Get Mystery Box with random crypto!

#የመራም_ማስታወሻ            ክፍል ~ ➊➏ ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ ወደ ውጭ ወጥቼ ወ | ISLAM IS UNIVERSITY

#የመራም_ማስታወሻ
           ክፍል ~ ➊➏
ፀሀፊ ☞አሚር ሰይድ




ወደ ውጭ ወጥቼ ወደ ምድር አንገቴን አስግጌ ልጁን ተመለከትኩት ከፊት ለፊቱ ወዳየው ሰው ሩጫ ቀጠለ ሩጫውን ተከትየ ሰመለከት አይኔን ማመን አቃተኝ .....

ከነመፈጠራችን የረሳንን አባቢን አየሁት ልጁን አቅፎ ሲሰመው ጉሮሮየን ሳግ አፈነው ቃል ማውጣት አልቻልኩም እንባ ከአይኔ ከመፍሰስ ውጭ መናገር አቃተኝ፡፡ ስጠላውና ስኮንነው የኖርኩት አባቴ ዛሬ በሀዘን ተንሰቅስቄ እንዳለቅሰ አረገኝ

ያ የሚያምረው ግርማ ሞገሱ ድምጥማጡ ጠፍቷል፡፡ስጋው አልቆ አጥንቱ ቀርቷል ሁለት ትላልቅ ጅማቶች ግንባሩ ላይ በትልቁ ተጋድመው ከሩቅ ያስታውቃል ጥርሱ አርንጓዴ አይሉት ቢጫ የነጭነቱ መልክ ጠፍቶ ወደ ጥቁነት ተቃርቧል ግንባሩ ላይ ያሉ ጅማቶች እጆቹንም ወረውታል ...ያረጀ ጫማ ኮሌታው
...ግንባሩ ላይ ያሉ ጁማቶች እጆቹንም ወረዉታል ያረጀ ጫማ ፤ኮሌታዉ የተቀደደ ሸሚዝ፤ የተቀደደ ሱሪ ...ለብሷል ደነገጥኩ ያ! ባለግርማ ሞገሱ አባቴ አልመስለኝ አለኝ በጣም አፈጠጥኩበት ከሚስቱ ጋር ከፍ ባለ ድምፅ እየጮሁ ይጨቃጨቃሉ ፡፡ ትንሽ ራቅ ስላልኩ በምን ተጣልተዉ እንደሚያጨቃጭቃቸዉ ማወቅ አልቻልኩም ብቻ ለደቂቃዎች አይኔ ከነሱ አልተነቀለም ጭቅጭቃቸዉ የሚያልቅ አይደለም

እኔም መጨረሻቸዉን ለማየት ጓጉቼ ቁሜ ቀረሁ ከመሀል ልጃቸዉ ፈይሰል ከሩቅ ሲያየኝ እየሮጠ መጣና በሀዘን አይኖቹ እያየኝ ልብሴን እየጎተተ በትናንሽ ጣቶቹ ወደእናትና አባቱ እያመለከተ እባክሽ ገላግያቸዉ የሚል ይመስላል

እኔም በጉልበቶቼ በርከክ ብየ የፈይሰልን ፀጉር እያሻሸሁ ፈይሰል ምን ሁነህ ነዉ እየሮጥክ የመጣሀዉ?? ብየ ጠየቁት የፈይሰል መልስ እንዳሰብኩት ነበር
....."እማየና አባየ ተጣሉ" አለኝ
ከነሱ መጣላት የልጁ አንገት መድፋት ሳይ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም አለቀስኩ በእዝነት አይኔ እያየሁ ጥያቄየን ቀጠልኩ
.....ፈይሰል ሁሌም ነዉ ወይስ ዛሬ ብቻ ነዉ እናትና አባትህ የሚጣሉት ??? ብየ ጠየኩት
.....ፈይሰልም " ጥዋትም ማታም ሁሌም እንደሚጨቃጨቁ ሲጨቃጨቁ ጃሮዉን በእጆቹ ይዞ ተዉ ተዉ....እያለ ከቤት እንደሚወጣ ባስ ሲልም እርስ በርስ እንደሚመታቱና በተደጋጋሚ ጎረቢቶች እንደሚገላግሏቸዉ ነገረኝ ፡፡ አዘንኩ ወደ ኋላ በሀሳብ ተጓዝኩ እማየ ትዝ አለችኝ በርግጥም በዱንያም ሆነ በአኼራ ሰዉ የዘራዉን ያጭዳል አባቢ እማየን እንዳስለቀሳት አሁን ሚስቱ ታስለቅሰዋለች!!!

