Get Mystery Box with random crypto!

Freshman and Preparatory Students Channel

የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel F
የቴሌግራም ቻናል አርማ g12_freshman — Freshman and Preparatory Students Channel
የሰርጥ አድራሻ: @g12_freshman
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.97K
የሰርጥ መግለጫ

👇👇👇
https://www.youtube.com/c/atcnews1
Contact us 🔽
@atcads

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-03-27 11:29:25

691 viewsATC, 08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 23:21:59
#ከተጋገዝን_እናሸንፋለን

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢያቸው የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነ እና በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቹ #Fail አድርገው የህክምና እርዳታ ለማግኘት ገንዘብ በማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚገኝ ጓደኛቸውን ለመርዳት በሚል "ዶንኪ ቲዩብ" የተሰኘ የዩትዩብ ገፅ በቅርቡ ይፋ ያደረገውን ማለትም ለአሸናፊው #500ሺህ ብር የሚያሸልመውን ውድድር በመወዳደር የሽልማቱን ገቢ ለጓደኛቸው ድጋፍ ለማዋል አስበዋል።


ቻሌንጁ "Donkey Tube" የተሰኘውን የዩትዩብ ገፅ ሰብስክራይብ በማድረግ ከላይ በምስሉ በሚታየው መልኩ screenshot @legesecharitybot ላይ መላክ ብቻ ነው።

የውድድሩ አዘጋጆች እስከ 1.5k Subscribe ያስደረጉ አስር ሰዎችን በማወዳደር ለአሸናፊው ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚሸልሙ በመሆኑ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የበጎ አድራጎት ክበብ አባላት ለአንድ ዓላማ እድላቸውን ለማስፋት በሚል በርካታ Subscription Screenshot እንደሚያስፈልጋቸው ነግረውናል። በመሆኑም ይህንን መልዕክት የሰማቹህ በሙሉ መልካም ስራቸውን ለመጋራት ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ Screenshot --> @legesecharitybot ላኩላቸው


፨ይህን መልዕክትም በብዛት #Share አድርጉት።


፨ውድድሩ የፊታችን #ሰኞ ይጠናቀቃል።

#ከተጋገዝን_እናሸንፋለን


@atc_news @atc_news
533 viewsMuJa. M, 20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 13:53:58
ራያ ዩኒቨርሲቲ ስራውን በማስጀመር ዙርያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አደረገ

የራያ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት አመታት ከተቋረጠ በኋላ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዴት መጀመር እንዳለበት ከአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር በመጋቢት 12/2015 ዓ/ም ውይይት አካሄደ። የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለሁለት አመታት ከተራዘመ ጦርነት እና አስከፊ ሁኔታ በኋላ ሰራተኞቹን በማግኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በአዲስ መንፈስና ጉልበት የመማር ማስተማሩን ሂደት እንዲቀጥል ጠንካራና ጠንካራ ሆነው እንዲቀጥሉ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል። በተጨማሪም ክልሉ ከገባበት ጥልቅና ውስብስብ ችግሮች ለመዳን ዩኒቨርሲቲው እና ህብረተሰቡ ጠንካራ ቁርጠኝነት ስለሚፈልግ የሀብት አጠቃቀምን በወቅቱ አጽንኦት ሰጥቷል።
ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲስ መንፈስና ጉልበት ለመቀጠል ያላቸውን ፍላጎት እና ተነሳሽነት ገልፀዋል ።
ባለፉት ሁለት አስከፊ አመታት ህብረተሰቡ ያጋጠሙትን የተወሳሰቡ የስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን ለመቅረፍ እና ለማቋቋም በሚችሉት ሁሉ የድርሻቸውን ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል።


፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
392 viewsMuJa. M, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 21:51:26
ጋና ውስጥ የሚገኝ ዩንቨርሲቲ
572 viewsMuJa. M, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 14:32:38
#እንተባበር

