Get Mystery Box with random crypto!

🌹 የኢስላም ልጆች 🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ fireketu_neja — 🌹 የኢስላም ልጆች 🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ fireketu_neja — 🌹 የኢስላም ልጆች 🌻
የሰርጥ አድራሻ: @fireketu_neja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.15K
የሰርጥ መግለጫ

☝️አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ከረሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም።እሱ እጅግ በጣም እሩህሩህና አዛኝ ነው።
.
.
.

.
.
.
.
.
.
.
🖊 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @Mahmmud_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-20 08:00:43 ተብለው ሲጠየቁ "እንደኔ ሀሳብ የዚህ ዘመን (ሙጀዲድ)የተሃድሶ አራማጅ ሸይኽ አልባኒ ነው።" ብለው መናገራቸው ነው።
እኔም እንዲህ ብዬ ላወድሳቸው " እርሶ በሀዲስ እውቀት ላይ የአንቀፁ ልጅ፣ የዓረፍተነገሩ ወንድም፣ የሀረጉ አባት ናችሁ ብዬ ልመሰክር እደፍራለሁ። በስፍራዎ የጥበብ ብርሃኖች ሲንፀባረቁሎት ይታየኛል። እውነትም ከሐዲስ በላይ ምን ጥበብ አለና!"
በመጨረሻም እንዲህ ልበል "የሸይኹን ስም የፈለገ 1 የሐዲስ ኪታብ ገልጦ ይመልከት።"

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينے

••●◉Join us share◉●••
abdu_rheman_aman
226 viewsHidayan nafaki ...., 05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:00:43 የደማስቆው ኮከብ፤ የአልባኒያው ልጅ!
****
«ከሰማይ ጠለል በታች በዘመነ ሐዲስ እንደ ሸይኽ ሙሀመድ ናሲሩ አድ-ዲን አል-አልባኒ ስለ ሐዲስ ይበልጥ የሚያውቅ ሰው አላየሁም።» ሲሉ ሸይኽ ዐብዱል ዓዚዝ ቢን ባዝ መስክረዋል።
"ሸይኽ ሙሃመድ ናሲር አድ-ዲን አልባኒ" ይባላሉ!

