Get Mystery Box with random crypto!

Freshman and Preparatory Students Channel

የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel F
የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel
የሰርጥ አድራሻ: @g12_freshman
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

👇👇👇
https://www.youtube.com/c/atcnews1
Contact us 🔽
@atcads

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-01 14:08:18
451 viewsMuJa. M, 11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 12:38:17
የውጭ ሃገር የስራ ዕድል ለዜጎች !!

ለሚመለከተው ሁሉ

የስራና ክህሎት ሚንስቴር የስራ ፈጠራ፣ ስልጠና እና የስራ ስምሪት ላይ ሰፊ የሪፎርም ስራ እያከናወኑ እንደሚገኝ ይታወቃል። በተለይም በውጪ ሃገር የስራ ስምሪት ዘመናዊ አገሎግሎት መስጫ ማዕከል ገንብቶ ለአገለግሎት ማብቃት ፣ የዜጎችን ክብር እና ደህንነት የሚያስጠብቅ፣ ፈጣን እና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት የሚሰጥ ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ከማስገባት በተጨማሪ የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ለመላክ ከተለያዩ ሃገራት ጋር እየተሰራ ይገኛል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሞያ መስኮች ላይ የተፈጠሩ የስራ ዕድሎች በመኖራቸው ፍላጎት ያላቹ ዜጎች በሙሉ https://www.lmis.gov.et ድህረ-ገፅ ላይ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እና የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሚንስቴር መስሪያ ቤታችን ጥሪ ያቀርባል።

1. Nurse
2. Engineering
3. Architecture
4. Health care
5. Nanny
6. Cleaner
7. House Keeper
8. Baby Sitter
9. Caregiver/Caretaker
10. Security Guard/ Security Officer
11. Driver
12. Laborer
13. Cook
14. Beautician/Beauty Salon Operator
15. Specialty Arabian Food Cook

የምዝገባውን ሂደቱን ቅደም ተከተል በቪድዮ ለምትፈልጉ





@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
884 viewsMuJa. M, 09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:26:54
wollo university
freshiman program dean office

remedial student mid exam schedule

የሪሜድያል ተማሪዎች የmid-exam ፕሮግራም
1.1K viewsMuJa. M, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 19:14:09
የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 85 ሺህ ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ለማሰማራት አቅዶ ማከናወን የቻለው 66 በመቶ ብቻ ነው ብሏል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ስድስት ሚሊዮን ዜጎች በስራ ፈላጊነት መመዘገባቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን የገለጸው ትላንት ሐሙስ ሚያዝያ 19፤ 2015 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው። የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና እንዲሁም በውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ላይ መስሪያ ቤታቸው ያከናወናቸውን ስራዎች ለፓርላማው አብራርተዋል።

የሚኒስትሯን ሪፖርት ተከትሎ ጥያቄዎችን ከሰነዘሩ የፓርላማ አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ዮሃንስ መስፍን፤ “የውጭ ሀገር የስራ አማራጮችን ተጠቅሞ ለዜጎች ብቁ ስራ ዕድል ለመፍጠር ምን ታስቧል?” የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ አሰግድ ጌታቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ከውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ የመዳረሻ ሀገራትን ለማበራከት ጥናት መጀመሩን ተናግረዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.0K viewsMuJa. M, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 17:58:08
"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል":- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው ዓመት በኹለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.2K viewsMuJa. M, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 12:36:52
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ይጠናቀቃል

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ ነገ ሚያዚያ. 20/2015 ዓም ከቀኑ 11:30 ላይ እንደሚጠናቀቅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታዉቋል።

እስካሁን ያልተመዘገቡ ተፈታኝ ተማሪዎች እስከ ነገ እንዲመዘገቡ አገልግሎቱ ማሳሰቡን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል። በማንኛውም ምክኒያት ያልተመዘገቡ ተፈታኞችንም አገልግሎቱ ከነገ በኋላ የማያስተናግድ መሆኑን አሳስቧል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.4K viewsMuJa. M, 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 10:15:18
ዘመኑ ከፍቷል ወገን

