Get Mystery Box with random crypto!

ኩፍኝ (measles) ምንድን ነው? ኩፍኝ፦ አጣዳፊና በፍጥነት የሚተላለፍ በቫይረስ የሚመጣ አየ | Fast mereja

ኩፍኝ (measles) ምንድን ነው?

ኩፍኝ፦ አጣዳፊና በፍጥነት የሚተላለፍ በቫይረስ የሚመጣ አየር ወለድ በሽታ ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ከአምስት ዓመት እድሜ በታች ያሉትን ህፃናት የሚያጠቃ ቢሆንም በሁሉም የእድሜ ክልል ይከሰታል።

ከሦስት ወር በታች ባሉ ህፃናት ግን የመከሰት እድሉ አነስተኛ ነው። በጣም ተላላፊ ስለሆነ በወረርሽኝ መልክ ይከሰታል።

በተላይ የምግብ እጥረት ባለባቸው ህፃናት፣ክትባት ባልወሰዱ እና ተጓዳኝ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ይጠቃሉ ።

ምልክቶቹስ?
የመጀመሪያዎቹ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው ፡-
•  ትኩሳት - እስከ 104ºF (40ዲሴ)
• እንደ ጉንፋን አይነት  ስሜትና ደረቅ ሳል
• የምግብ ፍላጎት ማጣት
• ጠፍጠፍ ያሉ ቀይ ቀለም ያላቸው  ከጭንቅላት ጀምሮ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል የሚስፋፋ የቆዳ ሽፍታ
• በአፍ ውስጥ ያሉ ነጠብጣቦች - koplik spot
• የአይን መቅላት አና ማንባት (red watery eye)
• በአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት (coryza)

አጋላጭ ሁነቶች
• የኩፍኝ ክትባት ያልወሰደ ሰው
• ኤችአይቪ/ኤድስ ወይም ካንሰር ያለባቸው ሰዎች
• ነፍሰጡር ሴቶች
• በቂ ምግብ ወይም ቫይታሚን የማያገኙ ሰዎች
• ከአምስት ዓመትበታች እና ከ ሃያ ዓመት በላይ የእድሜ ክልል ባሉ  ሰዎች ላይ በሽታው ሊፀና ይችላል።

መተላለፊያ መንገዶቹስ?
ኩፈኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን በቫይረሱ የተበከለውን አየር ሲስቡ ወይም ቫይረሱ ያረፈባቸውን ዕቃዎች በእጃቸው ከነኩና ከዚያም አፍንጫ፣ አፍና አይኖቻቸውን ከነኩ በቀላሉ ይተላለፋል።
የከፋ የሚያደርገው ደግሞ በሽተኞቹ ሲስሉና ሲያነጥሱባቸው በነበሩባቸው ከፍሎችና አካባቢዎች ለሁለት ሰአታት በአየር ላይና በቁሳቁሶች ላይ የመቆየት ችሎታ አለው፡፡

በሽታው  በፍጥነት ሊተላልፍበት የሚችሉበት ቀናት ደግሞ  የቆዳ ሽፍታ ከመታየቱ ከሦስት ቀን በፊትና ሽፍታ ከታየ ከአራት እስከ ስድስት ቀናት በሁኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።

ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት (complication ):
1/የሳንባ ምች (pneumonia)-ይህ የሚያስፈራ ሕፃናትን ህወታቸውን ሊያሳጣ የሚችል በኩፍኝ ቫይረስ (measle virus) የሚመጣ የሳንባ ቁስለትን ያስከትላል።

2/የጆሮ እንፌክሽን :አብዛኛው ጊዜ በኩፉኝ የተያዘ ሰው በጆሮ እንፌክሽን የሚጠቃ ሲሆን በአንዳንድ ሰዎች ላይ ዘላቂ የሆነ የመስማት ችግር ሊያስከትል ይችላል።

3/ተቅማጥና ትውከት፡ በማምጣት በሰውነቱ ያለውን ፈሳሽ እዲያልቅ (dehydration ) በማስከተል ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
4/የማየት ችግር (corneal clouding)፡ በማምጣት ዘላቂ የሆነ የማየት ችግር (blindness) ያስከትላል።

5/የምግብ እጥረት (malnutrition)፡ በማስከተል ና በሽታ የመከላከል አቅምን በማዳከም ለሌሎች በሽታወች ለምሳሌ እንደ ትቢ (tuberculosis ) ላሉ በሽታወች ያጋልጣል።

6/የአንጎል ኢንፌክሽን (Encephalitis): አልፎ  አልፎ የሚከሰት ቢሆንም አደገኛ የአንጎል ጉዳት በማሰከተል ለሚጥል በሽታ (epilepsy ) እና የአእምሮ እድገት ወደ ኋላ መቅረትን ያጋልጣል።

የኩፍኝ በሽታ ምርመራ አለ?
አዎ !! የኩፍኝ በሽታን ለመመርመር የደም ምርመራ ማድረግ ይችላሉ።ግን እነዚህ ምርመራዎች ሳያስፈልጉ የኩፍኝ በሽታ እንዳለበት በምልክቶቹ  ይታወቃል። ማንኛውም ሰው ትኩሳት፣ ሳል፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የአይን መቅላት እና በአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት ካለ ኩፍኝ ሊሆን ስለሚችል ወደ  ጤና ተቋም ይሂዱ።

እንዴት ይታከማል?
• ቫይታሚን ኤ መውሰድ
• በቂ እረፍት ማድረግ
• ብዙ ፈሳሽ መጠጣት(መውሰድ )
• ትኩሳት እና ህመምን ለመርዳት የህመም ማስታገሻ መውሰድ
• ከላይ የተዘረዘሩት ውስብስ ችግሮች ካሉ ማከም

ድንገት ኩፍኝ ካለበት ሰው አጠገብ ብሆንስ?
ድንገት ለቯይረሱ ተጋልጠው ከሆኑ በሽታው አንዳይከሰት መከላከል ይቻላልን? አዎ የኩፉኝ ክትባቱን በ72 ሰዓትት ውስጥ ካገኙ የኩፍኝ በሽታን ሊያስቆም ወይም ከባድ እንዳይሆን ማድረግ ይችላል።

መከላከያ መንገዶችስ
በክትባት ከምንከላከላቸው ተላላፊ በሽታዎች አንዱ እና ዋነኛው ኩፉኝ (measle) ነው።
በአገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም ህፃናት  በተወለዱ በ9 ወር እና በ15 ወር የኩፍኝ ክትባት መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ይህን ክትባት አንድ ጊዜ ብቻ መውሰድ ከበሽታው እስከ 95 % መከላከል የሚያስችል ሲሆን ሁለተኛው ክትባት ከተወሰደ ደግሞ የመከላከል ችሎታው እሰከ 98% ከፍ ይላል፡፡ስለዚህ አንድ ልጅ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ሁለተኛውን ክትባት መውሰድ ይኖርበታል

source: ዶ/ር ሃብታሙ ድልድል የህፃናት ስፔሻሊስት