Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.00K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-09-19 20:50:18 ይህን ያውቁ ኑሯል

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ኢስራ ወል ሚዕራጅ ደርሰው ሲመጡ በየሰማያቱ እነማንን እንዳገኙ...

:➊. 1ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ አደም (ዐ.ሰ)

➋. 2ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ የህያ (ዐ.ሰ) እና ኢሳ(ዐ.ሰ)

➌. 3ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ)

➍. 4ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ኢድሪስ (ዐ.ሰ)

➎. 5ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ሃሩን ቢን ኢምራን (ዐ.ሰ)

➏. 6ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ሙሳ ቢን ኢምራን (ዐ.ሰ)

➐. 7ኛ ሰማይ ላይ ያገኙት ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ)……ናቸው፡፡
http://t.me//@arebgendamesjid
SHARE SHARE
የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ
1.6K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 13:01:08         መፍቱሀ ዓሊይ መስጂድ የሚገኘዉ የሴቶች ጀመአዉ ላይ አሚር ስለሆነች እኔ በተለለያዩ ነገር እንድሳተፍ አደረገችኝ፡፡በሳምንት ቅዳሜ የኛ የሴቶች ጀመአ ዝግጅት አለን.... እናም እሳተፋለሁ.., ሁሌም መፍቱሀ አንቺ ተሰጥኦ ታለንት አለሽ ትለኛለች፡፡ መፍቱሀ ግጥም ትፅፍ እና እኔ ነኝ የማቀርበዉ....መነባነብ ለራሱ እንደ እኔ የሚሆን የለም .....እናም በመሀል ቀልድም ሲያስፈልግ እኔ ነበርኩ ፈታ የማረጋቸዉ፡፡
በሂደት እኔዉ የተለያዩ ግጥሞች ታሪኮች ፅፌ ለሷ አነብላታለሁ እሷም ይሄ ጀመአ ላይ መቅረብ አለበት እያለች የተለያዩ ኢስላማዊ ይዘት ያላቸዉ ዝግጅቶች አቅራቢ ሆንኩኝ፡፡

ድፍረቴን ተስጦኦየን አይተዉ ዝግጅት ሲኖር የጀመአዉ መድረክ መሪ አስተዋዋቂ እኔዉ ሆንኩኝ፡፡ ፕሮግራም መሪ..ፕሮግራም ያላቸዉ...እናም የሚቀርቡትን ነገሮች ይመጥናል አይመጥንም እያልኩ እኔዉ እገመግማለሁ፡፡
ዝግጅት ሲኖር ሀሳባቸዉን ሁሉም ለኔ ትተዋል፡፡ እኔም በዚህ መድረክ መምራት ማንንም አልፈራም

መፍቱሀን ዛሬም ነገም ለወደፊትም ብሆን ዉለታዉን መመለስ ባልችልም ሁሌም ሳመሰግናት እና በልቤ ዉስጥ አስቀምጫታለሁ
★★★ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል በጎ ነገር ላደረገላችሁ ሰዉ ወረታዉን መልሱ ..ካልቻላችሁ ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን በማለት ዱዐ አርጉለት ብለዋል ፡፡
በሌላ ሀዲሳቸዉ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ሰዉ ላደረገለት በጎ ተግባር ሰዉን ያላመሰገነ አላህንም አያመሰግንም ..ብለዋል፡፡ ሁሌም ቢሆንም ለእኔም ዱአ ሳደርግ ለመፍቱሀም አብሬ ዱአ አደርጋለሁ

ይሄ ጀመአ የሴት ብቻ አይደለም ወንዶችም እራሳቸዉን ችለዉ አላቸዉ የጀመአችን ስም አንድ ነዉ Telegram ..Whatsap..Youtube አድራሻዎች አሉን በጂማ ታዋቂ ነዉ፡፡ ፋዉንዴሽንም አለዉ የቲሞችን የተቸገሩን ጧሪ ቀባሪ የሌሊቸዉን ወረሀዊ መዋጮ አለ በተጨማሪም ከባለሀብቶች በማስተባበር እየሰበሰብን በወር ብዙ ችግረኞችን የቲሞችን እንደጉማለን

   ጅልባብ ለባሽ ከሆንኩ ቡሀላ ከጀመአም ልጆች መስጊድ ከሌላም ቦታ የምንገናኝ ሙስሊም እህቶቼ በጣም ይቀርቡኛል ፡፡ አንድ አባባል አለ አንተ ጥሩ ቦታ ከሆንክ የሚቀርቡህ ጥሩ ነገር ነዉ፡፡ መጥፎ ቦታ ከሆንክ የሚጠጋህ መጥፎ ባለጌ ሰዉ ነዉ...አላህ ከወደደህ ሁሉ ሰዉ ይወደሀል አይደል የተባለዉ ሀቅ ነዉ ፡፡ እኔ ለዲኔ ጠንካራ ሆንኩኝ ለሊት እየተነሳሁ መስገድ ሱና ሶላቶች እና ሱና ፆሞችን መፆም ከጀመርኩ ቆየሁ ፡፡

ግን ሁሌ በመደጋገም ዱአ ማደርገዉ አለ ...አላህ ሆይ ከማንነቴ የሚወደኝ እኔን የሚረዳኝ የትዳር አጋር ስጠኝ እያልኩ ዱአ አደርጋለሁ

በጀመአ ዝግጅት መድረክ መሪ በሆንከበት ጊዜ ብዙ ሰዉ አይን ዉስጥ መግባት እና ለኔ ጥሩ ጥሩ ሲለሚወራ ለሰሚ ጆሮ አገኘሁ፡፡ እኔ ዝግጅት መሪ ስሆን አዳራሽ ተከራይተን ዝግጅት ስናዘጋጅ ወንዶች በመጋረጃ ተከልለዉ ይታደማሉ ፡፡ እኔ መድረክ መሪ በመሆኔ ከተለያዩ ወንዶች አድናቆት እየጎረፈ ነዉ..........፡


#ክፍል

ይ.........ቀ.............
.......ጥ...........ላ.................ል

JOIN
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
1.8K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 13:00:52 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ አራት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ማንንም እንዳፈሪ ጅልባቡን ሳታወልቂ ለብሰሽዉ ነይ አለችኝ........
የመፍቱሀ ንግግር ልቤ ዉስጥ ገባ ..ሰዉ ምን ይለኛል የሚል ፍርሀትን አስወግጄ ወኔ ፈጠረብኝ ....ማንንም አልፈራም ደግሞ ለዘንድሮ ሰዉ ብየ ጅልባቡን እንደለበስኩኝ ከቤቴ ወደ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ መሔድ ጀመርኩኝ....ግን እደሄድኩ የመጀመሪያየ ስለሆነ እየተንቀጠቀጥኩ እየፈራሁኝ ነዉ፡፡ ሰዉ ሁሉ በመንገድ ስሄድ ሲያየኝ ምን ሁና ነዉ የሚለኝ ይመስለኛል.... በጣም ነበር የማያስፈራዉ፡፡ እንደ ምንም ብየ ኮሌጅ ደረስኩኝ...

ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ሁሉም እየተጠቋቆሙ እኔን ነዉ የሚያዩት ...በጣም ነዉ የገረማቸዉ ያልጠበቁት ተአምር ነዉ የሆነባቸዉ፡፡ ከትምህርት ቤታችን ቁጥር አንድ በፋሽን ልብስ ዘናጭ የተባልኩኝ ተማሪ ዛሬ ጅልባብ ለብሼ ከች ስል ሁሉም ገርሞት መልኬ እስከሚገፍ ተመለከቱኝ ግን እኔን ደፍሮ ለመናገር የሞከረ የለም ዝም አሉኝ

  መፍቱሀ ከሩቁ አየችኝ ፊቷ በደስታ የሚያበራ ይመስላል ..ከተቀመጠችበት ቁማ ጠበቀችኝ እሷ ጋር ስደርስ ነዋልየ ወላሂ ለአላህ ብየ እወድሻለሁ ዛሬ ደግሞ በጣም አስደሰትሽኝ ብላ በደስታ እቅፍ አድርጋ ሳመችኝ....ደስታዋን የምገልፅበት ቃላት አጠራት የደስታ እምባ እያነባች በለበሰችዉ ክሪም እምባዋን ትጠርግና አይን አይኔን ታየኛለች መልሳ እቅፏ ዉስጥ ታስገባኝ እና ትስመኛለች፡፡ ነዋልየ አኮራሽኝ ወላሂ እንዴት እንዳስደሰትሽኝ ...አላህ ሁሌም ያስደስትሽ ነዋልየ ወላሂ እንዴት እንዳማረብሽ ልነግርሽ አልችልም፡፡ ደስታየን አንድ ቀን ብቻ እንዳታደርጊዉ ነገም ለብሰሽ እንድመጪ አንድ ቀን ብቻ ለብሰሽ እንዳታወልቂዉ አለችኝ
......እኔም እሺ መፍቱሀ ኢንሻ አላህ አለብሳለሁ አልኳት፡፡ ክላስ ገብተን ተምረን ወደ ቤታችን ተለያየን፡፡

እድሜ ለሰጠዉ ሰዉ ወደ ሞት እየተጓዝን ቢሆንም ከቀናችን አንድ ቀን ለመቀነስ መንጋቱ አይቀርም..ይሄዉ ዛሬም ነጋ ..እንደትናቱ ጅልባቤን ለብሼ ወደ ኮሌጅ አመራሁኝ ...እዛም እንደ ደረስኩ የትምህርት ቤት ልጆች እንደትናትናዉ ለመናገር አልፈሩም ..የብዙ ሰዉ አስተያየት ተቀበልኩ፡፡ የሚገርማችሁ ክርስቲያን የሆኑ የኛ ክላስ ልጆችና ትምህርት ቤት የምግባባቸዉም የማልግባባቸዉም ነዋል ይሄ አለባብስ አምሮብሻል አታዉልቂዉ .....ትናንት ለብሰሽዉ ስናይሽ ለአንድ ቀን ብቻ የለበሽዉ መስሎን ነበር የሁሌም ልብስሽ ብታደርጊዉ ያምርብሻል አሉኝ፡፡
ብዝዎቹ ክርስቲያን የክላስ ልጆችም ነዋል አንቺ ቀይ ስለሆንሽ በጥቁር ጅልባብ ከሁሉም ሴቶች አንቺ ላይ አምሮብሻል አሉኝ ፡

አስተያየት ከሰጡኝ ሁሉም ክርስቲያኖች 100% እንደአማረብኝ አታዉልቂዉ አምሮብሻል ብለዉ መሰከሩልኝ ፡፡ እዉነታቸዉን ነዉ አልተሳሳቱም መልኬ በጣም ቀይ ነኝ ጥቁር ጅልባቡ ሲጨመርበት ምንም የማይሳነዉ ጀሊሉ አምጥቶ ዉበቱን ደፋብኝ..

ብሩክታይትም ደስ ብሏት ማርያምን አምሮብሻል እንዳታወልቂ አለችኝ፡፡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶቼም ማሻ አላህ አሉኝ በጣም ደስታ ተሰማኝ፡፡

ደግሞ በተዘዋዋሪ ሙስሊም ሁነዉ ፋሽን ተከታይ ሴቶች  ደግሞ ምን ሁነሽ ጅልባብ ለበሽ?? አንቺ ገና ነሽ ወጣት ነሽ እንደ በፊቱ ብዘንጪ ነዉ የሚያምርብሽ እያሉ በለበስኩት ጅልባብ አንቋሸሹብኝ ወላሂል አዚም በጣም ተአጀብኩኝ ሙስሊሞቹ ከሰጡኝ አስተያየት 35% መልበሴን የተቃወሙ ናቸዉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚያመለክተዉ ዲነል ኢስላም ላይ ገና አለመሰራቱ እና ሙስሊም ናቸዉ እንጂ ኢስላም ሀይማኖት ምን እንደሆነ ገና የሚቀረን ማህበረሰቦች ነን ያለነዉ ማለት ነዉ...አሁን ላይ በእንደዚህ ያሉ የሀይማኖት ተከታዮች ተተብትቦ ዲነል ኢስላም የምናሰድበዉ ፡፡ ዲነል ኢስላም መመዘን ያለበት በሀይማኖቱ ዉብነት ለሰዉ ልጅ ፍትህ እንደሆነ እንጂ በዲነል ኢስላም አንዳንድ ተከታዮቹ ኢስላም ቢፈተሽ አንድም ሰዉ ወደ ኢስላም ባልገባ ነበር..ግን ምን ይደረጋል ዲነል ኢስላም በአንተም በአንቺም በእሱም በእሷም በእነሱም በእነዛም የሚመዘን አይደለም ሀቅ በያዙ ደጋግ አቢድ ሷሊህ በሆኑ ባርያዎቹ እንጂ፡፡

ክርሰቲያኖች በመንገድ የሚያገኙኝ አድንቀዉኝ ሙስሊሞቹ እንደዚህ ሲያንቋሽሹኝ በእኔ ሳይሆን ሙስሊም ሁነዉ እንደዚህ በማሰባቸዉ አፈርኩባቸዉ፡፡
      የቱርክ የቻይና የዱባይ ፋሽን ተብየ ልብስ መልበስ ትቼ ጅልባብ ብቻ መልበስ
ጀመርኩኝ....,ልብስም ከገዛሁ የምገዛዉ የተለያዩ ጅልባቦች በተለያዩ ከለሮች እና የጅልባብ ማላበሻ ክሪም ብቻ ሆነ፡፡