ሚስት ለአንድ ዩትዩበር ብር ከፍላ ባሏን እሷ በሌለችበት ሰዓት በካሜራ የታገዘ ክትትል ይደረግላት ዘንድ ታዛለች። ዩትዩበሩም ስራዬ ነው ብሎ በድብቅ ካሜራ ባልን ይከታተላል።

አቶ ባል ሚስት በሌለችበት የሰፈሩ ሴት ልጅ ጋር በር ዘግተናል ብለው በነፃነት አሸሸ ገዳሜ ይላሌ።መርፌና ክሩን ሳይቀር ድብቁ ካሜራ በመያዝ ለሚስት ሪፖርት ያቀርባል።

ሚስት ጥርጣሬ አድሮባት ባሏን በዚህ መልኩ በተደጋጋሚ ታሰልላለች። የሆነ ቀን ላይ ዩትዩበሩ ለሚስት ሆዬ ነይ በአካል ጉድሽን ተመልከች ብሎ ወደ ቤቷ ተያይዘው ይሄዳሉ። በር ከፍታ ስትገባ አቶ ባል ቅምጧን የሆነ ቦታ ወሽቆ ቢለዋ ይዞ ወጥ እንደመስራት ተፍ ተፍ ይላል። ሚስት እርርር ትክን ብላ ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ ብትነግረውም ራቀቱን በመሆን ለሷ ምግብ እየሰራላት እንደሆነ በመንገር ግግም ይላል።

በኋላም ዩትዩበሩ ድብቅ ካሜራዎቹ ያሉበትን ቦታ እና እያንዳንዱን ነገር እንዳዩ ይነግረዋል። ሙሉ ክስተቱን በዚህ ሊንክ

በኩል መመልከት ትችላላቹህ።

===================

ሁላችንም ፈጣሪ ሸፍኖልን እንጂ ብዙ ነውሮች አሉብን። ሰውን በዚህ ልክ እየተከታተሉ እንጀራ መብላት ለኔ ደስ አይልም።ፈጣሪም የሰውን ነውር እንከታተል ዘንድ አልሾመንም።የዩትዩበሩ ስራ ከላይ ሲታይ ጥሩ ነገር ቢመስልም በኔ ምልክታ ግን ልክ አይደለም።ቢያንስ የቀረፀውን ቪዲዮ ለጉዳዩ ባለቤት ብቻ ቢያሳይና ቪድዮውን ከምድረ ገፅ ቢያጠፋው ከዚያም ባልና ሚስት ለችግራቸው መፍትሄ ቢያበጁ ይሻላል ነኝ።(ከሆነ እንኳን)

ሚስትዬዋን በተመለከተ ምንም ማለት አልፈልግም። ልክም ናት ተሳስታለችም ማለት ይከብደኛል።

ይህንን ቪዲዮ ያያቹህ ወይም ታሪኩ በከፊል የገባቹህ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ምን ትላላቹህ?
1.5K viewsMuJa. M, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 12:29:58
#Update

ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ለአምስት ቀናት ተራዝሟል።

ምዝገባው ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በኦንላይን ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል።

የተፈታኞቹ ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህትርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም በኋላ በግለሰብም ሆነ በተቋም የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #የማያስተናግድ መሆኑን አገልግሎቱ አሳስቧል።

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ2015 ትምህርት ዘመን ፈተና የመፈተኛ ጊዜን ከምዝገባው መጠናቀቀ በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.0K viewsMuJa. M, 09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 10:21:43
ቴሌግራም ላይ ቪዲዮው ቶሎ ዳውንሎድ ለማድረግ
709 viewsATC, edited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 15:20:48 የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢያቹህ ላይ ስላለው ችግር በተለይም ከመብራት መጥፋት ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር በውስጥ መስመር ፃፉልኝ
727 viewsMuJa. M, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