አዘነ


....ከአጠገቡ በፍጥነት አንድም ቃል ሳልተነፍስ ተነስቼ መንገድ ጀመርኩ
>>>>> ልጄ መራም መራሜ የኔ ልጂ እያለ ተከተለኝ
ምን ፈለክ ያንተ ልጅ ማን ናት??? እኔ እኔ ነኝ ያንተ ልጅ እኔ... የእብድ ሳቅ መሳቅ ጀመርኩ አባቢ ደነገጠ እይዉልሽ የኔ ልጅ የፈለግሽዉን በይኝ ፤ያሻሽን ተናገሪኝ...የፈለግሽዉን ስደቢኝ፤ ብቻ አባቴ አይደለህም አትበይኝ የኔ ልጅ በአላህ ተረጂኝ አዉፍ በይኝ ከስራየ በላይ የስቃይን ጥግ አይቻለሁ አይታይሽም ከሰዉነት ጎዳና እንዴት እንደወጣሁ??...."ንግግሩን አላስጨረስኩትም አቅፌዉ አለቀስኩ እሱም አቅፎኝ አለቀሰ .......በዚህ የሀዘን አይሉት የደስታ ለቅሶ ላይ ስልኬ ሲጠራ ነበር የነቃሁ

...የደወለዉን ስመለከት አብዲ ነዉ አነሳሁት ..ኮምቦልቻ ገብቻለሁ የምሰሪበት እየደረስኩ ነዉ ተዘጋጂ አለኝ ... ደስታየ እጥፍ ድርብ ሆነ ፡፡

አባቢ ምንም ቢሆን አባቴ አባቴ ነዉ አቃለሁ የቤተሰባችን የሀዘንና የስቃይ ሰበቡ እሱ ነዉ ግን ደሙ በእሱ ሰበብ ከደሜ ተወህዷል ስጋዉ ከሱተቆርጦ የተሰጠኝ ስጋየ ነዉ አባቱነቱን መፋቅ አልችልም! አባት በሌላ አባት እንደቁስ አይቀየርም አይሸጥ አይለወጥ ነገር.....

እናቴ ልትሞት ስትል የነገረችኝን አስታወስኩ አባታችሁ ይወዳችሆል ያለችን...ነገሮችን ሳስተነትን የወለዳቸዉን ልጆች ወንዱን በሞተዉ ወንድሜ ስም ፋይሰልና ሴቷን ደግሞ በምወዳት እናቴ ስም ለይላ ማለቱ አባቴ ተቸግሮ የሰራዉ ስራ አሳፍሮት ነዉ እንጂ የቤተሰብ ፍቅር እንዳለበት ተረዳሁ

መቸም ሰዎች ስንባል አዉቀንም ሆነ ሳናቅ እንሰሳታለን ስህተታችንን አዉቀን ከተመለስን እንዴት ይቅርታ እንነፈጋለን!
አላህ ይቅር እንዲለን ከፈለግን እኛም ለበደሉን ይቅር ማለት አለብን አላህ ይቅር እንዲለዉ የማይፈልግ እስኪ ማን ነዉ"??? ማንም!!!!

....ለአባቢን ይቅርታ ለማረግ ብዙ ማሰብ አልተጠበቀብኝም በፍጥነት ነበር አዉፍ ያልኩት ወድያዉ ወደ ቤት እንሂድ ብየ ጋበዝኩት
......መሄድ አልችልም በአላህ እሺ በይኝና ልጆቼን እንዳያቸዉ እዚሁ ይዘሽልኝ ነይ ልጄቼን የማይበት አይን የለኝም ብሎ አንገቱን ደፋ
....እኔ በሰራሀዉ ስራ አዉፍ ብየሀለሁ.... እናቴ ደግሞ የእህት ወንድሞቼ አደራ ለኔ ነዉ የሰጠችኝ ...እኔ ይቅር ካልኩህ እነሱም እንደሚሉህ እርግጠኛ ነኝ አልኩት