አንድ ቀን እኔና ብሩክቲ አንድ ላይ ቁመን
አንድ ወንድ ክርስቲያን የክፍላችን ልጅ እኔ እና ብሩክቲን መጥቶ ሰላም አለን.... ወንድ ልጅ ጋር መጨባበጥ ሀራም እንደሆነ አቃለሁኝ ግን እሱን እንዳይደብረዉ ብየ ነበር ሰላም ያልኩት
...... ብሩክቲም እንዴት ወንድ ሰላም ትያለሽ ?? መፍቱሀ የአጂ ነብይን እጅ የጨበጠ ጀሀነም እሳትን እንደጨበጠ ነዉ ስትል ሰምቻታለሁ እንዴት ትጨብጫለሽ ? ደግም ከአሁን ቡሀላ ጅልባብ ለብሰሻል ወንድ ልጅ መጨበጥም አቁሚ አለችኝ ክርስቲያን ጓደኛየ ብሩክቲ
....እኔም እሺ ልክ ነሽ ብሩክቲ አልኳት ፡፡ በጣም አፈርኩኝ ብሩክቲ ክርስቲያን ሁና ስለ ኢስላም አዉቃ እኔ እንዴት እያወኩኝ መተግበር አቃተኝ ?? እንዴት አጂ ነብይ መጨበጥ ሀራም መሆኑን እያወኩ እንዴት ሰላም እላለሁ ?? ከአሁን ቡሀላ ወንድን ልጅ ማንም ይሁን ማንም ሰላም ላልል ለራሴ ቃል ገባሁ

   መፍቱሀ ከትምህርት ሰአት ዉጭ መርከዝ ገብተሽ ተማሪ አለችኝ.....
... እኔም መርሀባ በማለት ጅሬን ሰፈር የሚገኘዉ አባጅፋር መርከዝ ተመዘገብኩኝ ቁርአኔን ሙራጅአ ማድረግ ጀመሬ ብዙም ሳልቆይ ጨረስኩኝ ኪታብ መቅራትም ጀመርኩኝ በኡስሉሰላሳ ጀመርኩኝ በሉገል መራም ሌላ ኪታቦች እዛዉ ቀራሁኝ ....ሰአት እያመቻቸሁ ሌላ ቦታ ሪያደሷሊህን መቅራት ጀመርኩኝ.....እኛ ሰፈር ያለዉ አጂፕ መስጊድ ሰአት እያመቻቸሁ ቁርአን ተፍሲር መቅራት ተያይዠዋለሁ፡፡
የመፍቱሀ ግፊት ለኔ በሒወቴ መስመር የያዝኩበት ኪታብ የቀራሁበት ዲነል ኢስላምን ያወኩበት ነዉ ...መፍቱሀ ለኔ ሁለ ነገሬ ናት
#የትአሉ_ለአላህ_ብለዉ_የተዋደዱ!!!!!"
መፍቱሀን አላህ የሰጠኝ ለሂድያ ስበብ የሆነችኝ የጨለመዉን ሒወቴን መብራት ያበራችልኝ ናት

★★★★ባልደረባክን ጓደኛክን ምረጥ ……
ተወዳጁ ነብያችን ﷺ በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ:-
ሰውየው ሀይማኖት በጓደኛው ላይ ነው አንድኛችሁ ባልደረባ አድርጎ ወደያዘው ሰውዬ ይመልከት

>>>አሏህ ይዘንላቸውና ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ:- የኸይር ባልተቤቶች የሆኑትን ሰዎች ጓደኛ አድርገክ በመያዝ ጓጓ ትኩረት አድርግ መልካም ጓደኞች በጠመምክ ጊዜ ይመሩካል፣ በተሳሳትክ ጊዜ ያቀኑካል፣ አሏህን በረሳክ ጊዜ ያስታውሱካል፣ ጃሂል ( መሀይም) በሆንክ ጊዜ ያስተምሩካል።ብለዋል
1.6K viewsedited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 06:31:21 ልቧ ባይቆሽሽ አትራቆትም ነበር ከሂጃብ መራቆቷ ራሱ የወንጀል መብዛት አንዱ ምልክት ነው ሸይጧን ሴትን ልጅ ወንጀል እንድታበዛና እንድትሰራ ይገፋፋታል ከዛ በኋላ ግን ከሂጃቧ እንድትገፈፍና ክብር እንዳይኖራትና በባለጌዎች እንድትደፈርና እንደ ቀላል እንድትታይ ያደርጋል፡፡ ሒጃቧን በአግባቡ የምትለብስ ሴት ግን ሁሉም ዘንድ ክብር አላት ባለጌዎች ዘንድም ክብር አላት እሷን ቀና ብለው እንኳን አያዩዋትም መልካም ሰዎች ዘንድም ልዩ ክብር አላት።

⇘ሒጃብ ኢማን ነው ኢማን ማለት:– በልብ ማመን በምላስ መናገር በአካል መተግበር ነውና።
አንዳንዶች ካሉበት ሸሪዓን የሚቃረን ተግባር እንዲመለሱ ሲነገራቸው ኢማን በልብ ነው ልቤን ከፍተህ አይተሀል? እያሉ የውሸት ቅንብራቸውን ስያቀናብሩ ይስተዋላሉ። ጥያቄ አለኝ ልባችሁ ካመነበት ተግባራችሁ ሊመሰክር ምን ከለከላችሁ? ለአላህ ግን መዋሸት አይቻልም! ለማነኛውም ኢማን ሶስት ክፍሎች አሉት ከነዛ ውስጥ ምንም ማጉደል አይቻል ታዲያ 3ኛው በአካል መተግበር ነውና ተግብሪ ሒጃብሽን ጠብቂ አንቺ ሒጃብ ብለሽ የምትጠሪው በወገብሽ ልክ አጣብቀሽ የሰዉነት ክፍልሽን የሚያሳይ አድርገሽ ከሴቶች ሱሪ ከሚለብሱት የማይሻል አድርገሽ የምታሰሪዉ ሳይሆን ኢስላም/ሸሪዓ ሒጃብ ብሎ ያስቀመጠልሽን ሒጃብ ነው የምልሽ።

⇘ሒጃብ የህፍረተ–ገላ መደበቂያ ነው። ሴት ልጅ ደግሞ መላ ሰውነቷ ህፍረተ–ገላ ነውና መላ ሰውነቷን ልትሸፍነው ይገባታል!! አንዳንድ (ፈቂህ መስለው ሙተፈቂሆች) ስለ ዲኑ ሳይገነዘቡ የተገነዘቡ የሚመስሉ ሰዎች እና ሴትን ልጅ ልቅ እንድትሆን ከአጂ ነብይ ጋር እንደፈለገች እንድትተራመስ ኢስላምን ታኮ የመጣ ኢስላም መስሎ ኢስላምን የሚያዳክም ሊያጠፋ የመጣ የአህባሽ አስተምሮን ይመስል አይ እጅና ፊት እንኳን ሱና ነው ኪላፍ አለበት ምናምን… የሚሉትን ተረታቸውን ትተሽ አንቺ ለአላህ ብለሽ ተቃራኒ ፆታዎችን ላለ መወስወስ ብለሽ መላ ሰውነትሽን ልትሸፋፈኚ ይገባል።

⇘ሒጃብ የሼመኝነት ምልክት ነው። የሴት ልጅ ተፈጥሮ ሼመኝነት ነውና ተፈጥሮን ጥለሽ ሌላን ለመሆን መሞከር አደጋው የከፋ ነው።
ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሴት ሁና በወንድ የምትመሳሰልና ወንድ ሁኖ በሴት የመመሳሰልን አላህ ረግሟቸዋል ብለዋል። ልብ በይ እህቴ የአላህ እርግማን ነው ያለበት!

