Get Mystery Box with random crypto!

#ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ__!! --------------------------------------- የዋህነት | 🌹 የኢስላም ልጆች 🌻

#ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ__!!
---------------------------------------
የዋህነትህን ሞኝነት አድርገው፡
መከራ ሲግቱህ አፍህን መንግገው፡
ምን ይሆን ከዚህ ውጭ የምትፈልገው!?
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
ከትላንቱ ስህተት ዛሬም አልተማርንም!!
ሁሌ ቀብድ መሆን እውነት አያመንም?
የህዝቡ ሰቆቃ አይዘገንነንም......!?
የክልሉ መንግስት አንተን ቢያገልህም፡
በአሏህ ተመካ አብሽር ግድ የለህም፡
ወተት በመገፋት ቅቤ እንደሚወጣው፡
ከችግር ኋላ ነው ደስታ የሚመጣው፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
መከራው ተገፎ እስኪመጣ እፎይታ፡
ወሎ ነፃ እስኪሆን በማራኪ እይታ፡
ለአለም ፈጣሪ ለጌታችን ታምነን፡
በአላማ ፅናት በትግሉ አንድ ሆነን፡
ተስፋችንን አርገን በአሏህ እርዳታ፡
ምንም ብንበደል ቢበዛም ፍንዳታ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
አብሽሪ ሀገሬ ቀን ይወጣልሻል፡
ደግሞም ኢንሻ አሏህ አሏህ ይረዳሻል፡
ወሎን የሚዘርፈው በግዛቱ አስታኮ፡
ክልሉ አሁን የለም የሚገርመውኮ!!
የቆቦን መወረር ክልሉ አልሰማውም፡
የወሎ መከራ ምንም አይመስለውም፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
የአማራ ክልል እስካሁን አልሰማም፡
የኛ ግፍ ደስታው ነው በዚህ አይታማም፡
ግን ደግሞ ኢንሻ አሏህ አሏህ ይረዳናል፡
በወራሪያችን ላይ ድል ያቀዳጀናል፡
ወሎ ይከበራል በንፁህ ህዝቦቿ፡
በአብራኳ ክፋይ በጀግና ልጆቿ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
በሀገር መከታ በመከላከያው፡
በሀበሻ ጀግና በጦር ባለሙያው፡
በፈጣሪ እርዳታ ወሎ ይከበራል፡
በቅርቡ ኢንሻ አሏህ ጨለማው ይበራል፡
ያኔ ከናንተ ጋር እንተያያለን፡
የምንጠይቀው ብዙ ሒሳብ አለን፡
እስከዚያ ግድ የለም የወሎ ህዝብ ይሙት፡
ዱሮስ ሞቱን እንጂ ፍቅሩን መች ስትሰሙት፡
ግን ደግሞ ኢንሻ አሏህ ወሎ ይከበራል፡
መሪወች ጠፍታችሁ ህዝብ ግን ይኖራል፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
ሀገሬ ፍቅር ነው ሁሉንም ያስጠጋል፡
ወሎ ገራገር ነው ሁሌስ መች ይሰጋል፡
በተቻለው አቅም መልካሙን ያደርጋል፡
በየዋህነቱ ሁሌም ቢሆን ያድጋል፡
ጠላቱ ብዙ ነው ግን ምን ይደረጋል፡
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
ወሎ መከራ እንዳይ ሁሉም ተሰብስቦ፡
ሸፍጥና ክህደትን በጀርባው አንግቦ፡
የጀግኖቹ መንደር ቢወረርም ቆቦ፡
ነፃ እንሆናለን የአሏህ ትዕዛዝ ቀርቦ፡
ክብሩን ያስከብራል ተጠምቶ ተርቦ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
ክልሉም ፌደራል ቀብድ ቢያደርግሽም፡
መከላከያሽ ግን ፈፅሞ አይተውሽም፡
ከሁሉም በላይ ግን አሏህ አይረሳሽም፡
ተስፋ አለን በአሏህ ድጋሜ አይቀጣሽም፡
የአርሹ ባለቤት እባክህ ጌታችን፡
ሰላም አድርግልን ሀበሻ አገራችን፡
በሴራ ድርብርብ ቢደጋገም ጥቃት፡
ከክፉ መከራ ሀገሬን ጠብቃት፡
#ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ!!
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
ባህሪው ስለሆነ በዚህ ባይታማም፡
የክልሉ መንግስት እስካሁን አልሰማም፡
የውሸትም ቢሆን አልዘገበም ዜና፡
ወሎ እንድጨፈጨፍ ፕላን ነድፏልና፡
ግን አሏህ ሳይወስን መች ይሆናልና!!
#ወሎ_ፅናት_ይስጥሽ!!
ጠላት አንችን ወሮ ምን ቢፈታተንሸ፡
ክልሉ አድሞብሽ ባለ አንጣ ቢሆንሽ፡
አሏህ ድሉን ላንች እንዳቆናጥጥሽ፡
በርታ የሀገሬ ህዝብ ወሎ ፅናት ይስጥሽ፡
▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵▵
#በኑረዲን_አል_አረብ
▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾▾
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi