2022-09-08 10:25:45
አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
#ክፍል ☞ ሁለት
ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ
የቤት ሰራተኛችን እያለቀሰች እንዲህ አለችኝ፡- ነዋል አሁን ለአንቺ መንገር አልችልም ገና ልጅ ነሽ ....የወር አበባ ማየት ስጀምሪ የዛን ጊዜ እነግርሻለሁ እንድነግሪሽ አታጨናንቂኝ አለችኝ እያለቀሰች ፡፡
...እኔም መንገር ካልፈለክሽ አላስገድድሽም አትጨናነቂ አልኳት ፡፡
እሷን ማጨናነቅ አልፈለኩም.. በቤት ሰራተኛችንም አልፈረድም ለምን እኔ እና አባቴ በጣም እንቀራረባለን ይሄ ሚስጥር እሷ እንደነገረችኝ ከአወቀ አባቴ ጋር እንደሚጣሉ አቃለሁ .......
የሚገርማችሁ እኔ ሳድግ እቤት ጥሩ ኑሮ ብንኖርም ብር ብቻ ለሰዉ ልጅ ደስታን አይፈጥርም እናት እና አባቴ ሁሌ እንደተጣሉ እንደተጨቃጨቁ ነበር... በሰላም ሳይጣሉ ያደሩበትን ቀን መቁጠር ይቀላል፡፡ እኔ ታዳ ማታ ማታ በተጣሉ ቁጥር እኔ መጨነቅ መጠበብ ነዉ ስራየ..
ሁሌ ታዳ እናቴ አባቴን በነገር ስትወጋዉ ከሳሎን ተነስቶ ሌላ ክላስ ገብቶ ብቻዉን ቁጭ ይላል.....እኔም ለአባቴ እራቱን ይዤ ያለበት ክላስ እሄዳለሁ ... አባቴም ፀጉሬን እያሻሸ እንዲህ ይለኛል .....ነዋልየ የአይኔ ማረፊያ እናትሽ ጋር ብዙ ቀን ለመፋታት አስባለሁ ግን አንቺ ትዝ ትይኛለሽ እኔና እሷ ተፋተን አንቺ ስትሰቃይ አባቴን ወይ እናቴ ናፈቁኝ እያልሽ ስትሰቃይ በአይኔ እየታየኝ እንደገና እተወዋለሁ....እኛ ስንጣላ አትጨናነቂ መኝታ ክላስ ግቢ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ ነዋል ይለኛል፡፡
_እናቴ ደግሞ እንዲህ ትለኛለች.......በሂወቴ አንቺን ካረገዝኩ ጊዜ ጀምሮ አሁን ድረስ የተረገመ ሒወት ዉስጥ ነዉ የገባሁት ምነዉ ተወልደሽ ባልነበር ትለኛለች እየተናደደች ...
.......እናቴ ከምነግራችሁ በላይ በጣም ሀይለኛ ቁጡ ዉሀ ለምን ቀጠነ ብላ የምትጨቃጨቅ ...ለሰዉ በቀላሉ የማትመለስ ናት ፡፡ እኔን ለራሱ ስትናገረኝ ሁሌም ቢሆን ለኔ ክብር የላትም ቃላቶችን መጥና ከአፏ መወርወር አትችልም ... በተዘዋዋሪ ደግሞ አባቴ አስተዋይ እረጋ ያለ ነገሮችን በትግስት የሚያልፍ ለቤተሰቡ ክብር ያለዉ እና በተናደደ ሰአት ደግሞ ፊቱ ለመቅረብ የሚፈራ ቁጡ ሀይለኛ ነዉ ግን ለነገሮች ሁሉ አይቸኩልም ፡፡ አባቴ ትዳሩ እንዳይበተን ተረጋግቶ ይዞት ነዉ እንጂ እንደ እናቴ ሀይለኝነት ትዳሩ ፈራሽ ነዉ ፡፡
ትዳር ማለት የአንዱን ጎዶሎ አንዱ ይሞላል ማለት ይህ ነዉ፡፡ አባቴ የእናቴን ጎዶሎ እየሞላ ትዳራቸዉ እንዲቀጥል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
እናቴ ይሄን የነብዩ ሀዲስ የረሳችዉ ይመስለኛል
★★★ተወዳጁ የአላህ መልዕክተኛ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል ፡-በሚስት ላይ ያለባት ከባዱ ሀቅ የባሏ ሀቅ ነዉ..በወንድ ላይ ደግሞ ያለበት ከባዱ ሀቅ የእናትና አባቱ ሀቅ ነዉ..በማለት የባል ሀቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማሳየት ሞክረዋል..