⇘ሒጃብ መልካም የሆነች አማኝ ሴት በህሪ ነው። አላህ ይጠብቅሽና እህቴ የዚህ ተቃራኒ መሆንሽ ምንኛ የከፋ ነው? መልሱን ቆም ብለሽ እንድትመልሺው ለአንቺው ተውኩት


       አንድ ኡስታዝ ደአዋ እያደረገ.. የተለያዩ ሀይማኖቶች ስብከታቸዉን እያካሄዱ ሙስሊሙ ተዳክሟል ምን ይሻላል? ተብሎ ተጠይቆ እንዲህ ብሎ መልሷል ፡-እኔ ግን የሚያሳስበኝ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሌሎች ስብከት ሌላን ሀይማኖት ይከተላል የሚለው ጉዳይ ሳይሆን በስሜት ተከታይነት ይጠፋል የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ ብሏል፡፡
⇘አዎን! በትክክል ተጨባጩም የሚያስገነዝበው ይህን ነው
በአሁኑ ሰዓት ስለ ዲኑ ጠንቅቆ የሚያውቀው በጣም አናሳ ነው በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አብዘሀኛው ማለት በሚያስችል መልኩ ትንሽ ያውቃል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበትም አላህ ያዘነለት ሲቀር የስሜቱ ተከታይ ነው በስሜት ተከታይነት ሀራሙ እንደ ሀላል ተቆጥሮዋል በስሜት ተከታይነት ሱና ቢድዓ ይደረጋል ቢድዓ ደግሞ በተቃራኒው እንደ ሱና ይታያል በስሜት ተከታይነት ሽርክ እንደ ተውሂድ የሚቆጠርበት ቦታም አለ… ሌላም ሌላም
ይህንኑ የሚያበረታቱና ባለ በሌለ ሀይላቸው የሚያስፋፉ የሸይጧን ወዳጆች ደግሞ በዛው ልክ በዝተዋሉ!

ልብ በይ እህቴ!!!!! አንቺ የህብረተሰቡ መሰረት ነሽ አንቺ ከተበላሸሽ ይህ ህብረተሰብ ይበላሻል አንቺ ከተስተካከልሽና ከለማሽ ህበረተሰቡም ይስተካከላል አንቺን ለማጥመምና ከተፈጥሮሽ ለማውጣት ከሂጃብሽ ለማላቀቅ ከአላህና ከመልዕክተኛውﷺ ተከታይነት አስወጥተው የሸይጧንና የስሜትሽ ተከታይ ሆነሽ የጀሀነምን ገደል ገብተሽ ህብረተሰቡንም ወደ ጀሀነም ገደል እንድታስገቢ ሸይጧንና የሸይጧን ወዳጆች የሚያደርጉትን ጥረት አውቀሽ ለእነሱ አላማ የሚመቻቸውን አካሂድ እርግፍ አድርሽ ትተሽ ወደ አላህ ተመልሰሽ ሒጃብሽን ጠብቀሽ ስለ ዲንሽ ተምረሽ አውቀሽ ተግብረሽ ምርጥ ትውልዶችን የጀነት ሙሹሮችን አፍሪ
ይህቺ አለም እያየሻት ነው አጭርናትና ለዘላለማዊ አለም ጥሩ ስንቅ ሰንቂ።



       እኔም ጅልባቡን ልልበስ አልልበስ እያልኩ ለብቻየ ሳመነታ ዉሳኔየ ሲምታታብኝ ለመፍቱሀ ደዉየ ጅልባቡን ለብሼ ልመጣ ነበር የሰዉ አይን ማየት እና ሰዉ ምን ይሉኛል ብየ ፈራሁ ምን ይሻለኛል?? አልኳት
......መፍቱሀም ነዋልየ አንቺ የምፈሪዉ አላህን ከሆነ ጅልባቡን እንደለበሽ ሳታወልቂ ነይ ... አንቺንም እኔንም እነሱንም የፈጠረንን አላህን ብቻ ፍሪ አላህን ካልፈራሽ ማንን ትፈሪያለሽ ??...ግን ሰዉ ከሆነ የምፈሪዉ ቀይረሽዉ ትመጫለሽ ማለት ነዉ..ለሰዉ በጭራሽ እንዳትጨነቂ ....ማንንም እንዳፈሪ ጅልባቡን ሳታወልቂ ለብሰሽዉ ነይ አለችኝ........

ነዋል ጅልባቡን ትለብሰዉ ይሆን???

#ክፍል

ይ........ቀ ......
.....ጥ.........ላ........ል


JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
           `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•
1.6K viewsedited  03:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 06:30:35 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ሶስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ




ቅዳሜ ደረሰ መፍቱሀ ጋር አብሬ ሬፍት ቫሊ ኮሌጅ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ ዓሊይ መስጊድ ጀመአቸዉ የሚገናኙበት ሄድኩኝ.....

