Get Mystery Box with random crypto!

Freshman and Preparatory Students Channel

የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel F
የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel
የሰርጥ አድራሻ: @g12_freshman
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

👇👇👇
https://www.youtube.com/c/atcnews1
Contact us 🔽
@atcads

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-04 11:41:55
#ሪሜዲያል

ትምህርት ሚኒስቴር ከአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?

- በ26/10/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕርግራም ፈተናዎች #ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ እንዲደረግ ተወስኗል።

- ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ #ካምፓስ ያላቸውን #የግል_ከፍተኛ_ትምህርት ተቋማት ፈተና  ወደ ፊት ቀርቦ በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም  እንዲሰጥ እንዲደረግ።

- በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች ፈተና መስጠቱን ወደ መስከረም ወር ማስተላለፉ በተማሪዎችና በተቋማት ላይ የሚያሳድረውን ጫና ከግምት በማስገባት የተዘጋጁትን ፈተናዎች በመለወጥ ፈተናዎች ኢንክሪፕትድ ሆነው ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ደርሰው እንዲባዙና ሁሉም ፈተናዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እንዲሰጡ እንዲደረግ።

- የፈተና ጥያቄዎች ለዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንቶች ከመድሳቸው በፊት ተማሪዎች #ከቀኑ_6 ሰዓት ላይ ተፈትሸው ወደ መፈተኛ አዳራሽ ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ በማድረግ እንዲፈፀም ውሳኔ ተላልፏል።

ተቋማት ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው ውሳኔ መሰረት ተማሪዎቻቸው #ከቀኑ_6 ሰዓት ተፈትሸው ወደመፈተኛ ክፍል ገብተው ፈተናውን እንዲጠባበቁ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል።


ለኢንትራንስ ተፈታኞች
https://t.me/ATC_UEE

ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news
954 viewsMuJa. M, 08:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 12:24:21
ለ6ኛ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ጀምራል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች በጋራ የተዘጋጀ ሞዴል ፈተና በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ የ6ኛ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሰጠት ጀምራል፡፡

ሞዴል ፈተናው ከሰኔ 7-9 /2015 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የፈተና አስተዳደርና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተማሪዎች በሞዴል መልስ መስጫው ላይ በቂ ልምምድ እንዲያደርጉ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዘንድሮው ከተማ አቀፍ ሞዴል ፈተና በ8ኛ ክፍል 75̡100 ተማሪዎች በ766 ት/ቤቶች እንዲሁም በ6ኛ ክፍል 75̡090 ተማሪዎች በ788 ትምህርት ቤቶች በመደበኛ በማታና በግል እንዲሁም 53 535 የሚሆኑ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች የሞዴል ፈተናውን የሚወስድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
297 viewsMuJa. M, 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 12:13:04
በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው ዓመት ሥራ ይጀምራሉ፡፡ -ትምህርት ሚኒስቴር

በሰሜኑ ጦርነቱ ምክንያት ሥራ አቁመው የነበሩ በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች በመጪው መስከረም ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በክልሉ የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሀ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ የመማር ማስተማር ሂደት ከመጀመራቸው በፊት የምግብ፣ የመኝታ እና የህክምና አገልግሎቶች ቅድሚያ የሚያሟሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ራያ ዩኒቨርሲቲ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማሟላት ትላንት ሰኔ 06/2015 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

መቐለ እና አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣይ ወራት ትምህርት መጀመር የሚያስችላቸውን ተግባር እንደሚጨርሱና ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው፤ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ ጉዳት በማስተናገዱ የተወሰነ ጊዜ ሊዘገይ እንደሚችል ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ መሰረታዊ ነገሮችን አሟልተው በመጪው መስከረም ሥራ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ብለዋል። #ኢፕድ

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
318 viewsMuJa. M, 09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 22:35:40
Dilla University #Revised Academic Calendar!!!


@atc_news @atc_news
760 viewsMuJa. M, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 11:11:26
#Update

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰኔ 05/2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ የተላከ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የተቀበሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ዝርዝር፣ ፈተናውን የሚወስዱበት ካምፓስ ማዕከልና የከተማ ሙሉ አድራሻ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና የሚረክብ የተቋም ኃላፊ ወይም ባለቤት መረጃ እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ድረስ ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እና በትምህርት ሚኒስቴር ለአካዳሚክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ መላክ እንዳለባቸው ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከላይ ይመልከቱ፡፡)

