Get Mystery Box with random crypto!

ጡት የሚያጠቡ እናቶች በተደጋጋሚ የሚጠይቋቸው 12 መሰረታዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው ስለ እ | Fast mereja

ጡት የሚያጠቡ እናቶች በተደጋጋሚ የሚጠይቋቸው 12 መሰረታዊ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው

ስለ እናት ጡት ወተት ጥቅሞች በደንብ የተረዳች እናት የሚከተሉትን 11 መሰረታዊ ጥያቄዎችን ትጠይቃለች እኔም ለዚች ንቁ እና ጠንቃቃ እናት መልሶችን አቅርብያለው::

#ጥያቄ 1: ልጄን በቀን ዉስጥ ስንት ጊዜ ነው ማጥባት ያለብኝ

ህፃናት ገና በተወለዱ በ 1 ሰአት ዉስጥ ጡት መጥባት መጀመር አለባቸው ከዛ ጀምሮ በ24 ሰአት ዉስጥ ቢያንስ ቢያንስ 8-12 ጊዜ ጡት መጥባት አለባቸው
ሆኖም በተጨማሪም ሕፃኑ ለመጥባት በሚፈልግበት ጊዜ ሰአት ሁሉ ማጥባት ተገቢ ነው::

#ጥያቄ 2: ህፃናት ጡት ለመጥባት ሲፈልጉ ምን አይነት ምልክቶችን ያሳያሉ
እጃቸው መጥባት
በደንብ ነቅተው አፋቸውን ማንቀሳቀስ
ምላሳቸውን ወጣ ወጣ ማድረግ
(ይሄ የእንጥል መውረድ ምልክት አይደለም )
መነጫነጭ
ማልቀስ : ሆኖም ልጅሽ እስከሚያለቅስ መጠበቅ የለብሽም ምክንያት አንዴ በኃይል ካለቀስ ጡትሽ ለማስያዝ ትንሽ ልትቸገሪ ትቺያለሽ::

#ጥያቄ 3: ልጄ ከተኛ ቀስቃሼ ማጥባት አለብኝ
አዎ በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሶስት ሳምንት  ዉስጥ በራሳቸው ከእንቅልፋቸው ካልነቁ ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ መቀስቀስ እና ማጥባት አለብሽ ::

#ጥያቄ 4: መነሳት ካለበት ሰአት በፊት ቢነሳስ
ልጅሽን ለማጥባት "ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ" ተባለ እንጂ የተለየ የሰዓት ቀመር የለውም ልጅሽ ጡት በፍለገ ጊዜ ሁሉ ማግኘት አለበት::

#ጥያቄ 5: ልጄ አንዴ ሲጠባ ለምን ያህል ደቂቃ መጥባት አለበት
ሁሉም ህፃናት የሚጠቡበት ፍጥነት እና ብቃት ይለያያል ይሄ ማለት አንዳንዱ ህፃን በ 10 ደቂቃ ዉስጥ ጠብቶ እና ረክቶ ስተኛ አንዳንዱ ደሞ 30 ደቂቃ ሊፈጅበት ይቺላል::

#ጥያቄ 6 : የጡቴ ወተት እንደሚያጠግበው እና እንደማያጠግበው በምን አውቃለሁ

ጨቅላ ህፃን ልጅሽ በጡትሽ ወተት ከጠገበ የሚከተሉትን ነገሮች ያሳያል::(ከ 1 ሳምንት - 4 ሳምንት)

ጠብቶ እና ሆዱ ሙሉ ሆኖ ቢያንስ ለ 2 ሰአት ይተኛል
ሰውነቱ ላይ ከባድ ቢጫነት አይታይም
ኪሎ በየቀኑ እየጨመረ ይሄዳል
በቀን ቢያንስ 5-6 ሽንት ይሸናል
በቀን ቢያንስ 3-4 ካካ ይኖረዋል
(የመጨረሻው ለሁሉም ህፃናት ላይሰራ ይቺላል)