ዓሊይ መስጊድ ደረስን የሴቱ ጀመአ በጣም ብዙ ናቸዉ
.....መፍቱሀም አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ ዉድ የኢስላም እህቶቼ ዛሬ አንድ እህታችን መጥታለች ስሟም ነዋል ትባላለች ብላ ከሁሉም ጋር በአንዴ አስተዋወቀችኝ፡፡ ደስ የሚሉ ጀመአዎች ነበሩ ሲጀመር እኔም በባህሪየ ሰዉ ጋር መቀራረብ ሰዉ ጋር መላመድ ችግር የለብኝም ..ሁሉም ጋር ብዙም ቀን ሳይፈጅብኝ ተግባባን፡፡


መፍቱሀም፡- ሁሌ ቅዳሜ መቅረት አይቻልም የጀመአዉ አባል ተብለሽ ተመዝግበሻል አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ እመጣለሁ አልኩኝ..
    መፍቱሀ ጋር ወደ ቤት እየተመለስን ግን የወደፊት አላማሽ ምንድን ነዉ ?? ለወንድ ልጅ ያለሽ አመለካከትስ እንዴት ነዉ ?? አለችኝ
.....እኔም ወንድ ልጅን በፍቅር አልቀርብም አላህ ባለቀን boyfrind ሳልይዝ እኔን ከማንነቴ ተቀብሎኝ ቀጥታ ቤተሰብ የሚጠይቅ ነዉ የምፈልገዉ ..እኔ በዘንድሮ ፍቅር አላምንም አልኳት
...መፍቱሀም ማሻ አላህ ወላሂ የኔም ሀሳብ እንደዚሁ ነዉ የኔ ሀላል ባሌ የምፈልገዉ እኔን በቻት በተለያዩ መህበራዊ ሚዲያ ሳይጀነጅነኝ በመስኮት ሳይሆን በበር የሚገባ ለቤተሰቦቼ የሚያሳዉቅ ነዉ የምፈልገዉ አለችኝ ፡፡ሁሌ ተገናኝተን ስለፍቅር ስለትዳር ካወራን አስተሳሰባችን አንድ አይነት ነዉ፡፡

መፍቱሀ ጋር ከምነግራችሁ በላይ በጣም እንዋዳደላለን ከጓደኛ በላይ እንደ እህት ነዉ የማያት ...ጓደኝነታችን በጣም ቅርርብ ስላለን ብቻየን እኔ ከሄድኩ ወይ መፍቱሀ ብቻዋን ከሄደች ምነዉ ጓደኛሽ ዛሬ የለችም ወይ?..ወይ እሷን ነዋል ዛሬ የለችም ወይ ?ብለዉ ይጠይቁናል.. ብዙ ጊዜ በጀመአም በስብሰባም በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የሆነ ጥያቄ ሀሳብ ካስፈለገ የእኔና የእሷ ሀሳብ ሁሌም አንድ ነዉ፡፡ እኔ የሆነ ነገር ሳስብ እሷም አስባዉ አገኛታለሁ..የሆነ ኸይር ስራ ለመስራት ሳስብ ላማክራት ስል ወይ እሷ ትቀድመኛለች ወይ ስነግራት እሷም እንደ አሰበችዉ ትነግረኛለች ..እሷም የሆነ ሀሳብ ስታማክረኝ እኔም የአሰብኩት ሀሳብ ሁኖ አገኘዋለሁ....ከአካል አልፎ ልባችን ለራሱ ጓደኝነት ፈጥሯል..ሰዉ ብዙ ጓደኛ አለዉ  ..በጣት የሚቆጠር የልብ ጓደኛ የሚለዉ አለ ነገር ግን ጭራሽ ልብ ለልብ አይገናኙም ጭራሽ የሆድህን ለማስረዳት ጓደኛም ለመረዳት ሳይቻል ይስተዋላል..ይሄ ገና ጓደኝነቱ ብዙ ይቀረዋል ማለት ነዉ፡፡ ለምን ጓደኝነት በሀሳብ ገና ፊትህን አንብቦ የልብህን የሚያቅ ሲሆን ነዉ፡፡ የሚገርማችሁ አመናችሁም አላመናችሁም ያዉ በአላህ ፍቃዴ እኔና መፍቱሀ የወር አበባ ለራሱ የምናይበት ቀን ድረስ የተመሳሰለ ነበር...ብዙ ቀናቶች እኔ ታምሜ ሀኪም ቤት ስሄድ እሷም ትታመም ነበር...አንድ ሀኪም ሙድ ይይዝብን ነበር ዛሬ ጓደኛሽ አልታመመችም ወይ እስከ ማለት ደርሰዉ ነበር..ይሄን ያህል ድረስ ነበር የኔና የመፍቱሀ ልብ ለልብ ጓደኝነታችን


አንድ ቀን መፍቱሀ በስጦታ መሸፈኛ የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ
...የተጠቀለለዉን ስከፍተዉ ኪታብ ነበር ...እኔም ደስ ብሎኝ አብረን ኪታብ መቅራት ጀመርኩኝ ..ለሒወቴ ትልቅ ለዉጥ እያመጣችልኝ ነዉ፡፡

ደግሞ በሌላ ቀን መፍቱሀ በስጦታ የተጠቀለለ ነገር ሰጠችኝ
...መፍቱሀ የተጠቀለለ ነገር ከሰጠችኝ ለኔ አስፈላጊ በጣም የሚጠቅም ነገር እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለዉም
....እኔም ምንድን ነዉ ?? አልኳት
.......እሷም የዛሬዉ ስጦታ እቤትሽ ሒደሽ አይተሽዉ ከዛ ትደዉይልኛለሽ አለችኝ
.....እኔም የሰጠችኝን ስጦታ እስከማየዉ እየቸኮልኩኝ እቤቴ ደረስኩኝ
........የስጦታ ወረቀቱን ስፈታዉ ጥቁር ጅልባብ ነዉ፡፡
እኔም ወደ መፍቱሀ ደዉየ ጅልባቡን ወድጀዋለሁ አላህ ይስጥልኝ አልኳት
.......እሷም ነዋል ......ልበሽዉ እና በመስታወት አንቺ ጋር እንዴት እንደሚያምር ተመልከቺዉ ከዛም ዛሬ የዙሁርን ሶላት ስገጂበት...ሰግደሽበት በጣም ትወጅዋለሽ እርግጠኛ ነኝ ትሞህርት ቤት ለብሼዉ እመጣለሁ ነዉ የምትይዉ አለችኝ

እኔም መፍቱሀ እንዳለችኝ ጅልባቡን ለብሼ በመስታወት ሳየዉ በጣም ነዉ ያማረብኝ ....መፍቱሀ እንዳለችኝ ጅልባቡን ለብሼ ዙሁሩን ሰግጄ ጨርሼ ሳሰላምት አባቴ ከሆላየ ቁማል

...አባቴም ዛሬ በሰላም ነዉ እቤት የመጠሀዉ?? አልኩት
አባቴም የምፈልገዉ እቃ ነበር ጠዋት እረስቼዉ አሁን ልወስድ ነዉ .....ነዋል ጅልባቡን መቼ ገዝተሽዉ ነዉ ??? ነዋልየ የኔ ልጅ ወላሂ እንደዚህ አምሮብሽ አይቸሽ አላቅም ወደ ቤት ስገባ ጅልባብ ለብሰሽ ስሰግጂ እንዴት ደስ እንዳለኝ ከምነግርሽ በላይ ነዉ ደስታየን መቆጣጠር አቅቶኝ የደስታ እምባ አነባሁ፡፡ ነዋል አምሮብሻል አታዉልቂዉ አለኝ፡፡
....እኔም ጓደኛየ ስጦታ ሰጥታኝ ነዉ አባቢ አልኩት
.......አባቴም ጥሩ ጓደኛሽ ናት፡፡ ለወደፊትም እሷን ጓደኛ አርገሽ ያዢ ብሎ ከአንጀቱ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ ዱአ አደረገላት...ነዋል ሲመቸኝ ጓደኛሽን ታስተዋዉቂኛለሽ አለኝ አባቴ
...,,,እኔም እሺ አስተዋዉቅሀለሁ አልኩት ...አባቴም የረሳዉን እቃ ይዞ፡ከቤት ወጥቶ ሄደ
  