....የእህት የወንድሞቼን አደራ ለኔ ነዉ የሰጠችኝ ስለዉ አባቴም በጣም በማዘን እምባዉ ኩልል እያሉ እየወረደ እኔ ነኝ የእሷ ሞት ምክንያት እያለ ሲያለቅስ--እኔም አብሬዉ እያለቀስኩ አባቴ ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም ሰዉ መሳሳቱን አያቅም እንጂ ቢያዉቅማ አያጠፋም ነበር አልኩት
1.5K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:39:15   #የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊➎
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ


" መሪ ሶስት ቀን ያህል ለመቆየት አዲስ አበባ መሄዴ አይቀርም እዛ ትንሽ እኔን የሚፈልግ ስራ አለ እሱን አስተካክየ በቻልኩት ፍጥነት እመለሳለሁ!" ሲለኝ በጣም ደነገጥኩ
... "እና ትተህን ልትሄድ ነዉ ?! አዩብ አይናፍቅህም ይወድሀልኮ!" አልኩት፡፡ አዩን ምክንያት አረኩ እንጅ እኔ ራሱ ገና ሳይሄድ ልሄድ ነው ሲል ነው የናፈቀኝ
......"በጣም ነው እንጂ የሚናፍቀኝ ሁላችሁም ትናፍቁኛላችሁ መሪ ደግሞ ካልሰለቸሁሽ በየሰአቱ ነው የምደውልልሽ" አለኝ
..... "አትሰለቸኝም ደውልልኝ!? አልኩት በደስታ ከተናገርኩ በኃላ ግን መውደዴን ያወቀብኝ መሰለኝ እና አፈርኩ፡፡ ቤት እንደደረስን አዩ ገና እንዳየው ሩጦ ተጠመጠመበት
"አየሀው ከእኔ አንተን አስበለጠ" አልኩት ተገርሜ፡፡
...."እና እየቀናሽ ነው እንዴ!?" ብሎ ሳቀብኝ ገና ከመቀመጣችን ለሪም እና ለማማየ "አብደልከሪም ሊሄድ ነው!" አልኳቸው በደከመ ድምፅ ሁለቱም እኩል "የት ነው የሚሄደው!!?" አሉ ደንግጠዋል፡፡ እማማየ ወደሱ ዞረው "ወዴት ነው የምትሄደው ልጄ!?" አሉት በጣም ስለተላመድን አዲስ አበባ መኖሪያው መሆኑን ረስተነው እንጅ እንደ እውነቱ እማ አንድ ቀን ወደ መኖሪያው እንደሚመለስ ብናውቅም ተላምዶ መለየት ከበደን "ለ3 ቀን ብቻ ነው እንጅ እመለሳለሁ!" አለ በርግጥ እሱም መለየት ከብዶታል፡፡


አዩ መሄዱን ሲሰማ "እኔን ትተከኝ ልትሄድ ነው!?" አለው በአይኑ እየተለማመጠ
..... " እመለሳለሁኮ አዩ ከዛ የትም ሳልሄድ አብረን እንሆናለን እሺ" አለው፡፡ ጉንጮቹን በእጁ ይዞ ወደ ደረቱ እያስጠጋ፡፡ ሪም ምንም ሳትል ደንግጣ ወሬውን ታዳምጣለች፡፡ እማማየ በቃ ነገ መንገደኛ ከሆንክ መቼም ሰው አይሸኝም ይቀበሉታል እንጅ "ሪም ምግብ ስሪ ቡናም ይፈላል" አሉ፡፡ ሪም ተነሳች እኔም አብሪያት ተነሳሁ ምግብ ሰራን ቡና ከተጠጣ በኃላ ከፋኝ.. ለካ አብደልከሪም ይሄዳል ግን እስካሁን አዩብ አለቀቀውም እንደተቃቀፉ ናቸው፡፡

