Get Mystery Box with random crypto!

🌹 የኢስላም ልጆች 🌻

የቴሌግራም ቻናል አርማ fireketu_neja — 🌹 የኢስላም ልጆች 🌻
የቴሌግራም ቻናል አርማ fireketu_neja — 🌹 የኢስላም ልጆች 🌻
የሰርጥ አድራሻ: @fireketu_neja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.15K
የሰርጥ መግለጫ

☝️አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ከረሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም።እሱ እጅግ በጣም እሩህሩህና አዛኝ ነው።
.
.
.

.
.
.
.
.
.
.
🖊 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @Mahmmud_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:35:14 ሸር አድርጋችሁ አሰራጩት

#ዘመንመለወጫ!!?

ማነሽ እንቁጣጣሽ..!!?
25 viewsHidayan nafaki ...., 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:29:36 የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-

* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።

3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-

* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
59 viewsHidayan nafaki ...., 10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:51:57 አነስ ረ.ዐ እንዳስተላለፉት ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል 'አንዳችሁ እምነት ሊኖረው አይችልም ለራሱ የወደደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ'

[ቡሀሪ ዘግበውታል]
58 viewsHidayan nafaki ...., 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:50:07
#ከእሳት ውስጥ ነው…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما كان أسفَلَ مِنَ الكَعبَيْنِ مِنَ الإزارِ؛ فهو في النّارِ﴾

“ልብሱን (ኢዛሩን) ከቁርጭምጭሚት በታች አውርዶ የለበሰ ከእሳት ውስጥ ነው።”

ቡኻሪ ዘግበውታል: 5787
111 viewsHidayan nafaki ...., 06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:33:59 ኢማን ከ 73 እስከ 79 ወይም ከ 63 እስከ 69 የሚደርሱ ቅርንጫፎች አሉት። ከፍተኛውና በላጩ «ላኢላሀ ኢልለላህ»ን ማለት (ከአላህ ሌላ የሚመለክ ኃይል እንደሌለ መመስከር) ሲሆን፣ የመጨረሻውና ዝቅተኛው ከመንገድ ላይ እንቅፋትን ማስወገድ ነው።«ሐያእ» የኢማን አንዱ ዘርፍ ነው።” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ ዘግበውታል)
104 viewsHidayan nafaki ...., 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:57:12
#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
118 viewsHidayan nafaki ...., 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:51:09 #ጓደኝነት_በወታደርነት_ውስጥ__!!
<===================>

ነገሩ እንድህ ነው ...

ጀግኖቹ ጦርነት ላይ ነበሩ እና………!!

=>ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡

=>አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ
ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም'በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

=>ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡

=> ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤

=>አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡

=> ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ፡፡

=>አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣

=>አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው

ወታደሩም[[ #እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ]]።

እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው!
አሏህ እውነተኛ አድርጎ እውነተኛ ጓደኛ ይስጠን
ያ አሏህ
151 viewsHidayan nafaki ...., 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 06:23:25 ከዑመር ኢብኑ አል ኸጣብ
ምክር ውስጥ ይህ ይገኝበታል
አመፀኛን አትጎዳኝ
አመፁን ትማራለህና
ጠላትህን ራቅ ጓደኛህንም
ተጠንቀቅ ያ ታማኙ ሲቀር
ታማኝ ጓደኛ ደግሞ የለም
አላህን የሚፈራ እነጂ
በንግግርም ጊዜ ተናነስ
የአላህን ትእዛዝም ስትፈፅም
ለአላህ ተዋደቅ
ወንጀል ላይ ልትወድቅ ስትልም
በአላህ ተጠበቅ
በጉዳይህም ላይ እነዚያ አላህን
የሚፈሩ ሰዎችን አማክር