እኔም አምሮብኛል ማለት ነዉ ??ብየ መልሼ መልኬ እስከሚገፍ መስተዋት ላይ አፈጠጥኩኝ፡፡

ዛሬ  ከሰአት ክላስ አለን ጅልባቡን ለብሼዉ ልሂድ ወይስ አልሄድ ??ጅልባብ ስለብስ የመጀመሪያየ ነዉ ሰዉ ምን ይለኛል ??? እያልኩ ብቻየን እያሰብኩ መልበሱን ፈራሁ

★★★ በዲነል ኢስላም ሀይማኖት ዉስጥ እምነት የሚለዉ ቃል በአረበኛ ትርጉሙ ሲፈታ አንድን ነገር እዉነት ብሎ መቀበል ሲሆን ኢስላማዊ ትርጉሙና ትንታኔ ግን ሰፊ ቢሆንም የኢስላም ሊቃዉንቶች በአጭሩ ሲያስቀምጡት እንዲህ ይላሉ አል አሚኑ ማወቀረ ፊል ቀልብ ወሰደቀሁል አመል ..ትርጉሙም፡-እምነት ማለት በልብ ወስጥ ተደላድሎ የተቀመጠ እና ስራ ወይም ተግባር ያረጋገጠዉ ነዉ በማለት ይገልፁታል፡፡ ሌሎች የኢስላም ሙሁራን እምነትን ሲገልፁ በልባችን (በቀልባችን)እዉነት ነዉ ብለን የምንቀበለዉ..በምላሳችን ሙሉ ፍቃደኝነት የምንናገረዉ እና በሰዉነት አካላችን የምንተገብረዉ ነገር ነዉ...በማለት ይገልፁታል ፡፡እኔም ታዳ ጅልባብ መልበስ ሰዉ ምን ይለኛል ብየ ከፈራሁ እምነቴ ላይ ችግር አለ ሀይማኖቴ ከልቤ ሳይገባ ተደላድሎ አልተቀመጠም ማለት ነዉ::

ለኔ ጅልባብ መሸፈኛየ መከበሪያየ ነዉ፡፡
ምን ያህል ስለ ሒጃብ ጥቅሞች እናዉቃለን???

★★★ ሒጃብ ለአላህና ለመልዕክተኛው መታዘዝ እንጂ የሆነ ሀገር ባህል ተከታይነት አይደለም።

ሒጃብ ጥብቅነትና ንፅህና ነው። ሒጃብን የማትለብስና
ከሂጃብ የተራቆተች እንስት ሁለት ነገሩዋ ቆሽሿል ፡፡ አንዱ ንፁህ ቢሆን እንኳን አንዱ ንፁህ አይሆንም አንደኛ ልቧ ቆሽሿል ፡፡ ሁለተኛ ሸይጧን አሳስቷት ሰውነቷን በተለያየ ወንጀል አቆሸዋለች በዝሙትና በተለያየ ነገር ሰውነቷን አጨማልቃው ሊሆን ይመቻል የሚፀዳው ሒጃቧን ለብሳ ክብሩዋን ጠብቃ ጥንቁቅ ሆና ወደ ጌታዋ ቁሩጥ ያለን መመለስ ስትመለስ ብቻ ነው!!!
1.6K views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 06:08:33 አንድ ቀን እረፍት ሰአት ላይ ቁጭ ብየ ብቻየን እያሰብኩ ናርዶስ የምትባል የክፍላችን ልጅ ...ወደ እኔ መጥታ ከጎኔ ቁጭ አለች.......
.....ናርዶስም ነዋል በሰላም ነዉ ብቻሽን ቁጭ ያልሽዉ ?? አለችኝ
.......እኔም አዎ በሰላም ነዉ ከይቅርታ ጋር ብቻየን መሆን ፈልጌ ነዉ ናርዶስ ብቻየን እንደሆን ፍቀጅልኝ ......የምፈልጊኝ ከሆነ ክፍል ስንገባ እንገናኛለን አልኳት
......እሺ ነዋል አንድ ነገር ብቻ እንድናገር ፍቀጅልኝ ብቸኝነት አታብዢ አትጨናነቂ የሰዉ ወሬ እንደሆነ መቼም አያልቅም የዘንድሮ ሰዉ እንዳያወራ አፉን ቢዘጉት በቂጡ ማዉራቱ አይቀርም.....ከአንቺ የባሰ ሒወት የሚኖሩ አሉ እኮ የኔ ተመስገን የተሻለ ነዉ ያስብላል አንቺም ልትይ ትችያለሽ......ስለሆነም አንቺ ስታለቅሺ ስትተክዢ ማየት አልፈልግም ...ለምን ብትይ አንቺ ለኔ ጥንካሬ ብርታት እንድትሆኚኝ እፈልጋለሁ ነዋል አለችኝ
........እኔም ግራ ገባኝ ከአሁን በፊት ናርዶስ ጋር ብዙም አንግባባም ከክፍል ጓደኝነት ዉጭ.....ሚስጥር አዉርታኝም አዉርቻትም አታቅም አላዉቅም ......ናርዶስ የክርስቲያን ሀይማኖት ተከታይ ናት """ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ?? አልገባኝም"""አልኳት
.......ናርዶስም፡- ቅዳሜ ከሰአት ብንገናኝ በሰፊዉ ላወራሽ እችላለሁ ይመችሻል ??? አለችኝ
........እኔም አዎ ይመቸኛል አልኳት......
ናርዶስም እሺ ቅዳሜ 10 ሰአት ላይ ዶሎሎ ሆቴል መናሀሪያ አካባቢ እንገናኝ አለችኝ
.....እኔም እሺ እንገናኛለን አልኳት፡፡ ከዛም እረፍት ሰአት አልቆ  ተደዉሎ ወደ ክላስ ገባን....

ናርዶስ ያለችኝ ነገር በጣም ግራ ገባኝ በአእምሮየ እየደጋገምኩ ማብሰልሰል ጀመርኩ""" ከአንቺ የባሰ ሒወት የሚኖሩ አሉ እኮ የኔ ተመስገን የተሻለ ነዉ ያስብላል አንቺም ልትይ ትችያለሽ......ስለሆነም አንቺ ስታለቅሺ ስትከዢ ማየት አልፈልግም ...""" እንዴት እንዲህ ልትለኝ ቻለች???? እያልኩ ብቻየን ማሰብ ይዣለሁ.........

