Get Mystery Box with random crypto!

Fast mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ fetanmereja24 — Fast mereja F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fetanmereja24 — Fast mereja
የሰርጥ አድራሻ: @fetanmereja24
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.97K
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ በፍጥነት ያደርሶታል።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-23 18:34:37 ኩፍኝ (measles) ምንድን ነው?

ኩፍኝ፦ አጣዳፊና በፍጥነት የሚተላለፍ በቫይረስ የሚመጣ አየር ወለድ በሽታ ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ከአምስት ዓመት እድሜ በታች ያሉትን ህፃናት የሚያጠቃ ቢሆንም በሁሉም የእድሜ ክልል ይከሰታል።

ከሦስት ወር በታች ባሉ ህፃናት ግን የመከሰት እድሉ አነስተኛ ነው። በጣም ተላላፊ ስለሆነ በወረርሽኝ መልክ ይከሰታል።

በተላይ የምግብ እጥረት ባለባቸው ህፃናት፣ክትባት ባልወሰዱ እና ተጓዳኝ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ይጠቃሉ ።

ምልክቶቹስ?
የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው ፡-
•  ትኩሳት - እስከ 104ºF (40ዲሴ)
• እንደ ጉንፋን አይነት  ስሜትና ደረቅ ሳል
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ጠፍጠፍ ያሉ ቀይ ቀለም ያላቸው  ከጭንቅላት ጀምሮ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል የሚስፋፋ የቆዳ ሽፍታ
• በአፍ ውስጥ ያሉ ነጠብጣቦች - koplik spot
• የአይን መቅላት አና ማንባት (red watery eye)
• በአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት (coryza)

አጋላጭ ሁነቶች
• የኩፍኝ ክትባት ያልወሰደ ሰው
• ኤችአይቪ/ኤድስ ወይም ካንሰር ያለባቸው ሰዎች
• ነፍሰጡር ሴቶች
• በቂ ምግብ ወይም ቫይታሚን የማያገኙ ሰዎች
• ከአምስት ዓመትበታች እና ከ ሃያ ዓመት በላይ የእድሜ ክልል ባሉ  ሰዎች ላይ በሽታው ሊፀና ይችላል።

መተላለፊያ መንገዶቹስ?
ኩፈኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን በቫይረሱ የተበከለውን አየር ሲስቡ ወይም ቫይረሱ ያረፈባቸውን ዕቃዎች በእጃቸው ከነኩና ከዚያም አፍንጫ፣ አፍና አይኖቻቸውን ከነኩ በቀላሉ ይተላለፋል።
የከፋ የሚያደርገው ደግሞ በሽተኞቹ ሲስሉና ሲያነጥሱባቸው በነበሩባቸው ከፍሎችና አካባቢዎች ለሁለት ሰአታት በአየር ላይና በቁሳቁሶች ላይ የመቆየት ችሎታ አለው፡፡

በሽታው  በፍጥነት ሊተላልፍበት የሚችሉበት ቀናት ደግሞ  የቆዳ ሽፍታ ከመታየቱ ከሦስት ቀን በፊትና ሽፍታ ከታየ ከአራት እስከ ስድስት ቀናት በሁኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።

ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት (complication ):
1/የሳንባ ምች (pneumonia)-ይህ የሚያስፈራ ሕፃናትን ህወታቸውን ሊያሳጣ የሚችል በኩፍኝ ቫይረስ (measle virus) የሚመጣ የሳንባ ቁስለትን ያስከትላል።

2/የጆሮ እንፌክሽን :አብዛኛው ጊዜ በኩፉኝ የተያዘ ሰው በጆሮ እንፌክሽን የሚጠቃ ሲሆን በአንዳንድ ሰዎች ላይ ዘላቂ የሆነ የመስማት ችግር ሊያስከትል ይችላል።

3/ተቅማጥና ትውከት፡ በማምጣት በሰውነቱ ያለውን ፈሳሽ እዲያልቅ (dehydration ) በማስከተል ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
4/የማየት ችግር (corneal clouding)፡ በማምጣት ዘላቂ የሆነ የማየት ችግር (blindness) ያስከትላል።

5/የምግብ እጥረት (malnutrition)፡ በማስከተል ና በሽታ የመከላከል አቅምን በማዳከም ለሌሎች በሽታወች ለምሳሌ እንደ ትቢ (tuberculosis ) ላሉ በሽታወች ያጋልጣል።

6/የአንጎል ኢንፌክሽን (Encephalitis): አልፎ  አልፎ የሚከሰት ቢሆንም አደገኛ የአንጎል ጉዳት በማሰከተል ለሚጥል በሽታ (epilepsy ) እና የአእምሮ እድገት ወደ ኋላ መቅረትን ያጋልጣል።

የኩፍኝ በሽታ ምርመራ አለ?
አዎ !! የኩፍኝ በሽታን ለመመርመር የደም ምርመራ ማድረግ ይችላሉ።ግን እነዚህ ምርመራዎች ሳያስፈልጉ የኩፍኝ በሽታ እንዳለበት በምልክቶቹ  ይታወቃል። ማንኛውም ሰው ትኩሳት፣ ሳል፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የአይን መቅላት እና በአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት ካለ ኩፍኝ ሊሆን ስለሚችል ወደ  ጤና ተቋም ይሂዱ።

እንዴት ይታከማል?
• ቫይታሚን ኤ መውሰድ
• በቂ እረፍት ማድረግ
• ብዙ ፈሳሽ መጠጣት(መውሰድ )
• ትኩሳት እና ህመምን ለመርዳት የህመም ማስታገሻ መውሰድ
• ከላይ የተዘረዘሩት ውስብስ ችግሮች ካሉ ማከም

ድንገት ኩፍኝ ካለበት ሰው አጠገብ ብሆንስ?
ድንገት ለቯይረሱ ተጋልጠው ከሆኑ በሽታው አንዳይከሰት መከላከል ይቻላልን? አዎ የኩፉኝ ክትባቱን በ72 ሰዓትት ውስጥ ካገኙ የኩፍኝ በሽታን ሊያስቆም ወይም ከባድ እንዳይሆን ማድረግ ይችላል።

መከላከያ መንገዶችስ
በክትባት ከምንከላከላቸው ተላላፊ በሽታዎች አንዱ እና ዋነኛው ኩፉኝ (measle) ነው።
በአገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም ህፃናት  በተወለዱ በ9 ወር እና በ15 ወር የኩፍኝ ክትባት መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ይህን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ መውሰድ ከበሽታው እስከ 95 % መከላከል የሚያስችል ሲሆን ሁለተኛው ክትባት ከተወሰደ ደግሞ የመከላከል ችሎታው እሰከ 98% ከፍ ይላል፡፡ስለዚህ አንድ ልጅ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ሁለተኛውን ክትባት መውሰድ ይኖርበታል

source: ዶ/ር ሃብታሙ ድልድል የህፃናት ስፔሻሊስት
13.8K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 14:05:16 ጡት የሚያጠቡ እናቶች በተደጋጋሚ የሚጠይቋቸው 12 መሰረታዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ስለ እናት ጡት ወተት ጥቅሞች በደንብ የተረዳች እናት የሚከተሉትን 11 መሰረታዊ ጥያቄዎችን ትጠይቃለች እኔም ለዚች ንቁ እና ጠንቃቃ እናት መልሶችን አቅርብያለው::

#ጥያቄ 1: ልጄን በቀን ዉስጥ ስንት ጊዜ ነው ማጥባት ያለብኝ

ህፃናት ገና በተወለዱ በ 1 ሰአት ዉስጥ ጡት መጥባት መጀመር አለባቸው ከዛ ጀምሮ በ24 ሰአት ዉስጥ ቢያንስ ቢያንስ 8-12 ጊዜ ጡት መጥባት አለባቸው
ሆኖም በተጨማሪም ሕፃኑ ለመጥባት በሚፈልግበት ጊዜ ሰአት ሁሉ ማጥባት ተገቢ ነው::

#ጥያቄ 2: ህፃናት ጡት ለመጥባት ሲፈልጉ ምን አይነት ምልክቶችን ያሳያሉ
እጃቸው መጥባት
በደንብ ነቅተው አፋቸውን ማንቀሳቀስ
ምላሳቸውን ወጣ ወጣ ማድረግ
(ይሄ የእንጥል መውረድ ምልክት አይደለም )
መነጫነጭ
ማልቀስ : ሆኖም ልጅሽ እስከሚያለቅስ መጠበቅ የለብሽም ምክንያት አንዴ በኃይል ካለቀስ ጡትሽ ለማስያዝ ትንሽ ልትቸገሪ ትቺያለሽ::

#ጥያቄ 3: ልጄ ከተኛ ቀስቃሼ ማጥባት አለብኝ
አዎ በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሶስት ሳምንት  ዉስጥ በራሳቸው ከእንቅልፋቸው ካልነቁ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ መቀስቀስ እና ማጥባት አለብሽ ::

