Get Mystery Box with random crypto!

Freshman and Preparatory Students Channel

የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel F
የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel
የሰርጥ አድራሻ: @g12_freshman
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

👇👇👇
https://www.youtube.com/c/atcnews1
Contact us 🔽
@atcads

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-18 15:46:22
ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች


፨የሪሚዲያል ፈተና ማለትም በዩንቨርሲቲው የሚዘጋጀው ከ50% የሚሰጠው ምዘና ከሰኔ 15/2015 በፊት ይሰጣል።

፨ተመራቂ ያልሆናቹህ መደበኛ የግቢው ተማሪዎች ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከው መርሃ-ግብር መሰረት በዩንቨርሲቲው አካዳሚክ ካሌንደር ላይ ማስተካከያ የሚደረግበትና የማጠቃለያ ፈተናዎችም ወደዚህ የሚሳቡ መሆኑን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዝግጅት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.1K viewsMuJa. M, 12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 13:39:01
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ።


የትምህርት ሚኒስቴር የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።


ትምህርት ሚኒስቴር


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
956 viewsMuJa. M, 10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 23:56:43
፨ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች
፨ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
፨ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች

ጉዳዩ፡ የአገር አቀፍ ፈተና ቀናትን ስለማሳወቅ

1) በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፈተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ።


2) በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 13 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ።


3) የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ።

በመጨረሻም ከ2016 ጀምሮ የትምህርት ካላንደሩን ሁሉም ተቋማት ፕሮግራሞቻቸውን በዚህ ማዕቀፍ ያስተካክሉ ዘንድ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሳስበዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
373 viewsMuJa. M, 20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 21:52:02 ዛሬ ከትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ከተላከ ደብዳቤ ያገኘነው መረጃ

1) በ2014 የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፈተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ።


2) በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 13 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ።


3) የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
577 viewsMuJa. M, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 18:55:20
#AAU

ዩኒቨርሲቲው በመውጫ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ምክንያት የ2015 የምረቃ በዓሉን ቀየረ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ተመራቂ ተማሪዎቹን ሐምሌ 08/2015 ለማስመረቅ በማቀድ የሚሊኒየም አዳራሽን ትብብር ጠይቆ ፈቃድ አግኝቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የመውጫ ፈተና መስጫን አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የምረቃ በዓሉን በአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ማለትም ሐምሌ 01/2015 ለማከናወን የሚሊኒየም አዳራሽን የተለመደ ትብብር ጠይቋል።

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
750 viewsMuJa. M, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 10:23:15
የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ከትምህርት ሚኒስቴር የተሠጡ አቅጣጫዎች በሚል ያጋራው መረጃ

1, የሬሜድያል ተማሪዎች ፈተና ሰኔ መጨረሻውዎቹ የሚሠጥ ይሆናል።

2, የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ሀምሌ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንት ውስጥ የሚሠጥ ይሆናል።

3, በ2ተኛ ወሰነ ትምህርት ያልተመዘገቡ እና ለምርቃት ብቁ ያልሆኑ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች ቀጣይ አመት ፈተናው የሚወስዱ ይሆናል።(የዓመቱ መጀመሪያ ላይ)

4, የምርቃት ፕሮግራም በተመለከተ በተቋማት የሴኔት ውሳኔ ማድረግ የሚቻል ይሆናል።

5,  የፈተናው አጠቃላይ የጥያቄ መጠን እንደ ትምህርት አይነቱ  ከ 100-150 ነው።

6, ማለፊያ ነጥብ 50% እና ከዚያ በላይ ነው።

7, ፈተናው የሚሠጠው በ online  ነው።

8,  የፈተናው ይዘት ሙሉ ምርጫ ነው።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
881 viewsMuJa. M, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 21:09:57
በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፋርማሲ ት/ቤት ለተማሪዎቹ ሞዴል የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ሰጠ።


በሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለአምስተኛ አመት የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ሞዴል የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) መስጠት ተጀምሯል::

የፋርማሲ ት/ቤት ኃላፊው አቶ ሕዝቅኤል ኤንጊሶ ስለፈተናው አላማ ሲያብራሩ ተማሪዎቻችን በእስካሁኑ ዝግጅታቸው ምን አይነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ራሳቸውን እንዲገመግሙና የትምህርት ክፍሉም በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያለበትን ስራ ለማወቅ መሆኑን ገልጸዋል። ኃላፊው አክለውም ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ይሰጣል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ በኮሌጁ ደረጃ ብሎም እንደ ፋርማሲ ትምህርት ቤት በርካታ የስነ-ልቦና ዝግጅትና በፈተናው ይዘቶች ላይ ለተማሪዎች ገለጻና የማጠንከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናው ሊሰጥ የሁለት ወራት ጊዜ ያህል ብቻ የቀረው በመሆኑ ይህን ሞዴል ፈተና ለማዘጋጀት መወሰኑን ተናግረዋል።