ሸይኹ በ1914 ዓ·ል መገኛዋን ደቡብ ምስራቅ አውሮፓ ባደረገችው አልባኒያ ምድር "አሽቁደራ" በተሰኘችው ጥንቲቷ ከተማ ተወለደ። ምንም እንኳን ቤተሰቡ በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ውስጥ የነበሩ ቢሆንም አባቱ ወደ ኢስታንቡል በማቅናት የተማረውን የሸሪዓ አስተምህሮት በሀገሩ ላሉ ወገኖች በማስተማር ያገለግል የነበረ ታላቅ ባለአደራ ሰው ነበር። በዘመኑ የተሾመው ገዥ መሪ [አህመድ ዙጞ] በሁሉም የህይወት ትግበራዎች ላይ ምዕራባዊያንን አርአያ በማድረግ የሀገሩን የአስተዳደር ስርዓት ወደ secularism(መንፈሳዊነትንና ሸሪዓን ያገለለ አለማዊ አገዛዝ) በመለወጥ ብዙ የጥፋት መስመሮችን ዘረጋ።
ሙስሊሟ የአልባኒያ ሴት በግድ ሒጃቧን እንድታወልቅ ፣ ወንዱም አለባበሱ ምዕራባዊያንን የተከተለ እንዲሆን ተደረገ። ብዙ… ብዙ… ብዙ ተደረገ። በዚያን ወቅት ስለ እምነታቸው የተጨነቁ፣ ስለ መጨረሻው መጥፎ ፍፃሜ የሰጉ ምስኪን የሀገሩ ህዝቦች ወደ ሌሎች ሀገራት መሰደድ ጀመሩ። የአልባኒ ቤተሰቦችም ስለ ሀገሩ ዕጣ ፈንታ በማሰብ በሀዘን ቢጨለጡም ምርጫቸውን ስደት አድርገው ሻም ወደምትገኘው የስልጣኔ ማዕከል "ደማስቆ" ገቡ።
ይህ ሀገሩን ለቆ የተሰደደው ልጅ "አል-ኢስዓፍ አል-ኸይሪይ" በተባለችዋ የደማስቆ ትምህርት ቤት ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ተማረ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ አባቱ ትምህርቱን እንዲቀጥል አልፈለገም። ታዲያ እምነታዊ ትምህርቶችን የሚማርበት የተስተካከለ መደበኛ ፕሮግራም ቀረፀለት። ቁርአን፣ ተጅዊድ፣ ሰርፍ፣ የሀነፊያ መዝሀብ ፊቅሂን በማስተማር ይኮተኩተው ያዘ።
ልጁን ከራሱ በላይ ለማድረግ የሚታትር እንዲህ አይነት አባት ያስደስታል። የሀዲስ ጠቢብን የቀረፀ አባት መቼም ቢሆን አሻራው አይለቅም። ይህ ልጅ በአባቱ እጅ ላይ ቁርአንን በመሀፈዝ ለማኽተም በቃ ፣ ብዙ የትምህርት ዘርፎችንም ወረሰ። እንዲሁም አቅራቢያው ከነበሩት ሸይኾች የዓረብኛን ሰዋሰው ትምህርት ቀሰመ።
ወጣቱ እድሜው ወደ 20 ዓመት ገደማ ሲሆን ሸይኽ መሀመድ ረሺድ ሪዳ የሚባል ሰው ያዘጋጀው በነበረው "አል-መናር" ጋዜጣ ጥናት ተፅዕኖ ስር በመውደቅ ወደ ሀዲስና ስነ ሀዲስ ዘርፍ ጥናት በጥልቀት ይመራመር ገባ። በርግጥ አባቱ የሀነፊያን መዝሀብ አጥብቆ እንዲይዝ ይመክረውና በስነ ሀዲስ ጥናት ስር እንዳይገባ ያስጠነቅቀው ነበር። ወጣቱ ግን ሱንናን በግልፅና ትክክለኛ በሆነ መረጃ መከተል የሚሻ ስለነበር ጉዞውን በሀዲስ መስመር ላይ አደረገ። እጅግም ወደደው። ደማስቆ ውስጥ "ዟሂሪያ" በተሰኘችው ቤተ መፅሃፍት በቀን ውስጥ ለ12 ሰዓታት በዚህ ዘርፍ ጥናት ሲቸክል ይቆይ ነበር። ምግብ ትዝ ሲለው ሁሉ አብዛኛውን ጊዜ ቤተ መፅሀፍት ውስጥ ነበር የሚመገበው። ሁኔታውን ሲመለከቱ የቤተ መፅሀፍቱ አስተዳደር በጥናቱ ጉዳይ እንዲበራታ ልዩ ክፍል አበጁለት። እጅጉኑ ለፋ! የሀዲስ ጠቢብ ለመሆንም በቃ! ሙሀዲስ(የሀዲስ ጠቢብ) የሚለው የማዕረግ ስም እንዲሁ የተወሰኑ ትምህርቶችን ላስተማረ ሰው የሚሰጥ ተራ ስም እንዳይመስላችሁ! ብዙ ልፋት ያስፈልገዋል።
(ከአሁን በኋላ ከሊቃውንት ተርታ ተሰልፏልና በአንቱታ ልጥራው)

ሸይኹ ደማስቆ ውስጥ ስማቸው በስፋት ይጠራ ጀመር። ለመጀመሪያ ጊዜ የፃፉትና በተደጋጋሚ ለህትመት የበቃው መፅሃፍ "ተህዚሩ አስ-ሳጂድ ሚን ኢት-ቲኻዚል ቁቡር አል መሳጂድ" ተሰኝቷል። ከዚያ በኋላ ስማቸው እጅግ ከመሰራጨቱ የተነሳ መዲና የምትገኘው ኢስላማዊቷ ዩኒቨርሲቲይ በስነ ሀዲስ አስተማሪነት አጨቻቸው። ለ3 አመታት መዲና ውስጥ ካገለገሉም በስተኋላ የሀዲስ ጥናታዊ ትምህርታቸውን ለማሟላት ወደ ደማስቆ ተመለሱ።
ሸይኹ እጅግ ይደንቃሉ። በሀዲስ ቁልመማ ኡማውን ሲያወናብዱ የነበሩ ቀጣፊዎችን በማጋለጥ የሱንና ጠበቃ ሁነው ነበር።
የሀዲስ ጥናት የህይወታቸው አንድ ክፍል ሆነ። በደም ስራቸው ውስጥ የሚተላለፈውም ደምም የሀዲስ ጥናት ነበር ማለት ማጋነን አይሆንም። በጊዜው የነበሩ ጎጠኛ የቢድዓና የመዝሀብ ጭፍን ተከታዮች እርሳቸውን በጥቁር ዓይናቸው እያዩ የጥላቻን እንባ ያቀሩ ነበር። ሸይኹን በምን አጊንተን እንበቀል የሚለውም የዘወትር ጭንቀታቸው ነበር።ምንም አጥፍተው አይደለም። ቁርአናዊና ሀዲሳዊ መረጃን መሰረት ያደረገን ጉዞ ስለተጓዙ እንጂ! በግፍና በጥላቻ ስሜት ምክንያት ሁለት ጊዜ እስር ቤት ተወረወሩ። ሸይኹ እንዲህ የሚለውን የዩሱፍ (ዐለይሂ ሰላም) ንግግር ይደጋግሙ ነበር፦ «ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው፡፡»