#ጥያቄ 4: መነሳት ካለበት ሰአት በፊት ቢነሳስ
ልጅሽን ለማጥባት "ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ" ተባለ እንጂ የተለየ የሰዓት ቀመር የለውም ልጅሽ ጡት በፍለገ ጊዜ ሁሉ ማግኘት አለበት::

#ጥያቄ 5: ልጄ አንዴ ሲጠባ ለምን ያህል ደቂቃ መጥባት አለበት
ሁሉም ህፃናት የሚጠቡበት ፍጥነት እና ብቃት ይለያያል ይሄ ማለት አንዳንዱ ህፃን በ 10 ደቂቃ ዉስጥ ጠብቶ እና ረክቶ ስተኛ አንዳንዱ ደሞ 30 ደቂቃ ሊፈጅበት ይቺላል::

#ጥያቄ 6 : የጡቴ ወተት እንደሚያጠግበው እና እንደማያጠግበው በምን አውቃለሁ

ጨቅላ ህፃን ልጅሽ በጡትሽ ወተት ከጠገበ የሚከተሉትን ነገሮች ያሳያል::(ከ 1 ሳምንት - 4 ሳምንት)

ጠብቶ እና ሆዱ ሙሉ ሆኖ ቢያንስ ለ 2 ሰአት ይተኛል
ሰውነቱ ላይ ከባድ ቢጫነት አይታይም
ኪሎ በየቀኑ እየጨመረ ይሄዳል
በቀን ቢያንስ 5-6 ሽንት ይሸናል
በቀን ቢያንስ 3-4 ካካ ይኖረዋል
(የመጨረሻው ለሁሉም ህፃናት ላይሰራ ይቺላል)

#ጥያቄ 7: ልጄ ሳጠባ ጡቴ ማቀየር ያለብኝ መቼ ነው
ልጅሽ አንደኛውን ጡትሽን እየጠባ ሳይጨርስ ቶሎ ወደ ሁለተኛው ጡት መቀየር የለብሽም
ምክንያቱም መጀመርያ የሚያገኘው ወተት(foremilk) አብዛኛው ዉሃማ ሲሆን ለ ሰውነቱ እድገት ዋና የሆነውን ምግብ (ቅባት እና ፕሮቲን) የሚያገኘው እስከ መጨረሻው ሲጠባ እና መጨረሻ ያለውን ወተት(hindmilk) ሲያገኝ ነው::

#ጥያቄ 8: ልጄ ለምንድነው ሌሊት ቶሎ ቶሎ እየነቃ  የምያለቅሰዉ

አንዳንድ ህፃናት በጣም በተደጋጋሚ እና ለ ረጅም ሰአት ጡት የሚፈልጉበት ሰአት አላቸው ይህ ባህሪ "cluster feeding " ይባላል::
በነዚህ ሰዓት ላይ ልጅሽ ነጭናጫ እና ወተቱ ያለበቃው ይመስላል ግን አይደለም ዝም ብለሽ በትዕግስት አጥቢው
ሌላው ጨቅላ ጨጓራ እና አንጀታቸው ትንሽ ስለሆነች ትንሽ ትንሽ ነው መጥባት የሚችሉት ስለዚህ ያቺ ትንሽ ወተት ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል ስታልፍ ይርባቸዋል ስለዚህ ቶሎ ቶሎ ይነቃሉ ያለቅሳሉም ::

#ጥያቄ 9: የጡት ወተቴን አልቤ ማስቀመጥ እና ከተወሰነ ሰአት በዋላ ማጥባት እችላለሁ

አዎ ትቺያለሽ በተለይ ወደ ስራ ቶሎ የምትገቢ ከሆነ ቀድመሽ ጡትሽን እያለብሽ ማስቀመጥ ልምድ ይኑርሽ::
የጡትሽን ወተት የምታልቢበት እና የሚታስቀምጭበት ዕቃ ንፁህናው በደንብ የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል

#ጥያቄ 10 አንዴ የታለበ ወተት ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም ይቻላል

ከ ፍሪጅ ዉጭ 4-6 ሰአት መቆየት ይቺላል
አንዴ ጠብቶ የተረፈውን በ 2 ሰአት ዉስጥ መጠቀም
በ ፍሪጅ ዉስጥ (በኔጌትቭ 4 c)ከተቀመጠ እስከ 4 ቀን
በበረዶ ቤት (በኔጌትቭ 18 c) ከተቀመጠ 6 ወር