ሰአቱ እየመሸ ነው አዩብ ያለወትሮው እንቅልፍ ከሱ ርቆ ንቅት ብሏል አትሄድም ብሎ የሙጥኝ ብሏል፡፡ "ይሄ ልጅ ዛሬ አለቀቀህም ልጄ ነገ መንገደኛ ነህ ናቶሎ እዚህ ጎንህን አሳርፍ" ብለው መኝታቸውን ለቀው እኛ ጋር መተው ተኙ፡፡ "አዩብ እና አብደልከሪም ተቃቅፈው ተኝተዋል፡፡ እኔ ግን እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነጋ፡፡ ቁርስ ከበላን በኃላ አብዲ ተሰናብቶን ወጣ፡፡ ቤቱ በሀዘን ተሞላ እርስ በእርሳችን ተኮራርፈን ቁጭ አልን፡፡ እኔ በጣም ደብሮኛል ቤቱ ሁሉ አስጠላኝ! ቶሎ ወደ ስራ ሂጄ ራሴን ቢዚ ማድረግ ፈለኩ፡፡


አብደልከሪም ከሄደ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑ ነው፡፡ እየተደዋዉልን ስለሆነ ነገ እንደሚመጣ ነግሮኛል፡፡ የዛሬው ቀን ረዝሞብኛል ዛሬ አልፎ ቶሎ ነገ እስኪደርስ በጣም ቸኩያለሁ፡፡ በደስታና በንቃት ስራየን እየሰራሁ ነው፡፡ ከስራ ወደ ቤት ስሄድ ሪም ለነገ አቀባበል ዛሬ ሽርጉድ እያለች ነበር፡፡ ምን እሷ ብቻ አዩ ከሷ ብሷል እንጅ በደስታ እየዘለለ ይቦርቃል ለተመለከተን ሰው ሁለት ቀን የተለየን ሳይሆን ለብዙ አመታት የተለየንን ሰው የምንጠብቅ እንመስላለን፡፡

ነገን በመናፈቅ ደስ በሚል ተስፋ ደስ የሚል መኝታ ደስ የሚል ንጋት! ዛሬ አብደልከሪም ይመጣል! እኔ ወደስራ መሄድ አለብኝ፡፡ አብዲ ቀድሞ እኔ ጋር ስራ ቦታ እንደሚመጣ ነግሮኛል፡፡

እኔም እሱን በማግኘት ተስፋ ስራየን ተያይዣለሁ ደቂቃ በሰአታት እየቀፈራረቁ ሰአታትን አስቆጥረው እኩለ ቀን ደረስን ከ6-7 ባሉት ሰአት በጣም የስራ ውጥረት ይኖራል፡፡ 7 አልፎ 8 ሰአት ደረሰ አሁን ስራ ውጥረት ቀነሰ ከስራ ለመውጣት አብዲን እየተጠባበኩ ባለበት ሰአት------- አንዲት ሴት ሁለት ህፃናት ልጆችን ይዛ ወደ ካፌው ገባች አለባበሷ ቅጡ የጠፋው ከእድሜዋ ጋር የማይሄድ ሙስሊም ትሁን ካፊር ግራ የምታጋባ ግን ደግሞ በየወሬዋ መሀል ወላሂ እያለች መሀላ የምታበዛ ነች :ጫት እየቃመች አፏ የጌሾ ሙቀጫ መስሏል ከ3 ወይም 4 አመት የማያልፈው ወንድ ልጅ እና በወራት እድሜ ያለች ልጅ ይዛለች፡፡ ወንበር ይዘው ተቀመጡ የስራ ሰአቴ ስላለቀ ካሽሪዋ ጎን ቁጭ ብየ አብዲን እየጠበኩ ነው፡፡

