Get Mystery Box with random crypto!

Fast mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ fetanmereja24 — Fast mereja F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fetanmereja24 — Fast mereja
የሰርጥ አድራሻ: @fetanmereja24
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.97K
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ በፍጥነት ያደርሶታል።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-10 12:12:48
ዘጠነኛው የጉማ ሽልማት ስነስርዓት ትናንት ሰኔ 2 2015 ዓ.ም ምሽቱን በ ስካይላይት ሆቴል ተካሄዷል ።

በዘጠነኛው የጉማ አሸናፊዎች ታዉቀዋል

1.ምርጥ አጭር ፊልም፡
  የጉድ ሀገር መንገድ /ብስራት ተስፋ

2.ምርጥ የተማሪ አጭር ፊልም ፡ መሐይማን / አማኑኤል ተሾመ

3. ምርጥ ተከታታይ ኮሜዲ ድራማ : አሰኳላ

4.ምርጥ ዉርስ ትርጉም ድራማ : አደይ

5.ምርጥ ዶክመንተሪ ፡ ባሌ ብሄራዊ ፓርክ /አዚዝ አህመድ

6.ምርጥ ዉርስ  ድራማ ተዋናይት ፡ በእምነት ሙሉጌታ / አደይ

7. ምርጥ ዉርስ  ድራማ ተዋናይ : አለማየሁ ታደሰ / አጋፋሪ

8.ምርጥ የፊልም ሙዚቃ :  የሱፍ አበባ 

9.ምርጥ ስኮር : ረመጥ / ብሩክ አሰፍ

10.ምርጥ ሜካፕ : ተሚማ ሁላላ / ረመጥ

11.ምርጥ ፊልም ፅሁፍ : ረመጥ / ዳንኤል በየነ

12. ምርጥ ቅንብር : የሱፍ አበባ /እስክንድር ተፈራ

13.ምርጥ ሲኒሚአቶግራፊ : የሱፍ አበባ / ዋለልኝ አደገ

14.ምርጥ ተስፍ የተጣለበት ተዋናይነት : ክሱት / እየሩሳሌም አሰፍ

15.ምርጥ ተስፍ የተጣለበት ተዋናይ : ፊናፍ / ብሩክ ግርማ

16.ምርጥ ረዳት ሴት ተዋናይት : የማር ዉሃ / መስከረም አበራ

17.ምርጥ ረዳት ተዋናይ : ጥላዬ / እንግዳሰዉ ሀብቴ

18. ምርጥሴት ተዋናይት : ክሱት / ጠረፍ ካሳሁን

19.ምርጥ ወንድ  ተዋናይ : ሄኖክ በሪሁን  /ረመጥ

20.ምርጥ ዳይሬክተር : ረመጥ/ ዳንኤል በየነ

21.ምርጥ ፊልም : የሱፍ አበባ /ለገሰ ገነቱ

22.የህይወት ዘመን ተሸላሚ : አርቲስት ኪሮስ  አለማየሁ

23.የሔርሜላ አሸናፊ : ገነት ከበደ

24. አርአያ ሰብ ከያኒ : አርቲስት  መሰረት መብራቴ አሸናፊዎች ናቸዉ።
4.9K views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 15:50:46
መርጌታ  አብረሐም የባህል መድሐኒት ቀማሚ ህይወት ጥበብ ናት።
0909819126ብለው ይደውሉ
መምጣት ለማይችሉ ደንበኞች የለምንም መሰናክል መላክ እንችላለን
የምንሰጣቸዉ የጥበብ አገልግሎት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
ለጥያቄዎ
0909819126
0909819126
2.2K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 12:23:54
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የሰኔ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

#የሁሉም_ነዳጅ_ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በግንቦት ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት :-

1. ቤንዚን  ----- ብር 69.52 በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ ---- ብር 71.15 በሊትር

3. ኬሮሲን ---- ብር 71.15 በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ ---- ብር 65.35 በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ ---- ብር 57.97 በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ ---- ብር 56.63 በሊትር

መረጃው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ ነው።
5.8K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 16:12:31
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ " አንዋር መስጂድ " ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ስለማለፉና ጉዳት ስለመድረሱ በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

በአሁን ሰዓት የተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በመስጂዱ በነበረው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዛን መሰማቱ ተነግሯል።

ከዚሁ ጋር በተያየ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ " በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው " ብለዋል።

" ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ " ያሉቱ ኡስታዝ አቡበከር " በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ስለ ዛሬው የአንዋር መስጂድ ሁኔታ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሚሰጡት መረጃ / መግለጫ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።

በተመሳሳይ በመንግስት / በከተማው አስተዳደር በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

ባለፈው ሳምንት ጁመአ በአንዋር መስጂድ በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለው የመስጂዶች ፈረሳ ተግባር በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ በቀረበበት ወቅት በተወሰደ እርምጃ የሰዎች ህይወት ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።
9.4K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 13:52:57 በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረኤሊያስ ወረዳ በሥላሴ አንድነት ገዳምና አካባቢው ሰሞኑን ስለደረሰው የሰላም መድፍረስ ፣የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ትላንት ባወጣው መግለጫ “ከመንግስት ያፈነገጡና የታጠቁ” ያላቸው ሰዎች በገዳሙ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ይሰጡ እንደነበር አረጋግጫለሁ ብሏል። አንድ የገዳሙ አገልጋይ የሆኑ አባት ግን ከገዳሙ ሁለት ታጣቂዎች ውጪ መሣሪያ የታጠቀ ኃይል የለም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
7.7K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 07:33:28
በአዳማ ከተማ 30 ዓመት የኖሩና መነሻቸው ከኤርትራ የሆነ ሰዎች ቤታቸው እንደፈረሰባቸው ተገለጸ!

በአዳማ ከተማ በ1985 ከኤርትራ ወደ ከተማው በመግባት የመኖሪያ ፍቃድ በመጠየቅ ቦታ ተመርቶላቸው ቤት ሰርተው ሲኖሩ የነበሩ ሰዎች ‹‹ሕገ ወጥ ናችሁ›› በሚል ምክንያት ቤታቸው እንደፈረሰባቸው ተገለጸ፡፡

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እና አዳማ ከተማ ስለፈጸመው የቤት የማፍረስና የአስገድዶ ማፈናቀል እንቅስቃሴዎች ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

ኢሰመጉ በመግለጫው፤ በግንቦት 10/2014 ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ‹‹ሕገ ወጥ ናችሁ›› በሚል ምክንያት የ14 አባወራ እና እማወራ ቤቶች መፍረሳቸውን አቤቱታ ቀርቦልኛል ብሏል፡፡ የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ፤ የቤቶቹን መፍረስ በሥፍራው በመሄድ ማረጋገጡንም አስታውቋል፡፡

የፈረሱት ቤቶች ጠቅላላ ዋጋው ከ8 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን፤ ኢሰመጉ በጉዳዩ ላይ ማስረጃ እንዲሰጠው የአዳማ ከተማ አስተዳደርን በደብዳቤ ቢጠይቅም መልስ ማግኘት አለመቻሉን ጠቁሟል፡፡(አዲስ ማለዳ)
9.2K views04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 13:54:36
#ወልድያ..!

በወልድያ ከተማ ከግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የስአት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሸያ ተደርጓል። በዚህም መሰረት:-

1. ማንኛዉም አገልግሎት ሰጪ የንግድ ድርጅቶች እስከ  ምሽቱ 4:00 ሰዓት ብቻ  አገልግሎት መስጠት ይችላሉ።

2. ተሽከርካሪዎች ከጧቱ 12:00 ሰአት እስከ  ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ብቻ  ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ የተፈቀደ ነዉ።

3. የሰው እንቅስቃሴ በተመለከተ እስከ ከጧቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 4:00 ብቻ ባለው ጊዜ መንቀሳቀስ እንደሚቻል ተገልጿል።
9.0K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 11:06:08 አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል !

ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች።

ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ።

ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተቀባይንት ያገኘ ሲሆን፣ ማሻሻያ እንዲደረግበት ለፓርላማው ተመልሶ ቀርቦ ነበር።

ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው ረቂቅ ሕግ ላይ  ማንኛውም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ  የሚያደርግ ነበር።

ሆኖም ግም ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህ ሰዎች እንዲታሰሩ እና በአካላዊ ገጽታቸው ብቻ እንዲከሰሱ ያደርጋል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ሕጉ እንዲሻሻል ወደ ፓርላማ መልሰውት ነበር።