ወህኒ ቤትኮ ለሊቃውንት ራሳቸውን የሚያሰለጥኑበት መድረክ፣ ደስታን የሚላበሱበት ጨፌ እንጂ ምንም አይደለም። ሸይኹም ወህኒ ቤት ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ለአላህና ለመልዕክተኛው ቃል ተገዥ እንዲሆኑ ዳዕዋ አድርገውላቸው ብዙ ሰዎች ዳዕዋቸውን ያለማቅማማት ተቀብለው ነበር። የሚገርመው በደማስቆ የተሳሩበት ወህኒ ቤት ሸይኹል ኢስላም ቢን ተይሚያህ ታስረው የነበሩበት ወህኒ ቤት ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢብኑ ተይሚያህ በኋላ ወህኒ ቤት ውስጥ ሰላተል ጁሙዓ የተቋቋመው እኚህ የአልባኒያ ተወላጅ በታሰሩ ጊዜ ነው።
ሸይኹ በህይወታቸው በርካታ መፅሃፍትን አበርክተው ያለፉ ሲሆን ለህትመት ያልበቁም መፅሃፍትም አሏቸው።
"ኢርዋኡል ጘሊል" ፣ "ሲልሲለቱል አሓዲሲ ሰሒሓ" ፣ "ሲልሲለቱል አሓዲሲ ዶዒፋህ" ዝነኞቹ ሲሆኑ
"ተወሱል" ፣
ኹጥበቱል ሓጃህ፣
ሲፈቱ ሰላቲ አን-ነቢይ፣
ሰላቱ አትተራዊህ ፣
አህካሙል ጀናኢዝ፣
አዳቡ አዝ-ዚፋፍ ………… ወዘተ ለአብነት ተጠቃሾች ናቸው።
ከርሳቸው የእውቀት ማዕድ የተጠቀሙና ሌሎችን በመጥቀም የሚለፉ የርሳቸው ተማሪዎች በርካታ ናቸው።
ሸይኽ ሓምዲ ዐብዱል መጂድና ሸይኽ ዐብዱርራህማን ዐብዱል ኻሊቅ ……ግዙፎቹ ናቸው።
ህልፈት
ሸይኹ ኡርዱን ውስጥ በምትገኘው ኦማን ከተማ በ1999 ዓ·ል ጥቅምት ወር ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ቶሎ ቅበሩኝ ሲሉ አደራ ብለው ነበርና ከዒሻእ ሰላት በኋላ ሊቀበሩ ችሏል።
ሊቃውንት ስለክብራቸው ሲናገሩ፦
«ከሰማዩ ጠለል በታች በዘመነ-ሀዲስ ስለ ሃዲስ እንደ ሸይኽ ሙሀመድ ናሲሩ አድ-ዲን አል-አልባኒ ይበልጥ የሚያውቅ ሰው አላየሁም።» ሸይኽ ቢን ባዝ
ሸይኽ መሀመድ አል አሚን አሽሺንቂጢ መዲና ላይ እያስተማሩ ሸይኽ አልባኒን ሲያልፉ ከተመለከቷቸው ትመህርታቸውን አቋርጠው ቆመው ሰላም ይሏቸው እንደነበር ተወስቷል።
" መፅሃፎቹን ባነበብኩባቸው ጊዜያት ውስጥ በሀዲስ ላይ የብዙ እውቀት ባለቤት መሆኑን አውቂያለሁ።" ሸይኽ ቢን ዑሰይሚን
"በሸይኽ (አል-አልባኒ) መፅሃፎች እውቀትን የምንጨምር ከመሆን አልተወገድንም።" ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋዲዒ
"ይህ ሰው ተበድሏል። ዐረብ ደረጃውን አላወቀለትም። " ሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊ
"ሸይኽ(አል-አልባኒ) ልትተው የማትገባን ድልብ ለትውልዱ አስተላልፈዋል።"
(ሃፊዝ ቢን ዓብዱር'ራህማን አልመደኒይ)
በጣም የደነቀኝ ሸይኽ ቢን ባዝ የዚህ ዘመን (ሙጀዲድ) የተሓድሶ አራማጅና የለውጥ ኃዋሪያ ማን ነው?
217 viewsHidayan nafaki ...., 05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 07:12:25
ታላቅ የዳእዋ ጥሪ

በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳእዋ ፕሮግራም በኮምቦልቻ ከተማ አንሷር መስጅድ ነገ እሁድ15/12/2014 አ·ል ከጧቱ 2:00 ጀምሮ በታላላቅ መሻይኾች አምራና ደምቃ ትውላላች ። ጥሪ የተደረገላችሁ በሙሉ በሰአቱ በመገኝት የዳዕዋው ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በታላቅ ደስታ ተጋብዛችኋል ።

ተጋባዥ እንግዶቻችን
❶ ሸይኸ ሙሐመድ መኪን(ከደሴ)
❷ ሸይኽ አወል አሕመድ(ከኬሚሴ)
❸ ሸይኽ ሀሰን አሊ(ከደሴ)
❹ ሸይኽ አሕመድ አወቀ (ከኮቻ)
❺ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን (ከደሴ)
❻ ሸይኽ በድሩዲን ሰኢድ (ከደሴ)
❼ ሸይኽ ሁሴን ዑመር አቡ ሶላሀዲን (ከደሴ)
❽ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ(ከኬሚሴ)
❾ ኡስታዝ አቡ ሙአዝ (ከደሴ)
❿ ኡስታዝ አቡ ረይስ (ከደሴ)
❶❶ ወንድም አቡ ዑበይዳ (ከኬሚሴ)
❶❷ ወንድም አቡ ሂበቲላህ (ከደሴ)
❶❸ ወንድም አቡ አኢሻ (ከደሴ)
❶❹ ገጣሚው ወንድማችን ኑረዲን አል አረቢ (ከደሴ)
❶❺ ወንድም ሰለሀድን አቡ ኡበይዳ (ከአል ኢህሳን መርከዝ)

አድራሻ :- ኮምቦልቻ ልዩ ቦታው በርበሬ ወንዝ አዲሱ ድልድይ ተሻግሮ ደዌ ሰፈር አንሷር መስጅድ

የፕሮግራሙ አስተባባሪ:- የአንሷር መስጅድ ሰለፍይ ወጣቶች
❶ አንዋር ደሳለኝ(0913203890)
❷ ሙሐመድ ሰኢድ(0988288264)
❸ ሐሚድ(0921533042)
❹ አቡ ማሒ ኢብኑ ኢድርስ(0912988994)
ቦታው ለማታውቁ በዚህ ደውላችሁ መረጃ ማገኝት ትችላላችሁ ።

ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ።

ላልሰሙ ወንድሞችና እህቶች በማሰማት በሰኣቱ በመገኘት ተጠቃሚ እንድትሆኑ ተጋብዛቹሃል፡፡

በእለቱ በማርፈዶ ምክንያት ብዙ መልእክት ሊያመልጦት ስለሚችል በግዜ ይገኙ።

https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
195 viewsHidayan nafaki ...., 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:48:14 ቅዲሚያ ለተውሂድ እንላለን ምክንያቱም
ተውሒድ ከትዕዛዛት ሁሉ በላጭ ነውና


➧ የተውሂድን ታላቅነት ከሚያሳዩ ጠቋሚዎች
ውስጥ አንዱ ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
እንዲ ማለታቸው ነው፡