ልጇ የተቀመጠበት ወንበር ከእኔ ፊት ለፊት ነበር፡፡ የልጁን መልክ ሳይ ልቤ ቀጥ ብላ የቆመች መሰለኝ ደነገጥኩ ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ ሁሉ ነገሩ የሞተውን ወንድሜ ፈይሰልን ይመስላል፡፡ "ፈይሲ" አልኩኝ ለራሴ በሚሰማ ድምፅ በእጀ ምልክት ሰጥሁት ና አልኩት ተነስቶ ወደኔ መጣ ምንም ሳልለው ተንበርክኬ አቀፍኩት ደጋግሜ ሳምኩት በደከመ ድምፅ "ስምህ ማነው?" አልኩት
......."ፈይሰል" አለኝ በሚጣፍጥ አንደበት ድንጋጤ ይበልጥ ጨመረ ስሙም የሞተዉ ወንድሜ አይነት ፈይሰል ጋር አንድ ሆነብኝ እሱን እያስታወስኩ እንባየ ያለገደብ መፍሰስ ጀመረ እጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ... የመተዉ ወንድሜ ጋር በጣም ይመሳሰላል "አባትህ ማነው ስሙ?" አልኩት "
.....አባቴ እዛ ነው ምሳ በልቸ እናቴጋ እንሄዳለን" አለኝ፡፡
........ "ምሳ እስካሁን አልበላህም!?" አልኩት አንጀቴ በሀዘን እየተላወሰ ቅንጭላቱን በመነቅነቅ አወንታውን ገለፀልኝ፡፡ ጭምቅ አድርጌ አቀፍኩት እና ደግሜ የአባቱን ስም እንዲነግረኝ ጠየኩት "አባቴ ስሙ አባቢ ነው" አለኝ፡፡ " እሽ ህፃኗ ስሟ ማነው አልኩት
....." እህቴኮ ናት " አለኝ፡፡ "
.....እኮ ስሟን ንገረኝ ??አልኩት
..... እናቴ ሩማን ናት ብላለች አባቴ ደግሞ ለይላ ናት ብሏል ስም የላትም" አለኝ እየሳቀ

ነገሮች ሁሉ ተዘበራረቁብኝ በድንጋጤ ደርቄ ቀረሁ እና ከተደረደሩት ኬኮች ውስጥ እያስመረጥኩት
....."ቤታችሁ የት ነው?" አልኩት በእጁ ምልክት እየሰጠኝ "እዛ ነው" አለኝ፡፡ የምፈልገውን መረጃ ከሱ ማግኘት አልቻልኩም እና አቅፌ ወደ እናቱ ወሰድኩትና ከእሷ መረጃ ለማግኘት በዘዴ ቀረብኳት፡፡
....."ሰላም እንዴት ነሽ ማሻአላህ ደስ የሚል ልጅ አለሽ" አልኳት ለመግባባት ያህል ...ግን የእሷ መልሷ አስደነገጠኝ " ......ካማረሽ ወስደሽ አሳድጊው ሰጠሁሽ ልጁን አልፈልገውም" አለችኝና ወደ ልጁ ዞራ "አንተ ደደብ ደንቆሮ አርፈህ ቁጭ በል ብየህ አትሰማም አይደል ምናለ በሞትክና በተገላገልኩህ" ብላ በጥፊ ላሰችው፡፡ በቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ እናት ስለመሆኗ ተጠራጠርኩ እማ በቅፅበት በህሊናየ ውል አለችብኝ
....." ለምን ትመችዋለሽ ??ልጅ እኮ ነው ደግሞ ምንም አላጠፋም አንችም እንደ እናት ከአጠገብሽ ሲርቅ አስበሽ የት ሄደ ብለሽ አልፈለግሽውም" አልኳት በንዴት

ልጁ ጉንጩን በእጁ ይዞ እንባው ይረግፋል፡፡ አሳዘነኝ የገዛሁለትን ኬክ አስቀምጨ እንባውን ጠረኩለት "ጎሽ ጎበዝ ልጅ ለዛሬ ራስህን ችለህልኛል ከወጭ አሳረፍከኝ ዳይ ተነስ እንሂድ" ብላ ምሳዉን ሳይበላ የገዛሁለትን ኬክ አንጠልጥላ እየጎተተች ወሰደችው፡፡ "እውነት አሁን ይችም እናት ትባል ይሆን!!?" ብየ እማን አስታውሸ እንባየ ፈሰሰ ዳግም የልጁ ሁኔታ ፊቴ ድቅን አለ


ወደ ውጭ ወጥቼ ወደ ምድር አንገቴን አስግጌ ልጁን ተመለከትኩት ከፊት ለፊቱ ወዳየው ሰው ሩጫ ቀጠለ የልጁን ሩጫውን ተከትየ ሰመለከት አይኔን ማመን አቃተኝ ......