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.1K viewsMuJa. M, 08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 21:10:34
በእንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና የማሕበራዊ ሚድያዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 12/2015 ዓ ም ተማሪዎቹን እንደሚቀበል እየተነገረ የሚገኘው መረጃ ትክክለኛ #አለመሆኑን እና እስካሁንም መቐለ ዩንቨርሲቲ የሰጠው ኦፊሽያል መግለጫ አለመኖሩን ዩንቨርሲቲው ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
976 viewsMuJa. M, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 23:12:21
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ዜና " ግነት የበዛበት ነው " አለ።

ዩኒቨርሲቲው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ ከዩኒቨሲቲው እውቅና ውጪ ባልተፈቀደ ሁኔታ በቀን 03/10/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) " አንፈተንም "በሚል በዋናው ግቢ በዉስን ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ብሏል።

" የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ በጥቂት የማህበራዊ ሚዲያዎች የፀጥታ ችግር እንዳለና መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ላይ መስተጓጎል እንዳለ በማስመሰል ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ እንዳለ ለመገንዘብ ችለናል " ብሏል።

" በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨው ዜና ግነት የበዛበት " ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " የተፈጠረውን መጠነኛ ያለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው ደህንነት ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከሀዲያ ዞን ፖሊስ፣ ከሌሞ ወረዳ ፖሊስ እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት በመስራት በአስተማማኝ ሁኔታ ሠላማዊ የሆነ የመማር ማስተማር ሥራ ማስቀጠል ተችሉዋል " ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ባስተላለፈው መልዕክት በነበረው መጠነኛ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ በተማሪዎች ላይ " ምንም ዓይነት ጉዳት " ያለመድረሱንና ዩኒቨርሲቲው ወደተለመደው መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መመለሱን አሳውቋል።

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ላይ በቪድዮ እና በፎቶ ስለተያዙት ማስረጃዎች ምንም ያለው ነገር የለም።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.2K viewsMuJa. M, 20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 13:42:50

1.4K viewsMuJa. M, 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 11:22:25
በትላንትናው ዕለት በዋቻሞ ዩንቨርሲቲ የተፈጠረው ምንድነው?

ትላንት ማለትም ሰኔ 03 ዕለተ ቅዳሜ በበርካታ ዩንቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተናን ለመቃወም ቀጠሮ ተይዞ እንደነበር በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ከነበሩ መልዕክቶች ተረድተናል።

በዚህ ቀጠሮ መሰረትም የዋቸሞ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው የመውጪ ፈተናን በተለይም ደግሞ ፈተናውን ያላለፈ ተማሪ አይመረቅም መባሉን እየተቃወሙ ሳለ የፀጥታ ሀይሎች አስለቃሽ ጭስ እና ሀይል በመጠቀም ሰልፉን እንደበተኑት የግቢው ተመራቂ ተማሪዎች ነግረውናል።

ተማሪዎቹ ይህ(ሰልፍ መበተኑ) በብዙ ዩንቨርስቲዎች የሚከሰት ዋቻሞ ላይም ተከስቶ የሚያውቅ ነገር ቢሆንም ያልተለመደው ክስተት የተፈፀመው የከተማው ፖሊሶች በየዶርሙ ቆልፎ የተቀመጠን ተማሪ በር እየሰበሩ ፤ ክስተቱ ምን እንደሆነ እንኳን ሳያውቁ ተኝተው በነበሩ ተማሪዎች ላይ ሳይቀር አሰቃቂ በሆነ መልኩ በሰደፍ እና በእርግጫ መደብደባቸው መሆኑን ገልፀውልናል።

በትላንቱ ግርግር የተማሪዎች የግል ንብረት እንደተዘረፈ እና ቀላል የማይባል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሴት እና ወንድ ተማሪዎች መኖራቸውን የዋቻሞ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ጨምረው ገልፀውልናል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ዩንቨርሲቲው የሚሰጠውን ምላሽ ይዘን እንመለሳለን።

ከላይ የተያያዘው ቪዲዮ በትላንትናው ዕለት በዋቻሞ ዩንቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች ላይ የደረሰውን እንግልት የሚያሳይ ነው።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.2K viewsMuJa. M, 08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 22:08:27
በዛሬው ዕለት የዋቻሞ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና የወደቀ ተማሪ አይመረቅም የሚለውን የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ በመቃወም ሰላማዊ ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ለተማሪዎቹ ጥያቄ በዩንቨርሲቲው የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች የሰጡት ምላሽ ከላይ በተንቀሳቃሽ ምስል የተያያዘው የዱላ ውርጅብኝ ነበር

ተማሪዎቹ ያቀረቡትን ጥያቄ ወይም ቅሬታ ተነጋግሮ መፍታት ሲቻል ከላይ በሚታየው መልኩ ከባድ የሃይል እርምጃ መውሰድ ምን ይባላል?

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.4K viewsMuJa. M, 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