➧ [ኑህ ሊሞት ሲል ለልጁ በላኢላሀ ኢለላህ
አዝሀለሁ።

➧ ሰባቱ ሰማያትና ሰባቱ መሬቶች
በአንዱ የሚዛኑ ክፍል ላይ ቢቀመጡ፣

➧ ላኢላሃ ኢለላህ ደሞ በሌላኛው የሚዛኑ
ክፍል ላይ ብትቀመጥ፣ ላኢላሃ ኢለላህ
በነሱ ላይ ሚዛን ትደፋ ነበር።]

➧[ ሸይኹል አልባኒይ ሶሒሕ ብሎታል]።

@fireketu_neja
@fireketu_neja
205 viewsHidayan nafaki ...., edited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:20:24
ተክቢራ
37 views... ...., 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:50:03 የዓረፋ ቀን ዱዓ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የዐረፋ ቀን ከሚፈፀሙ ትላልቅና ወሳኝ ዒባዳዎች ውስጥ አንዱ ዱዓ ነው
||
የእዝነቱ ነብይ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በተከበረው ሐዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
" خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ".
*
"በላጭ ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔንም ከእኔ በፊት የነበሩት ነብያቶችም ከተናገርነው ንግግር በላጩ ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም ብቻውን ነው ተጋሪም የለውም ንግስናም የእሱ ነው፣ ምስጋናም የእሱ ነው እሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው"። የሚለው ንግግር ነው።
119 viewsHidayan nafaki ...., 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:46:09 የነገውን የሀሙስ ፃም እንዳያመልጠን እንፁመው። ብዙ መልካም ነገሮችን አቅፎ የያዘ ነው።

①) ነብዩ ሲፃሙት የነበረ የውዱ ነብያችን ሱና ነው
②) ስራዎች ወደ አላህ የሚወጣበት ቀንም ጭምር ነውና ስራችን ፃመኛ ሆነን አላህ ዘንድ እንዲቀርብልን የሚያደርግ ነው።
③) ይህ ቀን ደግሞ እጅግ ውድ በሆኑት የዙልሂጃ አስር ቀናቶች ውስጥ መገኘቱ ሌላው መለያ ነው።
④) በዙልሂጃ የሚፃም ሱና ፃም ከሌላ ጊዜ ከሚፃመው የበለጠና የላቀ አጅር ስለሚያስገኝ
⑤) ከነገ ወዳ እለተ ጅሙአ የአረፋ ፃም ነው። ነብያችን ጅሙአን ብቻ ነጥሎ መፃምን ከልክለዋል። ጅሙአን መነጠልን ሳይሆን አረፋ ፃም በጅሙአ ቀን ስለተከሰተ መፃሙ የሚቻል ቢሆንም አንዳንድ ኡለማዎች ለጥንቃቄ ሀሙስንም ብንጨምር ብለዋልና ይህም ሌላ መለያ ነው።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
142 viewsHidayan nafaki ...., 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:46:09 ➪አኢሻ ቢንት አቡበከር
➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ዛሬ ላይ የምናወሳት ተምሳሌትሽ ቀዳሚዋ ልእልት አኢሻ ናት፡፡ ይህች ልእልት በእውቀቷ የላቀች ፣በጥብቅነቷ የታወቀች ናት፡፡ ለሙናፊቆች ውንጀላ ያልተምበረከከች ድንቅ ስብእና ፣ ስለ ንፅህናዋ በአዛኙ ጌታ የታወቀች ጥብቅ እንስት ፣ የምእመናን ድንቅ እናት ፣ የቁርጥ ቀን እንስቶች ዋና ማሳያ ድንቋ አኢሻ ቢንት አቡ በከር፡፡

➲የዘመኑ ሴቶች በእውቀት ማነስ ቢወነጀሉም አኢሻ ግን በእውቀቷ ወደ ላይ ተስወንጭፋለች፡፡

☞︎︎︎የእውቀቷ ደረጃ ከሴቶች ድንበር የተሸገረና ከወንዶችም መጥቃ ሰማይ ነክታለች፡፡
𒊹︎︎︎ይህ የእውቀት ደረጃዋ ሲታሰብ የሷ አምሳሎች ተፈጥረው የምናይበትን ቀንን የእውነት ያስመኛል፡፡