#ክፍል ➊➏
ይቀጥላል.......


https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.5K viewsedited  05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:29:27 የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

  "ከአቡበክር በስተቀር ማንኛውንም ሰው ወደ እስልምና ስጋብዘው ያላመነታና ያላንገራገረ የለም።..." ረሱል ﷺ
   
                    ክፍል አራት

              የአስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ያሰብዕና ቁልፍ
  ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡፡ "ከሰዎች ሁሉ በእውነተኛ እምነቱ ወደር የማይገኝለት ስው አቡበክር አስ-ሲዲቅ ነው፡፡” እንዲህም ይላሉ... "ከሰዎች ሁሉ በጽኑ እምነቱ አቻ የማይገኝለት ሰው አቡበክር አስ-ሲዲቅ ነው።”

   ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- “የኡማው ኢማን በአንድ መዳፍ፤ የአቡበክር ኢማን ደግሞ በሌላ መዳፍ ሆኖ ቢመዘን የአቡበክር ኢማን ባመዘነ ነበር፡፡” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "አቡበክር የበለጣችሁ በሶላትና በፆም ብዛት ሳይሆን በቀልቡ ውስጥ ጸዳል በሆነው ኢማኑ ነው፡፡” ሲሉመስክረዋል፡፡

   የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) የስብዕናቸው ቁልፍ የሆነው ለእውነት - የነበራቸው ፍጹም ውዴታ ነበር፡፡ ለእውነት መስዋእት
ለመሆን ሲሉ እድሜያቸውንም ሆነ ደማቸውን ከመስጠት ለአፍታም አላንገራገሩም፡፡
    አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ሕይወታቸውን ሁሉ ምንም ሳይሰስቱ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰጡት የእውነት ሁሉ መገኛ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በመሆናቸው ነበር፡፡
     ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ዝንተ-ዓለማዊው ሕይወት
በተሸጋገሩበት ቅጽበት ሶሀባዎች ሁሉ ተደናግጠው የሚያደርጉትን ሲያጡ ግልጽና ትክክለኛ አቋም የወሰዱት ብቸኛው ሰው አቡበክር (ረ.ዐ) ነበሩ፡፡ የአቡበክርን (ረ.ዐ) ሕይወት ምንጊዜም ቢሆን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው እውነት ብቻ ነበር፡፡

   ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መካ ውስጥ የእውነት ተምሳሌት ሆነው ብቅ ሲሉ አቡበክር (ረ.ዐ) በእጃቸው ያለውን ነገር ሁሉ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)
በመስዋኣትነት አቀረቡ፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለሕልፈት ሲበቁም አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) በእውነት መስመር ላይ ጸኑ፡፡

   ዑለማዎች አንድ በጋራ የሚስማሙበት ነገር አለ፡፡ ይኸውም
ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በመቀጠል ለመጀመሪያ ጊዜ ለአላህ (ሱ.ወ) ሱጁድ ያደረጉ(በግንባሩ ተደፍቶ የስገደ) እመቤት ኸዲጃ (ረ.ዐ) ናቸው፡፡ ከወንዶች መጀመሪያ የሰለመው ደግሞ አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ናቸው። ከሕፃናት የመጀመሪያው እስልምናን የተቀበለ ደግሞ ዓሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረ.ዐ) ሲሆኑ ከአገልጋይ ደግሞ መጀመሪያ እስልምናን የተቀበሉት ዘይድ ቢን ሐሪስ (ረ.ዐ) ናቸው፡፡

   ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለመጀመሪያ ጊዜ ኣቡበክርን (ረ.ዐ) ወደ እስልምና ሲጋብዟቸው ያለምንም ማመንታት ነበር የተቀበሏቸው፡፡ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ይህንኑ አስመልክተው እንዲህ ይሉናል "ከአቡበክር በስተቀር ማንኛውንም ሰው ወደ እስልምና ስጋብዘው ያላመነታና ያላንገራገረ የለም፡፡ አቡበክር ግን ስለ እስልምና ስነግረው ወዲያውኑ ያለማመንታትና ያለማንገራገር ተቀበለኝ፡፡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው በማለት እዚያው መሰከረ፡፡”

  ሰይድ አቡበክር (ረ.ዐ) ወደ እስልምና ጥሪ ሲደረግላቸው
ወዲያውኑና ያለማመንታት የተቀበሉት እንዲሁ በስሜትና በዘፈቀደ
ኣልነበረም፡፡ ምንም ዓይነት ራዕይ ሳይኖራቸው ቀርቶም አይደለም፡፡
ይልቁንም ሐቅ የተባለን ነገር ወዲያውኑ የመቀበልና የማመን ቋሚ
ባህሪ ስለነበራቸው ነው። የእስልምናን እውነት ከተቀበሉበት ዕለት
አንስቶ የብርሃን ፀዳል ቀልባቸውን ይሞላ ጀመር፡፡
እዚህ ቦታ ላይ ለአፍታ ቆም ብለን በማስተዋል ከእኝህ ታላቅ
ሰው መማር ይኖርብናል። እስልምና እውነት መሆኑን አምነን
እስከተቀበልን ድረስ፤ ሁለመናችንን በእስልምና ጥላ ሥር ማኖር
ይገባናል፡፡ አቡበክርን (ረ.ዐ) ተምሳሌት ማድረግ ይኖርብናል፡፡

   ከላይ እንደተጠቀሰው አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) እኛን የበለጡን በሶላት ወይም በዖም ብዛት ሳይሆን የእውነትን ብርሃን ሲመለከቱ በዚያ ውስጥ ተጠቅልለው ለመኖር አንዳችም ባለማመንታታቸው ነው። ነፍሳቸውን፣ ሃብታቸውን፣ ጊዜያቸውን ሁሉ ለእውነት ሰውተዋል፡፡ ለእውነት ሲሉ ደማቸውን ሰጥተዋል፣ ገንዘባቸውን ሁሉ አፍስሰዋል። ኃይላቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ልጆቻቸውን ለእውነት ሰጥተዋል።

      ከአቡበክር (ረ.ዐ) ልንማር ከሚገባን ቁም ነገር አንዱ አንድን
እውነት ካወቅን ሕይወታችንን በሙሉ ለዚህ እውነት መስጠትን ነው::

    አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) እስልምናን ሳያወላዱ የተቀበሉት ብዙ ተነግሯቸው ሳይሆን ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጣፋጭ አንደበት በሰሟት ጥቂት ንግግር ነበር፡፡ የእስልምናን መልዕክት ለማስራጨት ባጭር ታጥቀው የተነሱት ወዲያው እንደሰለሙ ነበር፡፡ ለዳዕዋ በተነሱ በመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ ጀነት ከተበሰረላቸው (ዐሸረቱል ሙበሸሪን) አስር ሰዎች ውስጥ ስድስቱ በእርሳቸው እጅ ለመስለም በቅተዋል፡፡ እነዚህም፦1. ሰዐድ ቢን አቢ ወቃስ 2.ዙበይር ቢን አል-ዓዋም 3. ጦልሐ ቢን 4. አቡ ዑበይዳህ ቢን አል-ጀራህ 5. ዐብዱራህማን ቢን ዐውፍ 6. ዑስማን ቢን ዓፋን ናቸው፡፡
    እነዚህ ሁሉ ዕንቁዎች በአቡበክር (ረ.ዐ) አማካኝነት የሰለሙት
በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ወቅት አስ-ሲዲቅ ስለ
እስልምና ያውቁ የነበረው ጥቂት ነገር ብቻ ነበር።

