2023-05-19 20:04:18
#AASTU
የ2015ዓ.ም ዲፖርትመንት ምደባ ተከትሎ አንዳንድ ተማሪዎች በደረሳቸው ምደባ ላይ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል። በመሆኑም የቅሬታችሁን አግባብነት ለማወቅ ያክል የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ግቢ ለምደባ የተጠቀማቸው 5 መስፈርቶች ይሄን ይመስላሉ:-
1. የዲፖርትመንት ተማሪዎች መቀበል አቅም: እያንዱ ዲፖርትመንት በየአመቱ አጠቃላይ 200 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለው። ይሁን እንጂ በ3 ዲፓርትመንቶች ማለትም በኤሌክትሪካል፣ በሲቪል እና በኤሌክትሮ ሜካኒካል የተመዘገበው ተማሪ ብዛት እሄን ይመስል ነበር:-
Electrical engineering: 535
Civil engineering: 201
Electro-mechanical engineering:209
ያለውን የተማሪ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ ዲፓርትመንቶች የመቀበል አቅማቸውን ወደ 250 ተማሪ ከፍ አድርገዋል። ነገር ግን ኤሌክትሪካል ዲፓርትመንት ላይ የተፈጠረውን የተማሪ ብዛትና የመቀበያ ቦታ አለመጣጣም በሚቀጥሉት የመለያ መስፈረቶች መሰረት አወዳድሮ 285 ተማሪዎችን ለመጣል ተገዷል።
2.የተማሪ ፍላጐት: ተማሪዎች የመረጡት ዲፓርትመንት የመቀበል አቅም ያለው እንደሆነ፣ የመጀመሪያ ምሩጫቸው የተጠበቀ ይሆናል። ነገር ግን ዲፓርትመንቱ ቦታ የሌለው እንደሄነ፣ ተማሪዎች እታች ባሉት መለያ መስፈርት መሰረት ተማሪዎች ቦታ ባላቸው ዲፓርትመንቶች ውስጥ ባስገቡት ምርጫ ቅደም ተከተል መሰረት ይመደባሉ።
3. ውጤት ( cumulative) : ቦታ እጥረት እና ፍላጐት ተከትሎ፣ ተማሪዎች ባገኙት የትምህርት ውጤት ይወዳደራሉ። ፉክክር የነበረባቸው 3 ዲፓርትመንት መቀበያ ዝቅተኛ ነጥብ እንደሚከተለው ነበር
Electrical engineering
Male: 3.28 female: 2.8
Civil engineering
2.28 both
Electro mechanical engineering
3.15 both
4. በሁሉም ዲፓርትመንት 25% ለሴት ተማሪዎች የተቀመጠ ነው(affirmative action(
5. Emerging regions ወይም እያደጉ ካሉ ክልላት የመጡ ተማሪዎች ምርጫቸው 100% እንደተጠበቀ ነው የሚሆነው።
የተማሪዎች ሕብረት የአካዳሚክስ ዘርፍ ተጠሪ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.3K viewsMuJa. M, 17:04