"ዶንኪ ቲዩብ" የተሰኘ የዩትዩብ ገፅ በቅርቡ የጀመረው የ Subscribe Challenge አሸናፊ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደሚሸለም አሳውቋል። ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢያቸው ውስጥ ሁለተኛ ዓመት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ የሆነ እና በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ኩላሊቶቹ #Fail አድርገው የህክምና እርዳታ ለማግኘት ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ የሚገኝ ጓደኛቸውን ለመርዳት በሚል ይህንን ቻሌንጅ ጀምረዋል።

ቻሌንጁ "Donkey Tube" የተሰኘውን የዩትዩብ ገፅ ሰብስክራይብ በማድረግ ከላይ በምስሉ በሚታየው መልኩ screenshot @legesecharitybot ላይ መላክ ብቻ ነው።

አንድ ደቂቃ በማይወስድ ተግባር ትልቅ ድጋፍ እናድርግ።


ቻሌንጁ ነገ ቅዳሜ ይጠናቀቃል


@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
819 viewsMuJa. M, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 17:17:07
የሪሜዲያል ትምህርት ለሚማሩ የተፈጥሮና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች #Mathematics የገፅ ለገፅ ቲቶርያል ቪድዮዎችን አዘጋጅተን ገዝተው መጠቀም ለሚፈልጉ ተማሪዎች አቅርበናል።

፨ቪድዮዎቹ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው Course Outline መሰረት የተዘጋጁ ናቸው።

፨ Natural Mathematics *ch1-ch10 (47 Videos) 300birr፥
፨ Social Mathematics *ch1-ch8 (42 videos) 250birr

የክፍያ አማራጮች ፡ በንግድ ባንክ ፣በአቢሲንያ ባንክ ወይም በቴሌብር ብቻ

መማር የምትፈልጉ @muedu ላይ በማንኛውም ጊዜ ክፍያ ፈፅማቹህ ቪዲዮዎቹን መጠቀም ትችላላችሁ።

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዩትዩብ ላይ የተመረጡ የፊዚክስ ቲቶርያሎችን በመስራት ላይ እንገኛለን።
446 viewsATC, 14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 17:30:51
#ArsiUniversity

በ2015 ዓ.ም በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት መጋቢት 25 እና 26/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-

➧ የማህበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በበቆጂ ካምፓስ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➧ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፡፡

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
433 viewsMuJa. M, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:28:22 ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ ግርግር ለመፍጠር የሚሞክሩ ተማሪዎች ያለምንም ማስጠንቀቂያ በቀጥታ ከትምህርት ተቋሙ #ይባረሩ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ከትምህርት ሚኒስቴር ለዩንቨርሲቲዎች መተላለፉን ሰምቻለሁ።

#አንፈተንም የሚል ቅስቀሳ እሱንም ተከትሎ ጥቂት ግቢዎች ላይ እየተፈጠረ ያለው ግርግር ለአንዳንድ ተማሪዎች መጥፎ ፍፃሜ እንዳይሆን እፈራለሁ

ተመራቂዎች የቱንም ያህል አንፈተንም ብላቹህ ብታምፁ ትምህርት ሚኒስቴር እንደማይሰማቹህ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው ይህን የምላቹህ።

ፈተናው አይቀርም። ብትወድቁም እስክታልፉ መፈተን ትችላላችሁ። በማይሆን ነገር ጊዜያችሁን አታቃጥሉ
872 viewsMuJa. M, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:18:29
#MoE

250 ሺህ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው ሐምሌ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና እንዲወስድ የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
725 viewsMuJa. M, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 09:33:26
#KabridaharUniversity

በ2015 ዓ.ም በቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መጋቢት 19 እና 20/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት፣
➧ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣
➧ አጋዥ የትምህርት መጽሐፍት፡፡

፨ለጥቆማ
@atc_newsbot
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
899 viewsMuJa. M, 06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