...."ፈይሰል የት ሂደህ ነዉ? ለምን እዚህ መጣህ?"የአባቢ ንግግር ነበር ከገባሁበት የሀሳብ ማእበል ያነቃኝ ደነገጥኩ ቀና ብየ ለማየትም ቀፈፈኝ እባቢ አይኑን ወደ መሬት ወርዉሮ የኔ ልጂ አመሰግናለሁ ና ፈይሰል" አለና ልጁን ይዛ ለመሄድ ሲቻኳል ፊቴን ወደመሬት ስላደረኩ አላየኝም ወይም ከነመፈጠሬ ረስቶኝ ይሆናል ብየ ሳስብ ፈይሰል"አልሄድም ከአንተ ጋር አልሄድም ብሎ ተጠመጠመብኝ
..... አባቢም ና ፈይሰል እኔ እቸኩላለሁ አለና ጎንበስ ሲል አይን ላይን ተገጣጠምን

ከፊቱ ያየሁትን የመደንገጥ፤የፀፀት፤ የደስታ፤የሀዘን...ድብልቅልቅ ያለ ስሜት መቸም አረሳዉም "መመመመመ...."እንዴት ችሎ ስሜን ይጥራዉ?? አልቻለም ደጋግሞ ሞከረ መመመመ"ከሚባሉ ፈደላት ዉጭ ሙሉ ስሜት ከአፉ ማዉጣት አቃተዉ እንባዉ ጉንጫቹን አልፎ በአንገቱ እየወረደ የለበሰዉን ሸሚዝ አራሰዉ እኔም ቁሜ ማልቀስ ጀመርኩ እንዴት ችየ አባቴ ልበለዉ?? አልቻልኩም የእማየ የስቃይ ሞት፤የኔ ሂወት፤ የእህቴና የወንድሜ በድህነት ማደግ የሁላችን ተጠያቂ እሱ እንጂ ማን ነዉ? እና እንዴት ችየ አባቴ ልበለዉ?! እንዴት? ከበደኝ!!!

... መጥቶ በሁለት እጁ እያለቀሰ በናፈቀ ስሜት አቀፈኝ ሩጨ የምሄድበት መሰለዉ አካሌን ከፀጉሬ ጀምሮ ዳበሰዉ አላምን አለ ......በደስታ አንዴ ይስቃል አንዴ ያለቅሳል በዚህ ስሜት እያለ ሚስት ተብየዋ መጥታ "አንተ ሰዉየ ጭራሽ እኔን ትተህ ቆንጆ መዳበስ ጀመርክ?? ይሄ ነበር የቀረህ!!!! እንዲህ ነችና በል እስከዛሬም ታግሸሀለሁ አሁን ትግስቴ አልቋል ልጂህን ተረከብ እና የምትዳብሳት ሴት ጋር መኖር ትችላለህ " ብላ ልጇቹን ሰጥታዉ ሲጋራዋን እያቦለለች አባቴን ገለማምጣዉ ጥላዉ ሄደች
...አባቢ ዝም ብሎ እኔን ከማየት ከመዳበስ ዉጭ እሷን ለማየትም ለመስማትም ጊዜ አልነበረዉም ጥለዉ ስትሄድ ምንም ቃላት ሳያወጣ ዝም አለ።

ከደቂቃዎች ቡኋላ ነበር ልጆቹን እናታቹህ የት ሄደች ??? ብሎ የጠየቃቸዉ ልጆቹም ጥላቸዉ እንደሄደች ነገሩት ...እናቲቱ በሰራችዉ ስራ በጣም አዘነ