ነብዩ ሰ.ዐ.ወ በሌላ ዘገባቸዉ ማንኛዉም ሴት ባሏ እርሷን እየወደዳት በርሷ ላይ ተደስቶ ከሞተች ጀነት ትገባለች...ብለዋል፡፡ እናትሽ ፀባዯን አላህ ያስተካክልልኝ ብላችሁ እስኪ ዱአ አድርጉልኝ
በትርፍ ሰአቱ ቁርአን ቤት እየሄድኩ ስቀራ ኡስማን ከሚባል ልጅ በፍቅር ወደኩኝ........በፍቅር ስል የሌላ እንዳታደርጉት በልጅነት ስናድግ በጣም የምንቀራረብ ልጆች ነን፡፡ አንድ ቁርአን ቤትና ትምህርት ቤት ነን
የኡስማን አባት እና እናት የመንግስት ሰራተኛ ናቸዉ .......ኡስማን አንድ እህት አለችዉ ... ቁርአን የሚያቀራን ሸህ ስለሚገርፉን መድረሳ እንገናኝና የኡስማን ቤተሰቦች እቤት ካሉ ቁርአን እንቀራለን ግን እቤት ከሌሉ ዛሬ የሉም ስራ ናቸዉ ከተባለ ቁርአናችንን መቅራት ትተን አሱር አዛን እስከሚል ድረስ እነ ኡስማን ቤት ሂደን ስንጫወት ስንደባደብ እንዉላለን ....አሱር አዛን ሲል እኔ ወደ ቤቴ ተመልሼ ቁርአን የቀራሁ መስየ እሄዳለሁ፡፡
ኡስማን ጋር ያዉ የልጅነት ነገር መጫወት መደባደብ እንጂ ሌላ ነገር የለም ግን የእቃቃ ባል ይባል የለ ....ኡስማን ጋር በልጅነታችን በጣምምም እንዋደዳለን፡፡
አባቴ ከትምህርት መልስ ቁርአን ቤት እንድቀራ የፈለገዉ የሰፈር ልጆች ጋር እንድቀራረብ ስለማይፈልግ ነዉ....ከሰፈር ልጅ ጋር አብሬ አላደኩም የወንድም የሴትም የሰፈር ልጅ ጓደኛ የለኝም፡፡ ለምን ያቺ ልጅ ከሰደበችኝ ቡሀላ ከሰፈር ልጆች ጋር እኔም መጫወት እየከበደኝ መጣ .....
አንዳንዴ ብቸኝነት ሊዉጠኝ ሲደርስ ልጆቹ ጋር ልጫወት ስቀርባቸዉ የሚጫወቱትን ጨዋታ ትተዉ ይነሱና እኔን ብቻየን ጥለዉኝ ይሄዳሉ
.....እኔም ስማቸዉን እየጠራሁ ለምን ትሄዳላችሁ??አብረን እንጫወት እንጂ ??? ስላቸዉ
..........እነሱም ቤተሰቦቻችን አንቺ ጋር እንዳንጫወት ከልክለዉናል አንቺ ጋር አንጫወትም እያሉኝ ጥለዉኝ ይሄዳሉ..........እኔ ለመጫወት ወደ ልጆቹ ሲሄድ እነሱም ይሸሹኛል ወይ ክፉ እድል.......