➪ወንድሜ ዛሬ ሴቶች እውቀትን ለመፈለግ ወደ ወንዶች ሲያቀኑ ማየትህ አይሸንግልህ፡፡
❁ምክንያቱም ትናንት ወንዶች እውቀትን ለመፈለግ አኢሻ ጋር ተገኝተዋል፡፡

☞︎︎︎ያውም እንዳንተ ተራ ወንዶች ሳይሆኑ እጅግ ብርቱ ወንዶች ወይም የነብዩ ﷺ ባልደረቦች ፣ እነዛ ትውልድን የመሩ ከዋክብቶች አቡል ሙሳ አል አሽአሪ  የነብዩን ﷺ ሰሓቦች ድርጊትን ባወሳበት ሒደቱ ተከታዩን ብሏል

ما أشكل علينا أصحاب رسول الله صلى الله عليه وسلم حديث قط فسألنا عائشة إلا وجدنا عندها منه علما٭.

እኛ ሶሓቦች በነብዪ ሐዲስ ላይ ችግር
ሲገጥመን አኢሻን እንጠይቅ በሱም አወቂ ሆና እናገኛት ነበር٭

[ሱነን አት-ቲርሚዚይ ቁ. 3886 ሐዲሱን አልባኒ ሶሒህ ብለውታል፡፡]

➧አየሽ እህቴ አኢሻ እንዲህ አዋቂ ነች፡፡ እንደሷ እውቀትን ከሻሽ በቶሎ ድራማውን እርሺ አኢሻን ግን አስታውሺ!!!

ምንጭ ሙስሊሟ እህቴ ማስታወሻ ገፅ 44-45
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

https://t.me/muslim_negn
127 viewsHidayan nafaki ...., 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:46:08
115 viewsHidayan nafaki ...., 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 00:00:42ከሄዱ በኋላ ማለቃቀስ አይነፋም!!

➭በል ወንድ ልጅ አያምርበትም!

➭በኋላ ቁጭት ህመም ለቅሶ ለምን ሆነብህ?


ወይ አታቅህም ወይ አታስብህም ለምን ኡነቱን ተናግረህ ቁርጥህን አታቅም

ኡነተኛዋ ሱኒይ ሰለፊ ሴት እንደሆነች ሚሟዘዙትን አትወድም! ቆራጥ ጀግናን እንጂ
ዛሬ የማልቀስህም ሆነ የመበሳጨትህ መንስኤ እንተው ራስህ ነህ።


በመንሀጃችሁ ላይ አንድ ከሆናችሁ ምክኒያቱም ዋና መስፈርቷ መንሀጅህ ስለሆነ የሱኒይ ሰለፊያህ ሴት መስፈርት ምን እንደሁ ታውቃለህ መስፈርቷ አጠገብህ ከተገኙ እስክታመልጥህ ምን አስጠበቀህ ሊያውም ስታስባት ኑረህ


ትወዳታለህ ግን አትደፍርም አው ስትሟዘዝ ስተጠማዘዝ አው ለ1ንግግር 12ንግግር ስትናገር አይታክ (አኡዙ ቢሏህ ሚን ሀዛ ወ ሚን ሚስሉ ብላህ ይሆናል)

ምን አጠማዘዘህ ምን አስቀባጠረህ ኡነታውን ቁጭ አድርገህ አታርፍም።

ብዙ እል ነበር ተውኩት ለተገነዘበ ይህ በቂውነው

የፃፍኩትም ያየሁትን የሰማሁትን ነው

እናማ አንዳንድ ወንድሞች በውስጣቸው ይዘው ይኖራሉ ግልፅ ሳይናገሩ ተስፋን ብቻ ይዘው በኋላ ካመለጧቸው ወድያ ቅስማቸው ይሰበራል ህመም ቁጪት ይሰፍርባቸዋል
አዝነው ያሳዝናሉ!
እናም ያ ከመሆኑ በፊት እዉተኞችና
በራሳችሁ ምትተማመኑ ከሆናችሁ እውታውን መግለፁ ለናንተም መድሀኒት ይመስለኛል! ወላሁ አእለም የተሻለ መስሎ ከተፀማኝ አንፃር!!

➧ተነካክቶ የተወሰዴ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
150 viewsHidayan nafaki ...., 21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