#ጥያቄ 7: ልጄ ሳጠባ ጡቴ ማቀየር ያለብኝ መቼ ነው
ልጅሽ አንደኛውን ጡትሽን እየጠባ ሳይጨርስ ቶሎ ወደ ሁለተኛው ጡት መቀየር የለብሽም
ምክንያቱም መጀመርያ የሚያገኘው ወተት(foremilk) አብዛኛው ዉሃማ ሲሆን ለ ሰውነቱ እድገት ዋና የሆነውን ምግብ (ቅባት እና ፕሮቲን) የሚያገኘው እስከ መጨረሻው ሲጠባ እና መጨረሻ ያለውን ወተት(hindmilk) ሲያገኝ ነው::

#ጥያቄ 8: ልጄ ለምንድነው ሌሊት ቶሎ ቶሎ እየነቃ  የምያለቅሰዉ

አንዳንድ ህፃናት በጣም በተደጋጋሚ እና ለ ረጅም ሰአት ጡት የሚፈልጉበት ሰአት አላቸው ይህ ባህሪ "cluster feeding " ይባላል::
በነዚህ ሰዓት ላይ ልጅሽ ነጭናጫ እና ወተቱ ያለበቃው ይመስላል ግን አይደለም ዝም ብለሽ በትዕግስት አጥቢው
ሌላው ጨቅላ ጨጓራ እና አንጀታቸው ትንሽ ስለሆነች ትንሽ ትንሽ ነው መጥባት የሚችሉት ስለዚህ ያቺ ትንሽ ወተት ወደ ታችኛው የአንጀት ክፍል ስታልፍ ይርባቸዋል ስለዚህ ቶሎ ቶሎ ይነቃሉ ያለቅሳሉም ::

#ጥያቄ 9: የጡት ወተቴን አልቤ ማስቀመጥ እና ከተወሰነ ሰአት በዋላ ማጥባት እችላለሁ

አዎ ትቺያለሽ በተለይ ወደ ስራ ቶሎ የምትገቢ ከሆነ ቀድመሽ ጡትሽን እያለብሽ ማስቀመጥ ልምድ ይኑርሽ::
የጡትሽን ወተት የምታልቢበት እና የሚታስቀምጭበት ዕቃ ንፁህናው በደንብ የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል

#ጥያቄ 10 አንዴ የታለበ ወተት ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም ይቻላል

ከ ፍሪጅ ዉጭ 4-6 ሰአት መቆየት ይቺላል
አንዴ ጠብቶ የተረፈውን በ 2 ሰአት ዉስጥ መጠቀም
በ ፍሪጅ ዉስጥ (በኔጌትቭ 4 c)ከተቀመጠ እስከ 4 ቀን
በበረዶ ቤት (በኔጌትቭ 18 c) ከተቀመጠ 6 ወር

#አጠቃቀሙም:
ወተቱን ከፍርጅ ከወጣነው በዋላ ወተቱ ያለበትን ጡጦ/ኩባያ ሞቅ ያለ ዉሃ ዉስጥ በማስቀመጥ ሙቀቱን ለመለካት በክንድ ላይ ጠብ አርጎ የማያቃጥል መሆኑን ካየን በዋላ መስጠት ይቻላል::

#ጥያቄ 11: #ጡቴ ጫፍ የለውም ለልጄም ሊያዝለት አልቻለም መፍትሄው ምንድነው

እናቶች ጡታቸውን ማየት እና ማስተካከል ያለባቸው ከወለዱ በዋላ ሳይሆን ቀድመው በእርግዝና ወቅት ነው
እርግዝና ወቅት የሚከታተልሽን ሀኪምሽ አማክረሽ በተለያዩ ዘዴዎች ጫፉ እንዲወጣ እና እንዲስተካከል ማድረግ አለብሽ
ከወለድሽ በዋላ ደሞ ጫፉ እስኪወጣ ድረስ ጡትሽን በማለቢያ እያለብሽ ወተቱን ለልጅሽ በጡጦ/ኩባያ መስጠት ይኖርብሻል ::
የጤና ባለሙያዎችን አማክሮ በተለያዩ ዘዴዎች ጫፉ እንዲወጣ መሳብ ለምሳሌ በ ተገለበጠ ሲሪንጅ