[روضة العقلاء، ابن حبان (٨٩)].
ምንጭ
111 viewsHidayan nafaki ...., edited  03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:35:27 #ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ__!!
---------------------------------------
የዋህነትህን ሞኝነት አድርገው፡
መከራ ሲግቱህ አፍህን መንግገው፡
ምን ይሆን ከዚህ ውጭ የምትፈልገው!?
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
ከትላንቱ ስህተት ዛሬም አልተማርንም!!
ሁሌ ቀብድ መሆን እውነት አያመንም?
የህዝቡ ሰቆቃ አይዘገንነንም......!?
የክልሉ መንግስት አንተን ቢያገልህም፡
በአሏህ ተመካ አብሽር ግድ የለህም፡
ወተት በመገፋት ቅቤ እንደሚወጣው፡
ከችግር ኋላ ነው ደስታ የሚመጣው፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
መከራው ተገፎ እስኪመጣ እፎይታ፡
ወሎ ነፃ እስኪሆን በማራኪ እይታ፡
ለአለም ፈጣሪ ለጌታችን ታምነን፡
በአላማ ፅናት በትግሉ አንድ ሆነን፡
ተስፋችንን አርገን በአሏህ እርዳታ፡
ምንም ብንበደል ቢበዛም ፍንዳታ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
አብሽሪ ሀገሬ ቀን ይወጣልሻል፡
ደግሞም ኢንሻ አሏህ አሏህ ይረዳሻል፡
ወሎን የሚዘርፈው በግዛቱ አስታኮ፡
ክልሉ አሁን የለም የሚገርመውኮ!!
የቆቦን መወረር ክልሉ አልሰማውም፡
የወሎ መከራ ምንም አይመስለውም፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
የአማራ ክልል እስካሁን አልሰማም፡
የኛ ግፍ ደስታው ነው በዚህ አይታማም፡
ግን ደግሞ ኢንሻ አሏህ አሏህ ይረዳናል፡
በወራሪያችን ላይ ድል ያቀዳጀናል፡
ወሎ ይከበራል በንፁህ ህዝቦቿ፡
በአብራኳ ክፋይ በጀግና ልጆቿ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
በሀገር መከታ በመከላከያው፡
በሀበሻ ጀግና በጦር ባለሙያው፡
በፈጣሪ እርዳታ ወሎ ይከበራል፡
በቅርቡ ኢንሻ አሏህ ጨለማው ይበራል፡
ያኔ ከናንተ ጋር እንተያያለን፡
የምንጠይቀው ብዙ ሒሳብ አለን፡
እስከዚያ ግድ የለም የወሎ ህዝብ ይሙት፡
ዱሮስ ሞቱን እንጂ ፍቅሩን መች ስትሰሙት፡
ግን ደግሞ ኢንሻ አሏህ ወሎ ይከበራል፡
መሪወች ጠፍታችሁ ህዝብ ግን ይኖራል፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
ሀገሬ ፍቅር ነው ሁሉንም ያስጠጋል፡
ወሎ ገራገር ነው ሁሌስ መች ይሰጋል፡
በተቻለው አቅም መልካሙን ያደርጋል፡
በየዋህነቱ ሁሌም ቢሆን ያድጋል፡
ጠላቱ ብዙ ነው ግን ምን ይደረጋል፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
ወሎ መከራ እንዳይ ሁሉም ተሰብስቦ፡
ሸፍጥና ክህደትን በጀርባው አንግቦ፡
የጀግኖቹ መንደር ቢወረርም ቆቦ፡
ነፃ እንሆናለን የአሏህ ትዕዛዝ ቀርቦ፡
ክብሩን ያስከብራል ተጠምቶ ተርቦ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
ክልሉም ፌደራል ቀብድ ቢያደርግሽም፡
መከላከያሽ ግን ፈፅሞ አይተውሽም፡
ከሁሉም በላይ ግን አሏህ አይረሳሽም፡
ተስፋ አለን በአሏህ ድጋሜ አይቀጣሽም፡
የአርሹ ባለቤት እባክህ ጌታችን፡
ሰላም አድርግልን ሀበሻ አገራችን፡
በሴራ ድርብርብ ቢደጋገም ጥቃት፡
ከክፉ መከራ ሀገሬን ጠብቃት፡
#ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ!!
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
ባህሪው ስለሆነ በዚህ ባይታማም፡
የክልሉ መንግስት እስካሁን አልሰማም፡
የውሸትም ቢሆን አልዘገበም ዜና፡
ወሎ እንድጨፈጨፍ ፕላን ነድፏልና፡
ግን አሏህ ሳይወስን መች ይሆናልና!!
#ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ!!
ጠላት አንችን ወሮ ምን ቢፈታተንሸ፡
ክልሉ አድሞብሽ ባለ አንጣ ቢሆንሽ፡
አሏህ ድሉን ላንች እንዳቆናጥጥሽ፡
በርታ የሀገሬ ህዝብ ወሎ ፅናት ይስጥሽ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
#በኑረዲን_አል_አረብ
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
147 viewsHidayan nafaki ...., 15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:56:53 يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِنْ يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَى ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ
164 viewsHidayan nafaki ...., 08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