....ከአጠገቡ በፍጥነት አንድም ቃል ሳልተነፍስ ተነስቼ መንገድ ጀመርኩ
>>>>> ልጄ መራም መራሜ የኔ ልጂ እያለ ተከተለኝ
ምን ፈለክ ያንተ ልጅ ማን ናት??? እኔ እኔ ነኝ ያንተ ልጅ እኔ... የእብድ ሳቅ መሳቅ ጀመርኩ አባቢ ደነገጠ እይዉልሽ የኔ ልጅ የፈለግሽዉን በይኝ ፤ያሻሽን ተናገሪኝ...የፈለግሽዉን ስደቢኝ፤ ብቻ አባቴ አይደለህም አትበይኝ የኔ ልጅ በአላህ ተረጂኝ አዉፍ በይኝ ከስራየ በላይ የስቃይን ጥግ አይቻለሁ አይታይሽም ከሰዉነት ጎዳና እንዴት እንደወጣሁ??...."ንግግሩን አላስጨረስኩትም አቅፌዉ አለቀስኩ እሱም አቅፎኝ አለቀሰ .......በዚህ የሀዘን አይሉት የደስታ ለቅሶ ላይ ስልኬ ሲጠራ ነበር የነቃሁ

...የደወለዉን ስመለከት አብዲ ነዉ አነሳሁት ..ኮምቦልቻ ገብቻለሁ የምሰሪበት እየደረስኩ ነዉ ተዘጋጂ አለኝ ... ደስታየ እጥፍ ድርብ ሆነ ፡፡

አባቢ ምንም ቢሆን አባቴ አባቴ ነዉ አቃለሁ የቤተሰባችን የሀዘንና የስቃይ ሰበቡ እሱ ነዉ ግን ደሙ በእሱ ሰበብ ከደሜ ተወህዷል ስጋዉ ከሱተቆርጦ የተሰጠኝ ስጋየ ነዉ አባቱነቱን መፋቅ አልችልም! አባት በሌላ አባት እንደቁስ አይቀየርም አይሸጥ አይለወጥ ነገር.....

እናቴ ልትሞት ስትል የነገረችኝን አስታወስኩ አባታችሁ ይወዳችሆል ያለችን...ነገሮችን ሳስተነትን የወለዳቸዉን ልጆች ወንዱን በሞተዉ ወንድሜ ስም ፋይሰልና ሴቷን ደግሞ በምወዳት እናቴ ስም ለይላ ማለቱ አባቴ ተቸግሮ የሰራዉ ስራ አሳፍሮት ነዉ እንጂ የቤተሰብ ፍቅር እንዳለበት ተረዳሁ

መቸም ሰዎች ስንባል አዉቀንም ሆነ ሳናቅ እንሰሳታለን ስህተታችንን አዉቀን ከተመለስን እንዴት ይቅርታ እንነፈጋለን!
አላህ ይቅር እንዲለን ከፈለግን እኛም ለበደሉን ይቅር ማለት አለብን አላህ ይቅር እንዲለዉ የማይፈልግ እስኪ ማን ነዉ"??? ማንም!!!!

....ለአባቢን ይቅርታ ለማረግ ብዙ ማሰብ አልተጠበቀብኝም በፍጥነት ነበር አዉፍ ያልኩት ወድያዉ ወደ ቤት እንሂድ ብየ ጋበዝኩት
......መሄድ አልችልም በአላህ እሺ በይኝና ልጆቼን እንዳያቸዉ እዚሁ ይዘሽልኝ ነይ ልጄቼን የማይበት አይን የለኝም ብሎ አንገቱን ደፋ
....እኔ በሰራሀዉ ስራ አዉፍ ብየሀለሁ.... እናቴ ደግሞ የእህት ወንድሞቼ አደራ ለኔ ነዉ የሰጠችኝ ...እኔ ይቅር ካልኩህ እነሱም እንደሚሉህ እርግጠኛ ነኝ አልኩት

....የእህት የወንድሞቼን አደራ ለኔ ነዉ የሰጠችኝ ስለዉ አባቴም በጣም በማዘን እምባዉ ኩልል እያሉ እየወረደ እኔ ነኝ የእሷ ሞት ምክንያት እያለ ሲያለቅስ--እኔም አብሬዉ እያለቀስኩ አባቴ ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም ሰዉ መሳሳቱን አያቅም እንጂ ቢያዉቅማ አያጠፋም ነበር አልኩት