የተቀጣጠርንበት ቀን ቅዳሜ ደረሰ በተባባልነዉ በ10 ሰአት ስሄድ ናርዶስ ጋር ጅማ የሚገኘዉ ዳሎል ሆቴል ተገናኘን ...ከዛም ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ ወንበር ይዘን ተቀምጠን
የሚጠጣ አዘን አንዳንድ ወሬ ካወረን ቡሀላ ....>>>>>ምንድን ነበር የምነግሪኝ ናርዶስ??? አልኳት
.....ናርዶስም አደራ የምነግርሽ ቤተሰቦች ወንድሜም እህቴም እናት እና አባቴ የማያቁት ሚስጥር ነዉ......የምናቀዉ  ፈጣሪ  እኔ እና ከዛሬ ጀምሮ ደግሞ አንቺ ነሽ...ስለሆነም ሚስጥራችን እዚሁ ይቅር አለችኝ
..........ከዛም እሺ ናርዶስ ለማንም አላወራም ብየ ቃል ገባሁ
>>>>>>>>_ናርዶስም ወደ መሬት አጎንብሳ የምታወጣቸዉን ቃላቶች ከየት ልጀምር እያለች እንደ ምጥ ከብዷታል.......ምን መሰለሽ ነዋል እኔ በልጅነቴ ....................___


#ክፍል
ይ...........ቀ........
.........ጥ.........ላ.............ል


Join

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFXIlKIXVySUTDcA
941 viewsedited  03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 06:08:33 አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አምስት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ


ኡስሚ አንዳንዴ እየቀለደ ነዋል አፈቅርሻለሁ እኮ ምናምን ሲለኝ እዉነት እየመሰለኝ ልቤ ድንግጥ ይላል ወይ የልጅነት ፍቅር ...
ሴትን ልጅ ሁለት ቃላቶች ላይ ልባቸዉ ይንጠለጠላል አንደኛዉ፡-እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ የሚባለዉን ቃል ሲሰሙ እዉነትም ይሁን ዉሸት ልባቸዉ ይሰረቃል ሁለተኛዉ ደግሞ በመንገድ ላይ እየሄዱ ቅናሽ እቃ ይሄቃ በዚህ ዋጋ ነበር አሁን ቀንሶ በዚህ ዋጋ ሲባል ከሰሙ አሁንም ልባቸዉ ይንጠለጠላል....
 
..የክላስ ልጆች ኡስማንና ነዋል ይዋደዳሉ ሲባል ደስ ይለኛል...ግን ኡስማን ይሄን ወሬ ሲሰማ በጣጣጣም ይቆጣል ይናደዳል ..ነዋልን ወላሂ የማያት እንደ እህቴ ነዉ በሌላ አይን አትዩን እያለ የክፍል ልጆች ጋር ብዙ ቀን ተጣልቷል
 
ኡስማን ጥፋት ሳጠፋ በጣም ይቆጣኛል... በአለባበሴም ቀን በቀን ምን ልብስ እንደለበስኩ ይከታተለኛል ሱሪ ለብሼ ስመጣ ስለሚቆጣኝ ሒጃብ መልበስ ክሪም መልበስ ኡስሚ እንዳይቆጣኝ እያልኩ በዛዉ ሂጃብና ክሪም መልበሱን ጀመርኩኝ .... ከትምህርት እንደተለቀቅን እቤታችን ደርሰን ሁሌም ቁርአን ቤት እንሄዳለን ፡፡ ኡስማንን እኔ ብወደዉም እሱ ግን እንደ እህት እንጂ ሌላ አስቦ በጭራሽ አያቅም ልቡን አሳምኖታል፡፡

ቁርአን ቤት እየሄድን ...ነዋል ቁርአን ማን ጋር ደረሽ??? ልታከትሚ ስንት ጁዝ ቀረሽ ?? ትናንትና ስንት ፊት ቀራሽ?? እያለ ቀን በቀን ይቆጣጠረኛል ...........ነዋል ነግሬሻለሁ ቶሎ አክትሚ እና የቁርአን ክትሚያ በግ አርደሽ አብሊን እያለ በጣም ይከታተለኛል ...ኡስሚ በጣም ጥሩ ልጅ ነዉ..እሱ በቁርአን ይበልጠኛል ነገር ግን እኔ እንደአክትም ይቆጣጠረኛል...
   ሶላት መስገድ የጀመርኩት በኡስማን ነዉ በፊት የምሰግደዉ በረመዷን ብቻ ነበር..የረመዷን ቃልቻ ነኝ ማለት ነዉ..

የአሁኑ ዘመን ፋሽን ተከታይ ነን ባዯች የአሁን ዘመን
እኛዉ ትዉልዶች ለሶላት ያለን አመለካከት በጣም ዝቅተኛ ነዉ

በፊት የነበሩ ምርጥ ትዉልዶች ለሶላት ያላቸዉ አመለካከት ምን ይመስላል ???እስኪ ከዓሊ (ረ.ዐ) እንጀምር

★★★ዓሊ(ረ.ዐ)እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር ፡-የምእመናን አዛዥ ሆይ! የሶላት ሰአት ሲቃረብ የፊትዎ ቀለም የሚቀያየረዉና የሚንቀጠቀጡት ለምንድን ነዉ ??
ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት መልስ ሰጡ """ይህ ሰአት ሰማያትና ምድር እንዲሁም ተራሮች ሊሸከሙት እንዳልቻሉ በመግለፅ ያልተቀበሉትን አደራ ወደ ባለቤቱ የመመለሻ ሰአት በመሆኑ ነዉ ፡፡እኔ በትክክል መቻሌን አለመቻሌን አላዉቅም