በዚህ መሠረት ተሻሽሎ አሁን ላይ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀልነት ወንድ ከወንድ ጋር በሚያደርገው ወሲባዊ ድርጊቶች ላይ የተወሰነ ሆኗል።

ይህንን ሕግ ተላልፈው የተገኙም እስከ እድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።

ለከባድ ወንጀሎች ማለትም ወሲባዊ ጥቃቱ #በሕጻናት_ላይ ፣ በአካል ጉዳተኛ እንዲሁም ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ በሚፈፀምበት ጊዜ አሊያም የጥቃት ሰለባዎቹ ለዕድሜ ልክ ህመም የሚዳረጉ ከሆነ በድርጊቱ ፈፃሚ ላይ #የሞት ቅጣትን ይደነግጋል።

ማኅበረሰቡ #በሕጻናት ወይም በሌሎች ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰቡ አባላት ላይ ማንኛውንም ዓይነት የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት በሚያዩ አልያም በሚሰሙበት ጊዜ ለባለሥልጣናት ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው ፤ ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

#ምዕራባውያን ሀገራትና #ተቋማት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ በዩጋንዳ ፓርላማ የተላለፈውን ውሳኔ ሲቃወሙና ፕሬዜዳንቱ #እንዳይፈርሙ ሲያሳስቡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
9.2K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 16:17:26
በሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉት ኢትዮጵያን ተማሪዎች 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀቁ።

ኢትዮጵያን ወክለው በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉት ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀቁ። ውድድሩ ከግንቦት 16 እስከ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በቻይና ሼንዘን ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል። ተሳታፊዎቹም ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል። (FBC)
8.3K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 15:25:34 #ይወረሳሉ !

" በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎች #ይወረሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

በሕገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ መኪናዎችን የመለየት ሥራ መሰራት ከተጀመረ አንድ ወር ሆኖታል ተብሏል።

ባለሥልጣኑ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ጥናት በባለሥልጣኑ የሚመዘገበው የገንዘብ መጠን እና ለገቢዎች ቢሮ የሚቆረጠው ደረሰኝ ተመሳሳይ ያለመሆን ሁኔታዎች መኖራቸው አመላክቷል።

በዚህም በተለይ የአዲስ ተሽከርካሪዎች ዋጋ የሚቆረጥበት ደረሰኝና ገዢዎች ለመኪናው የሚከፍሉት ዋጋ ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑ ተረጋግጧል።

መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ግዥና ሽያጭ ማግኘት የሚገባውን የታክስ ገቢ እያገኘ አይደለም ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህንን እና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎችን የመለየት ሥራ ተጀምሯል ብሏል።

ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት ሁለት አይነት ሕገወጥ ተግባራት እንደሚያጋጥሙት ገልጿል እነዚህም ፦
- ከክልል በዝውውር የሚመጡ መኪናዎች ላይና
- በተጭበረበረ ሰነድ የተመዘገቡ መኪናዎች ናቸው።

ይህንን ለመከላከል የሚያግዝ ዘመናዊ ሥርዓት የመኪናዎቹን ሕጋዊነት የማጣራት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አሳውቋል።

የማጣራት ሥራው የሚሠራው ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ ሲሆን ከዚህ በፊት አንድ የመኪና ሻጭ በስሙ የነበረውን መኪና ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ የማጣራት ሥራ እንዳልተሠራ እና በዚህም መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ታክስ እንዳላገኘ ተገልጿል።

አሁን ግን ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን አዲስ ሥርዓት መዘርጋት ተችሏል ተብሏል።

ሥርዓቱም መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ማግኘት የሚገባውን ታክስ እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ መኪና ገዢዎች እንዳይጭበረበሩ እና መንግሥት ሕገወጥነትን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት የሚያጠናክር እንደሆነ ተገልጿል።

በሂደቱም በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎች #እንደሚወረሱ ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ፤ የአዲስ መኪና ገዢዎች የሚከፍሉት ዋጋ በደረሰኙ ላይ መጠቀሱን በማረጋገጥ ሊገዙ ይገባል ብሏል።

ይህንን ማድረግ ለገዢው በርካታ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ከመሆኑ ባለፈ የሚሰበሰበው ገቢ ለከተማዋ መሠረተ ልማት የሚውል በመሆኑ በኃላፊነት ሊታይ እንደሚገባ አሳስቧል።

#ኢፕድ
8.9K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