#አጠቃቀሙም:
ወተቱን ከፍርጅ ከወጣነው በዋላ ወተቱ ያለበትን ጡጦ/ኩባያ ሞቅ ያለ ዉሃ ዉስጥ በማስቀመጥ ሙቀቱን ለመለካት በክንድ ላይ ጠብ አርጎ የማያቃጥል መሆኑን ካየን በዋላ መስጠት ይቻላል::

#ጥያቄ 11: #ጡቴ ጫፍ የለውም ለልጄም ሊያዝለት አልቻለም መፍትሄው ምንድነው

እናቶች ጡታቸውን ማየት እና ማስተካከል ያለባቸው ከወለዱ በዋላ ሳይሆን ቀድመው በእርግዝና ወቅት ነው
እርግዝና ወቅት የሚከታተልሽን ሀኪምሽ አማክረሽ በተለያዩ ዘዴዎች ጫፉ እንዲወጣ እና እንዲስተካከል ማድረግ አለብሽ
ከወለድሽ በዋላ ደሞ ጫፉ እስኪወጣ ድረስ ጡትሽን በማለቢያ እያለብሽ ወተቱን ለልጅሽ በጡጦ/ኩባያ መስጠት ይኖርብሻል ::
የጤና ባለሙያዎችን አማክሮ በተለያዩ ዘዴዎች ጫፉ እንዲወጣ መሳብ ለምሳሌ በ ተገለበጠ ሲሪንጅ
15.1K views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:58:16 #የጥቁር #አዝሙድ #የጤና #ጥቅሞች



#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

ዉድ pተከታታዮች ለዛሬ ስለ ጥቁር አዝሙድ ጥቅሞች ልንነግራችሁ ወደድን ተከታተሉን
ጥቁር አዝሙድ ከመቶ በላይ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ከነዚህ መካከል ፕሮቲን ፣ካርቦሃይድሬት፣የስብ አሲዶች ፣ካልሲየም ፣ፖታሲየም ፣ብረት ፣ዚንክ፣ማግኒዥየም ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ሲ በዋናነት ይይዛል፡፡
#ጥቅሞች

ለመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን
በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት፤ በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት እንዲሁም ሁለት ማንኪያ በፈላ ውኃ ውስጥ ጨምሮ
በእንፋሎቱን ቤትን ማጠን

ለራስ ምታት
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ፤ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር
አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት

ለጀርባ ሕመም
የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት
በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት

ለልብ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት
ይረዳል

ለደም ብዛት
ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር
አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ማግኘት

ለጨጓራና ለአሲድ
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ

ለኩላሊት ኢንፌክሽን
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፤ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በባዶ ሆድ መጠጣት

ለሐሞት ከረጢት
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ እሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት

ለጉሮሮ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና  አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት

ለቆዳ ውበት
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና
መታጠብ

የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለመጨመር
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናና ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ
ቀናት መውሰድ

ለጭንቀት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ሰዉነትን ያረጋጋል አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል
14.1K views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 15:31:57 #በባዶ #ሆድ #ውሃ #የመጠጣት #የጤና #ጥቅሞች

1. በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት አንጀትን በማጽዳት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲመጥ ይረዳናል፡፡
2. አዲስ የደም እና የጡንቻ ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋል።
3. ክብደትን ለመቀነስ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ሲነሱ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት ሜታቦሊዝምን ያፋጥናል፡፡
4. ሲያዩት የሚያምርና ጤናማ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ውሃ በደም ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ነገሮችን ጠራርጎ በማስወጣት ቆዳችን ንጹህ፣ ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡
5. የሊምፍ ሥርዓታችን (Lymph System) የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ እነዚህ ዕጢዎች የዕለት ከዕለት ተግባራችንን በትክክል እንድንወጣ፣ የሰውነታችን ፈሳሽ የተመጣጠነ እንዲሆን እና ኢንፌክሽንን እንድንዋጋ ይረዱናል፡፡
#ውሃን #በመጠቀም #የሚደረግ #ህክምና
በአሁኑ ጊዜ ከወደ ጃፓን የመጣ አዲስ ልምድ አለ ጃፓኖች በሚመገቡበት ጊዜ ለብ ሻይ ይጠጣሉ ይህም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው ህክምና ሲሆን ይህ ህክምና ከጠዋት ጀምሮ ቀኑን ሙሉ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ውሃ መጠጣትን ያካትታል፡፡ ይህም ህክምና በሚጀምሩበት ሰሞን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት የሚያጋጥም ሲሆን በጃፓን የህክምና ማህበር ከብዙ በሽታዎች የመፈወስ አቅሙ 100% መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ከነዚህም በሽታዎች መካከል የራስ ህመም፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም፣ የልብ ህመም፣ አርትራይተስ፣ ለፈጣን የልብ ምት፣ ለሚጥል በሽታ፣ ለአስም፣ ቲቢ፣ መንጋጋ ቆልፍ፣ ለኩላሊትና ሽንት በሽታ፣ ማስመለስ፣ ጨጓራ፣ ተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት፣ ለሁሉም የአይን በሽታ፣ ለካንሰርና የወር አበባ ችግር፣ ለጆሮ አፍንጫና ጉሮሮ ህመሞች ፈውስ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
#ቀዝቃዛ #ውሃ #መጠጣት
ምግብ በምንመገብበት ጊዜ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት የራሱ የሆነ የጐንዮሽ ጉዳቶች አሉት፡፡ በተመገቡት ምግብ ውስጥ የሚገኝው ዘይት እንዲወፍር ያደርገዋል፤ ይህ ማለት የምግብ ስልቀጣ ሥርዓትን ከማዘግየቱ በተጨማሪ ምግብን ከሚፈጨው አሲድ ጋር ግጭት ይፈጥራል፤ አንጀታችን ምግብን በፍጥነት ይመጣቸዋል፣ ወደ ስብ(ፋት) ይቀይራቸዋል ስለዚህ ከምግብ በኋላ ያልቀዘቀዘ ወይም ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ወይም ሾርባ ይጠቀሙ፡፡
#ህክምናው #እንዴት #ይተገበራል (የህክምናው ዘዴ)
1. ጠዋት ጥርስዎን ከመፋቅዎ በፊት 160 ሚ.ሊ. በሚይዝ ብርጭቆ አራት(4) ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡
2. ጥርስዎን ይቦርሹ ወይም ያጽዱ ነገር ግን ለ 45 ደቂቃ ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ እንዳይወስዱ፡፡
3. ከ 45 ደቂቃ በኋላ ምግብ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ይችላሉ፡፡
4. ቁርስ፣ ምሳ ወይም እራት ከበሉ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ለሁለት(2) ሠዓት ያክል ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ አይውሰዱ፡፡
5. ዕድሜያቸው የገፋና የታመሙ ሰዎች ከትንሽ ውሃ በመጀመር 4 ብርጭቆ ውሃ ላይ እንዲደርሱ ይመከራል፡፡
6. ይህ ህክምና በህመም ላይ የሚገኙ ወይም የታመሙ ሰዎችን የመፈወስ አቅም አለው፡፡
20.2K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 18:52:02
ሸኖ ላይ ቤትም ሆነ ባዶ ቦታ መግዛት ሲፈልጉ በ0983839300 ላይ ይደውሉልን።
6.8K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:33:45
#መግለጫ

ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሣመት በፈጸሙት አባቶች መካከል ስምምነት የተደረሰ ሲሆን ስምምነቱን በተመለከተ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው መረጋገጡን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።

@fetanmereja24
4.5K views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 16:41:15
የተረጋጋ ሰላም ባላትና ከ አ.አ 78 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ሸኖ ከተማ ላይ ለባንክ የሚሆን የሚከራይ ቤት ከፈለጉ 0983839300 ላይ ይደውሉልን
2.2K views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 20:41:18
የሚሸጥ ቤቶች አሉን 200 ካሬ 500 ካሬ ቤት ያለው እንዲሁም ባዶ ቦታዎች አድራሻ ሸኖ ከተማ ከ አአ 70 ኪሜ ርቀት ላይ ወደ ደብረብርሃን መስመር ገዥ ብቻ
+251983839300
+251913088453
2.4K views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 20:54:44
+251913088453
+251983839300
ሸኖ ከተማ የሚገኙ ናቸው ባዶ ቦታ ወይም ቤት ያለባቸው ቦታዎች አለን ከላይ ባሉት ቁጥሮች ይደውሉልን።
5.0K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 20:09:21
የሚሸጥ ቤቶች አሉን 200 ካሬ ላይ አድራሻ ሸኖ ከተማ ከ አአ 70 ኪሜ ርቀት ላይ ወደ ደብረብርሃን መስመር ገዥ ብቻ በ 0983839300 ላይ ይደውሉልን
7.3K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