2022-09-07 11:54:18
አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
#ክፍል ☞ አንድ
ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ
በሰዎች ዉሳኔና ፍላጎት ምኞት እና ጉጉት ብቻ ተፈፃሚ የሚሆን ነገር የለም የአሏህ ፍቃድ እስካልታከለበት ድረስ.. አንዳንዴ በሰዉ በዘመድ ተከበህ ሰዉ ይናፍቃል. እዉነት ነዉ በአለም ላይ በቢሊየን የሚሆን ህዝብ እያለ የዉስጡን የሆዱን የታፈነ ነበልባል አንድ ሰዉ ላይረዳህ ይችላል...የዚህን ጊዜ ብቸኝነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት ይቻላል ፡፡
ዉሀ ላይ ሁኜ ዉሀ ይጠማኛል
እሰዉ ጋር ሁኜ ሰዉ ይናፍቀኛል
የያዘኝ በሽታ ወንድም ያሰኘኛል
አንድ መንዙማ ላይ የሰማሁት ነዉ . እዉነት ነዉ ዉሀ ጠምቶህ ጠጥተሀዉ ሆድህ ቢገባም ዉሀዉ ጥምህን የማይቆርጥ ከሆነ
በሰዉ መሀል ተከበህ ሰዉ ሲያስፈልግህ ሰዉ ግን አንተን ለመረዳት ሳይፈልግ በአንተ ላይ የሚሳለቅ ከሆነ ሰዉ መሀል ተከበህ ጥቅሙ የሚሆነዉ የሰዉ ቆጠራ ጊዜ አብሮ ተቆጥሮ አለ ይሄን ያህል አለ ለማለት ያህል ካልሆነ በቀር ....
የተፈጠርንበት ማንነት ዲነል ኢስላም በወንድምነት በእህትነት አስተሳስሮን ነገር ግን ዛሬ ጓደኛ ነገ ደግሞ ጥላት እየሆነ የመጣ ይመስላል. ታዳ መቼ ይሆን ለሰዉ እዉነተኛ ሰዉ የምንሆነዉ???..ለሰዉ ልጅ በሽታዉም ህመሙም ያዉ አላህ እንደቀደረዉ ሁኖ ታንቆም መርዝ ጠጥቶም የሚሞተዉ ያዉ በሰዉ ምክንያት ነዉ ..ምክንያቱም ይህን ዉሳኔ የወሰነዉ መቼም ሰዉ ነዉ እና ጥፋት አይቀርም..አጥፍቶ መሄጃ ሲያጣ በአማከረዉ ሰዉ ወይም ለልብ ጓደኛዉ የልቡን ነግሮት ግን የተናገረዉን ከጆሮ ባልዘለለ ከልቡ ሳያስቀምጠዉ ሲቀር ያኔ ከሰዉ በላይ አላህ ይጠብቀን ሸይጧን ይቀርበዋል ይሳሳታል ይታነቃል ወይ መርዝ ይጠጣል ..ይሄን ዉሳኔ የሚወስነዉ ዱንያን መሮት እንጂ ተመቸቶኝ ብሎ ራሱን የሚያጠፋ የለምና...
በጥናት ዉጤት ስናየዉ አሜሪካ በአንድ አመት ብቻ 25,000 ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ቻይና በየዓመቱ 30,000 ሰዉ ራሱን ያጠፋል በአለም ላይ በየ20 ሰከንዱ ሰዎች ራሳቸዉን ያጠፋሉ ይህ ማለት በአለም ላይ ወደ በአንድ አመት ሁለት ሚሊየን ህዝብ እራሳቸዉን ያጠፋሉ ማለት ነዉ፡፡
ሁሉም ሰዉ ሊያወቀዉ የሚገባ የማይካድ ሀቅ ደስታ በዲነል ኢስላም አላህ ጋር ባለን ግንኙነት እንደሚወሰን መገንዘብ አለብን..የቁርአንን መመሪያ መከተል ለዚህ ያለእድሜዉ እራሱን ለሚያጠፋዉ እና በሂወት እያለ ሒወት እንደ ዥዋ ዥዌ ጨዋታ ለሆነችበት ቁርአን መፍትሄ እንደሆነ እርግጥ ነዉ .... አሁን ጊዜ ላይ ያለነዉ የሁላችንም ጥፋት የቁርአን መመሪያ እኛ መከተሉን ትተን በእኛ መስመር እንዲከተለን መፈለጋችን ነዉ፡፡
ታዳ ለዚህ ሁላ ራሱን ላጠፋዉ ተጠያቂዉ ሰዉ አይደለም ብላችሁ ታስባላችሁ??? ሰዉ ከሚሳሳትባቸዉ ምክንያቶች ዋናዉ እና አንደኛዉ ባለፈዉ ጊዜ ምን ምን ነገሮች ነበሩ??ዛሬ ምን ይደረጋል?ነገስ ምን ይመጣ ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች ሳያስተዉሉ ሁሉንም ነገር ለዛሬ ብቻ ሲሰጡ ነዉ፡፡
አንዳንድ ሰዎች ደስታ የሚገኘዉ በብር ብቻ ነዉ ብለዉ የሚያምኑ አሉ... ስህተት ነዉ ደስታ የሚገኘዉ በዲነል ኢስላም ነዉ :: ዲነል ኢስላምን አዉቆ ያልሰራበት ደስታ በጭራሽ አያገኝም..ለምሳሌ አሜሪካንን እንዉሰድ የአለም ኢኮኖሚ 50% በአሜሪካ እጅ ይገኛል ነገር ግን በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ አገሮች ቁጥር ተርታ ስትሰለፍ 116 ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡በተዘዋዋሪ ደግሞ በአለም ላይ በደስታ የሚኖሩ ሀገሮች የመሪዎችን ደረጃ የያዙት ሙስሊም ሀገራት ሲሆኑ.....ቁጥር 1 ናይጀሪያ ናት ..ናይጀሪያ እንደምናዉቀዉ የሙስሊም ሀገር ናት በኢኮኖሚዋ ዝቅተኛ ብትሆንም ግን የመጀመሪያ አላማቸዉ አላህን ማስደሰት ስለሆነ በአላቸዉ ተብቃቅተዉ በደስታ ይኖራሉ
የሰዉ ልጅ ብር ደስተኛ እንደማያረግ የጃፓኑን ትልቅ ድልድይ በቀን ከ300 መኪና በላይ የሚተላለፍበትን የገነባዉ ኢንጅነር በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ገቢ ያገኘ ቢሆንም ተመርቆ አገልግሎት በሚሰጥበት ቀን በትንሽ ቁራጭ ወረቀት ኑዛዜ አስቀምጦ ራሱን ከድልድይ ላይ በመጣል ራሱን አጥፍቷል...በኑዛዛዉ እንዳስቀመጠዉ """"እኔ የገንዘብ ችግር አላጋጠመኝም ደስታ በማጣቴ ብቻ ከዚህ አለም ለመሰናበት ፈልጊያለሁ"""" ነበር ያለዉ ፡፡
በአለም ላይ የሰዉ ልጅ ራሱን ለመቀየር 24ቢሊዮን ዶላር/ ሴቶች ለኮስሞቲክስ 18ቢሊዮን ዶላር /ፀጉርን ለመንከባከብ 38ቢሊየን ዶላር /ለሽቶ ደግሞ 15ቢሊዮን ዶላር በአመት ያወጣሉ... ታዳ ሰጥቶን ስጡ ለተባልነዉ ዱንያ የአላህ ወዴታን ለማግኘት ስንት አዉጥተናል?? ለተቸገረ ሰዉ ስንቶቻችን የችግሩ መፍትሄ ሁነናል??ስንቶቻችን ነን ደሀ እና ሀብታምን ሳንለያይ በአንድ አይን የምናየዉ???
ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ አንድ ሰዉ ጀሀነም እሳት ዉስጥ ለመግባት ሙስሊም ወንድሙን በዝቅተኛ አይን ማየቱ በቂ ነዉ ብለዋል..እስኪ ሆድ ይፍጀዉ
የኔ ታሪክ ስለ ሁላችንም የሰዉ ማንነት ላይ ዱንያ የደስታ ህይወት አለመሆኗን ያተኮረ ሲሆን እስኪ ሳይረፍድ ወደ ታሪኩ እንግባ
ቅድሚያ መተዋወቅ ይቀድማል እንተዋወቅ የእናንተን ባለቅም የእኔ ስም ነዋል እባላለሁ አሁን ላይ የኔ እድሜ አስራ ዘጠኝ ሲሆን ፡፡ እኔ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ ከእኔ በታች በሶስት አመት የምበልጠዉ አንድ ታናሽ ወንድም እና በጣም ታናሽ እህት አለችኝ..በጠቅላላ ለቤተሰቦቻችን ሶስት ልጆች ነን፡፡
ተወልጄ ያደኩት የፍቅር የመከባበር ሀገር በሆነችዉ የአባጅፋር ሀገር ጅማ ከተማ በአጂፕ ሰፈር አዲሱ ገቢዎች ግምሩክ አካባቢ ነዉ፡፡
አባቴ ጅማ ከተማ ላይ ታዋቂ ኮንትራከተር ህንፃ ተቋራጭ ሲሆን በዚህም የተነሳ ዉብ የሆነ ቤት እና ወደ ሰባት የሚሆን መኪና ያለን ሲሆን ጅማ ላይ እስኪ ብር ያለዉ ባለሀብት ጥሩ ቢባል ቁጥር አንድ የሚጠራዉ የኔ አባት ነዉ፡፡ እንደ መጀመሪያ ልጅ በመሆኔ ምንም ሳይጎልብኝ የፈለኩትን በልቼ የፈለኩትን ጠጥቼ ነዉ ያደኩት ፡፡ አባቴ በጣም ተንከባክቦ ነዉ ያሳደገኝ ፡፡
መቼም ማንኛዉ ሰዉ እድሜዉ ከትምህርት ከደረሰ ትምህርት ቢያነስረዉ መመዝገቡ አይቀርም ...እኔም ጅማ የሚገኘዉ ኮምዪኒቲ ትምህርት ቤት--KG1 ተመዘገብኩ፡፡ KG ትምህርቴን እንደ ጨርሼ አንደኛ ክፍልም እዛዉ ኮምዩኒቲ ትምህርት ቤት ተመዘገብኩ፡
የሰፈር ልጆች ጋር ከልጅነቴ ጀምረን ስጫወት እነሱ ግን እኔ ጋር መጨዋት አይፈልጉም ነበር
.....ለምን እኔ ጋር አትጫወቱም ስላቸዉ ??
....እናት አባቶቻችን አንቺ ጋር እንዳትጫወቱ ተብለናል ይሉኛል፡፡
እኔም ልጆቹ ያሉኝን ለአባቴ ሂጄ እነግረዋለሁ
...አባቴም አንጫወትም ካሉሽ አትጫወቺ ምን ያረጉልሻል እቤትሽ አድበሽ ተጫዋቺ ይለኛል
አንደኛ ክፍል እየተማርኩ የኔ ጓደኛ ለመሆን የማይጥር የለም ... ትምህርት ቤት ስሄድም ስመጣም መኪናዉ የራሳችን ስለሆነ አባቴ በያዘልኝ ሹፌር ነዉ የምመላለሰዉ ፡፡ የሀብታም ልጅ ስለሆንኩ ነዉ መሰለኝ ብዙ ሴት ልጆች እኔን ጓደኛ እንድሆናቸዉ ይቀርቡኛል
340 views08:54