★★★የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የልጅ ልጅ የሆነዉ ሀሰን(ረ.ዐ) ምን ጊዜም ዉዱዕ ባደረገ ቁጥር ፊቱ ይገረጣ ነበር
አንድ ዕለት አንድ ሰዉ ሀሰን ሆይ!!! ዉዱዕ ባደረግክ ቁጥር ፊትህ የሚገረጣዉና ወደ ቢጫነት የሚቀየረዉ ለምንድን ነዉ ?? በማለት ጠየቀዉ
ሀሰን (ረ.ዐ) የሚከተለዉን መልስ ሰጠ፡- ብቸኛዉ የሀይል ባለቤት ታላቅና ባለግርማ ከሆነዉ አላህ ፊት የመቅረቢያ ሰአት  በመሆኑ ነዉ ""
ሀሰን(ረ.ዐ) ወደ መስጊድ ሲገባ የሚከተለዉን ዱአ ያደርግ ነበር፡-
ጠባቂየ ሆይ!!!! ባሪያህ በቤትህ ደጃፍ ላይ ደርሷል፡፡ምህረት ሁሉ በእጅህ የሆነዉ ሆይ!!! ሀጢያተኛዉ ባሪያህ ወደ አንተ መጥቷል ፡፡ ቅን ባሪያዎችህ ሌሎች ሰዎች የሰሩባቸዉን መጥፎ ነገር ይቅር እንዲሉ አዘሀል፡፡ ምክንያቱም አንተ ይቅር ባይና ቸር ነህ፡፡ አላህ ሆይ በተለመደዉ ይቅሬ ባይነትህና ምህረትህ በደሌን ይቅር በል .እዘንልኝም፡፡ ብለዉ ለሶላት ክብር ፍራቻ ነበራቸዉ እኛስ ??ብዙዎቻችን የመስጊድ ሙአዚን አዛን ሲል ሳንጠላዉ እንቀራለን ብላችሁ ነዉ?? ከኔ ጀምር ማን ነዉ አላህን ፈርቶ ሶላትን የሚሰግደዉ??? መልሱን ሁሉም በየቤቱ

       ትምህርት ቤት ሱሪ ለብሼ መምጣት ሙሉ በሙሉ አቁሚያለሁ .........ቤተሰቦቼ ሶላት ስገጅ አይሉኝም ፡፡ ኡስማን ግን ትምህርት ቤት እና ቁርአን ቤት ስንገናኝ ሶላት ሰገድሽ ወይ እያለ ይጠይቀኛል እኔም አንዳንዴ ሳልሰግድ ሰገድኩ እላለሁ ...ኡስማንም ወላሂ በይ እንዳትዋሺ ዉሸት ሀራም ነዉ ይለኛል...እኔም በቃ ሙሉ በሙሉ ሶላት መስገድ ጀመርኩኝ አልሀምዱሊላህ....... እንደዚህ ኡስማን ጋር አሳልፈን ስድስተኛ ክፍል ጨርሰን ክረምት ገባ
በክረምት ግን ኡስማን ጋር ቁርአን ቤት እንገናኛለን ፡፡ ግን ያዉ ቁጥጥሩ ቁርአን ቅሪ ሰገድሽ ወይ ነዉ......

ኡስሚም ቁርአን ሲከታተለኝ በእኔም ጥረት ቁርአኔን ስድስተኛ ክፍል እንዳለሁ አከተምኩኝ፡፡አልሀምዱሊላህ ቁርአን ሳከትም ቤታችን በግ ታርዶ ተሰድቆ ተበላ፡፡ ከዛም ምላሽ መቅራት ጀመርኩኝ፡፡

ክረምት አልቆ ለበጋ ለአዲስ አመት ጊዜዉ አስረከበ ሰባተኛ ክፍል ተመዘገብኩ ....የትምህርት ቤት ተማሪዎች ኡስማን እና ነዋል በጣም ይዋደዳሉ እየተባለ መወራቱ በሰፊዉ ሁኗል .......ፍቅር የጀመርን አስመስለዉታል ሁሉም ተማሪ ኡስማን እና ነዋል ይዋደዳሉ ነዉ የሚሉት እኔ እንደዚህ ሲወራ ደስ ይለኛል ....
........መቼም ሴት ነኝ እና ከብዙ ሴቶች ጋር ማዉራቴ አይቀርም ..አንድ ቀን ለትምህርት ቤት ጓጀኞቼ የሞቀ ወሬ ይዘን እያወራን ዉሸቴን ኡስማን እኮ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ እወድሻለሁ አለኝ ብየ ለሁሉም ነገርኳቸዉ....
....... ይሄ የዉሸት ወሬ ኡስማን ጆሮ ሳይዉል ሳያድር ደረሰ.....


ኡስማን ጋር ከትምህርት ቤት ተለቀን አብረን ስንሄድም ቁርአንቤትም ስንገናኝ የፍቅር ጥያቄ አቀረበልኝ ብለሻል እንዴ ??? ብሎ እንኳ አልጠየቀኝም ....እኔ ግን ዉሸት ስለሆነ በተናገርኩት ቃላት አፈርኩኝ ግን ኡስሚ ሰምቶ ባልሰማ አለፈዉ....
  
ኡስማን በልጅነቴ መደፈሬን ያቃል ..,የኛ ሰፈር ልጆች እኔ ጋርም የተጣሉት እሱ ጋር በጣም ይግባባሉ ፡ለምን እሱ ወንድም ሴትም ይቀርበዋል እንኳን ይሄን ብዙ ሚስጥር ይነግሩታል፡፡ የኔ በልጅነቴ መደፈር በትምህርት ቤት ሳይቀር የሚወራ ወሬ ነዉ፡፡ ለኔ ያለዉ አመለካከት ቀረቤታ ምንም ነገር አልቀነሰብኝም....ከወንድሜ በላይ አስበልጬ ነበር የምወደዉ ...የወደፊት የትዳር አጋሬ ቢሆን ዱአየ ነዉ፡፡ አላህ ያሳካልሽ በሉኝ

  
   ትምህርት እየተማርን አንድ ቀን የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ነዋል እኮ በልጅነቷ ተደፍራለች ድንግል አይደለችም እያሉ ወሬዉን እንደ አዲስ ሰበር ዜና አናፈሱት .....እኔም ይህን ወሬ በጆሮየ ስሰማ መናደድ ማልቀስ ሆነ ስራየ .............
ይሄን ሚስጥር ያልሰሙትም እየመጡ ይጠይቁኛል...ምን መልስ አለኝ ቀን በዝምታ ማታ ከማልቀስ ዉጭ... በዚህ ወሬ እየተደጋገመ ሲወራ የክፍል ጓደኞቼም የማቃቸዉ ልጆች ሳይቀር እየጠየቁኝ ስቸገር .. ክፍል ዉስጥ ተቀምጦ መማር  እያስጠላኝ ጥያቄዉን ሲጠይቁኝ በጣም ስናደድ ትምህሬን ቀጥቼ እወጣና እዛዉ ት/ቤት ግቢ ዉስጥ ብቻየን ቁጭ ብየ እንባየን በማፍሰስ መደፈሬን ለመርሳት እሞክራለሁ ግን የማይረሳ የማይፋቅ ክስተት መቀየር አይችል ምን ይደረጋል ወደ ሰማይ ቀጥ ብሎ አልቅሶ ወደ መሬት እምባ ከማፍሰስ በቀር..ትምህሬትንም በተረጋጋ መልኩ ልማር አልቻልኩም ..ትምህርት ቤት የምሄደዉ እቤት ለምን አትሄጂም እንዳልባል ብቻ ነዉ እንጂ ትምህርት ቤት ግቢዉ ክላስ እየቀጣሁ ብቻየን ማሳለፍ ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ
844 viewsedited  03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