Get Mystery Box with random crypto!

የዓረፋ ቀን ዱዓ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ የዐረፋ ቀን ከሚፈፀሙ ትላልቅና ወሳኝ ዒባዳዎች ውስጥ አ | 🌹 የኢስላም ልጆች 🌻

የዓረፋ ቀን ዱዓ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የዐረፋ ቀን ከሚፈፀሙ ትላልቅና ወሳኝ ዒባዳዎች ውስጥ አንዱ ዱዓ ነው
||
የእዝነቱ ነብይ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በተከበረው ሐዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
" خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ".
*
"በላጭ ዱዓ ማለት የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔንም ከእኔ በፊት የነበሩት ነብያቶችም ከተናገርነው ንግግር በላጩ ከአላህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም ብቻውን ነው ተጋሪም የለውም ንግስናም የእሱ ነው፣ ምስጋናም የእሱ ነው እሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው"። የሚለው ንግግር ነው።