Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ menefesawinet — መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ menefesawinet — መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ
የሰርጥ አድራሻ: @menefesawinet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.71K
የሰርጥ መግለጫ

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16
"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

🕯ነፍሳችንን የሚያለመልመውን ቃለ እግዚአብሔር እንማማር።
ምንም አይነት ሀሳብ፣ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላቹ @hasabebot ላይ መላክ ትችላላችሁ።
@ty1921

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 05:04:36 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






6 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 02:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:52:54 Watch "እምጌቴ ሲማኒ አጫብር ወረብ በጫንጮ/ደ/ብ/ቅ/ እግዚአብሔር አብ እና ደ/ሲና ቅ/ ኪዳነምህረት አብያተ ክርስቲያናት ው/ብ/ሰ/ት/ቤት" on YouTube


219 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:19:46 ††† እንኳን ለቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ እና ለአቡነ ሰላማ ካልዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ †††

††† እነዚህ 7 ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: 7ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል:: ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት ለመጠበቅ ነው::

በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም: ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር: በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ::

ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ: ለጣዖትም ያልሰገደ: ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ: እጅ እግሩ ለእስር: ደረቱ ለጦር: አንገቱ ለሰይፍ: ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::

የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: #ኤፌሶን የግፍና የአመጻ ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ 7ቱ ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት::

ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል:: ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ወጣ::

ከመውጣቱ በፊት ግን 7ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::

ዓለምን ንቀው: ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው: ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር (በጐች አሉት) ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::

አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ 7ቱም አልወጡም:: በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ግን አልነቁም::

ያ የበጐች ባለቤት (ወታደር) ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው::

ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው ለ372 ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ::

በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን 400 ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ #አቤሜሌክ ብዙ መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች::

በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::

ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ #ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: (ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው)

በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም ( #አባ_ቴዎድሮስ ይባላል) ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: 7ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: 7ቱም ለ7 ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::

ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃየማኖት ተመልሰዋል:: 7ቱ ቅዱሳን ግን በ7ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ በ7 የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::

††† አቡነ ሰላማ ካልዕ †††

††† እኒህ ታላቅ ደግ ሰው የነበሩት በሃገራችን ኢትዮዽያ ከ1340 እስከ 1380 ዓ/ም ነው:: በትውልድ ግብጻዊ ቢሆኑም ለኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውለታን ውለዋል:: በዘመኑ ዻዻስ ሁነው ቢመጡም እንደ ሌሎቹ ዻዻሳት በቤተ መንግስት አካባቢ ሥራ ፈትተው መቀመጥን አልፈለጉም::

ወዲያው እንደ መጡ የግዕዝ ልሳንን ልቅም አድርገው ተማሩ:: ቀጥለው ኢትዮዽያውያን ሊቃውንትን ሰብስበው ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተረጉሙ ገቡ:: አሥራው መጻሕፍትን (81ዱን) ጨምሮ ብዙ መሠረታዊ መጻሕፍትን መተርጐም ችለዋል::

††† ይህም ሥራ አድካሚ በመሆኑ ከ30 ዓመታት በላይ ጊዜን ወስዷል:: ከተረጐሟቸው መጻሕፍትም:-
* #ስንክሳር
* #ግብረ_ሕማማት
* #ላሃ_ማርያም
* #ፊልክስዩስ(መጽሐፈ መነኮሳት)
* #መጽሐፈ_ግንዘት
*ድርሳን ዘቅዱስ #ያዕቆብ_ዘሥሩግ. . . ይጠቀሳሉ::

#አቡነ_ሰላማ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸውና በገዳማዊ ሕይወታቸው ይታወቁ ነበር:: በተጨማሪም በየቦታው እየዞሩ ይናዝዙ: ያጠምቁም ነበር:: በወቅቱ ልክ እንደ ስማቸው ሰላም እንዲሰፍን ይተጉ ነበር:: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን እያስታረቁ ለቤተ ክርስቲያን በአንድነት እንዲቆሙ አድርገዋል::

ጻድቁ አቡነ ፊልዾስን ጨምሮ ቅዱሳንን ገንዘውም ቀብረዋል:: በቀደመ ስማቸው #አባ_ፊቅጦር የሚባሉት ካልዕ (2ኛው) ሰላማ በ1380 ዓ/ም ከ40 ዓመታት ትጋት በሁዋላ ዐርፈዋል:: ሲጠሩም:-
* #መተርጉም (መጻሕፍትን የተረጐሙ)
* #ብርሃነ_አዜብ(የኢትዮዽያ ብርሃን)
* #መጋቤ_ሃይማኖት ተብለው ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን እንዳጸናቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† ነሐሴ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል (5ኛ ቀን)
2.ቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ
3.አቡነ ሰላማ ካልዕ (መተርጉም)
4.ቅድስት ሔዛዊ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
6.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት

††† "በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" †††
(2ቆሮ. 13:12)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
https://t.me/menefesawinet
543 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 18:01:02 https://vm.tiktok.com/ZMN7AaMEc/
478 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 19:34:40 https://www.tiktok.com/@dn_terefetesfaye/video/7134375490621607174?_r=1&u_code=dc52hl0gmcjleb&preview_pb=0&language=en&_d=e3950g7jd6g0h1&share_item_id=7134375490621607174&source=h5_m×tamp=1661267325&user_id=6820327366810027013&sec_user_id=MS4wLjABAAAAVEnw-HkNYypFQQ0J1bdcOZYPzfGl0FP5al_kmym0vQxzIhTqk_BhMWknEt6sT8D5&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7131037296568272645&share_link_id=eb006190-323b-4101-91f6-e7d238c20302&share_app_id=1233&ugbiz_name=Main
516 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:55:03 ወደ እግዚአብሔር መገስገስ

"የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው

የተደበቁ ነገሮችን መሰርሰር ትፈልጋለህ ፣ በአደባባይ የተሰቀለውን ጌታ ለማየት ግን ዓይንህን ትጨፍናለህ ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቋንጣ የሚሆነውን ዜና ተሻምተህ ትሰማለህ የዘላለሙን ምሥጢር ግን ችላ ትላለህ ፡፡ የመድኃኒት ሰዓትህን ለማስታወስ ማንቂያ ደወል ትሞላለህ ፣ ቅዳሴ ለመሄድ ግን ሲቀሰቅሱህ ትቆጣለህ ፡፡ የኤምባሲ ቀጠሮህን አትረሳም ፣ ሞትን ረስተህ ግን እንዳሻህ ትናገራለህ

ጦም መቼ ይያዛል የሚለውን ታውቃለህ ፣ ለምን እንደሚጦም ግን አትጠይቅም ፡፡ ፋሲካ መቼ ነው ? ብለህ በግ ትገዛለህ ፣ የታረደውን በግ ክርስቶስን ግን ገሸሽ ትላለህ ፡፡ ዘመን ሲለወጥ እንኳን አደረሳችሁ ትላለህ ያደረሰህን አምላክ ግን ከልብ አታመሰግንም ፡፡ ዘመን ሲጨመርልህ ከመለወጥ ያልጨረስከውን ክፋት ለመፈጸም እንደ ገና ታስባለህ፡፡ እባክህን አንተ ተወዳጅ ሆይ እግዚአብሔርን ማወቅ ሕይወት ልዑሉንም ማስተዋል ጥበብ ነው ፡፡ እርሱን ስታውቅ በማይናወጠው መንግሥቱ ያሳርፍሃል ፡፡ በማይለወጥ ባሕርዩ ያጸናሃል

https://t.me/menefesawinet
689 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 15:05:41 ​​#ነሃሴ_7
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ሊቀ_ሐዋርያት

ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ። በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ።

የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር። የዋሃን (ገና ምሥጢርን ያልተረዱ) ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን። ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት።

አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው። "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው። ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ።

ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ። "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው። እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ።

ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ። ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና። በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው። (ማቴ. 16:16)

ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት (መሠረት) ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ። ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ (ሥልጣን)" ተሰጠው።

ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ። ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ" ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም።
https://t.me/menefesawinet
1.2K viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:43:32 #የማክሰኞ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ

ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡

፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛሳሙ.፲፮፥፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡ እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡
በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡

በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡

ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡

ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
https://t.me/menefesawinet
1.1K viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:37:05 የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጉም
https://t.me/menefesawinet
751 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, edited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 08:15:52 እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡-

"ንጽሕት" ስንል፡-
ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር፣ ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት፡፡ "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ" ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል፡፡ (ተአምረ ማርያም)

"ጽንዕት" ስንል:-
ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት ቅዱስ ያሬድ "ወትረ ድንግል ማርያም" ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ)

"ክብርት" ስንል፡-
ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው እመቤታችንን ግን የምናከብራት "የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና፡፡

"ልዩ" ስንል፡-
ከእርሷ በቀር እናት ሆና ድንግል እመቤት ሆና አገልጋይ የሆነች በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና፡፡

በዚህም እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ እንላታለን፡፡
@menefesawinet
@menefesawinet
@menefesawinet
888 viewsĎň_ťėŕėfê_ŧëšfãýê @webzema, 05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