   ከዚህ አንፃር እስኪ የእኛን ሁኔታ እንገምግመው፡፡ ስለ እስልምና
ብዙ እናውቃለን፡፡ በእኛና በአቡበክር (ረ.ዐ) መካከል ያለው ልዩነት አንድ ነው፡፡ ይኸውም እርሳቸው እውነትን አወቁ ወዲያውኑ ጥቅልል ብለው ለእውነት ብቻ መኖር ጀመሩ፡፡ እኛ ግን እውነትን በብዙ አቅጣጫ አውቀናል፡፡ ለእውነት ለመኖር ግን ዝግጁዎች አይደለንም፡፡ እውነትን አውቀን ለእውነት ብቻ ለመኖር ካልቻልን በእውነት ስህተተኞች ነን።

   አቡበክር (ረ.ዐ) እውነትን አወቁ፡፡ ስሜታቸው ለእውነት ተማረከ።
ለእውነትም ሌትተቀን ሠሩ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ስድስት ዕንቁዎች
ሙስሊም እንዲሆኑ ምክንያት የሆኑት አቡበክር (ረ.ዐ) ናቸው። እነዚህ ሰዎች የሠሯቸው መልካም ሥራዎች ሁሉ (የነርሱ ምንም ሳይጓደል) ለአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) ነው የሚመዘገቡት፡፡ ያደረጉት ዒባዳ፣ ጂሐድ፣ ምጽዋት፣ ዳዕዋ... ሁሉ ምንዳው ለአስሲዲቅ (ረ.ዐ) ነው፡፡

    አቡ ዑበይዳ ቢን አል-ጀራህ ሻምን ሰዐድ ቢን አቢ ወቃስ ደግሞ
ኢራቅን የከፈቱና ያቀኑ ናቸው፡፡ የፋርስንም ቅኝ አገዛዝ ያንኮታኮቱ፡
ናቸው፡፡

    በአቡበክር (ረ.ዐ) እጅ የሰለሙት እጅግ በርካታ ሰዎች ናቸው።
ከእነዚህም ውስጥ አል-አርቀም ቢን አቢ አርቀም፣ ዑስማን ቢን መዝዑን ሊጠቀሱ ይችላሉ። ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በባሪያ ፍንገላ ሥር የነበሩ ብዙ ሰዎች በአቡበክር (ረ.ዐ) ገንዘብ ነፃ ሊወጡ ችለዋል። መጀመሪያ ነፃ የወጡት ሰባት ሰዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ቢላል ቢን ረባህ(ረ.ዐ) የመጀመሪያው ነው፡፡

  የቢላል ገዢ ኡመያ ቢን ኸለፍ ይሰኛል። በመስለሙ ምክንያት
ቢላልን ይቀጣውና ያስቃየው ነበር፡፡ አንድ ቀን ቢላልን እያሰቃየው ሳለ አቡበክር (ረ.ዐ) በአጠገባቸው ሲያልፉ ይህንን ይመለከቱና ለኡመያ እንዲህ ይሉታል። “ይህ ምስኪን አያሳዝንህም?" ኡመያም “አንተ እዘንለት” ሲል ይመልሳል፡፡ አቡበክርም (ረ.ዐ) “እሺ ስንት ልክፈልህና ነፃ ትለቀዋለህ?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ 

----------ኢንሻ አላህ ይቀጥላል--------------

የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
http://t.me//@arebgendamesjid
1.7K views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:21:45

768 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:37:38
የቁርአን ግብዣ
መልካም ጁምአ

https://t.me/Islam_and_Science
1.3K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:34:22
ከአንደኛዉ የአለም ጦርነት ቡሀላ ምን ተፈጠረ??
ለአስተያየት ☞ T.me/Aisuu_bot
https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
1.1K viewsedited  08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