ከአሱር ቡሀላ ከቁርአን ቤት ስመለስ እቤት እየመጣ ትምህርት የሚያስጠናኝ አንድ ልጅ አለ........ከዛ ዉጭ ግቢ ዉስጥ ታናሽ ወንድሜ እና እህቴ ጋር እየተጫወኩ ነዉ ጊዜየን የማሳልፈዉ፡፡
ጊዜዉ በቀልዱም በምሩም ቁሞ አይጠብቅም ቁርአን ቤት ሄድኩኝ እያልኩ ስጫወት መዋል ከጀመርኩ ሶስት አመት ሆነኝ ፡፡ ኡስማን እና እህቱ ጋር ከሁለተኛ ክፍል ጀምረን ነበር ቁርአን ቀራሁ እያልኩ መኖሪያ ቤታቸዉ እየሄድኩ የምጫወተዉ
ጉድ እና ጅራት ከስተቡሀላ ነዉ አይደል የሚባለዉ መቼም ይሄ ጉድ ተደብቆ አልቀረም....አንድ ቀን አባቴ ቁርአን ቤት መጥቶ ሸህየዉን ስለእኔ ሲጠይቃቸዉ ብዙ ቀን እንደማልመጣ እና እነ ኡስማን ቤት ስጫወት እንደምዉል መረጃዉ ደረሰዉ
እቤት ስገባ------- አባቴ ተቆጥቶ ፊቱ የእሳት ፉም መስሎ ጠበቀኝ.........
.... ነዋል ነይ ቁጭ በይ አለኝ በንዴት
......እኔም እሺ ብየ ቁጭ አልኩኝ.
...... ለስንት ደረጃ ትደርሻለሽ እያልኩ አንቺ ቁርአን ቤት ነኝ እያልሽ ሶስት አመት ስቀልጂ መቆየትሽን ዛሬ ቁርአን የሚያቀራሽ ኡስታዝ ነገረኝ....እንዴት እንደዚህ ትሰሪያለሽ ??? አለኝ
....እኔም ደንግጬ አፌ ተያያዘ የምመልሰዉ ጠፋኝ
አባቴም የመኖሪያ ቤታችንን በር ቆልፎ ለመጀመሪያ ጊዜ ገረፈኝ ....ከቀበቶ አልፎም እጄን አስሮ በርበሬ አጠነኝ
...አባቴ ከተናደደ ተናደደ ነዉ ብጮህ ብጮህ የሚገላግለሉኝ ሰዎች ወደ ቤት መግባት አልቻሉም.. አባቴ ገርፎ በርበሬ ከአጠነኝ ቡሀላ በሩን ከፈተዉ እና ጥሎኝ ሄደ
እናቴ ጎረቤት እና የቤት ሰራተኛችን ተሰብስበዉ ቢያባብሉኝ ቢያባብሉኝ እምባየ ሊቋረጥ አልቻለም
.........ከዚህ ቀን ቡሀላ አድቤ ቁርአን ቤት እየሄድኩ መቅራቴን ቀጠልኩ ... ከነኡስማን እና እህቱ ጋር ለጊዜዉም ቢሆን ጓደኝነታችንን ሰረዝን...
አባቴ እኔን ወደ ሶሰት ቀን የሚሆን አኮረፈኝ ...እኔም መልሼ አይኑን ማየት ፈራሁ ፡ አባቴ ሲመጣ ተጠምጥሜ እንደማልስመዉ ..አሁን ግን የእሱ መምጫ ሰአት ሲደርስ አይኑን ማየት እየፈራሁ መኝታ ክፍሌ እገባለሁ፡፡
ከሶሰት ቀን ቡሀላ አባቴ ነዋል ነይ ዛሬ ይዠሽ የምሄድበት ቦታ አለ አለኝ
...እኔም እሺ ብየ አባቴ ጋር መኪናዉን እየነዳ ከጅማ በ45Km በቅርብ እርቀት የምትገኘዉ ወደ አጋሮ ከተማ አባቦቃ መናፈሻ ወስዶ ሲያዝናናኝ ሲያስደስተኝ ዋለ
1.8K viewsedited 07:25