የፋርማሲ ትምህርት ክፍል አስተባባሪው አቶ ሙሉቀን አልታዬ በበኩላቸው በትምህርት ክፍሉ የተዘጋጀው ሞዴል ፈተና ዋናው የመውጫ ፈተና የሚያተኩርባቸውን ኮርሶች በመለየት የተዘጋጀ የመለማመጃ ፈተና በመሆኑ ተማሪዎች በዚህ ፈተና የሚያስመዘግቡትን ውጤት በመመልከት ምን ያህል ዝግጅት ማድረጋቸውን መገምገም ይቻላል ብለዋል።

ፈተናው በኦንላየን መሰጠቱ ከወረቀት የፈተና አሰጣጥ በአቀራረቡ የተለየ ቢመስልም በይዘት ግን ልዩነት የሌለው መሆኑን ተማሪዎች በመገንዘብ ከአላስፈላጊ ጭንቀት ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባም ጨምረው አሳስበዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
970 viewsMuJa. M, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 07:12:05
#WolloUniversity
New #Updated Academic Calendar

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል፣ በ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና በመውጫ ፈተና ምክንያት የ2015 ዓ.ም አካዳሚክ ካሌንደርን ማሻሻያ አድርጓል።

በተሻሻለው አዲስ ካሌንደር መሰረት

፨ከሰኔ 10-15/2015 ድረስ የሪሚዲያል ፈተና ይሰጣል።(Tentative)

፨ሰኔ 29 እና 30 የዩንቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎች ለኢንትራንስ ፈተና ሲባል ግቢው ለቀው እንዲወጡ ይደረጋል።

፨ከሀምሌ 05-14/2015 ድረስ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ይሰጣል።(Tentative)

፨ሀምሌ 15 እና 16/2015 የግቢው ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ወደ ግቢ ይገባሉ።

፨ከሀምሌ 17-27/2015 ድረስ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይሰጣል።

በዚህ አካዳሚክ ካሌንደር መሰረት የወሎ ዩኒቨርስቲ የተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ቀን መስከረም 19-20/2016 እንደሆነ ተገልጿል።


ዝርዝር መረጃ ለምትፈልጉ ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
946 viewsMuJa. M, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 23:51:22
#REMEDIAL #UEE #EXIT

በርካታ ተማሪዎች የሪሜዲያል ማጠቃለያ ፈተና ፣ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና እና የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና የሚሰጥበትን ትክክለኛ ቀን ጠይቀውናል። @atc_news ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አካዳሚክ ካላንደር ባገኘው መረጃ መሰረት

፨የሪሜድያል ፈተና ከሰኔ 25-30/2015 ድረስ ይሰጣል።

፨የ2015 የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከሀምሌ 05-14/2015 ድረስ ይሰጣል።

፨የ2015 ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከሀምሌ 17-27/2015 ድረስ ይሰጣል።

====================

ፈተናዎቹ በዩንቨርሲቲዎች በሚሰጡበት ጊዜ ተፈታኝ ያልሆናቹህ መደበኛ ተማሪዎች ከግቢ የምትወጡበት እና ወደ ግቢ የምትመለሱበትን ቀን ከዩንቨርሲቲዎቻቹህ updated academic calendar ላይ ተመልከቱ


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
926 viewsMuJa. M, 20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 10:43:37
#በነፃ_ይማሩ - የትምህርት ሚኒስትር


የቀረበው ትምህርት ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ ተማሪዎችን የብቃት ደረጃ ያሟላ ነው።

ለመደበኛ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ በየክፍል ደረጃው ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ትምህርቱን የበለጠ አስደሳች እና አሳታፊ ለማድረግ የተነደፉ መጣጥፎች፣ቪድዮዎች፣ምስሎች እና ሌሎች ሰፊ የትምህርት መርጃዎች ተካተውበታል።

ለመማር
Learn-english.moe.gov.et ወይም sizl.ink/moe ላይ ይማሩ

፨አቅርቦቱ ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነፃ ነው። በማንኛውም ቦታ መማር ይችላሉ።

Via-ትምህርት ሚኒስቴር

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
1.2K viewsMuJa. M, 07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